Friday, November 30, 2012



የአቃቤ ሕግን የመቃወሚያ ምላሽ ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍ/ቤት ለሚቀጥለው ሳምንት ኅዳር 27 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የችሎቱን ውሎ ቆየት ብለን እናቀርባለን፡፡ በአካባቢው የምንገኝ ሁሉ መሪዎቻችን ጊቢውን ሲለቁ እኛም ወደየአካባቢያችን እንበተናለን፡፡

 ድምፃችን ይሰማ




የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬም እንደተለመደው ልደታ እና አካባቢውን አጥረውታል፡፡ ወደ ፍርድ ቤቱ ጊቢ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ በአብነት እና ጦር ኃይሎች አካባቢ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በፖሊሶች ታቅበዋል፡፡ በአካባቢው ያሉ የንግድ ሱቆችን በሙሉ ፖሊሶች አዘግተዋል፡፡ ፖሊሶች ትንኮሳቸውን የጀመሩትም ገና ከማለዳው ጀምሮ ነው፡፡ እኛ የተለመደው ጥንቃቄ አሁንም አይለየን፡፡.



አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! ልደታ እና አካባቢው ሌላ ትርዒት በማስተናገድ ላይ፡፡ የሰዉ ቁጥር በሚያስደነግጥ መልኩ እየጨመረ ነው፡፡ ከሜክሲኮ አቅጣጫ የሚመጣው ሕዝብ በቁጥር የላቀ ይመስላል፡፡ ይሄ ሁሉ ሕዝብ ፍትህን ፍለጋ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን እያቋረጠ ነው በመምጣት ላይ የሚገኘው፡፡ ቁጥራችን በበዛ ቁጥር ጥንቃቄያችንም እየጨመረ ይሂድ፡፡ የፖሊሶቹ ፍላጎት ግጭት መፍጠር መሆኑን በደምብ እያስተዋልን ነው፡፡


ዛሬ ልደታ አካባቢ የነበረ ሰው በጣም አሳፋሪ ነገሮችን እንደተመለከተ እርግጠኛ ነኝ እኔ ካየዋቸው አሳፋሪ ድርጊቶች መካከል ለመንግስት ተብዬው ግብር እየከፈሉ የሚሠሩ ካፌዎች ያለ ፍላጎታቸው እንዲዘጉ ሲደረግ ነበር ሠው ሕጋዊ መብቱን ተጠቅሞ እንዳይንቀሳቀስ ሲታገት ነበር ታክሲ ሚጠብቁ ሰዎችን መርጠው ሲያባሩ ነበር እኔ ምለው ራዕያቸውን ምናሳካው ከተማዋን ያጥለቀለቁትን ሌቦች ትተን ንፁሐንን በመያዝና በማሸበር ነው እንዴ? የመንግስt ተብዮው ዋና አላማ የሕዝብ ድጋፍ ያላቸውን ታሳሪዎች ከሕዝብ መነጠል ነው ለምሳሌ እስረኛ የመጠየቅ ሕጋዊ መብት አለው አሁን ግን ንፁሐን ወንድሞቻችንን ከተመረጡ ሰዎች ውጪ ሌላ እንዳይጠይቃቸው አድርገዎል በተጨማሪ ማንም ሠው የማንንም ችሎት መከታተ ልይችላል የሚለውን ሕግ በመናድ ያለ ሠው ወንድሞቻችንን ችሎት እያቀረቡዋቸው ነው እነዚሕ ሁሉ ሕገወጥ ርምጃዎች ታሳሪዎቹን አሕዝብ ነጥሎ ለማዋጣት ነው ስለዚሕ ሕዝቡ ምንጊዜም ና በተባለበት ቦታ መምጣት አለበት ወላሁ አዕለም



VOA zegabiweche ferd bit endayegebu tekelekelew neber
Islame Selame Newe

የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የእኔ እይታ

ፍርድ ቤት አከባቢ ደረስኩት ከጧቱ 2፡40 አከባቢ ነበር በወቅቱ የሚበዙት ሴት እህቶቻችን የሆኑ ስብስቦች ፍርድ ቤቱ አከባቢ ይገኙ ነበር በወቅቱም ጠይቄ እነደነገሩኝ ትገባላችሁ ጠብቁ እንደተባሉ ነበር ነገር ግን ትንሽ ተቆይቶ ነገሮች ተቀያየሩ የፍርደ ቤት ወረቀት የሌለው መግባት እንደማይችል ተነገረ እኔ ለማየት እነደሞከርኩትም ከሙስሊም የገባ አላየሁም ፖሊሶቹ ቀጥሉ በቃ አትገቡም፣ ስለዚህ ዘወር በሉ አሉ በመቀጠልም ሃይል መጠቀም ጀመሩ ከዛም ሙስሊሙ ወደ ታች ማፈግፈግ ተያያዘ (ሌሎች እህቶችና ወንድሞች ወደ ልደታ ቤቴክርስቲያን አከባቢም እነደነበሩ ሰምቻለሁኝ) ሆኖም ፖሊሶቹ የሚወስዱት የሃይል እርምጃ የከፋ ሆኖ አይቸዋለሁኝ ከዛም በላይ መጥፎ ቃላቶችንና ስደቦችን ይሳደቡ ነበር(አነድ ደደብ ፖሊስ መጥፎ ቃላት በእህቶች ላይ ሲዘነዝር አንድ እህታችን ቆፍጠን ብላ ደደብማ አንተ ነህ ዝም ብለህ እነደ አሻንጉለት አድርግ የተባልከውን የምትፈፅም በማለት አፍህን ዝጋ ብለዋለች፣ በወቅቱም ሃቅ የተነገረው ደደቡ ፖሊስ የእህታችንን መልስ በከፍተኛ ንቀት ተመለክቶ ፖሊስ ጣቢያ ካልወሰድኳት ብሎ ዘራፍ ሲል የነበረ ሲሆን በአላህ ፍቃድ እህታችን በፖሊስ ከመወሰድ ተርፋለች) ሁኔታው እየገፋ መጥቶ የተወሰኑ እህቶቻችን በፖሊሶች ሲደበደቡ ተመልከቻለሁኝ በዚህ ወቅት ሸሽተው ኮምፒይተር ቤት ገብተው የነበሩ

አራት እህቶችን ተከትለው ፖሊሶች በመሄድ በዱላ ደብድበዋቸዋል፣ በወቅቱ ምንም ማድረግ ባለመቻሌ አዝኛለሁኝ በአከባቢው በጣም ብዙ አዲስ አባባ ፖሊሶች እንዲሁም በርካታ የፌድራል ፖሊሶች ተወሮ ስለነበር መፈናፈኛ አልነበረም፣ ቀላል ቁጥር የማይባሉት የጦር መሳርያም ታጥቀውም ነበር፣ ይህ ...በእንዲህ እያለ ሙስሊሙ እየተደበደበ እየተገፋ ወደ ኮካ ማዞርያ ደርሷል ይን ግዜ ግማሹ ወደ ኮካ ፋብሪካው ወደ ላይ ሲወጣ የተቀረው ወደ ጦር ሃይሎች አቅጣጫ እየተገፋ እንድያፈገፍግ ተደርጓል፣ እኔም የኮካው ጀመዓ 95 በላይ ሴቶች ነበሩ ወንዶች ጥቂት ከመሆናቸውም በላይ በተንተን ብለው ነበር፣ በተለይ ሴቶቹ ከብዛታቸው ጋር ሂጃባቸው የበለጠ እነዲጎሉ እና የፖሊስ ጥቃት እንድያይል አድርጎባቸዋል፣ እህቶቻችን ጎንተላው፣ ድበደባው፣ እንዲሁም በፖሊሶች የተወሰኑ እህቶች ተጠልፈው መወሰድ የተነሳ ወደ ኋላ ማፈግፈጋቸውን ቀጥለዋል ፖሊሶቹ በዱላም በስድብም በመታገዝ ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል በመሆኑም እህቶች መጨረሻ ላይ ወደ ኮካ መስጊድ በጀመዓ በመግባት ሁኔታው ረገብ አለ፡፡ የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ድጋሚ ወደ ፍርድ ቤት ተመልሳል ከቀድሞ ደሴ ሆቴል ጀምሮ እስከ ኮካ ማዞርያ ድረስ መኪና ማቆም ተከልክሏል፣ ከዚህም በላይ በየተወሰነ ሜትር ርቀት ላይ ፌድራል ፖሊሶች ቆመዋል በዛ ያለ ቁጥር ሰብሰብ ሲል ተበተን የሚል ትእዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡ ልክ የቀድሞው ጠ/ሚ የሚያልፉበት መንገድ ይመስል ነበር፣ ጉዜይን ቀጠልኩን ወደ ጦርሃይሎች በጣም በሚገርም ሁኔታ አስከ ጠር ሃይሎች አደባባይ ድረስ መንገዱን ፖሊሰች ሞልተውታል፣ አደባባበዩ ላይ በርካታ ሙስሊሞች ተሰብስበዋል እኔም ተቀላቀልኩኝ ሆኖም ግን ፖሊሶቹ አሁንም ስብስቡን ለመበተን ሙከራ ላይ ናቸው ቀጭን ትእዛዝ ያስተላልፋሉ ተበተኑ፣ ሆኖም ግን በታክሲም ሆነ በእግር ወደ ፍርድ ቤቱ አቅጣጫ መመለስ አትችሉም ውዝግቡ ቀጠለ በዚህ ግዜ ከፖለሶቹ አንዱ መሳሪያውን ወደ ሙስሊሙ አዙሮ ማስፈራራት ጀመረ፣ በዚህን ገዜ ሙስሊሙ መቶኮስ ከፈለክ ተኩስና ግደለን በማለት በቆርጠኝነት ቆምን ነገሩ ቀዝቀዝ አለ፣ ማለቴ የመሳሪያው ጉዳይ ማለት ነው ሆኖም ግን የተወሰኑት በዱላ መማታት ጀመሩ ከዛም አልፎ ሰዎችን ለመውሰድ ሙከራ ያደረጉ ነበረ ቢሆንም አልተሳካላቸውም፣ በሙስሊም ጥረት በመጨረሻ ላይ ጀመዓው ተነጋግሮ ወደ አደም በዳኔ መስጂድ 5፡20 አከባቢ በመሄድ ነገሩ ረገብ አለ ተመልከቱ መጨረሻ ውዝግብ የተደረገበት ቦታ ከጦር ሃይሎች አደባባይ አልፎ ወደ ውስጥ ወደ አስራ ስምንት በሚወሰደው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኙ መንገዶች ጭምር ነበር ይህ ማለት ከፍርድ ቤቱ ወደ 1.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡

በዘሬው የፍርድ ቤት ውሎ የህዝብ ድምፅ መስሚያ የሌለው ደንቆሮው መንግስታችን በተደራጀ ሁኔታ ተዘጋጅቶ የመጣ ይመስላል ማንም በምንም መልኩ እንዳይሰባሰብ ቆርጦ ነበር፣ የነበረው ሁኔታ ይህን ያሳያል በሌላ መልኩ እህቶቻችን በሚገርም ቁርጠኝነት እና ፅናት በመታገዝ ለኮሜቴዎቻችን ፣ ለዲኛችን ያላቸውን ታማኝነት አሳይተዋል፣ በጣም የሚገርመው ይሄን ሁሉ ሆነው በመጨረሻ ላይ በንዴት ሲነጋገሩ የነበሩት እንዴት እንበተናለን ለዲናችን ምን አድርገን ነው በማለት ሲቆጩ ሰምቻለሁኝ አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው፡፡ በመሆኑም የመንግሰት ዋነኛ አላማ ሰውን በማሰቃየት ተስፋ ለማስቆረጥ ይመስላል ግን ኢንሻአላህ መጨረሻ እሱ ራሱ ተስፋ ቆርጦ ያቆማል እንጂ እኛ ሙስሊሞች እሰከመጨረሻው ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፡፡

No comments:

Post a Comment