Tuesday, October 2, 2012

ህገወጥ ተግባር አንፈፅምም፤ የሚፈፅሙትንም በዝምታ አንመለከትም!

ድምፃችን ይሰማ
ዛሬ ላይ ይህ እውነት አይን አውጥቶ ታሪክ የማይረሳው የህግ ጥሰት እየተሰራ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገመንግስት አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ በወርቃማ ቀለም እንዲህ ሲል ያትታል ‹የሃይማኖት ተከታዮች ሀይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ› ድንቅ መብት ነው፡፡ ይህንኑ መብት በመጠቀም ለመንግስት የደህንነት ስጋት የማይሆን ለህዝበ ሙስሊሙም በቅንነት የሚያገለግል ሃይማኖታዊ አስተዳደር ይኑረን ብንል ምላሹ ብሶት የሚወልድና ዘመን ተሻጋሪ ቁስል የሚፈጥር እየሆነብን ነው፡፡

ተግባሩ ግን የህገመንግስት ጥሰት በመሆኑ በፍፁም በዝምታ አናልፈውም፡፡ የኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 እንደሚያትተው ‹ማንኛውም ዜጋ፤ የመንግስት አካላት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣኖቻቸው፤ ህገ መንግስቱን የማስከበርና ለህገመንግስቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው› ይላል፡፡ ለማንም የማይከብድ ግልፅ አንቀፅ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን ከማንም በላይ ህገመንግስቱን ለማክበርና ለማስከበር የስራ ቅጥር ፎርም ሲሞሉ ፈርመው ውል የገቡ ካድሬዎችና ሰራተኞች ቅጥራቸውና ውላቸው ህጉን ለመናድ እስኪመስል ቀይ መስመሩን እየረገጡት ይገኛሉ፡፡
 
የመንግስት ድብቅ አጀንዳ እነሆ በገሃድ ተጋለጠ
ህገወጥ ተግባር አንፈፅምም፤ የሚፈፅሙትንም በዝምታ አንመለከትም!
ፅሁፋችንን በክቡር አቶ ሙሉጌታ ውለታው የፌዴደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በሬዲዮና ቴሌቪዥን ንግግር እንጀምር፡፡ ‹‹የመጅሊስ የምርጫ ቦታን በተመለከተ ህዝቡ በፈለገው ቦታ ማድረግ መብቱ ነው፡፡ ቢፈልግ በቀበሌ ያድርግ፤ ቢፈልግ በመስጂድ ያድርግ፤ የመንግስት ስልጣንና ላፊነት ይህንን የህዝብ ፍላጎት ማስከበር ነው››፡፡ ምን ያማረ ንግግር ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ በመላ ሃገሪቱ በሚደንቅ አንድነትና ጥንካሬ በዒድ አደባባዮች ‹‹ምርጫችን በመስጂዳቸን፤ ሳይፈቱ ምርጫ የለም›› ሲል ድምፁን አሰማ፡፡


በየትኛውም የሃገራች ን ክፍል ‹‹ምርጫችን በቀበሌያችን›› ያለ አንድም የለም፡፡ እነሆ ምርጫው ግን በቀበሌ ለማድረግ የሽፍታ ስራ ተጀምሯል፡፡ ሰላማዊ የህዝብ ድምፅ ምን ያህል እየተናቀ እንደሆነ ከዚህ በላይ ምንም ማስረጃ ማቅረብ አያሻም፡፡ መንግስት እኛን ድብቅ አጀንዳ አላቸው እያለ ሲያሸማቅቅ ከርሞ ከመጅሊስ ምርጫ ጀርባ ያሴረው ድብቅ አጀንዳው በገሃድ ተጋልጧል፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ ለሰሚው ግራ የሆነ ግራ የገባው ስራ ምርጫን አስታከው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መምረጥም ሆነ መመረጥ ህገመንግስታዊ መብት እንደሆነ ሁሉ አለመምረጥ እና አለመመረጥም ህገመንግስታዊ መብት መሆኑን በመናድ አስፈፃሚዎች በጠራራ ፀሃይ እያሳዩን ነው፡፡ ቀድሞም ምርጫውን የኡለማ ምክር ቤት ነው የሚያስፈፅመው ሲባል ህጋዊ ስልጣኑም ሆነ መዋቅራዊ ብቃቱ ስለሌለው ከጀርባ ማን እንደተሰገሰገ ግልፅ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ይህ እውነት አይን አውጥቶ ታሪክ የማይረሳው የህግ ጥሰት እየተሰራ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገመንግስት አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ በወርቃማ ቀለም እንዲህ ሲል ያትታል ‹የሃይማኖት ተከታዮች ሀይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ› ድንቅ መብት ነው፡፡ ይህንኑ መብት በመጠቀም ለመንግስት የደህንነት ስጋት የማይሆን ለህዝበ ሙስሊሙም በቅንነት የሚያገለግል ሃይማኖታዊ አስተዳደር ይኑረን ብንል ምላሹ ብሶት የሚወልድና ዘመን ተሻጋሪ ቁስል የሚፈጥር እየሆነብን ነው፡፡ የመንግስትን መደበኛ ስራ እርግፍ አድርገው በመተው ደመወዛቸው የሚከፈላቸው ሙስሊሙን በማሳቀቅና በማንገገላታት እስኪመስል ድረስ ከወረዳ እስከ ክፍለከተማ ያሉ አመራርና ሰራተኞች መፈክራቸው ሁሉ ‹‹የቀበሌውን ምርጫ ባትመርጥ ወየውልህ›› ሆኗል፡፡ ይህ በመንግስት መደበኛ ምርጫ ላይ እንኳን ባልታየ ፅናትና ቁርጠኝነት የመንግስት ካድሬዎች ለመጅሊስ ምርጫ እንዲህ ቀን ከሌት መሮጥ ‹‹ስለምን›› ያስብላል፡፡ ተግባሩ ግን የህገመንግስት ጥሰት በመሆኑ በፍፁም በዝምታ አናልፈውም፡፡ የኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 እንደሚያትተው ‹ማንኛውም ዜጋ፤ የመንግስት አካላት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣኖቻቸው፤ ህገ መንግስቱን የማስከበርና ለህገመንግስቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው› ይላል፡፡ ለማንም የማይከብድ ግልፅ አንቀፅ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን ከማንም በላይ ህገመንግስቱን ለማክበርና ለማስከበር የስራ ቅጥር ፎርም ሲሞሉ ፈርመው ውል የገቡ ካድሬዎችና ሰራተኞች ቅጥራቸውና ውላቸው ህጉን ለመናድ እስኪመስል ቀይ መስመሩን እየረገጡት ይገኛሉ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ምርጫው በተጠየቀው መልኩ በነፃ አስመራጮችና በመስጂድ መሪዎቼ ተፈትተው ነው መካሄድ ያለበት በሚል ድምፁን ቢያሰማም ሰሚ ማጣቱ ነገ መዘዙ የከፋ እንደሚሆን እሙን ነው፡፡ ድምፁ አልሰማ እንኳን ቢል በህገወጥ ምርጫ አልሳተፍም ለሚለው አቋሙ አፀፋው የቤት ለቤት አሰሳ፤ ዛቻና ማስፈራሪያ ሆኗል፡፡ ህገመንግስታችን በአንቀፅ 26 ንዑስ አንቀፅ1 ላይ ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ፤ ግላዊነቱ፤ የመከበር መብት አለው ይለናል፡፡ ዛሬ ላይ ግን የቀበሌ ፋይል እየተፈተሸ በስልክ እየተደወለ ‹‹የምርጫ ካርድ የማትወስድ ከሆነ ወየውልህ› እየተባልን ነው፡፡ የመኖሪያ ቤታችንንና የስራ ቦታችን በካድሬዎች መመላለስና ማስፈራራት ግላዊነታችን ተጥሶ የግል ህይወታችንን በአቋማችን መምራት እየቻልን አይደለም፡፡ በዚሁ አንቀፅ የመኖሪያ ቤት ከመመርመር የመጠበቅ መብት የተደነገገ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግቢያችን ቀርቶ ጓዳችን ውስጥ የፈለግነውን አቋም እንዳንይዝ ‹‹ይህን ለምን አሰብክ፤ ይህንንስ ለምን ሰራህ›› እየተባልን የህግ ጥሰት እየተፈፀመብን ነው፡፡ አሁን ላይ የሚታየው የመጅሊስን ሹማምንት በህገወጥ መንገድ ማምጣት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብት በህገወጥ መንገድ መንጠቅ ነው፡፡ ህዝብ ደግሞ ክቡር ነው፡፡ ይህን መሰሉን የህግ ጥሰት ተሸክሞ የሚዘልቅበት ጊዜ ማለቁ አይቀርም፡፡ ያኔ በነሱ አጠራር ‹‹እነዚህ ሰዎች አሁንስ ጠነከሩ፤ በዚህ ከቀጠሉ አደጋ አለው›› የሚሉት ክስተት ላለመፈጠሩ ምንም ዋስትና የለም፡፡ ይህ ከመፈጠሩ በፊት የዜጎች መብት ሳይሸራረፍ ይከበር እንላለን፡፡ የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ከግብራችን የምንከፍላቸው ለቀጠርናቸው ሃላፊነት እንጂ በጓዳችን እየመጡ እንዲያስፈራሩንና እንዲዝቱብን አይደለም፡፡ የመስከረም 27 ምርጫ በየትኛውም መመዘኛ ሲታይ ህገወጥ ነው፡፡ አንዳንዶች ብልህ ልጅ የያዘውን ይዞ ነው የሚያለቅሰው በሚል ሆድ አደር አስተሳሰብ ምርጫውን መሳተፍ ተገቢ እንደሆነ በዘዴ ያስፈራሩናል፡፡ የጠየቅነው ትርፍ ነገር ሳይሆን ለሃገርና ለህዝብ የሚበጅ የመጅሊስ አስተዳደር በህዝብ ፍላጎት ይመረጥ በመሆኑ ያንን ማንም ሸራርፎ እንዲሰጠን አንፈልግም፡፡ ህገመንግስታዊ መብትን ለማስከበር የዜግነት መብታችንን ማስከበራችን አይቀርም፡፡ ይህንን ደግሞ ሁላችንም የምናየው ይሆናል፡፡ ሃይማኖታዊ ጨዋነታችን፤ የሰላማዊነት ታሪካችንንና የአሁን ማንነታችን ሰላማዊ እንድንሆን ቢያደርገን ይህን ያልተረዱ አካላት ግን ሰላማዊነታችንን ደካማነት አድርገው እየቆጠሩት ይገኛሉ፡፡ ታጋሽነትን መርጠነው እንጂ ለፍጡር ማጎብደድ ከእምነታችንም ከታሪካችን አልወረስንም፡፡ አናደርገውምም፡፡

No comments:

Post a Comment