ቃሉን የጠበቀ ኡማ ራዕዩን ያሳካል!
‹‹ትግል ጀግና ያወጣል›› እንዲሉ ላለፈው አመት ስናደርግ የቆየነው ትግል በርካታ ጀግኖችን አፍርቶልናል። ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን ግፍ አይመለከተኝም ብሎ ራስን ከማግለል ይልቅ ራስን ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ትውልድ ጎምርቶ አይተናል። ከመካከሉ አምኖ ‹‹ምሩኝ›› ሲል ለመረጣቸው መሪ ኮሚቴዎቹ ታማኝነቱን፣ ላስገቡት የሰላማዊነት ቃል ደግሞ ጠባቂነቱን አስመስክሯል። አላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ ሶሐቦችን ‹‹ከአማኞቹ በርሱ ላይ ለአላህ ቃል የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ›› ሲል አወድሷቸው ነበር - ቃል ጠባቂነት መልካም ባህሪ ነውና። የቢላል ዝርያ የሆኑት፣ ‹‹የኛዎቹ›› ብለን ስንጠራቸው ኩራት የሚሰማን የእናት አገራችን ሙስሊም ወንድምና እህቶችም ቃላቸውን ጠብቀዋል - ‹‹ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱ ምርጫ የለም!›› ለሚል መርሀቸው ተገዢ በመሆን የመንግጅሊስን ቅርጫ ጣቢያዎች ኦና አስቀርተዋቸዋል። መንገደኛውን ሙስሊም ሁሉ እያፈኑና እየጠለፉ፣ ለቀስተኛ ቀባሪውን ሁሉ እያግተለተሉ ወደቅርጫ ጣቢያዎች እስኪጎትቱ ድረስ የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል - ‹‹ሞኝ እምቢ ብሎ ያሸንፋል›› የሚሉትን ተረት በተግባር እስክናየው ድረስ ‹‹7 ሚሊየን ህዝብ በምርጫው አሳትፈናል›› የሚል መግለጫ እንዲሰጡ ተገድደዋል።
መንግጅሊሱ ‹‹አካሄድኩት›› የሚለው ምርጫ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ውጤት ምንም ሆነ ምንም የህዝቡ ዋነኛ ፍላጎት ይሰሩልኛል ብሎ የሚያምንባቸውን ግለሰቦች መምረጥ እንጂ መንግስት ያሻውን መርጦ እንዲያስቀምጥ ሆኖ አያውቅም። ከዚህ አንጻር መንግጅሊሱ የሰራው ስራ በፍጹም የህዝቡን ተቀባይነት ሊያገኝ የማይችል መሆኑ ግልጽ ነው። ሰው ካመነበት ደግሞ የመጅሊሱ አመራር አባላት እንደጉል

ቻ ቢቀያየሩ ሊፈጥሩ
የሚችሉት ለውጥም ሆነ ከህብረተሰቡ ሊያገኙ የሚችሉት ታዛዥነት አይኖርም። በህግ ደረጃ መጀሊሱ ለዓመታት ሲገለገል
የነበረው በመያድ ፍቃድ ሲሆን ያንንም በየሶስት አመቱ የማሳደስ ግዴታ ያለበት ተራ ኤን ጂ ኦ ነበር፤ ነውም!
ሙስሊሙን ህብረተሰብ የማስተዳደርም ሆነ የመወከል፣ በስሙ መደራደር፣ መስጊዶችንም የማስተዳደር ህጋዊ መብት የለውም።
ይህንን ሲያደርግ የቆየው ህዝቡ ግልጽ የወጣ ተቃውሞ ሳያነሳበት ስለቀረ ብቻ ነበር። ህጉ ግን አያውቀውም። አሁንም
ቢሆን መንግጅሊሱ በግድ ባደረገው ‹‹ምርጫ›› አሳብቦ ህግን በጣሰ አመራር በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ጫና ሊፈጥር
ቢሞክር ይህን የሚያደርግበት አንዳችም ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ለማሳሰብ እንወዳለን - ህግ ባለበት አገር ላይ
እስካለን ድረስ! በመሆኑም መጅሊሱ በህግ እይታ የመጅሊሱን ግቢ እና መያድ ድርጅት ከመቆጣጠር ባለፈ በመስጊዶችም
ሆነ በሌሎች ኢስላማዊ ተቋማት ላይ አንዳችም ህጋዊ መዋቅርን የተከተለ ውሳኔ መወሰን አይችልም፤ ይህ ልብ ሊባል
ይገባል! የብርቅዬ ኮሚቴዎቻችን ሰብሳቢ ካሁን በፊት ጉዳዩን እንዲህ ብሎ መግለጹ ነጥቡን የበለጠ ያብራራዋል፡-
‹‹… ስለዚህ መምረጥ ያለብን እኛው ነንና በየአካባቢያችን፣ በየመሳጂዶቻችን መሪዎቻችንን ለመምረጥ እንቅስቃሴ
መጀመር ግድ ይለናል ያ ኢኽዋን! አስመራጮችን እንመርጣለን። ከዛ በኋላ መሪዎቻችንን እንመርጣለን። ያፀድቁልናል -
እንቀበላለን! አያፀድቁትም - መስጂዶቻችንን እናስተዳድራለን! ከዛ በኋላ እነሱ የሚያስቀምጡት አሻንጉሊት ካለ ያው
የመጅሊሱን ግቢ ይዞ ይቀመጣል! አዎን! መጅሊሱን ግቢ ይዞ ይቀመጣል! እኛ ግን መስጂዶቻችንን እራሳችን ማስተዳደር
አለብን። የመረጥናቸው መሪዎች እንጂ የተመረጡልን፣ የተቀመጡልን መሪዎች እኛን ሊያስተዳድሩን አይችሉም!›› ኡስታዝ
አቡበከር አህመድ (24-10-2004)
ምርጫው ውድ ኮሚቴዎቻችን ሳይፈቱና እነርሱ ባስቀመጡት መስፈርት ሳይዘጋጅ እንዳይካሄድ በዒድ አደባባዮች ስናስታውቅ በጁምዓ ውሎአችን ደግሞ አስጠንቅቀናል፡፡ እነርሱ ግን ምንም ቢዘገይም ህዝብ አሸናፊ መሆኑን በመዘንጋት ቅርጫውን ህገወጥ በሆነ መንገድና ፍትሃዊነትም ሆነ ሃይማኖታዊ ይዘት ሳይላበስ መርጠንላችኋልና ተቀበሉ ብለውናል፡፡ ኮሚቴዎቻችንና ውድ የኢስላም ልጆችንም ለቀጣይ 14 ቀናት ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ምንጮቻችን ዘግበውልናል፡፡ በዚህም የድምፃችን ይሰማ ተማፅኖ ጆሮ ተነፍጎት ወደኋላ ልንል ወደማንችልበት የህልውና ትግል መግባታችንን አይቀሬ አድርገውታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ስልቱን አስመልክቶ እራስን የመፈተሸና ቆም ብሎ የመመካከሪያ ግዜ ያስፈልገዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ ስናካሂድ የቆየነውን የጁሙዓ ተቃውሞ በነገው ዕለት ጋብ የምናደርግ ይሆናል፡፡ በነዚህ ግዜያት ውስጥ ቀጣይ ትግላችንን በአጭር ግዜና በተባበረ ክንድ ውጤታማ ለማድረግ ልናከናውናቸው በሚገቡ ተግባራት ላይ ወሳኝ አቅጣጫዎችን በተከታታይ እንደምናሳውቅ እንገልፃለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች! አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment