አሠላዓለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበራካቱሁ
በአላህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩሕሩሕ
የአክብሮቱና አድናቆቱ አካል ነን ወይስ ዱላው እንደነበረ ይቀጥላል? (ነሐሴ 30 2004)
በማክሰኞ ምሽት የሁለት ሰዓቱ ዜና ላይ ኢቴቪ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት ምክንያት መላ ኢትዮጵያዊያን በኃዘን ላይ መሰንበታቸውን አስታውሶ የብሔራዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለሕዝቡ ያላቸውን አክብሮት እና አድናቆት በመግለፅ የሀዘን ሥነ-ሥርዓቱ መጠናቀቁ እና በኃዘኑ ምክንያት ዝቅ ብሎ የነበረው የሀገሪቱ ባንዲራ ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሶ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አውጇል፡፡
መላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላለፉት ዘጠኝና አስር ወራት ያነሷቸው ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎች ትኩረት አግኝተው ተገቢውን ምላሽ ሳያገኙ በመቅረታቸው በተቃራኒው ፍፁም ሥርዓቱን የጠበቀና ሠላማዊ የሆነ አካሄድ የተከተለውን የተቃውሞ ሒደት ጥላሸት በመቀባትና “አሸባሪ” የሚል ተቀፅላ በመስጠት ለማኮላሸት ሰፊ ርብርብ ቢደረግም ተቃውሞው ይዘቱን ሳይቀይር በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ሆኗል፡፡ በዒደል ፈጥር አደባባይ የነበረው የሕዝብ ማዕበል ያሰማው የተቃውሞ ድምፅ የተጀመረው ተቃውሞ አዲስ ጉልበት ያገኘ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ባገኘው አዲስ ጉልበት ጥያቄዎቹ ባለመመለሳቸው ምክንያት ተቃውሞውን አጠናክሮ ለመቀጠል ቢሰናዳም ከዒድ በዓል ውሎ አንድ ቀን በኋላ ማለትም ማክሰኞ ነሐሴ 14 ማለዳ ያልተጠበቀ እና መላ ኢትዮጵያዊያኖችን አስደንግጦ የኃዘን ድባብ ያላበሰ መርዶ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ተሠማ፡፡
አርቆ አስተዋይነትን በመላበስ በተቃውሞ ሒደት ውስጥ የከረመው ሕዝበ ሙስሊሙ በለመደው አስተዋይነቱ በመታገዝ ነገሮችን በሰከነ መልኩ ለመረዳት እና አቅጣጫዎችን ከግራና ከቀኝ በመመልከት ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ግዜ አልፈጀበትም ነበር፡፡ የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት የአገር ጉዳይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ “የሀገር ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ነው!” በማለት ሲያሰማ የከረመውን የአደባባይ ተቃውሞ ላልተወሰነ ጊዜ ጋብ ለማድረግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ይህም በዚህ ሳይገደብ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ሕልፈተ-ህይወት የተሰማውን ሀዘን በማስመልከት ድምፁን የሚያሰማበትን መግለጫ አወጣ፡፡ ይህም በዚህ ሳይገደብ መላ ሙስሊም ሕብረተሰብ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ ሕዝቡ የሚያደርገውን የሀዘን ጊዜ ሥነ-ሥርዓቶች ከመካፈል እስከ ማስተባበር ያለውን ድርሻ ተወጣ፡፡ ይህም በብዙዎች ዘንድ “እነኚህ ሙስሊሞች መብታችን ተረግጧል፣መንግስት በሐይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል … እያሉ ለተቃውሞ አደባባይ ሲውሉ አልከረሙም እንዴ? ዛሬ ታዲያ ይህን የሚያደርጉት ምላሽ አግኝተው ነው ወይስ ረስተውት?” የሚለው ወሬ እዚህም እዚያም አስከሚወራ ድረስ ሙስሊሞች አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ በተቃውሞ ሒደት ተሳታፊ የነበሩት መላ ሙስሊም ሕዝብ ኢትዮጵያዊያኖች ሐዘናቸውን ለመግልፅ ከወሰዷቸው ተግባራት በተቃራኒ ያንፀባረቁት አንዳች ንግግርም ሆነ ተግባር ፈፅሞ አልተገኘም፡፡ ይህ የሆነው ሙስሊም ሕዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጨዋ፣ ሕግ አክባሪ፣ ለሥነ-ሥርዓት ታዛዥ እና ለሀገሩ ጉዳይ እጅግ ቀናኢ ከመሆን ብቻና ብቻ የመነጨ በመሆኑ ነው፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ብሔራዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች በመገናኛ ብዙሃን በመቅረብ የሚያስተላልፉትን መልዕክትም ሆነ ትዕዛዝ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ገቢር ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ይህንን ሥነ-ሥርዓት እና ታዛዥነት ባልተጠበቀ ሁኔታ ያስተናገደው መንግስት ከአንድ ሁለቴ በላይ አክብሮቱን፣ አድናቆቱን እና ምስጋናውን ሲገልፅ የቆየ ሲሆን በማጠቃለያውም ይህንኑ በድጋሜ አሰምቷል፡፡
በተጨባጭ አገራችን እና ሕዝቦቿ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ-ህይወት ምክንያት ሀዘን ውስጥ እንገኛለን፡፡ በሐዘን ጊዜ መደረግ ያለበት ደግሞ እንደ ወጋችን እና ልማዳችን እርስ በርሳችን መፅናናት በመሆኑ ያለ አንዳች ልዩነት ይህንኑ በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት ችለናል፡፡ይህ በሳል አስተሳሰብ የታከለበት አካሄድ የሕዝበ ሙስሊሙ የአንድነት መገለጫ ሆኗል፡፡
መንግስት የኃዘን ሥርዓቱ መጠናቀቁን አውጇል፡፡ በመሆኑም ዝቅ ብሎ የሰነበተው ባንዲራችን ወደ ነበረበት ቦታው ተመልሶ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ መመሪያ ሲያስተላልፍ ለኢትዮጵያዊያን ያለውን አክብሮት እና አድናቆት ገልጧል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊያን ዜጋ ይህ እኛ ሙስሊሞችንም እንደሚመለከት እንወስዳለን፡፡ ይህ ምስጋና ለኛ ከዚህም በላይ ትርጉም እንዳለው ይሰማናል፡፡
ላለፉት በርካታ ወራት አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ስናሰማ የቆንበት ጉዳይ በዚህ መልካም ጅምር ታጅቦ መልካም የሚባል መቋጫ እንደሚኖረው ተስፋችን የላቀ ነው፡፡ ያቀረብናቸው ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎች እጅግ ግልፅ፣ ቀላል እና ከፖለቲካ የፀዱ መሆናቸው ያኮረፈውን ሰፊ ሕዝብ በማቅረብ ፊታችንን ወደ ጀመርነው የልማት እንቅስቃሴ በማዞር የክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩን ራዕይ ባጭር ጊዜ እውን የምናደርግበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር እናምናለን፡፡
በሰላም አገር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩትን ወንድሞቻችንን ኑና ጉዳያችንን ተሸክማችሁ አቤቱታችንን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ የመሪነት ሚናችሁን ተወጡ ብቻ በማለት ፊት ስላሰለፍናቸው፣ ስለ-ሰላም ስለሰበኩ እና እኛን ወክለው አደባባይ ስለወጡ ብቻ ያለወንጀላቸው “አሸባሪ” ተብለው ተጠርጥረው እነሆ በእንግልት፣በስቃይና በእስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ እነኚህ ወንድሞቻችን ፍፁም ንፁኃን እና የሠላም አምባሰደሮች እንጂ ሌላ ከቶ እንዳልሆኑ ድፍን ሙስሊም ሕዝብ ይተማመንባቸዋል፡፡ በመሆኑም መንግስት ሕገ ወጥ የመጅሊስ አመራሮችም ሆኑ ሌሎች ለጥቅም ያደሩ አካላት በሚያቀርቡለት ፍፁም ከእውነት የራቀ መረጃ ላይ ተንተርሶ በወንድሞቻችን ላይ እና በተቀሩት ሙስሊሞች ላይ እየወሰደ ካለው አላስፈላጊ እርምጃ ራሱን በመቆጠብ እስካሁን የተጓዘውን ርቀት መለስ ብሎ በመመርመር እና የወደፊቱንም አቅጣጫ ራሱን ከሰፊውና ፍፁም ሠላም ወዳድ ከሆነው ሕዝበ ሙስሊም ጋር በማሰለፍ ለመልካም ውጤት እንዲተጋ ተቃውሟችንን በዚህ መልኩ ጋብ በማድረግ ያገኘውን ፋታ በመጠቀም እንዲሰራ አደራችንን እናስተላልፋለን፡፡ ያቀረብናቸው መሠረታዊ ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎቻችን አንዳቸውም በአጥጋቢ መልኩ ሊመለሱ ይቅርና ተገቢውን ትኩረት እንኳን ሳያገኙ እንደቀሩ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም እነኚህ ነገሮች አቅጣጫቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በሚፈልገው መስመር እየተጓዙ መሆናቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ እና ሕገ-ወጥ የመጅሊስ አመራር እና የኡለማ ምክር ቤት ተብየው በዚህ ሠዓት እንኳን ያሻቸውን እየሰሩ ባሉበት ሁኔታ ተቃውሟችን በዒድ አደባባይ የገኘውን አዲስ ጉልበት ተጠቅሞ የማይቀጥልበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም፡፡
ከአክብሮቱና አድናቆቱ የሚተርፈው በእጅጉ የምንጠብቀው መልካም ፍሬ ይሆን? ወይስ ያው ቀድሞ የነበረው በተሳሳተ አስተሳሰብ የታጀበውና በሙስሊሞች ላይ ያልተገባ ስያሜ በመለጠፍ እየደረሰ የነበረው ወከባ፣ እንግልት፣ ድብደባ እና እስራት? የሚለው በዚህ ሰዓት በብዙ ሙስሊሞች አእምሮ የሚመላለስ ዓብይ ጉዳይ ነው፡፡ እኛ እንደ ጨዋ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የመጀመሪያው አማራጭ ብቸኛውና አማራጭ የሌለው አማራጭ እንደሆነ አድርገን እንወስዳለን፡፡
በመጨረሻም በአሁኑ ሰዓት የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን የከበደ ኃላፊነት ተሸክሞ ሚናውን ለመወጣት ዝግጅት ላይ የሚገኝ አካል እንዳለ እየተሰማን ለዚሁ አዲስ የአመራር ኃይል መልካሙን ሁሉ እየተመኘን ለዚህና መሰል የመንግስት እንቅስቃሴዎች ቀኝ እጅ ለመሆን ያለንን ቁርጠኝነት ከወዲሁ ለመግለጥ እንወዳለን፡፡
አላሁ አዕለም፡፡

No comments:
Post a Comment