የአኒቲ ብሎግ Aniti's Blog: ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው: Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind First Audition የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳ...
Friday, October 12, 2012
ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው
Invisible journalist asking
question through Magnetic Force of the mind
First Audition
የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው
ቅፅ ፻ የእንግዳችን ፕሮግራም አምድ ላይ ተጋባዥ ያደረግነው የጭንቅ ቀን ደራሹ የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ ከሆነው ሳላሀዲን ሰዒድ
ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
የእምነት ነፃነት መፅሄት፡ ሳላሀዲን መቼም በዚህ
አጭር ግዜ ውስጥ (ልምምድ ላይ እንደመሆንህ መጠን) ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ሆነህ ስለመጣህ እያመሰገንን በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን
ስም እንኳን በደህና መጣህ ለማለት እንወዳለን፡፡
ሳላሀዲን፡ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ የመጀመርያ
እንግዳም ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡
ጥያቄ፡ ሙስሊም እንደመሆንህ መጠን የመጅሊስ ምርጫ
በቀበሌ መባሉን እንዴት ነበር ያየህው?
ሳላሀዲን፡ በግልምጫ፡፡
ጥያቄ፡ ለምን?
ሳላሀዲን፡ ምክንያቱም ድርጊቱ በመረብ ኳስ ሜዳ
ላይ ጎል ተክሎ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን የመጫወት ያህል ነው፡፡
ጥያቄ፡ የመንግስት አካላት ምርጫው በቀበሌ መሆኑ
ህገመንግስቱን አይፃረንም ባዮች ናቸው አንተ ምን ትላለህ?
ሳላሀዲን፡ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆንኩ የመረዳት
አቅም የለውም በእግር ማሰብ አይደለም እንደማትለኝ እያመንኩ፡፡ ይህ ቀላል ጥያቄ ነው በሚቀጥለው ምርጫ 2007 የመንግስት ተወካይን
ለመምረጥ የሀገሪቱ ህዝብ በመስጊድ እና በቤተክርስታን ማከናወን እንደሚችል ቃል ከገቡና በምርጫ ቦርድ ወይም በፓርላማው እንደ አንድ
ፖሊሲ ካፀደቁት ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡
ጥያቄ፡ በሌላ መንገድ እምነት እና ፖለቲካን (ሰርግና
ሞት አንድ ነው ጨፍር ምንድነው) እንደሚለው የሀገራችን ቢሂል ካደረጉት እንደማለት ነው?
ሳላሀዲን፡ አግኝተህኛል (ፈገግታ.. )
ጥያቄ፡ እንዴት ነው ህዝቡ እንደምታውቀው በሰላማዊ
መልኩ ተቃውሞውን ላለፉት 11 ወራት ሲያካሂድ ነበር እንዴት ነው አንተስ ድምፅህን የምታሰማበትን አጋጣሚ ነበረህ?
ሳላሀዲን፡ በእርግጥ እንደዛ አይነት አጋጣሚን
አላገኘሁም ብዙን ግዜ ጌሞች ስለሚደራረቡብን እና ከካንፕ የምንንቀሳቀስበት ግዜ በትሬኒንግ የተጨናነቀ እንደመሆኑ መጠን ምንም አላገኘሁም፡፡
ነገር ግን በውስጤ ሁሌም እፀልያለሁ፡፡
ጥያቄ፡ እንደ አንደ የሀገራችን የእምነቱ ተከታይ
ብሎም ታዋቂ እንደመሆንህ መጠን ተቃውሞህን ለማሰማት ያሰብከው ነገር አለ?
ሰላሀዲን፡ ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ፡፡ በእርግጥ
ቀደም ብዬ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ብዙ አይነት የመቃወሚያ መንገድ እንደመኖሩ መጠን እኔ እስካሁን ሳደርገው የነበረው ፀሎት ወይም
ዱዓን ነበር፡፡ ፈጣሪ ከተበዳዮች ጎራ እንደሚቆም አልጠራጠርም፡፡
ጥያቄ፡ ሌላ ለማድረግ የፈለግከው ነገር እንዳለ
ከጓደኞችህ ሰምቻለው፡፡ ተቃውሞህን ለማሰማት ወሳኙ በሆነው በነገው ጫወታ ላይ፣ በሱዳን አቻችሁ ላይ ጎል እንዴት ነው አላስቆጥርም
ብለህ ነበር እንዴ?
ሰላሀዲን፡ በፍፁም! በፍፁም! ይሄ የአንዳንድ ካድሬ
የቤህራዊ ብድናችን ተጫዋቾች አስተሳሰብ ነው፡፡ አንተም ሆንክ እነሱ ግን ለመስማት ከፈለክ፣ እኔ እንደ ማንኛውም ሙስሊም የሀገርን
ህልውና እና ሠላምን በማይረብሽ ብሎም እንዲሁም ልክ እንደ ሌሎች የሀገሬ ሙስሊም ወጣቶች ተቃውሞ ኮሽታን
በማያሰማ አካልን ሳይሆን ልብ ያለው እእምሮ ላለው ጨቋኝነን በሚቆረቁር መንገድ ነው የማሰማው፡፡ እንደወትሮው ከቻልኩኝ ከአንድም ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ጥረት አድርጌ ባገባሁ ቁጥር ሀዘኔን እና
የሙስሊሙ ጉዳይ እኔንም እንደ አንድ ሙስሊም የሚያሳስበኝ እንደሆነ ለመግለፅ፡፡ አግብቼ የማልፈነድቅ ወይም የማልሮጥ ሲሆን ወደ
መሬት ሱዱጅ በመውረድ ተቃውሞዬን የምገልፅ ይሆናል፡፡ ይሄው ነው፡፡
ጥያቄ፡ መልካሙን ሁላ እየተመኘንልህ በመጨረሻ
የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ እድሉን ልስጥህ፡፡
ሳላሀዲን፡ አመሰግናለሁ ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድናችን፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመንግስት
ለእምነት ነፃነት ጥያቄያ ድምፃችን ይመጣ ዘንድ ምኞቴ እና መልዕኬቴ ነው፡፡
My own art to tell you the point
My own art to tell you the point
ከጫወታው አንድ ቀን በፊት
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››በህልሜ ካዋራኝ የተወሰደ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹
No comments:
Post a Comment