Radio Bilal September 5, 2012 ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 30/2004
- ነዋሪዎች መረጃ ለመስጠት ለደህንነታችን እንሰጋለን አሉ
- የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ነዋሪዎችን አስግቷል
- የቀድሞው የኢትዮጲያ ፕሬዝደንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም መኖሪያቸውን ቀየሩ
- ከአዋሽ ባንክ ሊዘረፍ የነበረ 1.6 ሚሊዮን ብር መያዙ ተገለፀ
ነዋሪዎች መረጃ ለመስጠት ለደህንነታችን እንሰጋለን አሉ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 30/2004
በአዲስ አበባና
በክልል የሚገኙ ነዋሪዎችና አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ለመገናኛ ብዙኃን መረጃ ለመስጠት ለደህንነታችን ያሰጋል ሲሉ ለሬዲዮ ቢላል
ገለፁ፡፡
የሬዲዮ ቢላል
ሪፖርተሮች ዛሬ ያነጋገርናቸውና በድምፅ መቀረፅ ያልፈለጉ በአዲስ አበባና በየክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለፁት ለሚዲያ መረጃ
ሰጥታችኋል በሚል ብዙዎች እየታሰሩ በመሆኑና እነሱም እያስፈራሯቸው በመሆኑ ለደህንነታቸው ሲሉ መረጃ መስጠት አይፈልጉም፡፡
ለረጅም ጊዜ
ለሬዲዮ ቢላል የተለያዩ ወቅታዊ የሙስሊሙን ጉዳይ በተመለከተ መረጃ በመስጠት ይተባበሩ የነበሩ ግለሰቦች አንዳንዶች ስልካቸው ዝግ
እንደሆነና ሌሎች ደግሞ ሲደወልባቸው ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን የሬዲዮ ቢላል ሪፖርተሮች ገልìªM::
-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ነዋሪዎችን አስግቷል
አዲስ አበባ ነሐሴ 30/2004
ምክንያቱ ባልታወቀና ነጋዴዎችም ሲጠየቁ ምላሽ
መስጠት ፈቃደኛ ባልሆኑበት ሁኔታ፣ የጤፍ
ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ
መናሩ ስጋት እንደፈጠረባቸው በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ ከወር በፊት
አንድ ኩንታል ማኛ
ጤፍ 1‚450 ብር ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ
ወዲህ ግን ዋጋው
በጣም አሻቅቦ 2‚100 ብር
መሸጥ ጀምሯል፡፡ አንዳንድ ነዋሪዎች ጤፍ
ከሚመረትበት ቦታ ወይም
በቀጣይ የሚፈጠር ችግር
እንዳለ በሚል ነጋዴዎቹን ሲጠይቋቸው፣ “ከፈለጋችሁ መውሰድ ትችላላችሁ አለበለዚያ ተውት”
እንደሚሏቸው ገልጸዋል፡፡
ወቅቱ የበልግ ምርት የሚደርስበት በመሆኑ የተወሰነ የዋጋ ቅናሽ መደረግ ሲገባው ያለምንም ምክንያት መጨመሩ እንዳሳሰባቸው የገለጹት ነዋሪዎች ፣ ምናልባት “እረኛና ነጋዴ የሚታየው ነገር ይኖራል” በሚል ፍራቻ 420 ብር ይሸጥ የነበረውን ግማሽ ኩንታል ሰርገኛ፣ ማኛ ጤፍ በሚገዙበት ዋጋ ሸምተው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ነጋዴዎች እንደገለጹት፣ የጤፍ ዋጋ በተወሰነ መጠን ጨምሯል፡፡ ሸማቾቹ እንደሚሉት ግን የተጋነነ አይደለም ይላሉ፡፡ ክረምት በመሆኑና ከአምራቾች የሚመጣው ምርት በመቀነሱ በኩንታል ከሁለት መቶ ብር ያልበለጠ ጭማሪ ተከስቷል በማለት ያስረዳሉ፡፡ ማኛ አንደኛ ጤፍ በኩንታል 1,700 ብር ድረስ ይሸጣል ነው የሚሉት፡፡ ምናልባት አንዳንድ በመኖሪያ አካባቢዎች የሚገኙ ሽያጭና የወፍጮ ሥራ የሚሠሩ ነጋዴዎች ሊያስወድዱ ስለሚችሉ፣ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የወረዳ ወይም የክፍለ ከተማ አስተዳደርና ለፖሊሶች በመጠቆም ሕገወጥነትን መከላከል እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የቀድሞው የኢትዮጲያ ፕሬዝደንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ
ኃ/ማሪያም መኖሪያቸውን ቀየሩ
አዲስ አበባ ነሐሴ 30/2004
ኢትዮጵያን ለ17 ዓመት በወታደራዊ መንግስት የመሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በዙምባቡዌ ዋና ከተማ ሀራሬ
የሚገኘውን መኖሪያ ቤታቸውን ቀየሩ፡፡ ኮለኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የቀድሞ መኖሪያቸውን ለቀው ከሀራሪ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ከምትገኘዋ
ሹምባ መግባታቸው ተገልፆዋል፡፡ ሰዜናውን ያስነበበው ዙምባቡዌ ሜል ጋዜጣ ኮሎኔል መንግስቱ የቀድሞ መኖሪያቸውን በመልቀቅ ወደ አዲሱ
መኖሪያ ቤታቸው የገቡት በሚስጥር መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኮሎኔል በቅድሚያመኖሪያስፋራቸው ላይ በሁለት ኤርትራዊያን ግድያ ተሞክሮባቸው እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በቅርቡ ትግላችን የሚል የአገዛዝ ዘመናቸውን የሚተርክ መፅሀፍ ማሳተማቸው ይታወቃል፡፡
ኮሎኔል በቅድሚያመኖሪያስፋራቸው ላይ በሁለት ኤርትራዊያን ግድያ ተሞክሮባቸው እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በቅርቡ ትግላችን የሚል የአገዛዝ ዘመናቸውን የሚተርክ መፅሀፍ ማሳተማቸው ይታወቃል፡፡
---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከአዋሽ ባንክ ሊዘረፍ የነበረ 1.6 ሚሊዮን ብር መያዙ ተገለፀ
ከአዋሽ ባንክ ሊዘረፍ የነበረ 1.6 ሚሊዮን ብር መያዙ ተገለፀ
አዲስ አበባ ነሐሴ 30/2004
መርካቶ አካባቢ ከሚገኘው የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ
የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ በተጭበረበረ መንገድ ሊዘረፍ ነበር የተባለ 1.6 ሚሊዮን ብር መያዙ ተገለፀ፡፡ ነሐሴ 24 ቀን 2004
ዓ.ም. በአንድ የቅርንጫፉ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቀነባባሪነት፣ ከደንበኞች አካውንት ተባባሪ ናቸው
ወደተባሉ ሁለት ግለሰቦች አካውንት እንዲገባ ከተደረገ በኋላ
ገንዘቡ ከቅርንጫፉ ሲወጣ
መያዙ ታውቋል፡፡ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ እንዲወጣ ሙያውን በመጠቀም የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥሯል የተባለው የባንኩ ሠራተኛና ገንዘቡን ሲያወጡ ተያዙ
የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተረጋግጧል፡፡ የባንኩ ሠራተኛና ሁለቱ
ተጠርጣሪዎች በአሁኑ ወቅት
በፖሊስ በቁጥጥር ሥር
ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነም ታውቋል፡፡ ከ80
በላይ ቅርንጫፎች ያሉትና በአገሪቱ የመጀመሪያው የግል ባንክ
ሆኖ የተመዘገበው አዋሽ
ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ
ሽፈራው ከሸፈ የተባለው የማጭበርበር ተግባር ስለመፈጸሙ ማረጋገጫ ቢሰጡም፣ ስለ
ጉዳዩ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በባንኮች ላይ ተደጋጋሚ ዘረፋዎች እየተከሰቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ አንድነት ቅርንጫፍና ከጎተራ ቅርንጫፍ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ መዘረፉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
No comments:
Post a Comment