- ባንድ ሐገር ሁለት የምርጫ ሥርዐት
- ‹‹ምርጫችን በመስጂዳችን›› በአፋር ተሳክቷል
በነገው ዕለት መንግስት በማናለብኝነት የሚያካሄደውን ቅርጫ ያስፈጽማል፡፡ ይሄ ቅርጫ በየትኛውም መመዘኛ ዴሞክራሲያዊና የሕዝቡን ፍላጉት ያማከለ ሊባል አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መንግስት በዚህ ምርጫ ጣልቃ ሳይሆን ከፊት ለፊት ገብቶ የምርጫ ድራማው ደራሲና አዘጋጅ፤ ተዋናይና አልባሽ በመሆን ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ሥራ ሠርቷል፡፡ ሁለተኛው ሙስሊሙ በማይፈልገው አወቃቀርና ቦታ በቀበሌ ሊያደርግ ቆርጧል፡፡ ሦስተኛ፡- ለማውራት የሚከብዱ አሳዛኝ የማስገደድ ሥራዎችን ቤት ለቤት ካድሬዎቹ ሲሠሩ ሰንብተዋል፡፡ መምረጥ መብት መሆኑ ቀርቶ ካልተፈጸመ የሚያስወነጅል ግዴታ እስኪመስል ድረስ ወከባ ተፈጽሟል፡፡ ሆኖም፤ የአቶ በረከት ስምዖን ምክትል የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ትናንትና ለቪኦኤ ‹‹መንግስት ካልመረጣችሁ ብሎ ማንንም አላስገደደም›› ሲሉ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የታዘበውን ነገር አይናቸውን በጨው ታጥበው፣ ሽምጥጥ አድርገው ክደዋል፡፡ አራተኛ፡- ምርጫው የሙስሊሙ ተወካዮች በግፍ ታስረው ባሉበት የለብ ለብና የችኮላ ሥራ ሆኗል፡፡ አምስተኛ፡- የማስመረጥ ሥልጣን የሌለው ዑለማ ም/ቤት ‹‹ምርጫ አስፈጻሚ›› ተብሎ ሕገ-ወጥ ሥራ ተፈጽሟል፡፡ መንግስት ይህን ሁሉ የሚያደርገው ምኑን ተማምኖ ነው? ሕግ እና ሥርዐት? በፍጹም፡፡ ጉልበቱን ተማምኖ፡፡
ከሁሉ አስገራሚው ግን ሐገር በሙሉ እመራለሁ የሚል ፓርቲና መንግስት ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የአፋር ወገኖቻችንን ምርጫ በመስጂድ ሲያደርግ ሌላው ኢትዮጵያ ላይ ግን በቀበሌ ተደርጓል፡፡ ምን የሚባል አሠራር ነው? መስፈርቱስ ምንድን ነው? ይህ መርህ አልባነት ምን ስያሜ እንዳለው አናውቅም፡፡ በአፋር ክልል ትግሉ ሙሉ በሙሉ ፍሬ ባያፈራም ምርጫውን በእምነት ተቋማቸው እንዲሆን ስላስደረጉ ደስተኞች መሆናችንን እንገልጽላቸዋለን፡፡ (በዚህ አጋጣሚ ሁላችንም አፋሮችን ብራቮ እንበላቸው)
ሆኖም፤ ደጋግመን ስንገልጽ እንደቆየነው ዛሬም ‹‹ስለ ነገ ማሰብ ይኑር›› እንላለን፡፡ ምክንያቱም፤ ዛሬ በማናለብኝነት በየቀበሌው ምርጫ ቢደረግም ነገ መንግስት ከሙስሊሙ ጋር ምን አይነት ግንኙነት ሊኖረው ነው? ከታች በሁለት አይነት መንገድ የተዋቀረው መጅሊስስ በፌደራል ደረጃ እንዴት ሆኖ ነው አወቃቀሩ የሚጣጣመው? ባንድ ሐገር ይህን የመሠለ መርሕ አልባነት (unprincipled) የሚታየው መንግስት ነገሮችን የሚያይበት ቋሚ መርህ ሳይኖረው ሲቀር አሊያም መንግስትን የሚያህል ትልቅና ውስብስብ ተቋም ልክ እንደ አንድ ቂመኛ እና እልኸኛ ግለሰብ ሲያስብ ነው፡፡ መንግስት ተኩኖ መብት ሲጠየቁ እንደመደፈር ማሰብ ስህተት ነው፡፡
በመጨረሻም ነገ በየቀበሌና ወረዳው የሚደረገው ምርጫ ሕገ-ወጥ መሆኑን ሙስሊሙም እንደማይቀበለው በድጋሚ እያስታወቅን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እንዲታይ እንጠይቃለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እንደ አፋር ወገኖቹ ‹‹ምርጫው በመስጂዱ›› እስኪሆን ትግሉ ይቀጥላል፡፡ አላሁ አክበር!!!

No comments:
Post a Comment