ቢጫው የዒድ ተቃውሞ እና ከፊል አንድምታው
በ2005 የዒድ አል-ዓድሃ (አረፋ) በዓል ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ለአስራ አንድ ወራት መቋጫ ያላገኘውን የመብት ጥያቄዎች እና መንግስት ለመመለስ ፈቃደኝነት አለማሳየቱ የወለደውን ቅያሜ በሚሊዮኖች ቁጣ አጅቦ ከአደባባይ ውሏል፡፡ ሃገር አቀፉ የዒድ አደባባይ ተቃውሞ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችንን እና እነሱን ተከትለው የደረሱብን የመብት ጥሰቶችን እንዲሁም የኮሚቴዎቻችን መታሰር ያሳደረብንን መጥፎ ስሜት ዛሬም መንግስት እንዲያውቀው ዋነኛ አላማው ቢያደርግም እንድምታው ግን ከዛም ያለፈ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዒዱ ቢጫ ተቃውሞ እውነትና እውነተኞች ጎልተው የወጡበትና ሀሰትና የሃሰት ጭፍሮች ደግሞ በዚህ ዘመን እያበሉ መኖር እንደማይቻላቸው በተግባር የተረዱበት ዕለት ነበር፡፡ ይህ ባለቤቱ ህዝብ የሆነው ትዕይንት ማስተዋል ላልተሳነው በሙሉ ከባድ መልእክትም ያዘለ ነበር፡፡ ከአደባባይ መዋል መደበኛ የህይወታችን ክፍል ሆኗልና የዒዱ ውሎ በመርህ ደረጃ ከቀደሙት ባይለይም በይዘቱ፣ ግዝፈቱ እና ሃገራዊ መልዕክቱ አኳያ ግን ሁሉም አካላት የመልእክቱን ጥልቀት ሊረዱት ግድ ይላል፡፡
የዒዱ ተቃውሞ በሁሉም ህዝብ የነፍስ ወከፍ ተሳትፎ የደመቀ ነበር፡፡ ከመብት ትግላችን መባቻ አንስቶ ኮሚቴዎቻችንን መምረጡና አጠቃላይ ሂደቱ የህዝብ የነቃ ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ባለቤትነትም በተግባር የታየበት ትግልም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ጠንሳሹም-ሕዝበ፤ አራማጁም-ሕዝበ፤ ተሳታፊውና ባለቤቱም ህዝብ በሆነው የመብት ማስከበር ትግል በመላ ሃገሪቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አስተባባሪዎችና መሪዎች እየተባሉ ታስረዋል፡፡ የመብት ማስከበር ትግላችን ይበልጥ እየጠነከረ እና ሃገራዊ ገጽታውም እያደገ መምጣቱን አመላካች ነው፡፡ ሕዝቡም ለእስር እና እንግልት መቼም ቢሆን እጅ እንደማይሰጥ ያረጋገጠበት የተግባር ምስክር ነው፡፡
በሃገር አቀፉ የዒዱ ቢጫ ተቃውሞም የታየው ይኼው እውነታ ነው፡፡ የትግላችን ህዝባዊ መሰረት የፀና መሆኑንም ሚሊዮኖች ሆነን አረጋግጠናል፡፡ ጉዳዩ የጥቂት ህብረተሰብ ክፍል ወይንም ከፊል የሃገሪቱ ከተሞች ጥያቄ ሳይሆን የመላው ህዝበ ሙስሊም መሆኑን ከትናንሽ የገጠር ቀበሌዎች እስከ ትላልቅ የክልል ከተሞች ድረስ የተቀጣጠለው የህዝብ ቅዋሜ አውጇል፡፡ በየትኛውም አረዳድ ቢመዘን በህዝብ ፍቃደኝነትና ባለቤትነት የሚመራ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ውሎ አድሮ ካለመበት ይደርሳል እንጂ ከማሱለት ጉድጓድ ሊወድቅ አይችልም፡፡ ህዝቡም አመት ሊሞላው ቀናት የቀረውን ሳምንታዊ የጁመዓ ተቃውሞ እና ቢጫ የዒድ ተቃውሞን በሰላማዊ የድምፅ ማሰማት ክልል፤ በአስገራሚ ትእግስትና ብስለት ታግዞ ጥግ ድረስ እያደረሰው መሆኑንን አሳይቷል፡፡ ሕዝቡ እንደ ህዝብ አቤቱታ ማቅረብ (ስሞታን ማሰማት) የሚባለውን ሚና በሚገባ ተወጥቷል፡፡ ቀሪ ጨዋታው ያለው በመንግስት ሜዳ ላይ እንደሆነም ይሰማናል፡፡
በዒዱ ውሎ ድምፃችንን ከማሰማታችን በተጨማሪ እኛም እንደህዝብ በርካታ ጉዳዮችን ተምረንበታል፡፡ መብትን መጠየቅ ለማንም የሚሰጥ ተግባር ሳይሆን በእያንዳንዳችን ላይ የተጣለ የተናጠል ግዴታ መሆኑን፣ አቅጣጫ ሊያስቱና ሂደታችንን ያለግብ ሊቀጩ ከሚችሉ አካሄዶች በመቆጠብ በሰላማዊ መንገድ ላይ ብቻ መፅናት፣ ይህንን በቃላት የማይገለፅ የተሳካ ሃገራዊ ተቃውሞ ማካሄድ ከቻልን በዚሁ መግባባት ላይም ተመርኩዘን ሃገራዊ ግባችንንም ማሳካት እንደምንችል፣ ጥያቄአችን ሃይማኖታዊ ቢሆንም በአካሄዳችን ግን የመንግስትን ስህተት በማረም የዜግነትን ሚና በመጫወት ሃገራዊ ሃላፊነታችንን እየተወጣን መሆኑ፣ እንደዜጋ በጋራ ያፀደቅናቸው የሃገራችን ህግጋት መከበር ያለባቸው በዜጎች ብቻ ሳይሆን በመንግስት አካላትም ጭምር መሆን እንዳለበት ለመላው ህዝብ በተግባር ማሳየታችን ከዒዱ ተቃውሞ ካተረፍናቸው ታሪካዊ ትሩፋቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በዒዱ የቢጫ ተቃውሞ ውሎ መላው ኢትዮጵያውያን እንደሚረዱት የማንጠራጠራቸው አያሌ እውነታዎች ውስጥ ሰላማዊ የመብት ማስከበር የትግል አማራጭ ከእምነታችን ሰላማዊነት በመቀጠል በሃገር ወዳድነታችን የመረጥነው አካሄድ መሆኑ አንዱና ዋነኛው ይሆናል፡፡ ሃገር ወዳድ ዜጎች በመሆናችን የራሳችንን መብት ለማስከበር ስንል የሌሎችን የህይወት ዑደት ማወክ ተገቢ ባለመሆኑ እየተበደልንም በሰላማዊነት ላይ እየፀናን እንገኛለን፡፡ በአንድ ተመሳሳይ እለት በመላው ሃገሪቱ ሚሊዮኖችን አደባባይ ማሰለፍ የቻለ አላማ በየትኛውም አይነት የሃይል ሚዛን ሊመከት እንደማይችል እሙን ነው፡፡
ጊዜው እየነጎደ፣ ሁኔታዎች እንዲወሳሰቡ ትልቅ በር እየተከፈተላቸው ቢገኝም አሁንም ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንዳልረፈደ ይታየናል፡፡ መንግስት ሕዝብን እንደሚያስተዳድር አካል ሆደ ሰፊነት ተስተውሎበት ነገሮችን ለማረጋጋት ተግቶ መስራት እንሚጠበቅበት የጠነከረ መልዕክታችን ሆኖ እንዲደርሰው እንፈልጋለን፡፡ የሰፊው ሕዝበ ሙስሊም ፍላጎት ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ በመሆኑ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ባካሄዳቸው ተቃውሞዎች ሁሉ የነኚህ መሰረታዊ መርሆች ጠንካራ መሠረት እንዳይናጋ ተንቀሳቅሷል፡፡ ከዚህ ድንቅ ስብዕና ከተላበሰ ዜጋ ጋር በመሆን ለነኚህ መሠረታዊ መርሆች የግብ ስኬት ጠንክሮ መስርት የድንቅ መንግስት መገለጫ ባህሪዎች ይሆናሉ፡፡
እኛ ሙስሊሞች ሕግና ሥርዓት በሚፈቅደው መልኩ ብቻ በመንቀሳቀስ ለአገራችን መንግስት በደላችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄዎቹ ተገቢው ትኩረት ተችሯቸው ምላሽ ባለመግኘታቸው የተቃውሞ ሂደቱ ቀጥሎ እዚህ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ምንም እንኳን አላስፈላጊ ጥርጣሬዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች የወለዷቸው ስንክሳሮች ዋጋ ቢያስከፍሉንም ነገሮች ረግበው ፊታችንን ወደ ጀመርነው የልማት አጀንዳ በፍፁም መመለስ የማያስችለን ደረጃ ላይ ደርሰናል ማለት አንችልም፡፡ ጥያቄዎቻችን እጅግ ቀላል፣ ግልፅና ፍፁም ሐይማኖታዊ አንደምታ የተላበሱ ናቸው፡፡ እነኚህ ጥያቄዎች በዚህ መልኩ ብቻ አረዳዳቸው እንዲሰርፅ ያላሰላሰ ጥረት ሲደረግ ዛሬ ‹‹አሸባሪነት›› ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ወኪሎቻችን ከፍተኛውን ዋጋ ይወስዳሉ፡፡ እነኚህ አካላት የሕዝብ ወኪሎች እንደመሆናቸው መጠን ዛሬም በህዝቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነትና ሚናቸው እንደ አለት የጠጠረ ቦታ እንደያዘ ይገኛል፡፡ የመብታችን ይከበርልን የረዥም ጊዜ ሠላማዊ ጉዞ ጥንስሱ ጠንካራ ሆኖ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ የነፍስ ወከፍ ድርሻውን ሲወጣ ከሕዝብ ዕይታ እንዲርቁ የተደረጉት ወኪሎቹ በልባቸው የተከሉት የፀና አስተሳሰብና እጅ ለእጅ በማስተሳሰር ያስገቡት ቃል ለስኬቱ መረጋገጥ አይነተኛ መገለጫ ይሆናል፡፡ ዛሬ ከፍርግግ አጥር ጀርባ የዋሉት ህጋዊ ወኪሎቹን ሕዝበ ሙስሊሙ ‹‹የሰላም አምባሰደሮች›› ሲል ይጠራቸዋል፡፡ እንደ ዓይን ብሌኑ የሚንከባከባቸውን ውድ ልጆቹን ‹‹አሸባሪ›› የሚለው ስያሜ ተለጥፎባቸው ሲያይ እንዴትነቱ እጅጉን ግራ አጋብቶታል፡፡ የኮሚቴዎቹ በእስር የመዋል አጋጣሚ ጥያቄውን በሠላማዊ መንገድ ይዞ ለመቀጠል፣ አለኝታነቱን ለመግለጫ፣ ቃላቸውን እንደማክበሪያ እና ራስን እንደ ማፅናኛም ቆጥሮታል፡፡ በመሆኑም‹‹መሪዎቻችን ይፈቱ!›› የሚለው ድምፅ የጥያቄው ተጨማሪ አካል ለመሆን ችሏል፡፡
የዚህ ረዥም ጉዞ መቋጫ ጊዜው ቅርብ መንገዱም ቀላል እንደሆነ ይሰማናል፡፡ መንግስት የከበደ ኃላፊነት ያለበት እንደመሆኑ መጠን መሠረት ከሌላቸው አጓጉል ጥርጣሬዎች ተላቆ፣ ማስተዋል የተሞላበት ኃላፊነትን በመጠቀም ሕጋዊ ወኪሎቻችንን ሊፈታ እና ለሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎቻችን አዎንታዊ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ስንል ዛሬም እንጠይቃለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment