The Grand Anwar Mesjid Demonstration Oct19, 2012 |
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩሕሩሕ
የተሳካ የተቃውሞ ውሎ በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሂዶ ዋለ!
መላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎት በላያቸው ላይ የተጫነው የጭቆና ቀንበር ሸክሙ በከበደበት በዚህ ሰዓት መላ አገሪቱን ያካለለ ፍፁም ሠላማዊው የተቃውሞ ስርዓት ተካሂዷል ፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የመጀመሪያ የፓርላማ ንግግራቸውን ባቀረቡበት አጋጣሚ ከብዙኃኑ ሙስሊም ህብረተሰብ ፍላጎት በተቃራኒ በመሰለፍ የጥቂቶችን ድምፅ በማስተጋባት በብዙኃኑ ላይ የማሸማቀቅ ሙከራ ቢያደርጉም እነሆ “ብዙሃኑ ያሸንፋል!” ሲል ሙስሊሙ ዜጋ ዛሬም ለተቃውሞ አደባባይ ላይ ውሏል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በታ
ላቁ አንዋር እና በኑር መስጂዶች (በኒ መስጂድ) የተሰበሰበው ኡማ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያሳየው የተቃውሞ ሂደት ስኬታማ እንደነበር ለማየት ተችሏል፡፡
ፍፁም ሠላም ወዳድ ከመሆናችን ጋር በተያያዘ በየትኛውም ሰዓትና አጋጣሚ ተቃውሟችንን ማካሄድ መቻላችንን በመተማመን እና ለሁኔታዎች ፋታ በመስጠት ምርጫው በተካሄደበት እሁድ መስከረም 27 እና ባለፈው ጁምዓ ተቃውሞ እንዲኖር ከፍተኛ የሕዝብ ግፊት የነበረ ቢሆንም ሁለቱም ቀናቶች ምንም ዓይነት ተቃውሞ ሳያስተናግዱ አልፈዋል፡፡
ይሁንና ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሰከነ ልቦና ሚዛናዊነታቸው ተጠብቆ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ ሁኔታዎች ይሰራባቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው በይፋ እየተስተዋሉ የነበሩት ተግባራት አሸማቃቂ፣ የሙስሊም ልብ የሚያቆስል እና ይበልጥ ተቃውሞው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚገፋፉ ብቻ ነበሩ፡፡
በዛሬው ዕለት መላ አገሪቱን ያካለለ ተቃውሞ ተመሳሳይ ገጽታ ተላብሶ ሲካሄድ እንዲያስተላልፍ የተፈለገው መልዕት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በዒድ አደባባይ ለሚደረገው ታላቁ የተቃውሞ ትዕይንት እንደ መንደርደሪያ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ታላቅ ታሪክ በመስራት ላይ የሚገኘው ሙስሊሙ ኡማ እየተደረገበት ያለውን ሁለንተናዊ ጫና በመቋቋም እያሳየ ያለው የአቋም ጽናት እጅግ አኩሪ ነው፡፡ የህግ የበላይነት ሰፍኖባታል ተብሎ የሚታሰብባት አገር ዜጎች መብታችን ተጥሷል በማለት ስርዓቱን በተከተለ መንገድ በስልጣን ላይ ለሚገኘው መንግስት አቤቱታችንን ስናቀርብ ልንሰማ ሲገባን በተቃራኒው መንግስት አስከፊ ተግባራትን መፈፀሙን ቢቀጥልበትም ዛሬም እንደትላንቱ አንድነታችንን ጠብቀን ለተሻለና ፍፁም ሠላማዊ ለሆነ የትግል ስልት ራሳችንን በማዘጋጀት ከወዲሁ መቀነታችንን ጠበቅ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
በመጪው ጅምዓ በአንድ ቦታ ላይ የሚያሰባስበን የኡዱሒያ ቀን ታላቁ የተቃውሞ መድረክ መሆኑ ግንዛቤ የተወሰደ ከመሆኑ ጋር በዛሬው ጁምዓ በተቃውሞ ቦታ ላይ የተገኘው እጅግ በርካታ ሕዝብ እጅ ልእጅ በመተሳሰር አንድነቱን በማጠናከር በአንድ ድምፅ ቃል ገብቶ ተለያይቷል፡፡
የዛሬው የተቃውሞ ውሎ ከመዲናችን አዲስ አበባ በተጨማሪ በከሚሴ፣ በሀረር በባቲ እና በሌሎችም የአገራችን ክፍሎች ተካሂዶ ውሏል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment