ነገም ተቃውሞአችን ይቀጥላል!
ነገ ጁሙዓ ነው፡፡ ብሶታችን እና ድምጻችንን አገሪቷን እየመራ ያለው አስተዳደር እንዲያደምጥ የምንጠይቅበት ቀን፡፡ ይህ ቀን ለታላቁ አምላካችን አላህ ሱ.ወ ያለንን እምነትና መንፈሳዊ መተማመን የምናሳይበትም ነው፡፡ ግን ለምን ጁሙዓ ብቻ? ግን ለምን ተክቢራ ብቻ? የሚሉት ጥያቄዎች የሁላችንንም ምላሽ ይጠይቃሉ፡፡ በየሳምንቱ ጁሙዓ እየተገናኘን ብቻ የምንፈጽመው የተቃውሞ መርሐ ግብር እየደረሰብን ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረፍ እና ዳግም እንዳይከሰትም ዋስትና እነደማይሰጠን ሁላችንም እንረዳለን፡፡ ይህም በመሆኑ መረጃዎችን ተከታትሎ የማግኘት ጥረታችን፣ ያገኘነውን መረጃም የማሳወቅ ሓላፊነታችን እና አላህ ከፈተናው እንዲጠብቀን የምንማጸንበት ዱዓችን ሁሉ የትግላችን አካሎች መሆናቸውን በመረዳት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንን ከእነዚሁ ተግባራት ጋር ማያያዝ ግድ ይለናል፡፡
ዲናችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ፣ የማመን መብታችን ላይ የተፈጠረውን እክል በ10 ወራት ትግል ብቻ ሙሉ በሙሉ ልንቀርፈው አንችልም፡፡ የመሪ ተቋም እጦት እና አሕባሽን የመሳሰሉ አጀንዳዎችን ዛሬ ብንቀርፋቸው እንኳ ነገ ዳግም ላለመከሰታቸው ዋስትና የለንም፡፡ ለዚህ ደግሞ ማንም ወገን ዋስትና አይሰጠንም፡፡ የዋስትና ካርዱ በእጃችን ነው፡፡ ዋስትናችን ትግላችን ብቻ ነው፡፡ ትግላችን ጊዜን እና ሁኔታዎችን እያገናዘበ የሕይወት ዘመን ልምምዳችን እና ተልእኮአችን ሲሆን በእስልምናችን የመኖር መብታችን ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ይሆናል፡፡ ዛሬም በግልጽ ልናምን የሚገባው መብታችንን ማንም ለክቶ እና ቆርሶ እንዲሰጠን ልንጠብቅ አይገባም፡፡ ባለፉት 10 ወራት በፈጠርነው ንቅናቄ ምንያህል አመርቂ ጥቅሞችን እንዳገኘን

አንዘነጋውም፡፡
ይህ ንቅናቄያችን በቀናት ብቻ የተገደበ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ትግላችን በጥቂት ቀናት ብቻ የተገደበ እንዲሆን
ተጨባጫችን ፈጽሞ አይፈቅድም፡፡ የመኖራችን ዋስትና የሙሉ ጊዜ ትግላችን ብቻ ነው፡፡ ትግላችን በጁሙዓ ብቻ የተገደበ
አይሁን - የሙሉ ጊዜ የ24 ሰኣታት ይሁን፡፡ እምነት የሕይወት ዘመን ጉዞ ነውና፡፡
ነገ ጁሙዓ እለት ነው፡፡ የእለቱን የጁሙኣ ሶላት ካጠናቀቅን በኋላ የዘወትር ተቃውሞአችንን እናካሂዳለን፡፡ ነገ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ እና በፒያሳው ኑር መስጊድ እንሰባሰባለን፡፡ በክልሎች ደግሞ በዋና ዋና የከተማ መስጊዶች በመሰባሰብ የጁሙዓን ሶላት በጋራ እናከናውናለን፡፡ የጁሙዓው ሶላት እንደተጠናቀቀ ባለንበት ቦታ ሆነን አላህ ከጠላቶቻችን ሴራ እንዲጠብቀን ለ3 ደቂቃዎች ያህል በፍጹም ተናናሽነት ዱዓ እናደርጋለን፡፡ ቀኑ የዙልሂጃ ሦስተኛ ቀን በመሆኑ ዱዓችን ዒላማውን ይመታ ዘንድ ቀኑን በጾም ማጀባችን ለሁላችንም ቢሆን ጠቃሚ ነው፡፡ ለ3 ደቂቃዎች ያህል የምናደርገው ዱኣ እንደተጠናቀቀ ከጎናችን የሚገኙ ሰዎች ጋር እጅ ለእጅ ለ2 ደቂቃ ያህል በመያያዝ ዛሬም በአቋማችን፣ በወንድማማችነታችን፣ በእህትማማችነታችን ከሁሉም በላይ ደግሞ ለኮሚቴዎቻችን ያለንን ፍቅር እና ታዛዠነት እናሳያለን፡፡ በዚያውም የእለቱ ተቃውሞአችን ተጠናቅቆ ያለምምን ተክቢራ በሰላም እንበተናለን፡፡
ይህ ተቃውሞአችን በመጪው የኢደል አድሀ አረፋ በዓል ለምናደርገው አገር አቀፍ ሰላማዊ ተቃውሞ መዘጋጃ በመሆኑ በአዲስ አበባ ሁሉም ሙስሊም ኅብረተሰብ በቁጥር በመብዛት ለሃይማኖቱ መከበር ያለውን ቀናዒነት ለማሳየት አንዋር እና ኑር መስጊድ በመሄድ ተቃውሞውን ማከናወን ይኖርበታል፡፡ በክልሎችም የተገለጸውን የ5 ደቂቃ ተቃውሞ በማሳካት ለአገር አቀፉ የኢድ ተቃውሞ እንድንዘጋጅ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment