ኮሚቴዎቻችንና የኢማም አሕመድ ኢብን ሀንበል ጽናት
ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ
እ.ኤ.አ. በ833 ዓ.ል. የሙስሊሙ ዓለም ኸሊፋ በመሆን ስልጣን የተቆጣጠረው አል-ማእሙን በዘመኑ ለፈተና የተፈጠረው የሙዕተዚላ አንጃ የሚያራምደውን ርዕዮት በሰፊው ህዝብ ላይ ለመጫን ተነሳ፡፡ በተለይ “ቁርአን መኽሉቅ እንጂ ዘልዓለማዊ የአላህ ንግግር አይደለም” የሚለውን የሙዕተዚላ አቋም የማይቀበለውን ማንኛውንም አሊም አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት ቆረጠ፡፡ ለዚህም “ሚህና” የሚባል የሽብርና የፈተና ሸንጎአቋቋመ፡፡ በዚህ ሸንጎ ፊት ቀርቦ “ቁርአን መኽሉቅ ነው” የሚል ቃል ያልሰጠ አሊም በይፋ እንዲገረፍና ሀብቱ እንዲዘረፍ አወጀ፡፡
በዘመኑ የነበሩት ዑለማ በእጅጉ ተሰቃዩ፤ተገረፉ፡፡ በርካቶችም የኸሊፋውን ቅጣት በመፍራት “ቁርአን መኽሉቅ ነው” አሉ፡፡አንዳንዶችም ከሀገር ተሰደዱ፡፡ ታዲያ በዚያ የመከራ ዘመን ትክክለኛውን የአህሉ-ሱንና አቂዳ ለመጠበቅ ሰበብ ይሆን ዘንድ አላህ አንድ አስገራሚ ጀግና አስነሳ፡፡
ይህ ጀግና ታዋቂው አሊም ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል ነው (ረሒመሁላሁ ተዓላ)፡፡ኢማም ኢብን ሀንበል በማእሙን የ“ሚህና”ፈተና ሳይሸበር “ቁርአን ዘልዓለማዊየአላህ ቃል ነው፤ የአላህ ቃል“መኽሉቅ ነው” የሚሉ ሰዎች ከኢስላም አፈንግጠዋል” ብሎ ተናገረ፡፡ ኸሊፍ አል-ማእሙን ቃሉን እንዲያጥፍ ቢመክረው “እንቢ” አለ፡፡ በሹመት ቢያባብለውም በአቋሙ ጸና፡፡ በነገሩ የተናደደው አል-ማእሙን ኢማም ኢብን-ሀንበል በህዝብ ፊት እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ከዚያምወደ እስር ቤት ወረወረው፡፡ አል-ማእሙንከሞተ በኋላ የመሪነቱን ስልጣን የጨበጡትአል-ሙእተሲም እና አል-ወሢቅ የተባሉ ኸሊፋዎችም ኢብን ሀንበልን የሚችሉትን ያህል አሰቃዩት፡፡ ኢብን ሀንበል ግን ለቅጣት ሳይበገር በአቋሙ እንደጸና ቆየ፡፡
በ833 የተጀመረው የአል-ሚህና ፈተና ያበቃው በ848 ዓ.ል. አል-ሙተወኪል የተባለው ኸሊፋ ሲነሳ ነው፡፡ ይህኛው ኸሊፋ እውነተኛ ሙስሊም በመሆኑ የሚህናንሸንጎ ወዲያውኑ ነው የበተነው፡፡ ኢብን ሀንበልንም ከነበረበት እስር ቤት በማውጣት በክብር አኖረው፡፡ ለግርፋትና ለስቃይ ያልተበገረው ኢብን ሀንበል በታሪክ ፊት ታላቅ ሰው መሆኑም ተመሰረከረለት፡፡ እነሆ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) የተለኮሰው የእምነትና የእውነት ብርሃን የኢብን ሀንበልን ጽናትመሸጋገሪያ በማድረግ ወደኛ ዘመንም ደረሰ፡፡
*****
“ሀይማኖትን ልምረጥልህ” ባዮች ህዝበ ሙስሊሙን መፈተናቸው ከጥንትም የነበረ ነገር ነው:: በኢብን ሀንበል ዘመን የነበረው ፈተና መልኩን እየለዋወጠ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተከስቷል፡፡ በቅርብ ዘመን እንኳ ታላቋ ሶቭየት ህብረትና ሌሎች የኮሚኒዝም ደቀመዛሙርት ተራውን ህዝብ “ፈጣሪ የለም” በሚል ርዕዮት ለማጥመቅ ከፍተኛ ዘመቻ አካሂደዋል፡፡ ይሁንና የኮሚኒስቶቹ ራዕይ አንዳች ፍሬ ሳያፈራ የሚመጻደቁበት ኮሚኒስታዊ ፍልስፍናቸው ከነርሱ ቀድሞ ተንኮታኮተ፡፡ እነ ሙስጠፋከማል አታቱርክ “ለሀገራችን ኋላ ቀርነትመንስኤ የሆነው እስልምና ነው” በሚል ተረት ተነሳስተው ኢስላማዊውን ፋና ከ50-100 ዓመታት በሚሆን ዘመን ከምድረ-ቱርክ ለማጥፋት የሚያስችል ሰይጣናዊ ማስተር ፕላን ቢነድፉም ውጤቱ የተገላቢጦሽ ነው የሆነው፡፡ ሌላም ብዙ ምሳሌ መደርደር ይቻላል፡፡
*****
በሐምሌ 2003 ደግሞ የፈተናው እጣ ለኛ ደረሰ፡፡ ህዝብን እንዲያገለግሉ የተሾሙ ዋልጌዎች ከህዝብም ከህገ መንግስትም በላይ ሆነው ህዝበ ሙስሊሙን መተንኮስ ጀመሩ፡፡ “ወሃቢያ” ስለሚባለው ምናባዊ አውሬ የተለያዩ ወጎችን ማሰራጨት ጀመሩ፡፡ ከጋዜጣ ላይ የቃረሙትን ቅንጭብጫቢ ወሬ በመንተራስ “እስካሁን የቆያችሁበት እስልምና በጽንፈኝነትና በአክራሪነት የተሞላ ነው፡፡ ደግሞም ኋላቀርነት ስለሚበረታበት ለልማታችን አይበጅም፡፡ ስለዚህ ለዘመኑ እንዲስማማ ሆኖ የተዘጋጀ አሕባሽ የሚባል ዘመናዊ ርእዮት ከምድረ-ቤይሩት ስላስመጣንላችሁመጅሊስ ወደ ሚባለው ቢሮ እየቀረባችሁ እንድትጠመቁ ይሁን፣ ያልተጠመቀ ሰው በጸረ-ልማትና በጽንፈኝነት እንደሚፈረጅከወዲሁ እናስጠነቅቃለን” የሚል አዋጅ አስነገሩ፡፡
ህዝባችን ይህንን ህገ-ወጥ አዋጅ በህጋዊመንገድ ለማስቀልበስ እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡ በጥር ወር አጋማሽ ላይ ጥያቄዎቹን ለመንግስት የሚያቀርቡ ተወካዮቹን በመምረጥ ወደሚመለከተው አካል ሰደዳቸው፡፡ ውጤቱ ግን “እምቢታ”ሆነ፡፡ ሙስሊሙን ያለ ግብሩ “አክራሪ፤ ጽንፈኛ” እያሉ ማስፈራራትና መክሰስም ተጀመረ፡፡ በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ ንጹሃን ሰዎች በጥይት ተገደሉ፡፡ በመላውሀገሪቱ በርካቶች ወደ ከርቸሌ ተወረወሩ፡፡ ይባስ ብሎ አዋጁን ያወጁት አካላት በሚሊዮኖች ፊርማ የተወከሉትን የሀገር ሽማግሌዎችና ምሁራን “ህዝቡ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን እንዲገለብጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ አድርጋችኋል” የሚል የፈጠራ ክስ በመደረት በዘመነ ቀይ ሽብር የቅጣት ትርኢት ማሳያ ዓይነተኛ ቦታ በሆነው “ማዕከላዊ ምርመራ” አጎሯቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘትከገጠመው “የጸረ-ሽብር” ህግ የተለያዩ አንቀጾች እየተመዘዙ የሞት ፍርድ ወይም የእድሜ ልክ እስራት አሊያም የ15 ዓመት እስራት ወዘተ… እንዲፈረድባቸው የችሎት ሸንጎ ተጀመረ፡፡
*****
ወገኖቼ! ኢስላማዊው የህይወት ጎዳና ከተቀየሰበት ጊዜ አንስቶ ሙእሚን እንደተፈተነ ነው፡፡ ፈተናውን በብቃት ከተወጣ በዚህኛው ዓለምም ሆነ በመጪው ዓለም ከፍተኛ ሽልማት ይጠብቀዋል፡፡ ፈተናውን ከወደቀ ግን “ለካስ ‘በአላህ አምናለሁ፣ ለፈተና አልንበረከከክም’ የምትለው ሰውየ እንዲህ ሀሞተ ቢስ ኖረሀል!” ተብሎ ከቃል አባዮች ተርታ ይመደባል፡፡ በወዲያኛው ዓለም ደግሞ ሌላቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ ስለዚህ በአሕባሽ ተመስሎ የተቀሰቀሰውን ፈተና ወድቀን ከቃል አባዮች ጋር እንዳንሰለፍ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡ ፈተናዎችን በብቃት ለመወጣት እንዲቻለንም በአርአያነታቸው የሚጠቀሱ አውራዎችን መከተል አለብን፡፡ አሁን ከገጠመን ፈተናአንጻር ተገቢ አርአያ ሊሆነን የሚችለው ደግሞ ጀግናው ምሁር ኢማም አሕመድ ኢብን ሀንበል ነው፡፡ ለአስራ አምስት ዓመታት ለግርፋትና ለጉንተላ ሳይበገር ትክክለኛው የአህሉ ሱንና አቂዳ ወደኛ እንዲተላለፍ ሰበብ ከሆነልን ኢብን ሀንበል ወዲያ አርአያ ሊሆነን የሚችለው ማነው? ማንም!
*****
ኮሚቴዎቻችን ያለ ጥፋታቸው ታስረውብናል፡፡ ነገር ግን ፊት ከተነሱለት ዓላማም ሆነ ይከተሉት ከነበረው ርዕዮት ፍንክች አላሉም፡፡ በእስር ቤት ግርፋትና እመቃ ቢደርስባቸውም እስካሁን ድረስ ከጥንቱ መንገዳቸው አልተገለበጡም፡፡ በመሆኑም የኢማም አሕመድ ኢብን ሀንበል ጀግንነት በነርሱ ውስጥም እየታየ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ኢብን ሀንበል በመጨረሻው ላይ“ጀግና የህዝብ ልጅ! ትክክለኛው የኢስላም ጠበቃ!” ተብሎ በመቶ ሺሕ ህዝብአቀባበል እንደተደረገለት ሁሉ የኛዎቹ ኮሚቴዎችም ፈተናዎቹን ሁሉ በብቃት በመወጣት “የጀግኖች ጀግና” ተብለው የሚወደሱበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡ ኢንሻአላህ! በኢብን ሀንበል መንገድ ላይ በጽናት እንዲያቆማቸው ዱዓ እናድርግ፡፡ የኢብን ሀንበል መንፈስ በሁላችንም ውስጥእንዲሰርጽ ጌታችንን እንለምነው፡፡
ድል የኢስላም ነው!

No comments:
Post a Comment