ቢጫ ተቃውሞ ብለን ጠራነው ተሳካልንም
ከሕዝቡ አናት በላይ በነበረው አየር ላይ ምን ነበር ብትሉ ቢጫ ቀለም
(መስከረም 25 2012)

Yellow Caution Sign Was Delivered To Ethiopian Govt. |
ኢትዮጵያችንም ጉድ ማስተናገዷን ቀጥላለች እኛም ታሪክ መስራታችንን ቀጥለን፡፡ የብዙኃን ድምፅ በከፍተኛ
ደረጃተደፍጥጦ ጥቂቶች እንዳሻቸው እንዲሆኑ ተፈቅዶላቸው ማሰራያውን እንደበጠሰ ጥጃ ሜዳው ገደሉ አልበቃ ብሏቸው
/ጠቧቸው/ ቡረቃቸውን ቀጥለዋል፡፡ አላህ በፈጠረው ምላስ ነገን ፈፅሞ በመዘንጋት አባዜ ተውጠው እስከዛሬ ቋጥረው
ያስቀመጡት ቂም ያለ እስኪመስል ድረስ የሚያወሩትን ሁሉ እየሰማን እንገኛለን፡፡ ከመስማት ባሻገር በአቋማችን ላይ
ምንም አይነት ለውጥ ማምጣት ባለመቻላቸው ዲሞክራሲና ህገ-መንግስቱ በሚፈቅድልን መሠረት እነሆ ዛሬም በድምቀቱ
ለታሪክ የሚተርፍ ልዩ የተቃውሞ ትዕይንታችንን በመላ አገራችን አካሂደን ውለናል፡፡አልሐምዱሊላህ፡፡
ሕገ ወጡ የመጅሊስ አመራር እና ወኪሉ የ “ዑለማ ምክር ቤት” ሕገ ወጥ የሆነውን የ “ምርጫ” ሂደት መስከረም 27 ለማካሄድ ሽር ጉድ ማለት መቀጠሉን በይፋም በሚስጥርም ማወጁን በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት ሕዝቤ ዛሬ በተለይ በአዲስ አበባ በታላቁ የአንዋር መስጂድ በቢጫ ቀለም ያሸበረቀውን ደማቅ የተቃውሞ ትዕይንቱን ቀጥሏል፡፡ የዛሬው የተቃውሞ ውሎ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የተቃውሞ ሂደቶች ለየት የሚያደርገው መገለጫ ሆኖ የታየው ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ የታየው አስደናቂ ክስተት ነው፡፡ በዚህ ውጥረት በበዛበት ሁኔታ እና ከጥቂት ሂደቱን ከሚመሩት ወንድሞች እና እህቶች በተጨማሪ የመላው ሙስሊም ሕዝብ ድርሻ በጉልህ መታየት የግድ በሆነበት አጋጣሚ ያለምንም መሸራረፍ ነገሮች ፍንትው ባለ ትዕይንት በሕዝብ ሙሉ የኃላፊነት ስሜትና መነቃቃት ተራ በተራ ሲተገበሩ ማየት ምላሽ ያላገኘውን የመብት ጥያቄያችንን ተከትሎ እየተካሄደ ያለው የአደባባይ ተቃውሞ መቋጫው ሩቅ እንደሆነ ያረጋገጠ ሆኖ ታይቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበሩት ተከታታይ የተቃውሞ ትዕይንቶች እንደተስተዋለው ሁሉ በቴሌቪዥን መስኮት በመቅረብ “አስተያየት ሰጪ”፣ በሕዝብ ውስጥ ደግሞ እንደ ሠላይ እና አስፈራሪ… ሚና የነበራቸው አረመኔዎች ዛሬም እንደ ትላንቱ ወገኖቻችንን በማሳደድና በማሳሰር ተግባራቸው ተጠምደው እንደዋሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ወንድሞች እና እህቶች በዛሬውም የተቃውሞ ውሎ እንደታሰሩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በጥቅሉ የተቃውሞ ውሎ በሰላም ተጀም በሰላም ተጠናቋል፡፡
የዛሬው የተቃውሞ ውሎ የተለየ መልዕክት አስተላልፏል ከተባለ የ መስከረም 27 የ “ምርጫ” ሂደት ፍፁም ሕገ-ወጥ፣ እኛ ሙስሊሞች የማንሳተፍበት እና እውቅና የሌለው እንዲሁም እስከመጨረሻው ድረስ የምንታገለውና ለዚህም በአዲስ መልክ ቃል የገባንበት መሆኑ ነው፡፡ይህ ሂደታችን በቀጣይ የሚያስከፍለንን ዋጋ ጠንቅቀን የምናውቅ ወገኖች እንደመሆናችን መጠን ለዚሁ ዝግጁነታችንን ከመግለጣችን ባሻገር ይህም የሰላማዊ የተቃውሞ ሂደት አይነተኛ መገለጫ መሆኑን ተገንዝበን ሌሎችም ከዚሁ እንዲማሩ የማድረግ ቁርጠኝነታችን ወደር የለሽ መሆኑ እንዲታወቅልን ይገባል፡፡ኢንሻ አላህ-አላህም ይገዘን፡፡
የመስከረም 27 የ “ምርጫ” ሂደት ሙሉ በሙሉ የሰፊውን ህዝብ ሳይሆን ጥቂት ሕገ ወጦችን መደገፉን ያረጋገጠውን የመንግስት ሙሉ አጀንዳ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ባገኘናቸው የፈጠጡ ማስረጃዎች አማካይነት የተረዳነው እውነታ ሆኗል፡፡ መንግስት እና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ለዚህ ስራ “መሳካት” ያላቸውን ቁርጠኝነት እጃቸውን እስከ ክንዳቸው ድረስ በማስገባት አረጋግጠዋል፡፡ከዚህ እንደምንረዳው መንግስት እና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ማሳደዱንም፣ማሰሩንም፣መደብደቡንም፣ማንገላታቱንም ምናልባትም መግደሉንም እንደተጀመሩት ይቀጥላሉ፡፡ይህ ለዲናችን መከበር የምናደርገው በመሆኑ ያለመሳሳት ደረታችንን እንሰጣለን-ኢንሻ አላህ፡፡
መንግስት እና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ምርጫውን ለማካሄድ ቆርጠው በተነሱበት ሁኔታ ሜዳውም ፈረሱም ይመቻቸው ስንል በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊታቸው ሰፊው ሕዝብ በስሜት ተነሳስቶ አንዳች ነገር ያደርጋል፣ ይህም ተጨማሪ መልካም አጋጣሚ ፈጥሮላቸው ምድሪቷን የደም ኬላ ለማድረግ እንደተዘጋጁ የወጡ ምረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እኛ ዛሬ የምንማረው አዲስ ትምህርት የለንም ቀድመን ስንሰራ የቆየነውን አሁንም እንደምንቀጥል ሊያውቁት ይገባል፡፡ እሁድ መስከረም 27 ቀበሌውም አስፓልቱም በወታደሮችና በደሕንነት ኃይሎች እንደሚጠበቅ ይገመታል፡፡ እነሱ ሁሉን ነገር እንዳሻቸው ለማድረግ ሲፈነጥዙ ለዚህ ተባባሪ ያለመሆናችንን መግለፃችንን መቀጠላችን እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ዕለት ጎዳናውን እና “ምርጫ” ይካሄድበታል ተብሎ የሚታሰበውን አካባቢ በማራቆት (ጭር እንዲል በማድረግ) ሁላችንም ቀኑን በቤታችን ማሳለፍ ይጠበቅብናል፡፡በቤታችን መቀመጣችን ተቃወሟችንን ከመግለጡ በተጨማሪ በዕለቱ በሚመቻችላቸው አጋጣሚ ወገኖቻችንን ለማሰር የዶለቱትንም ዱለታ መና ያስቀራል፡፡
በዕለቱ ሁላችንም በቤታችን እንዋል!
በቢጫ ቀለም ሰማዩን አድምቆ የዋለው ተቃውሞ ከመዲናችን አዲስ አበባ በተጨማሪ በደሴ፣ በከሚሴ፣ በበደሌ፣ በአዳማ እና በሌሎችም የአገራችን ክፍሎች እንደተካሄደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:
Post a Comment