Saturday, October 27, 2012

አዲስ አበባ-የኢድ አል አድሐ በዓልና ተቃዉሞ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን የዘንድሮዉን በዓል ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ አንዳድ ሥፍራ ደግሞ ግጭትና እስራት አጥልቶበት እንደዋለ አንዳድ ዘገባዎች ጠቁመዋል።ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በዓሉ በየዓመቱ እንደሚደረገዉ ስታዲዮም በተካሔደ ሥግደት ቢከበርም መንግሥት በሐይማኖታዊ ነፃነታችንን አፍኗል፥ መሪዎቻችንን አስሯል፥ ሐባሽ የተሰኘዉን ሐራጥቃ ይደግፋል፥ የሚሉ ምዕመናን   ተቃዉሟቸዉን አሰምተዉበታል።ምዕመኑ ከስግደቱ በሕዋላ በተለይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያን ከብቦ ተቃዉሞን ሲያሰማ ነበር።አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ደግሞ ምዕመናኑ ከታላቁ አንዋር መስጊድ አጠገብ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ በመሰለፍ መንግሥት ያሰራቸዉን የሙስሊም ተወካዮች እንዲፈታና ሐይማኖታዊ ነፃነታቸዉን እንዲያከብር ጠይቀዋል።ሌሎች ምንጮች እንዳስታወቁት፥ ናዝሬትና ጂማን በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ሙስሊም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አዉግዟል።በምዕመናኑና በፖሊስ መካካል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች መጎዳት፥ መቁሰላቸዉ ተገዝግቧል።ዶቸ ቬለ  ዘገባዉን ከነፃ ምንጭ አላረጋገጠም።
የኢድ አልአድሃ አከባበርና ተቃውሞ
አስተያየት ከአዲስ አበባና ከደሴ

No comments:

Post a Comment