- ማለቂያው ያልታወቀው የመጅሊስና ዑለማ ም/ቤት ሕገ-ወጥነት
- ምርጫው ክስ ተመስርቶበታል
በብዙ አሳዛኝ መስፈርቶች ግምባር ቀደም በመሆን የሚታወቀው ህገ-ወጡ ዑለማ ም/ቤትና መጅሊስ ዛሬም ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል፡፡ ሕገ-ወጡ ምርጫ ሕገ-ወጥነቱ ሳያንሰው የጉልበት የምርጫ ካርድ ስርጭት ወይም ብተና ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ዳሩ ግን፤ ህዝበ-ሙስሊሙ በማታለያም ሆነ በማስፈራሪያ ካርዱን አልወስድም ብሏቸዋል፡፡ ሆኖም፤ በአጭር መንገድ ወደ ስልጣን ለመምጣት የቋመጡ ጥቂት ግለሰቦች ለመንግስት ባቀረቡት አቤቱታና ልመና ቅርጫው በታቀደው መሠረት መስከረም 27 ሊካሄድ ተወስኗል፡፡ በዚህ አሳዛኝ ድርጊት አፍረን ሳንጨርስ ሌላ አስገራሚ ዜና ተጨምሮልናል፡፡ ይኸውም፤ ሕዝቡ ‹‹በቅርጫው አልሳተፍም›› ማለቱ ያስጨነቃቸው አካላት የቅርጫ ካርድ መውሰጃ ጊዜውን እስከ መስከረም 26 ከምሽቱ 11፡30 ድረስ ማራዘማቸው ታውቋል፡፡ አላሁ አክበር!!!
በየትኛውም ደረጃውን የጠበቀ ምርጫ ይሄ አይነቱ ተግባር አይፈጸምም፡፡ በሚሊዮኖች ለሚሳተፉበት ሐገር አቀፍ ምርጫ የተመራጮች ማንነት ሳይታወቅ፣ መራጮች ሳይመዘገቡ፣ ሕግና ስርዐት ሳይከበር የሚደረግ ምርጫ ሕገ-ወጥ ነው፡፡ እንዴት ሆኖ ነው ለእሁድ ጠዋት ምርጫ እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ ካርድ የሚታደለው? ይህ ተግባር ብቻውን ይሄን ቅርጫ ሕገ-ወጥ አያደርገውምን?
በርግጥ የመስከረም 27ቱ ምርጫ ሕገ-ወጥ መሆኑን ሰፊው ሕዝበ-ሙስሊም ሲናገር ሰንብቷል፡፡ ነገም ይደግመዋል፡፡ መጅሊስና ዑለማ ምክር ቤትም ከዚህ ሕገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታገዱ ከኮሚቴዎቻችን በተገኘ ውክልና በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ውጤቱን እየተጠባበቅን ነው፡፡ አላህ መልካሙን ሁሉ ያሰማን!!! አላሁ አክበር!!!

Read Full Court Document
No comments:
Post a Comment