Thursday, October 11, 2012

በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጲያዉያን በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ የወከሉት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በመላዉ ሀገሪቱና ከኢትዮጲያ ዉጪ በሚኖሩ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጲያዉያን በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ የወከሉት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ:: የህዝበ ሙስሊሙን ሀይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል በተደጋጋሚ በማቅረብ ምላሽ እንዲሰጣቸዉ ጥረት በማድረጋቸዉ ብቻ ምላሽ መስጠት አሻፈረኝ ባለዉ መንግስት በሀሰት በሽብርተኝነት ተጠርጥረዉ ከታሰሩ ድፍን ሶስት ወር ሊሞላቸዉ ቀናት የቀሩት ሲሆን እስካሁኑ ሰአት ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸዉ በቀነቀጠሮ ብቻ እየተጉላሉ ይገኛሉ:: ለአራተኛ ጊዜ ከቀኑ 8:20 አራዳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ጉዳያቸዉን ለማየት የተሰየመዉም
ችሎት ከበፊት የተለየ የምርመራ ዉጤት ይኖራል ብሎ ቢጠብቅም ምርመራዉን እያካሄደ የሚገኘዉ መርማሪ ፖሊስም የምርመራ ሂደቴን አሁንም አልጨረስኩም:: የተለያዩ መረጃዎችን እያስተረጎምኩኝ በመሆኑ ተጨማሪ የ28 ቀነ ቀጠሮ እንዲሰጠዉ ጠይቆ እንደነበር ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: የኮሚቴዎቹ ጠበቃም በበኩላቸዉ ደንበኞቻቸዉ ያለምንም የምርመራ ዉጤት ለረጅም ጊዜ ቀነ ቀጠሮ እየተሰጠባቸዉ እጅጉን እየተጉላሉብኝ በመሆኑ የጊዜ ቀነ ቀጠሮ እንዲቀነስ ለችሎቱ መከራከሪያዉን ማቅረቡን ምንጮች ገልፀዎል:: በዚህም ጉዳዩን ለመከታተል የተሰየመዉ ችሎት ግራና ቀኙን ካዳመጠ ቡሀላ የኮሚቴዎቹን ጠበቃ ሀሳብ በመቀበል የ14 ቀን የጊዜ ቀነ ቀጠሮ በመስጠት ጥቅምት 15 ከሰአት ቡሀላ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በመወሰን ችሎቱ መጠናቀቁን ምንጮች አስታዉቀዎል:: የኮሚቴዎቻችንን የፍርድ ቤት ሂደት ለመከታተል በርካታ ሙስሊሞች ወደ አራዳ ፍርድ ቤት ቢጎርፍም ፖሊስ አካባቢዉን በማጠር የመጣዉን ሙስሊም ከአካባቢዉ ሲያባር እንደነበር የአይን እማኞች ገልፀዎል:: ኮሚቴዎቻችንም እየደረሰባቸዉ የሚገኘዉን አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ ሳይበግራቸዉ እስካሁን በአቖማቸዉ እንደፀኑ መሆናቸዉን ለማወቅ ተችሏል:: ኮሚቴዎቻችንን ብቻ ለብቻ በማሰር አንዱ በሌላኛዉ ኮሚቴ ላይ እንዲመሰክር ከፍተኛ ስቃይና ጫና እያደረሱባቸዉ ቢገኝም የሀበሻዉን ቢላል ታሪክ በመድገም የአረመኔዎቹን ምኞት የዉሀ ሽታ እያስቀሩ እንደሚገኙ የዉስጥ ምንጮች አስታዉቀዎል:: በአሁኑ ወቅት በጥሩ የስነ ልቦና ጥንካሬና ፅናት ላይ እንደሚገኙና የጤንነታቸዉ ሁኔታም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል:: ከፍርድ ቤት መልስም ከሚስቶቻቸዉ, ከልጆቻቸዉ እና ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር መገናኘታቸዉን ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: ኮሚቴዎቻችንን ወንጀለኛ በማሰኘት ለመንግስት ይቅርታ ጠይቀዉ እንዲወጡ የተለያዩ ግለሰቦችን በሽማግሌ ስም መንግስት ወደኮሚቴዎቹ ቢልክም በኮሚቴዎቻችን ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኝ እየከሸፈበት እንደሚገኝ የሚታወስ ነዉ:: በቅርቡም ለጊዜዉ ስማቸዉን የማንገልፀዉን ግለሰብ ከዉጪ ሀገር ለጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ ስርአት ለመካፈል ወደ ሀገር ቤት የመጣዉን ግለሰብ (ይህ ሰዉ የጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የቅርብ ጎደኛ እንደነበር ይነገርለታል) በመንግስት እየተሞከረ በኮሚቴዎቻችን አይበገሬነት እየከሸፈ የሚገኘዉን የይቅርታ ድራማ እንዲተዉን መታቀዱን የዉስጥ ምንጮች ጠቁመዎል:: መንግስት ካካሄደዉ ቅርጫ ቡሀላም ህዝቡን ለማሳመን ከፍተኛ ስራ ሀገር ዉስጥም ሆነ ከዉጪ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የሙስሊሞችን አንድነትም በቅርጫዉ ሽፉን ለማናጋት በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል:: በመሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ በማንኛዉም አይነት የመንግስት ዲስኩር ሳይታለል እንዲሁም በህዝበ ሙስሊሙ ተቀባይነት ይኖራቸዎል የሚባሉ ግለሰቦች በመጠቀም በመንግስት እየተሰራ የሚገኘዉን የመከፉፈል ሴራ ሙስሊሙ ነቅቶ እንዲጠብቅ እናሳስባለን:: በማንኛዉም ግለሰብም ሆነ አካል ሽፉን የሚደረግ የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ለማደናቀፍ የሚደረግ ጥረት ተቀባይነት አይኖረዉም!!! በማንኛዉም ግለሰብም ሆነ አካል በሚደረግ ጥረት ሰላማዊ ትግላችን እንደማይደናቀፍ አስረግጠን መግለፅ እንወዳለን!! "አላ ኢነ ነስረላሂ ቀሪብ! " "አዎጅ! የአላህ እርዳታ ቅርብ ነዉ"!!

No comments:

Post a Comment