Ibn Teymiyyah በኢብንተይሚያሕ (አልሐበሽይ) Facebook
part 1
እጅግ አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም
ዓላማ
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የመጣውን ፈተና ለመቀልበስና ለመታገል በመረጃ የተመሰረተና ሠላማዊ የሆነ፣ውጤት ተኮር የሆነ አቅጣጫን የሚከተልና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ሙስሊም ማህበረሰብን በመፍጠር ኢስላምን መጠበቅና ሙስሊሙን ከክስረት መታደግ፡፡
ግብ
በእውቀት ላይ የተመሠረተ ለዲኑ ተቆርቋሪና ታማኝ ሙስሊም ማህበረሰብን በመፍጠር በኢስላምና በሙስሊሙ ላይ የተነጣጠረውን መቅሰፍት አቅጣጫ በማዞር ትርፋማ ውጤትን ማስመዝገብ፡፡
መግቢያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ህብረ ብሔሮችና ሃይማኖቶችን አቅፋ የምትገኝ እንደሞሆኗ እነዚህን ህብረ ብሔሮችና ሐይማኖቶች ያስተናገደችባቸው ሁኔታ ግን አሉታዊ ጎኑ ያመዘነ ነበር ነውም።ከእምነቶች ስብጥር ብንመለከት ኢስላም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሺህ ዓመት በላይ የኖረና እንደሌሎች ዓለሞች ሁሉ በሠላማዊ መስመር የተስፋፋ ፍኖት ነው።ይሁን እንጅ ይህ ዲን ዛሬ ላይ ከመድረሱ በፊት የዛሬው ትውልድ ኩፍያ አሊያም ኢማማውን ለብሶ በራስ መተማመን ይሔድ ዘንዳ የትላንት አባቶቹ ዘርፈ ብዙ መሰዋዕትነትን ከፍለውበታል።እልፎች ደምና አጥንታቸውን ገብረውለታል።እልፍ አእላፍ አጥንቶች ተከስክሰውለታል። ዛሬ እኔና እርሰዎ ቀና ብለን ሙስሊም መሆናችንን እናውጅ ዘንዳ የፀረ-ኢስላማውያኑ የሰይፍ ስለት መሞከሪያ ሆኖ ዲኑን ማስቀጠልን በጠየቀበት ዘመን ለህይዎታቸው ሳይሳሱ ደምና አጥንት ገብረዋል።
እናም ይህ ዛሬ በሀገራችን ውስጥ እየታየ ያለው ፍፁም ኢ-ዲሞክራሲያዊ የጭፍለቃ አካሔድ በዚሁ ከቀጠለ ሀገራችን ምናልባትም ኢስላምን ለአንደዬና ለመጨረሻ ጊዜ ታጣዋለች አሊያም እንደ ትናንት አባቶቻችን ታቦት ሸኚ ብቻም ሳይሆን የፕሮቴስታነት ኃይሎች መቀለጃና መጫወቻ ሆነን በቁማችን መሞታችን አይቀርም።ስለሆነም አሁን ያለውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሔድ የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ ሓይላትን ሰላማዊና ፍፁም ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመታገል ዲናችንን የመጠበቅ ሀላፊነት እዚህ ትውልድ ላይ ወድቋል።ስለዚህም አሁን የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል ለማስቀጠልና ሁላችንም በያለንበት የሚጠበቅንን ሚና እንጫዎት ዘንድ በሚል ይህ መነሻ ፅኁፍ የተዘጋጀ በመሆኑ ህዝቡ በያለበት እንደተጨባጭ ሁኔታው እያሻሻለና እያረመ ይጠቀምበት ዘንድ አደራ እያልን፡፡ይህ ፅሁፍ በህዝበ -ሙስሊሙ ተመርጦ የነበረው ኮሚቴ ያዘጋጀው አለመሆኑን እያሳወቅን በፅሑፉ ውሥጥ ለሚገኙ ማናቸውም ግድገቶች ኮሚቴው የማይኮነን መሆኑንም አበክረን እናሳውቃልን።
አሁን ያለውን ሀገር አቀፍ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ለምን እንደግፈዋለን?
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለተለያዩ በደሎችን እያስሰተናገዱ የኖሩ ህዝቦች እንደመሆናቸው ለሚያጋጥማቸው ችግር ሁሉ መፍትሔ ማፈላለግ የሚችሉ ህዝቦች አልነበሩም።የሚያጋጥሙትን መሰረታዊ ችግሮች እንኳን የሚረዱትና ግንዛቤ የሚኖራቸው በቁጥር እጅግ በጣም ትቂቶቹ ሲሆኑ ብዙሀኑ በመሀይምነት የተዋጡ ማህበረሰብ ስለነበሩ ለዲናዊ እንቅፋቶች ምላሽ የሚሰያጥ አቋም ላይ አልነበሩም።ይህ በትቂቶች ዘንድ ብቻ ተሸብቦ የቀረው እውቀትና ግንዛቤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለብዙሀኑ መታወቅና መሠረታዊ የሚባሉ የዲን እውቀቶችን ህዝበ-ሙስሊሙ እንዲያውቅ በመደረጉ ይብዛም ይነስም ማህበረሰቡ ኢትዮጵያዊነትን እንደ ስጦታ ሳይሆን እንደ መብት መቁጠር ጀምሯል።ይሁን እንጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ከሚደርሱ አቢይ ኢኮኖሚያዊ፣ፓለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች መካከል ምንም እንኳን ሁሉም ጊዜ የማይሰጡ ቢሆኑም ቅሉ ትቂቶችን እና ዋና የቅል አንገት የሆኑትን ነቅሶ በማውጣት ከሚመለከተው አካል ጋር ሆኖ መወያየትና መፍትሔ ማፈላለግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ተነሳሽነትና ያለ ማንም አስገዳጅነት ውሥጡ ያለው ብሶት ገፍቶት ጥያቄዬን ያቀርቡልኛል፣እተማመንባቸዋለሁ፣ምንም ዓይነት የፓለቲካም ሆነ የጥቅም ፍላጎት የላቸውም፣ይህን ታሪካዊ ጥያቄ ስርዓት ባለውና እጅጉን ሠላማዊ በሆነ መልኩ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸውን 17 ኮሚቴዎችን መርጦና በፊርማው ውክልና ሰጥቶ የአደራ ጥያቄዎቹን አሸክሟቸዋል።
እነዚህ 17 የህዝብ ኮሚቴዎች ህዝቡን ስብጥር የወከሉ ሲሆን ከምሁራን፣ከዓሊሞች፣ከዱዓት፣ከወጣቶች፣ከነጋዴዎችና ከአባቶች የተሰባጠሩ ናቸው።ከብሔር ስብጥርም ሁሉንም ብሔሮች እንዲወክሉ ጥረት ተደርጓል። ከጎደፈ ታሪክ የጠሩ ስብዕናዎች ስብስብ ናቸው።እነዚህ ስብጥሮች በህብረሰተሰቡ ካላቸው ተቀባይነት በተጨማሪ በሳል የአመራርና የትግል ፅናት ክህሎትን የተላበሱ በመሆናቸው እንዲሁም ለዲናቸው ካላቸው መሠጠት (commitment) አንፃር ህዝቡ ይሆኑኛል ብሎ የመረጣቸው ናቸው።በድህረ ምርጫም ሆነ በቅድመ ምርጫ ማንነታቸው በህዝቡ ውስጥ በዲናዊ ትግላቸው እንጅ ከማንኛውም እኩይ ስነ-ምግባር የራቁ ለህዝበ ሙስሊሙ እጅጉን የሚጨነቁና ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ባለ አደራና ባለ ውለታ መሆናቸው አይዘነጋም።ከሚቴዎቹ የአላህ እርዳታ ተጨምሮበት ይህ እንቅስቃሴ ከተጀመረበትና ሃላፊነት ከተሰጣቸው እለት አንስቶ የሚያደርጓቸው ጉዞዎች እጅጉን የሚያስደምሙና ፍፁም ሠላማዊ መሆናቸውን ክስተቱን የሚከታተሉት ብቻም ሳይሆን ጆሮውን የደፈነው አካል በሙሉ አድናቆትን ችሮታል።
ይሁን እንጅ እነዚህ የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላፊ ስብዕናዎች ህዝበ ሙስሊሙን ብቻ አይደለም የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖችንም አልፎም መንግስትንም ያስደነገጠ እጅግ ተዓምራዊ የሆነ የሠላማዊ የትግል ሥልትን ተከትለዋል።በዚህም ለአመታት ሆዱ የቆሠለውን ሀበሻዊ ሙስሊም ይሁንታ በማግኘትና ህጉ የሚጠይቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ ጉዞ አድርገዋል።በኢህአዴግ የሚመራው ፀረ-ኢስላም ቡድን ግን ኮሚቴዎቹንም ሆነ ሌሎች ዓሊሞችን፣የስነ-ፅሁፍ ሰዎችን፣ጋዜጠኞችንና ታዋቂ ሙስሊሞችን ወደ ዘብጥያ ከመወርወርና ኢ-ሠብዓዊ ግፍ (torcher) ከመፈፀም ውጭ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ አንዱንም ሊመልስ ፈቃደኛ አልሆነም።ዛሬ ዛሬማ ለህዝበ ሙስሊሙ ያለው ንቀት ይፋ የወጣበትና እንደተራ ጎረምሳ “የውረድ እንውረድ” ፓሊሲ እያራመደ መሆኑ ኢህአዴግ ኮምፓሱን ወደ አጼ ዩሐንስ የቦሩ ሜዳ ውል እያዞረ መሆኑን በሀዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈፀማቸው ያሉ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎቹ በግልፅ ያሳያሉ።
ህዝበ ሙስሊሙ በህገ-መንግሥቱ አንቀፅ 31 የታወጀውን የመደራጀት መብት እውን ለማድረግ ህዝበ ሙስሊሙ የሚያምነውና በህዝበ ሙስሊሙ ይሁንታ ብቻ የተመሰረተ የመጅሊስ አደረጃጀት ይኑረን ብለው ላነሱት እዚህ ግባ ለማይባል ተራ ጥያቄ የኢህአዴግ መንግሥት ግን የሸሪዓ መንግሥት ለመመስረት ንያው አላቸው በሚል ተራ ውንጀላ ህዝበ ሙስሊሙን የሸሪዓ መንግሥት ምስረታ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል።ህዝበ ሙስሊሙ የጠየቃቸውን ዴሞክራሲያዊና ሠብዓዊ መብቶች በሠላማዊ ሁኔታ ለማስተናገድ ፍፁም ተነሳሽነት የሌለው የኢህአዴግ መንግሥት በሁሉም የሀገሪቱ ቅርንጫፎች ህዝበ ሙስሊሙን እዚህም እዚያም በእስርና በግዲያ ለማፈን እየሞከረ ይገኛል።በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ዜግነታቸው ተከብሮላቸዋል? ከሌላው ህዝብ ጋርሰ እኩል ናቸው? የሚለውን በቀጣይ በአላህ ፈቃድ በሌላ መፅሀፍ የምናየው ይሆናል።
ጠቅለል ሲደረግ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለኢትዮጵያ የእንጀራ ልጅ ናቸውን? የሚያስብሉ በርካታ ህገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው በኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ ተደቁሰው ይገኛሉ።ሙስሊሞች የፈለጉትን አስተሳሰብ ማራመድ አይችሉም፣የጁሙዓኹጥባ እንኳን የመስጅድ ኢማሞች በራሳቸው ማድረግ አይችሉም፣የአቢዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አህባሽ አስተሳሰብ ያልተቀበሉ ዓሊሞች በሽብርተኝነት እየተፈረጁ ፍፃሜያቸው ዘብጥያ ሆኗል፤አክራሪ ፕሮቴስታንት የኢህአዴግ አመራሮች ኢስላምን ለመድፈቅ የቤት ተልዕኳቸውን እየተወጡ ነው፡፡ሙስሊም ምሁራን ከፓለቲካ እንዲገለሉ አሊያም ከመንግስት ቤት እንዲጸዱ ተልካሻ የሽብር ሥም እየተለጠፈላቸው በሲስተም እየተወገዱ ነው።አይሁድ መራሹ የአህባሽ አንጃ “አህለ ሡና ወልጀመዓ” በሚል እነ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በአመቻቹለት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቧድነው እርስ በእርሳቸው የሚተላለቁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡እናም ይህን ሁሉ አምባገነናዊ አካሔድ አጨብጭበን የምንቀበል ግራ ፊትህን ሲመታህ ቀኝ ፊትህን አዙረህ ስጠው የሚል ትውልድ በሙስሊሞች ዘንድ ሊፈጠር አይችልም።በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ሠላማዊ ትግላቸውን በማጧጧፍ ይኖርባቸዋል።
ክፍል ሁለት
ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው ጥያቄዎች ይዘትና ጭብጥ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬ ላይ ሲደርሱ ያለ አንዳች መሠዋዕትነት አይደለም።ከንብረት እስከ ህይዎት ገብረዋል።ትላንት ህዝበ ሙስሊሙ ይከፍር ዘንዳ በተጎሰመው አዋጅ እጅጉን መከራ ላይ ሲወድቅ ዛሬ ደግሞ የትላንቱን የሚያስመሰግኑ የሙስሊሙን አንድነት በመናድና በመሸራረፍ ህዝቡን አላስፈላጊ ውጥረትና ስጋት እንዲገባ በማድረግ ኢስላምን በኢትዮጵያ በነበር ለማስቀረት የሚጥሩ ኃይሎች ተፈጥረዋል።ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን ጠብቆ ለተሻለ ራዕይና ስኬት መብቃት የሚቻለው አንድነትን በሚሸረሽሩ ጥቃቅን አቲካራ ውሥጥ በመጠመድ ሳይሆን የህዝቡን አንድነት በሚጠብቁ የጋራ
እሴቶችና ውበቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራትና የአንድነት መጠበቂያ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ሲጓዝ ብቻ መሆኑ አሌ የሚባል ጉዳይ አይደለም።ታዲያ ይህ በቁጥር ከአንዲት ሀገር በለይ የሚያል ኢትዮጵያውያን ሙስሊም አንዲነቱን ጠብቆ የተሻለ መንፈሳዊና ቁሳዊ ስኬት የሚያሳካው ጠንካራ አደረጃጀትና ህብረት ሲፈጥር ብቻ ነው።በመሆኑም ተዓማኒነት ያለውና ውጤታማ የሆነ አደረጃጀትን ቀርጾ መጓዝ ያስፈልገውም ስለነበር የትላንት አባቶች ይህ ጉዳይ በጊዜ ስለገባቸው የህዝበ ሙስሊሙ አስተዳዳሪና ተወካይ የሆነ ድርጅት (መጂሊስን) ዋጋ ከፍለው አቋቁመዋል።ይህ ድርጅት ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ መዋቅር ኖሮት ህዝበ ሙስሊሙን ማገልገልና መጠቀም በሚቸልበትን ዓላማ ሰንቆ የተነሳ ቢሆንም ያለመታደል ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከ1987ቱ ግርግር ወዲህ ዓላማውንና ግቡን እንዴት ህዝበ-ሙስሊሙን መበታተንና በሂደትም ማሽመድመድ ይቻላል በሚል ቀርጾ እንዲንቀሳቀስ በአህባሾችና በህቡዕ ኃይሎች ተጠልፏል።በህዝበ-ሙስሊሙ ጫንቃ ላይ ሆኖ በሙስሊሙ ጠላቶች መካከል እንደ ባንዳ ሆኖ ህዝቡን ለተለያዩ መከራና ስቃይ ከመዳረግ ባሻገር ይህ ነው የሚባል የልማትና የሠላም ታሪክ የሌለው ኢህአዴግ መራሹ መጅሊስ በህዝቡ ላይ የሚፈፅማቸው የአስተዳደራዊ፣ዲናዊና ቁሳዊ በደሎች አብጠውና አድገው ህዝቡን ለማስጨፍጨፍና ለማዋረድ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እያካሔደ በመሆኑ ይህ የህዝብ ውክልና የሌለውን መጅሊስ አቋምና ስሪት ቆም ብሎ መገምገም አና ስብራቱን አርቆ ለህዝቡ በሚጠቅም መልኩ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ወሳኝ የሚባልና ፍጹም ከፓለቲካ የፀዳ አውራ ጥያቄ ህዝቡ አንስቷል።
እንደሚታወቀው ይህ የሀገሪቱን ሲሶና ከዚያ በላይ የሚሆነውን ህዝብ የሚያስተዳድረው መጅሊስ ህጋዊ አቋሙ አምስት ሰዎች እንደሚያቋቁሙት መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር ( NGO) ሲሆን አቻ የሃይማኖት ተቋም እንደ ሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአዋጅ ሳይሆን በመመሪያ የተመሰረተ እና በሶስትና በአምሰት አመታቶች ለሚመለከተው የመንግስት ተቋማት ተግባሩንና እንቅስቃሴውን ኦዲት የሚያስደርግና የሚያስመረምር እንዲሁም የህልውናውንም ፈቃድ እያደሰ የሚኖር ማህበር ነው።እንዲህም ሆኖ መጅሊስ ታላላቅና ተወዳጅ መሪዎቹን ካጣ በኋላ ለህዝበ ሙስሊሙ ይህ ነው የሚባል ልማታዊ ሥራ ላይ የማይታወቅ ሆኖ ሳለ በተቃራኒው የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመሸራረፍና ለመናድ አልፎም ውጥረት ለማስፈን የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው።በእርግጥም የተሳካለት ይመስላል! በየ 5 ዓመቱ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ምርጫ በማካሔድ ህዝበ ሙስሊሙን ፍጹም አባታዊና ዲናዊ በሆነ መስመር ማስተዳደር ሲገባው ላለፉት በርካታ አመታት ያለ አንዳች ምርጫ ፍጹም የህዝብ ውክልናና እውቅና የሌላቸውን ግለሰቦች በዙፋኑ ላይ በመቀያየር በህዘቡ ላይ መጠነ ሰፊ በደል ሲያደርስ ኖሯል እያደረሰም ይገኛል።ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1. የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በመጠበቅ በህዝቡ መካከል ያሉትን እዚህ ገባ የማይባሉ ልዩነቶች ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ህዝበ ሙስሊሙን ማዋሀድና ማቀራረብ ሲገባው በተቃራኒው ፀረ-አንዲነት እቅዶችን አቅዶና አልሞ የሚንቀሳቀስ አንዱን ጀመዓ አቅፎ ሌላውን ከጅብ መንጋጋ ውሥጥ የሚከት አግላይና ፀረ-ወጣት፣ፀረ-ኡለማዕ፣ፀረ-ምሁር፣ፀረ-እንስት በመሆን ለነዚህ አራት ወገኖች የሚያሳየው ጭካኔ የተሞላበትና የአምባገነን ሥርዓቱ አቢይ ተጠቃሽ ነው።በተለይ በመላ ሀገሪቱ በህዝበ ሙስሊሙም ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፉ ዐሊሞችን በማግለልና በማሰቃየት የእሰሩልኝና የአግቱልኝ ደብዳቤዎችን ለመንግስት በመፃፍ ደማቅ ታሪክ ያለው ነው።መጅሊስ ወንበር ላይ ተቀምጠው የህዝቡን ሀብት የሚዘርፉትን አመራሮቹን በወር በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባለውን ደመወዝ ሲከፍል (ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ደመወዝ ሁለትና ሶስት እጥፍ ማለት ነው) አገር ቤት መሬታቸው ላይ መስጅድ ቀልሰው እልፍ ደረሶችን እያቀሩና ሙሉ ጊዜያቸውን ለኢስላም የሰጡ ዓሊሞች ግን እንደ ውሻ ሁለት መቶና ሶስት መቶ ብር እየተወረወረላቸው እንዲኖሩ ማድረጉ ለበርካታ ዓሊሞች መሰደድ እና እስራት ተጠያቂው ነው።
2. ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንደ ህዝብ ለሀገራቸው ማድረግ ወይም ማበርከት የሚጠበቅባቸው ሚና እጅጉን የሚጠበቅ ሆኖ ሳለ።ህዝበ ሙስሊሙን በሀገራዊ አጀንዳዎችና ሠላማዊ ልማታዊ የሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ በማሳተፍ ሀገሪቱ የተያያዘችውን ፀረ-ድህነት ትግል ህዝበ ሙስሊሙም የጎላ ሚና እንዲጫወት ከማድረግ ይልቅ የባለ ደርቦቹን(የመሪዎቹን) የስልጣን እድሜ እንዴት ማራዘም ይቻላል በሚሉ ተራ ሴራዎች ላይ ተጠምዶ ይውላል።በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎችን ትላንት እንደተገለለው ሁሉ ዛሬም ይህን እድል በራስ ወዳድ የመጅሊስ መሪዎች ጥበት የተነሳ እየተገለለ ይገኛል።
3. መጅሊስ ለምዕምኑ ማበርከት የሚጠበቅበት የዲናዊና ቁሳዊ ትምህርት ልማት፣ህዝቡ ራሱን ከዲህነት የሚያወጣበት የኢኮኖሚ ልማት፣የመንፋሳዊ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ልማቶች ላይ በተለይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ሲገባው ይህ ነው የሚባል ልማት ለህዝበ ሙስሊሙ ሳይሰራ አመራሮቹን እንዴት ተጠቃሚ ላድርግ በሚሉ ፕሮጀክቶች ላይ ተጠምዶ ይገኛል።አዛን የማይሰማባቸው ሰፈሮች በተንሳራፉበት ህዝበ ሙስሊሙ መስጅድ አጥቶ በቤቱ በሚሰግድበት ዘመን ላይ አንድትም መስጅድ አሰርቶ የማያውቀው መጅሊስ ትላንት አባቶች ዋጋ ከፍለው የደምና የአጥንት ዋጋ ከፍለው የቋቋሟቸውን መስጅዶች በመውረስ መጠነ ሰፊ ጉዳት አድርሷል።በታላቁ የአንዋር መስጅድ ዙርያ ያሉ ሱቆችን እና በራጉኤል ቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ ያሉ ህንጻዎችን ማነፃፀሩ በቂ ማስረጃ ነው።የአንዋር መስጅድ ዙሪያ የሚታወቀው በወደቁ ደሳሳ ጎጆዎቹ እንዲሁም በወሲብ ፊልምና የሙዚቃ ክሊፕ መሸጫነቱ ነው።ታዲያ ለዚህ ውድቀት ተጠያቂው ማን ይሆን?
4. እንደሚታወቀው በኢስላም ውስጥ በርካታ ጀመዓዎች መፈጠራቸው አይቀርም ተፈጥረዋልም። ታዲያ የአንዱ ጀመዓ ዋና ተጠሪ በመሆን ሌላውን የሚያገለው መጅሊስ ዛሬ ዛሬ ደግሞ በደዕዋና በአካሄድ እንጅ ብዙም የማይራራቁትንና ሙሉ ትኩረታቸውን ለዲኑ መጠናከር ላይ የሚሰሩትን ጀመዓዎች ከጅብ መንጋጋ ውስጥ በመጣል በዓለም ላይ ያሉ ምሁሮች በሙሉ ያወገዙትንና ከኢስላም ለመውጣቱ የምስክር ቃላቸውን የሰጡበትን አህባሽ የተሰኘ ጠማማ አንጃ ኢምፓርት በማስደረግ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በግድ እየጫነ ከመገኘቱም በላይ ይህን አስተምህሮ አልቀበልም ያለን ከመስጅድ ማባረር፣ማሳሰር፣ማስጨፍጨፉን ተያይዞታል።
ክፍል ሦስት
ለምን እና እስከምን ድረስ አህባሽን እናወግዘለን?
አህባሽ የተሰኘው አንጃ ሁላችንም እንደምናውቀው መስራቹ ሸሕ አብዱሏህ አል-ሀረሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩበት እድሜያቸው ለበርካታ ዓሊሞች ስቃይና መከራ እስራትና እንግልት አልፎም ስደት ዋና ተጠያቂ ሰው የነበሩና የአጼ ኃ/ሥላሴ መንግስት ባንዳ ሆነው በማገልገል መድረሳዎችን ያስዘጉ ግለሰብ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላም ዛሬ በዓለም ላይ ያሉና በህይዎት የሌሉ አንቱ የተሰኙና ኢስላማዊ የተውሒድ ተሀድሶ ምሁሮችን በጅምላም በተናጠልም ካፊር ብለው የፈረጁ በሶሪያና ዛሬ በሀገራችን ለሚገኘው ውጥረትና ስቃይ የመጀመሪያ ተጠያቂ የሆኑ ግለሰብ ናቸው።
ይህ ግለሰብ የፈጠሩት ርዕዮት ዋና ግቡ ዘመናዊ ሙስሊሞችን ማለትም እምነት በልብ የሚያዝ እንጅ በተግባር ባይገለጽም ችግር የለውም በሚል ሸባ አመለካከት ሰነፍ ሙስሊሞችን በመፍጠር በአጭር ጊዜ አሁን እየታየ ያለውን የሙስሊሞች ሰቆቃ በረጅም ጊዜ ደግሞ ለሙስሊሞች መጥፋትና ለዲነል-ኢስላም መወየብ (ዲኑ ስለማይጠፋ ነው ጠባቂው አሏሁ ወተኣላ በመሆኑ) ራዕይ ሰንቆ የሚንቀሳቀስ ፀረ-ኢስላም፣ፀረ-ሠላም፣ፀረ-ልማትና አድገት በመሆኑ ከአመለካከቱም ከምስራታውም ከዓላማውም በመነሳት እናወግዘዋለን እንቃወመዋለንም።ይህን ስንልም ያለ አንዳች መረጃ ዓይደለም።ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዓፄው መንግስት ከተገረሰሰላቸው ጀምሮ መጠነኛ የሚባል ነፃነት ተጎናፅፈዋል በተለይም በኢህአዴግ ዘመን በተግባርም ባይሆን መብቶቻቸው ወረቀት ላይ ሰፍረውላቸው ከሌሎች የእምነት ተከታይ ወገኖቻቸው ጋር በሰላም ውለው ተፋቅረውና ተዋደው እየኖሩ ይገኛሉ።ሆኖም ግን ይህ አንጃ ከመጣ ወዲህ መንግስት በየ መገናኛ ብዙሃን (ሚዲያ) ሰርክ በሚያስተላልፈው የሀሰት የውንጀላና የማስፈራሪያ ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ እስበራሱ እንዲፈራራና በመሀሉ ስጋትና ውጥረት እየነገሰ ይገኛል።ይህ ግዙፍ መሰናክልና ውድቀት የመጣብን ይህ አንጃ ኢትዮጵያ ውስጥ በረገጠ ማግስት መሆኑ ህሌና ያለው ማንኛውም አካል አይዘነጋውም።
ዛሬ ሙስሊም ሆኖ ፂም አስረዝሞ ሱሪ አሳጥሮ መገኘት የፀረ-ሽብርተኝነት ህግን የሚያስመዝዝበት ዘመን ላይ ደርሰናል።ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ቀይ ሽብር እዚህም እዚያም ለእስርና ለጭፍጨፋ ተደርጓል።በርካቶች ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ ለእስራትና ለግርፋት እየተዳረጉ ነው።በአብዘሃኛው ይህን አሁን ያለውን መብት የማስከበር ሒደት የሚደግፈው የተማረውና ዐሊሙ በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ላይ ማነቆው ጠብቋል።በቅርቡ እንኳን ወንዲሞቻችን መንገድ ላይ ዓሠላሙ ዓለይኩም ለምን ተባባላችሁ ተብለው ለእስርና ለግርፋት የተዳረጉበት አስገራሚ ክስተት ተፈጥሯል።ታዲያ ይህ ሁሉ መከራ እንዴትና ለምን እየተከሰተ እንደሆነ የሚጠፋው ሞኝ ካልሆነ ጤናማ ሊሆን አይችልም! ምክንያቱም ትላንት ይሕ የለም ዛሬ ታዲያ ምን ተገኘ-አህባሽ አዎ አህባሽ!!
ሌላውና መሰመር ያለበት አህባሽ የተሰኘው አንጃ እራሱን በኢትዮጵያ ውሥጥ እንደማንኛውም እምነት የማደራጀት የመስፋፋትና የማሳደግ ህገ-መንግስታዊ መብቱ ነው።በመሆኑም እኛ ሙስሊሞች እየተቃወምን ያለነው ለምን አደገ ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ ገባ ሳይሆን አንጃው በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተከፍለውባቸው የተገኙና ዛሬ ለእኛ ያወረሱንን ተቋሞችና አደረጃጀቶች ከጀርባው ባሉ የመንግስትና የምዕራባውያን አይሁዶች ሃይል በመታገዝ እየወረሰን በመሆኑ ነው።ትላንት አባቶቻችን የእስላም አገሩ መካ የአሞራ አገሩ ዋርካ! በሚባሉበት ዘመን እንኳን የሚጠለሉበትና የሚያርፉበት ጎጆ ሳይኖራቸው ዋጋ ከፍለው ያሰሯቸውን መሳጅዶች ይህ አንጃ ትላንት መጥቶ የእኔን አመለካከት ካልተቀበላችሁ እዚህ መስጅድ ማሰገድ፣አዛን ማድረግ፣ደዕዋም ሆነ ትምህርት መስጠት አትችሉም በማለቱ አጥብቀን እንቃወመዋለን ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ትግል በአላህ ፈቃድ ከመስጅዶቻችን ጠራርገን እናስወጣዋለን የሚለው የጭቁኑ ሙስሊም አቋምና ፍካሬ ሆኗል።
ስለዚህም ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው ጥያቄዎች መካከል ሁለተኛው ይህ ሲሆን በግልፅና በግልፅ ቋንቋ ለመድገም ያክል አህባሽ የተሰኘው አመለካከት በእጅ ጥምዘዛና በማስገደድ በህዝቡ ላይ የሚደረገው አጥምቆተ ሥርዓት ይቁምልን ነው።
ክፍል አራት
ሦስተኛው ጥያቄ-አወሊያ ነፃ እና ብቃቱ ባላቸው ከህዝቡ በተውጣጡ የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚለው ነው
አወሊያ በኢትዮጵያ ውሥጥ ካሉ የተለያዩ ሐይማኖቶች የሚሲዮን ት/ቤቶች መካከል የሙስሊሞች ብቸኛው ትምህርት ቤት ነው።ይህ ት/ቤት በውስጡ በርካታ ተቋሞች ያሉት ሲሆን የመንፈሳዊ(ዲናዊ) ትምህርቱና አለማዊ(ቁሳዊ) ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥቅምን የሚያበረክቱ ተቋሞችን እንደ ሆስፒታልና የቀርዓን ሒፍዝ ማዕከልን ያጠቃለለ ነው።ይህ ተቋም በቅርቡ ከላይ ለጠቀስነው መጅሊስ የተሰጠ ሲሆን መጅሊሱ በውሥጡ የተማሩትንና እየተማሩ ያሉ ማህበረሰቦችን እንዲሁም የአወሊያን ማህበረሰብ በሙሉ በሽብርተኝነትና በአክራሪነት በመፈረጅ “ዛሬ ትልቁን የአሸባሪዎች መፈልፈያ አፈራረስነው” እነዳለው የመጅሊስ መሪ ይህችን ብቸኛ የህዝበ-ሙስሊም ተቋም አፈራረሱት።እናም በእነዚሁ ፀረ-ሙስሊም አመራሮች ቀጥታ አመራርነት ሥር እንዲወድቅ ተደረገ።በዚህም ሳቢያ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ለግለዊ ጥቅሙ የማይፈነቅለው ድንጋይ የሌለው መጅሊስ (አመራሩን ማለታችን ነው) በጥቅሜ ላይ እንቅፋት ይሆኑብኛል ያላቸውንና በአህባሽ አጥምቆቱ ላይ ጋሬጣ ይሆኑብኛል ያላቸውን ሁሉ ከስራ በማባረርና በማገድ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም በአንድት ቀን ብቻ የመስጅዱን ኢማም ጨምሮ 50 መምህራንን በተለይም የአረቢኛ መምህራንን በአቶ ጀማል ፊርማ(ይህ ሠው በአንድ ወቅት በማጭበርበር ወንጀል በፓሊስ ይፈለግ የነበረና ስሙ ገብሬ ነበር) ከሥራ እንዲታገዱ ደብዳቤ መጻፉ ተማሪዎቹንና ህዝቡን አስቆጥቷል።ህዘበ-ሙስሊሙም ለዚህ ችግር መፍትሔ ለማፈላለግ በማሰብ ይህን ጥያቄ ለመንግስትም ሆነ ለሚመለከተው አ
ካል በሙሉ በተወካዮቹ አማካኝነት ለማቅረብ ተገዷል ሰላማዊና ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በመሆኑም ጥያቄውን ለሚመለከተው አካል ሥርዓት ባለው መልኩ ጠይቋል።እዚህ ላይ የሚጠቀሰው አወሊያ ለምን አንድ አጀንዳ ሆነ የሚለው ብቻ ሳይሆን ንቅናቄው ለምን ከአወሊያ ጋር ተያያዘ የሚለውም ነው።እንደሚታወቀው የአህመዲን ካቢኔ በሐምሌ 2003 በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የአህባሽን ሥልጠና በዶ/ር ሺፈራው አመራርነት በሊባኖሳውያኑ ከሠጡ በኋላ ስልጠናው ሲጠናቀቅ ያጸደቁት ቃለ ጉባኤ በአደገኛ የፀረ-ኢስላም ሠነድነቱ የሚታወቅ ነው።በዚህ ሰነድ ላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ መድረሳዎችና የሙስለሊም ሚሲዬን ት/ቤቶች ውስጥ እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሽብርተኝነትን ስለሚያስፋፋ ይህ ሥርዓተ ትምህርት የአህባሽን አስተምህሮ በሚያስፋፋ መልኩ እንደገና መከለስና መሻሻል ይኖርበታል የሚል አንድ ነጥብ ነበረው።ሌላው ደግሞ ይህ በአብዱሏሒ አል-ሐረሪ ተማሪዎች የተሰጠው ሥልጠና እና ትምህርት ትኩረቱን በህፃናት ላይ ማድረግ እንዳለበትና ከኬጂ ጀምሮ በየመድረሳው መሠጠት እንዳለበት የሚገልጸው ሌላኛው ነጥብ ጋር ተዳምሮ አደገኛ ውጥን ነበር።እናም ይህን ውጥን ተግባራዊ ለማድረግ የተንቀሳቀሱት የመጅሊስ አመራሮች አወሊያን ከተረከቡ በኋላ ስርዓተ-ትምህርቱን በወጠኑት መልኩ በአህባሽ አስተሳሰብ ለመከለስ በማሰብ ስርዓተ ትምህርቱ መከለስ አለበትና ለዚህ ዓመት ትምህርታችሁን ማቋረጥ አለባችሁ የሚለው መልዕክት በተማሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞን ማስነሳቱ አልቀረም።ከዚህ በተጨማሪ የቁርዓን ቋንቋ ለሆነው አረቢኛ ፀር እና ጠላት የሆነው መጅሊስ የአረቢኛ መምህራኖችን ማገዱ ሌላው የንቅናቄው ቅፅበታዊ ምክንያት (Immediate cause) ነበር፣የአህባሽን ሥልጠና ላለመካፈል ፈቃደኛ ያልሆኑትን ሸህ ዑመርን (የአወሊያው መስጂድ ኢማም) ከኢማምነታቸው ማስወገዳቸው ደግሞ ሌላው ፅንፈኝነታቸው በመሆኑ ተማሪዎቹ የንቅናቄውን ምሥረታ እንዲያበስሩ ጉልበት ሆኗቸዋል።በእርግጥ ይህ ሦስተኛው ጥያቄ ተራ የአንድ ት/ቤት ጥያቄ ቢመስልም በአወሊያ ህፃናት ላይ በቅድሚያ በሒደትም በአትዮጵያ ሙስሊም ህፃናት ላይ የመጅሊስ አመራሮች እና ኢህአዴግ የነደፉት ስትራቴጅ እጅጉን አደገኛ መሆኑን የተረዱት የአወሊያ ፋኖዎች ህዝቡን በማስተባበር ሚስጥሩን ይፋ አድርገውታል።በየትኛውም የኢትዮጵያ ጥግ የምንገን ሙስሊሞች በሙሉ የአወሊያ ጥያቄ ጥያቄያችን ነው የምንለውም “ጎረቤት ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ” በሚል የአበው ምክር አዘል አባባል ብቻ ሳይሆን አወሊያ ላይ እየተሞከረ ያለው የኢስላም ፈንገስ ነገ ጠዋት በየ መድረሳችንና በየ ቤታችን ለልጆቻችን በክትባት መልኩ እንደሚሰጥ በማወቃችን ጭምር ነው።አወሊያ ኢህአዴጋውያኑ እና የአቢዮታዊ አህባሽ መጅሊስ አመራሮች የሽብር መዓከልና የአክራሪ መፈልፈያ ነው ሲሉት በሰፊው ተደምጠዋል።እስከ ሐምሌ 7 ድረስ የህዝበ ሙስሊሙ ንቅናቄ መድረክ ሆኖ ሲያገለግል በነበረ ጊዜም አሸባሪዎች አወሊያ ላይ ሆነው የሚያደርጉት የሽብር ጉዞ ሲሉም ፈርጀውታል።ህዝበ ሙስሊሙ ግን አወሊያን የመረጠበት ምክንያት አወሊያ በአጥር የተከበበ፣ሰፊና የከባቢ ማህበረሰቡን ደህንነት የማያውክ ኪስ ቦታ በመሆኑ ደህንነትን ጠብቆ፣የተዋጣለት ሠላመዊ ትግል ለማድረግ ሲል ብቻ ነበር።ይሁን እንጅ የህዝቦች ደህንነትና ፀጥታ ሳይደፈርስ የሚደረገው ሠላማዊ ትግል ያንገበገበው መንግጅሊስ በደረቀ ሌሊት አረጋውያንንና ሴቶችን እንዲሁም መጅሊስ ውሥጥ የታደሙ ሰዎችን በአስለቃሽ ጭስ አፍነው በመደብደብና አፍሰው ወደ ዘብጥያ በመወርወራቸው የህዝበ ሙስሊሙን መድረግ ከአወሊያ ወደ መሐል ከተማ አንዋር እንዲዛወር ትልቁን ሚና ተጫውተዋል።
No comments:
Post a Comment