መሪዎቻችንን ‹‹አሸባሪ›› ማለት ሕዝባችንን አሸባሪ ማለት ነው፡፡
አሁን ነገሮች ሁሉ ጥርት ብለው ወጥተዋል፡፡ እውነቱ እንደ ረፋድ ጸሐይ ፈክቷል፡፡ ቀዳሚው የአቶ መለስ አስተዳደርም ሆነ የአሁኑ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ፣ አለፍ ሲልም የአስልምና ሃይማኖት ላይ የሚከተለው ፖሊሲ አዎንታዊ ነው ብለው ያምኑ ለነበሩ ወገኖች የትላንቱ የልደታ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት ውሎ ‹‹ተሳስታችኋል›› የሚል በእብሪት የታጀበ መልስ ሰጥቷል፡፡ ለሶስት ወራት ተኩል ያህል በማዕከላዊ ወህኒ ቤት ታስረው የነበሩ 9 የሙስሊሙ አመራር ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሙስሊም አረጋውያንን፣ የምግባረ ሰናይ ድርጅት ሐላፊዎችን፣ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሃይማኖታዊና ሞራላዊ ትምህርት ሲሠጡ የቆዩ ሰባኪያንን እና ለበቀሉበት ኅብረተሰብ ሞያዊ ግልጋሎት ይሰጡ የነበሩ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞችን በጥቅሉ 29 የሚደርሱ ግለሰቦችን የፌደራል አቃቤ ሕግ አሸባሪዎች ናቸው ብሎ ከሷቸዋል፡፡ ከመሪዎቻችን ጋርም ምንም ግንኙነት የሌላቸው እንስትም ከኮሚቴዎቻችን ጋር በጋራ ተከሰዋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ኢስላማዊ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችንም መንግስት በተመሳሳይ ወንጀል ከሷቸዋል፡፡
መሪዎቻችን መንግስታዊ እውቅና ተሰጥቷቸው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሕዝባቸውን በመወከል በሕዝብ ጉዳይ ከመንግስት ጋር ድርድር ሲያደርጉ ነበር፡፡ ከሕዘብ ይዘው የሄዱት ጥያቄም ሆነ ሰላማዊ አካሄዳቸው በመንግስት ሚኒስትሮች ምክር ቤትም ጭምር ምስክርነት ተችሮት ነበር፡፡ በወቅቱ ሕገ ወጦቹ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች ሲያቀርቡባቸው የነበረውን ውንጀላ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከመሪዎቻችን ጋር ለውይይት በተገናኙበት ወቅ

ት ‹‹እናንተን አሸባሪ ማለት ሊደራደራችሁ አብሮ
የተቀመጠውን መንግስት አሸባሪ ማለት ነው›› የሚል ምላሽ በመስጠት ስለ መሪዎቻችን ምስክርነት ሰጥተው ነበር፡፡
ሆኖም ከሚያዚያ 26 የመንግስትና የመሪዎቻችን የመጨረሻ ውይይት በኋላ፤ መሪዎቻችን መንግስት ለተነሱለት ሕገ
መንግስታዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዳልሠጠና ምላሽም እንዲሠጥ አበክረው መጠየቃቸው የመንግስትን ጥርስ
አስነክሶባቸው ለዛሬው ክስ በቅተዋል፡፡
ሕገ መንግስቱ ያጎናጸፈውን የመደራጀት መብት በመጠቀም በሕዝብ የተወከሉት መሪዎቻችን የተጣለባቸውን ሐላፊነት ለመወጣት ያደረጉት ጥረት በመንጀል ሲያስጠረጥራቸውና እንቅፋት ሲበዛባቸው ለጊዜው ነው ብለን ተጽናንተን ነበር፡፡ የሽብር ታፔላ ይለጠፍባቸዋልም ብለን ፈጽሞ አልጠበቅንም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይህ ሆኗል፡፡ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንደ ህዝብ አሸባሪ ተብለናል፡፡ መንግስት ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በአገር አቀፍ ደረጃ ይመሩኛል ብሎ ወዶ እና ፈቅዶ የመረጣቸውን አመራሮች በአሻባሪነት በመክሰስ የመረጣቸውንም ሕዝበ ሙስሊም በአሸባሪነት ወንጅሏል፡፡ ይህ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ጥቁር ነጥብ ለማስቀመጥ የተደረገ ሸፍጥ ነው፡፡ ይህንን ሸፍጥ እና ውንጀላ ግን የትኛውም ኢትዮጵያዊ ሊቀበለው አይችልም፡፡
እኛ መሪዎቻችን አሸባሪ ላለመሆናቸው እማኝ መጥራት አያሻንም፡፡ ታሪካዊ ስራቸው ምስክራቸው ነው፡፡ አደባባይ የዋለላቸው ህልቆ መሳፍርት ህዝብ፣ አርአያነታቸውን አይቶ በሰልፍ የተከተላቸው የኢትዮጵያ ሙስሊም፣ የሰሩትን ሰለማዊ ገድል ተናግሮና መስከሮ የማይጠግበው የአገራችን ጭቁን ሙስሊም ምስክር ነው፡፡ ከዚያ በተቃራኒው መሪዎቻችን የአሸባሪዎች ሰለባዎች እንደሆኑ በሙሉ አፋችን መናገር እንችላለን፡፡ ከሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ በግፍ እና አግባብነት በሌለው መልኩ በጸጥታ አካላት ታስረው፣ ሕገ መንግስቱ የሰጣቸው የእስረኛ መብቶቻቸው ተጥሰው ሕግ በማይገዛቸው የፖሊስ አባላት ነን ባዮች ግርፋት፣ ድብደባ እና ቶርች ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ ባልሰሩት ወንጀል የክስ ወረቀት ላይ ፈርሙ ተብለው በጨለማ ክፍሎች ታስረው ነበር፡፡ መንግስትን ይቅርታ ጠየቁ ተብለው በበረዶ ክፍሎች ቀናትን እንዲያሳልፉ ተገደው ነበር፡፡ እገሌ ላይ መስክሩ እየተባሉ ለወራት ቤተሰቦቻቸውን እንዳይገናኙ ተደርገው ነበር፡፡ የፍርድ ችሎታቸውን ቤተሰቦቻቸው፣ ጋዜጠኞችና ዲፕሎማቶች እንዳይገኙበት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ይህን የሚፈጽሙት አካላት ይህን ወንጀል እንዲፈጽሙ የትኛው ሕግ ነው የፈቀደላቸው? ከዚህ በላይስ ሕገ መንግስትን መጣስ፣ ሕዝብን ማሸበር አለ? ፈጽሞ የለም!
ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ሳይበቃ ለእኛ ለሙስሊሞች ሁሉ አፍራሽ አገራዊ ስዕል የሚሰጥ ውንጀላ በመሪዎቻችን ላይ ቀርቧል፡፡ ውንጀላው በሕገ ወጥነት የተሞላ ስለመሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ መንግስት የእምነት መብት ጥያቄን ወንጀለኝነት አድርጎ ከመመልከት ግንዛቤው በመነሳት የፈጠራ ውንጀላውን በፈጠራ ክስ እና ሰነድ በማጀብ መሪዎቻችንን በይስሙላ ፍርድ ቤቱ ሊያስፈርድባቸው ተዘጋጅቷል፡፡ ውንጀላውም በሌሎች እምነት ተከታዮችና ምዕራባውያን መንግስታት አመኔታ እንዲያገኝለት በአኬል ዳማ ፕሮፖጋንዳ እና የወሬ ነጋሪት ሊጎስምለት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከተራ የፖለቲካ ድራማነት ሊዘል አይችልም፡፡ ሙስሊሙም ሆነ ሌላው ኅብረተሰብ ውንጀላውን ፈጽሞ እንደማይቀበለው አስረግጠን ለመግለጽ እንወዳለን!
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment