• ትግሉ አልቆመም፤ አይቆምም!!!
• ጽንፈኞቹን ‹ሠላም› በተባለ በማያውቁት ሜዳ እንፋለማቸዋለን
• ከእስካሁኑ የትግል መንገድ ላይ የቀሩንን 998 መንገዶች አንድ በአንድ እየጨመረን ያለመታከት እንታገላለን
• ትግላችን ውጤታማ አይደለምን?
• የቢጫና ቀይ ትርጉም ምንድነው?

የትግላችንን ፍሬ እለት ተዕለት እያየን ነው፡፡ የልፋትን ውጤት ጌታችን እያሳየን እየረካን ነው፡፡ ሆኖም፤
ጥያቄያችን ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ ከቶም አናፈገፍግም፡፡ ጥያቄችን እንዳይመለስ ነክሶ የያዘው የመንግስት አካል
የሠለጠነው በረብሻ ነው፡፡ እኛ ግን የሠለጠንነው በሠላም ነው፡፡ በሠላም እያሸነፍን ነው፡፡ በሰላም በመታገላችን
የአህባሽ ጠመቃው እጅግ በጣም ቀንሷል፡፡ ሰላማዊ በመሆናችን በኛና በኃይማኖታችን ላይ የሚደረገውን ፕሮፓጋንዳ
አሸንፈናል፡፡ በሰላም በመታገላችን ‹‹መጅሊስን መቃወም መንግስትን መቃወም ነው›› ብሎ ሲያቅራራ የነበረው መንግስት
ሳይወድም ቢሆን ምርጫ መሰል ቅርጫ ለማካሄድ ተገዷል፡፡ እንዲያውም የተከበሩ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአደባባይ
እንደነገሩን የልማት ስራ እንኳ አቁመው ጉዳያችንን ሲያቦኩ ከርመዋል፡፡ መጀመሪያ ግን ‹‹እነ አህመዲን ጨሎ ሕጋዊ
ናቸው›› የሚል አጉል ክርክር ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው? ስለሁሉም አላህ የተመሰገነ ይሁን፡፡
በሐገራችን እየተለመደ የመጣ የፖለቲካ ድራማና ተውኔት አለ፡፡ ተውኔቱ በመንግስትና በተቀናቃኞቹ መካከል ሲካሄድ ተመልክተናል፡፡ የመንግስት ተቀናቃኞች የሚሠሯቸው ድራማዎች እንዳሉ ሆኖ መንግስትም አንድ ነገር መንሳት ሲፈልግ የሚሠራቸውን ተውኔቶችም በደንብ ተለማምደናቸዋል፡፡ ሕገ-ወጦችን በመጅሊሳችን አስርጎ ለዓመታት ቆየ እኛ ግን ‹‹እምቢ›› አልን፤ ጊዜው ደርሶ እነዚህን ሕገ-ወጦች ‹‹አንፈልግም›› ስንል ‹‹አክራሪ፣ እስላማዊ መንግስት፣ ቅብጥሴ›› ሲል ሊሸውድ ሞክሮ በብልጠትና በሠላም ውንጀላውን ከንቱ አስቀረንበት፡፡ አሁን ‹‹ቅርጫ በቀበሌ›› የተባለ ትያትሩን ሞክሯል፡፡ ይሄ ቅርጫም ለአስር ወራት ባደረግነው ፍጹም ሰላማዊ ትግል ድል በድል እንደሆንነው ሁሉ አሁንም በሠላማዊ ትግላችን ሕገ-ወጥነቱ ተረጋግጦ ፉርሽ እንደሚሆን ቅንጣት አንጠራጠርም፡፡ መንግስት ‹‹ምርጫችን በመስጂዳችን›› ስንል ‹‹ምርጫዬ በቀበሌዬ›› ብሎ በፖለቲካው ሜዳ ላይ የራሱን አጫፋሪ ፖለቲከኞች መርጧል፡፡ ስለዚህ፤ ምርጫው ‹የሙስሊሙ› ሊባል እንደማይችል እኛም እነሱም ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ሆኖም፤ መንግስት ‹‹ካፈርኩ አይመልሰኝ›› የሚል ልዩ ባሕሪ እንዳለው ስለምናውቅ ዛሬም እንደትናንቱ ‹‹ምርጫ ጠየቃችሁ፤ ይኸው ተመረጠ›› በሚል ቅርጫውን ለተጨማሪ ጭቆናና የመብት ጥሰቱ እንደምክንያት ሊጠቀመው እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ እስከመጨረሻው ድረስ በሰላም እንታገለዋለን፡፡ እናሸንፋለንም፤ መብታችንንም እንጎናጸፋለን-ኢንሻ አላህ፡፡
እኛ ማለት -ማለት- መሠረታቸውን በዋናነት አዲስ አበባ ያደረጉ የፖለቲካ ቡድኖች በሄዱበት መንገድ ልንሄድ እንደማንችል ትንሽ እንኳ ማሰብ የሚችል ሁሉ ይረዳዋል፡፡ ምክንያቱም፤ እኛ ሠፊ ሕዝብ እንጂ ፓርቲ አይደለንም፡፡ ምክንያቱም፤ እኛ መሠረታችን መላው ኢትዮጵያ እንጂ የሆነ ከተማ አይደለም፡፡ ምክንያቱም፤ አጀንዳችን የምንሞትለት ሃይማኖት እንጂ ፖለቲካ አይደለም፡፡ ስለዚህ፤ በየትኛውም የማምታታት ድራማና የማስፈራራት ዘመቻ አንረታም፡፡ መንግስት በጉልበቱ መታበዩ አውሮት እንጂ ሕዝብ የሚያዳምጥበት ትንሽዬ ጆሮ እንኳ ቢኖረው ኖሮ የዒድ ዕለት እንኳ ያዳምጥ ነበር፡፡
አይቀርም፤ እልህ አስጨራሽ ቢሆንም በሠላማዊ ትግላችን መብታቸንን ሙሉ በሙሉ ይከበራል፡፡ ሠላማዊ ትግል 1 ሺ አንድ መንገዶች አሉት፡፡ አስካሁን የተጠቀምነው ሶስቱን ብቻ በመሆኑ ገና ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት (998) ያልተነኩ ውጤታማ ዘዴዎች ይቀሩናል፡፡ ከእስካሁኑ የትግል መንገድ ላይ የቀሩንን 998 መንገዶች ጨምረን ያለመታከት እንታገላለን፡፡ የኮሚቴዎቻችንን ፈለግ ተከትለን መብታችንን እንጠይቃለን፡፡ መንግስት እስር ካዋጣው 40 ሚሊዮናችንንም አስሮ ይሞክረው፡፡
ቅርጫው ተቀባይነት የለውም፡፡ በቃልም በተግባርም ይህን አቋማችንን አሳውቀናል፡፡ ነጭም ቢጫም አሳይተናል፡፡ መንግስትን በቢጫ ካርድ አስጠንቅቀናል፡፡ አንዳንዶች ‹‹ቢጫው ትርጉሙ ምንድነው? ከቢጫው ቀጥሎ የሚታየው ቀይ ካርድስ ምን ለማለት ነው?›› የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡ ጽንፈኞቹ የመንግስት አካላትም ‹‹ቀዩ ሳይመጣ ቀይ እናሳይ›› ይሉ ይሆናል፡፡ የነሱ ቀይ ትርጉሙ ደም ማፋሰስ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ግን፤ ለሁሉም ማረጋገጥ የምንሻው ትግላችን መቼም ወደ ደም ማፍሰስ አያመራም፡፡ ጽንፈኞቹ የመንግስት ሹማምንት ቢፈልጉ እንኳ ወደ ሁከት አንገባም፡፡ እነዚህን ጽንፈኞች ‹ሠላም› በተባለ በማያውቁት ሜዳ እንፋለማቸዋለን፡፡ ትግላችን ቀለሙ እየተቀየረ ሲሄድ መነሻው ምናልባትም በመጪው ግንቦት በሚካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማሟያ ምርጫ ላይ ወጥ አቋም በመያዝ ኢህአዴግ ከመቅጣት አንስቶ ከፍ እያለ ሊሄድ ይችላል፡፡

No comments:
Post a Comment