“ታሳሪዎቹ ከመንግስት ጋር በአንድ ጠረፔዛ ተቀምጠው ሲወያዩ የነበሩ ናቸው” አቶ ተማም አባ ቡልጉ የኮሚቴዎቹ ዋና ጠበቃ ትላንት ማክሰኞ በወጣችው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ላይ የሰጡት ሙሉ ቃለ መጠይቅ፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ሃሙስ ህዳር 13\2005 የኢትዮፕያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የጊዜ ቀጠሮ ነበራቸው የችሎቱ ውሎ እንዴት ነበር ?
ተማም አባ ቡልጉ :- በእለቱ ደንበኞቻችን ላይ የቀረበው ክስ ተነቧል፡፡ 23 ገፅ ክስ ነው፡፡ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ የመጀመሪያው የፍርድ ቤት ቀነ ቀጠሮ ክሱና ማስረጃ ተብሎ የቀረበው ሰነድ ብዙ ስለነበር በአግባቡ ለይተን እንድንመጣ 19 ቀን ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቶን ስለነበር እሱን ለይተን የክስ መቃወሚያ በንባብ አቀረብን፡፡ ዐቃቤ ህግ የመቃወሚያ መቃወሚያ ለማቅረብ ለመጪው አርብ ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቶናል፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- የተከላካይ ጠበቆች ስንት ናችሁ ?
ተማም አባ ቡልጉ :- እኛ በእለቱ 10 ጠበቆች ሆነን ነው የቀረብነው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ከዚህ በፊት ጉዳዩን የያዛችሁት ስንት ጠበቆች ነበራችሁ ?
ተማም አባ ቡልጉ :- መጀመሪያ አካባቢ 2 ጠበቆች ብቻ ነበርን ፣የመጀመሪያውየፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ግን አምስትና ስድስት ጠበቆች ሆነን ነውየቀረብነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቀጠሮ ግን ሁሉም ተሟልቶ 10 ሆነን ቀርበናል፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ከሳሽ ዐቃቤ ህጎች ምን ያህል ነበሩ ?
ተማም አባ ቡልጉ :- ዐቃቤ ህጎቹ 4 ነበሩ፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- በአጠቃላይ የፍርድ ቤቱ ድባብ እንዴት ነበር?
ተማም አባ ቡልጉ :- እኔ ያየሁት የተለመደውን ነው፡፡ በችሎቱ ላይ ጋዜጠኞች ነበሩ፡፡ የእኛ ተከሳሾች ነበሩ 30 ሰዎች፡፡ ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው ችሎት ላይ አልነበሩም፡፡ አልተፈቀደላቸውምም፡፡ ሆኖም ችሎቱ ግልፅ ነው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- የታሳሪዎቹ አካላዊ ሁኔታ እንዴት ነበር ?
ተማም አባ ቡልጉ :- እኔ እንዳየኋቸው ንቁ ነበሩ፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ደንበኞችዎ ከታሰሩ ምን ያህል ቀናት ወይም ወራት ሆናቸው የቀረበባቸውስ ክስ ምን የሚል የሚል ነው ክሱስ እስከ ምን ያህል ግዜ ሊያስቀጣቸው ይችላል ?
ተማም አባ ቡልጉ :- ደንበኞቼ የታሰሩት ሃምሌ 2004 መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ዐቃቤ ህግ ካቀረበባቸው ክስ አንዱ ሽብርተኝነት ነው፡፡ ከፀረ ሽብር አዋጅ 652\2001 አንቀፅ 3 እና 4 ጠቅሶ ነው፡፡ ይሄ ክስ ብቻ ደግሞ ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ ነው፡፡ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመናድ መሞከር የሚል ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አብረው የተከሰሱት ሁለቱ ማህበራት ላይ የቀረቡ ክሶች ናቸው፡፡ ህገ ወጥ ድርጅቶችን ረድተዋል፣ ስብሰባም እንዲደረግ አድርገዋል የሚል ነው፡፡ እነዚህ ማህበራት ተከሳሾች ያሉበት ነው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ ደንበኞችዎ ጋር ለጥብቅና አገልግሎት እንደልብዎ መገናኘት ይችላሉ የእስር አያያዛቸውንስ ይጎበኛሉ እንደልብዎ መወያየት ይችላሉ በአጠቃላይ ህገ መንግስቱ የእስረኞች አያያዝ ብሎ እንደደነገገው ከጠበቆች ፣ከሃይማኖት አባቶች እና ከቤተሰብ ጋር መገናኘት የሚችሉበትስ ህጋዊ አሰራር አለ ?
ተማም አባ ቡልጉ :- አሁን ይሄ መብት የላቸውም፡፡ ከሌሎቹ በተለየ ነው የተያዙት፡፡ በተለይ የኮሚቴ አባል የነበሩትን ሰዎች እና አንድ ጋዜጠኛ አለ(የሱፍ ጌታቸው ነው ) ነጣጥለው ነው ያሰሯቸው፡፡ አንደኛ እኛ ጠበቆች አንድ ላይ አግኝተን ልናነጋግራቸው አልቻልንም ፣ተቸግረናል፡፡ ለሁሉም በአንድ ጉዳይ ላይ ነው የምንከራከረው፡፡ ነገር ግን የታሳሪዎቹ ሁኔታ አንደኛውን አንዱ ቦታ ላይ አድርገውታል፡፡ ሌሎቹን እዚያው ቃሊቲ በሌሎች ዞኖች ውስጥ በታትነዋቸው ስላሰሯቸው ተቸግረናል፡፡ 20 የሚሆኑት የኮሚቴ አባላት ዞን 3 ናቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ዞን 4 ፣ዞኔ 2፣6 እና ዞን 8 ናቸው ያሉት፡፡ ስለዚህ ሁሉንም አንድ ላይ አድርገን ማግኘት አልቻልንም ማለት ነው፡፡ በዚህየተነሳም የሚጎበኙበት ግዜ አጥሮባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ሌሎች እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚያገኙበት ግዜ እና የእኛ ደንበኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚያገኙበት ግዜ የተለየየ ነው፡፡ የእኛ ደንበኞችን አጭር ሰዐት ነው የፈቀዱላቸው፡፡ ከሌሎች በተለየ ሁኔታ እርስ በእርስ እንዳይገናኙ አድርገዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ እኔ ከዞን 6 ላይ አቡበከርን ባስጠራው ፣ቀጥሎ ደግሞ ዞን 1 ላይ ያለውን አህመድ ሙስጠፋን ባሰጠራ አንደኛውን አናግሬ ሳልጨርስ ሌላኛውን ማናገር አልችልም፡፡ አንደኛውን እያናገርኩ ሌላኛው በሌላ ፖሊስ ተይዞ ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ አንድ ላይ እንዲገናኙ አልተደረገም፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ማረሚያ ቤቱ ይህን ድጋፍ ለማድረግ የህግ ድጋፍ አለው ?
ተማም አባ ቡልጉ :- እንደዛ ማድረግ አይችልም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ፍርደኞች አይደሉም፡፡ ገና ጥፋተኝነት አልተወሰነባቸውም፡፡ በፍርድ ቤት በዳኛ አስካልተወሰነባቸው ድረስ ደግሞ ነፃ ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በእነዚህ ሰዎች ላይ የተለየ አያያዝ ለማድረግ ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡ ለምሳሌ እኛ ጠበቆች ሁለቱን ማህበራት ጨምሮ 30 ሰዎች ነው የምንወክለው፡፡ ስለዚህ ሰላሳዎቹን አንዴ ማናገር አለብን፡፡ አንድ አይነት ጉዳይ ላይ አንድ አይነት መከላከያ ነው የምናቀርበው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው አንድ ላይ መገኘት አለበት፡፡ ስለዚህ ሰላሳውንም ማናገር አልቻልንም ፡፡ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው ማረሚያ ቤቱ ይመስለኛል፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ደንበኞችዎን ከቀረበባቸው ክሶች ነፃ ለማውጣት ከአቃቤ ህጎቹ የሚከራከሩበት ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ምን ምን ናቸው ?
ተማም አባ ቡልጉ :- እንደሚታወቀው ደንበኞቻችን ምን አይነት ሰዎች መሰሉህ ግማሹ የህዝብ ተመራጭ ነው፡፡ የህዝብ ተመራጭ ማለት ከሚሊዮን በላይ ህዝብ ድጋፉን በፊርማ አሰባስቦ የመረጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከመንግስት ጋር በአንድጠረፔዛ ዙሪያ ተቀምጠው ሲወያዩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ መንግስት እስካሁን ድረስ የህዝብን ጥያቄ ህገ ወጥ ብሎ ያውቃል? ይህ አልሆነም፣ታዲያ እነዚህ ሰዎች የህዝብ ጥያቄ ይዘው እስከተነሱ ድረስ የህዝብ ጥያቄ ህግን የተላለፈ ነው አልተባለም፡፡ እንዲህ ከተባለም መጠየቅ ያለበት ህዝቡ ነው እንጂ እነሱ አይደሉም፡፡ መንግስት እራሱ እያለ ያለው የህዝብ ጥያቄ መልሻለሁ ይላል፡፡ የህዝብ ጥያቄ መልሻለሁ ያለው እራሱ ነው፡፡ የአኔ ደንበኞች እያሉ ያሉት ደግሞ የህዝቡበ ጥያቄ አልተመለሰም ነው ያሉት፡፡ ህዝቡም ጥያቄያችን አልተመለሰልንም እያሉ ያሉት፡፡ የህዝብ ጥያቄ መልሻለሁ በምትልበት ጊዜ ማረጋገጫዎች አሉ፡፡ መልሻለሁ በማለት ብቻ ሳይሆን ወይ ህግ መኖር አለበት መልሻለሁ የሚልበት ፣ሌላ ማጣቀሻ ማለት ነው፡፡ ወይ ደግሞ ሶስተኛ ወገን መኖር አለበት፡፡ ወይም ደግሞ ሪፈረንደም ነው መደረግ ያለበት፡፡ እንደዚህ ዘይነት ጥያቄዎች ልትጠይቁኝ አይገባምና ጥፋተኞች ናችሁ ከማለቱ በፊት ማለት ነው፡፡ ማድረግ ያለበት ሪፈረንደም አድርጎ ውጤቱን ይዞ ህዝቡ መልሶልናል ካለ በዛ መሰረት ተመልሷል ማለት ነው፡፡ ከዛ ውጪ ግን ጥያቄ ተጠየቀ፣ መልሻለሁ አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ህገ ወጥ ሆኖ ነው መንግስት የመጣው፡፡ ክሱን ብታየው የካቲት 26 የህዝቡን ጥያቄ መልሰናል፣ከዛም በኋላ እነዚህ ሰዎች ህገ ወጥ ርምጃ ለማድረግ ነው የተነሱት ይላል፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክንያት ሀምሌ 6 የሆነውን ሰሩ ነው መንግስት እያለ ያለው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ስለዚህ እርስዎ እንደጠበቃ መከራከሪያ ነጥቦች ወይም የታሳሪዎቹን ንፅህና የሚያሳዩባቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው ?
ተማም አባ ቡልጉ :- የታሳሪዎቹን ንፅህና የምናሳይበት በጣም ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ በሌላም በኩል የታሳሪዎቹን ንፁህ አለመሆን ዐቃቤ ህግ ማሳየት አለበት፡፡ በፍርድ ቤት ስትከራከር የከሰሰህ ነው አለ የሚለውን ጥፋት ማሳየት ያለበት፡፡ ከዛም ነገሮች ነገሮች ወደኛ ስለዞሩ የእኛ ሰዎች ጥፋተኛ አለሞናቸውን የምናሳየው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- የእርስዎ ደንበኞች ምን አይነት ስብእና የተላበሱ ሰዎች ናቸው ሲያደርጉ የነበሩት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችስ ሊያስከስስ የሚችል ነው ?
ተማም አባ ቡልጉ :- ደንበኞቼ የተከበሩ የሃገር ሽማግሌዎች፣ በጣም የተማሩ ሰዎች፣ በሃይማኖትም በአለማዊም ባህሪያቸው ጨዋ የተባሉ ደንበኛ ሀበሻ የሚባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ብዙዎቹ ከአንድና ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎችን የሚረዳ እርዳታ ድርጅት ያላቸው፣ ትልልቅ መፅሃፍት የፃፉ፣ ጋዜጠኞች፣ ሌሎቹም የህግ ባለሙያዎች፣ የተሳካለቸው ነጋዴዎች፣ በባህሪ ደግሞ በወንጀል ላይ ይሰማራሉ የምትላቸው ሰዎች አይነት አይደሉም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይም ሲከላከሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ በአወሊያ ተደረገ የተባለውንም ለ8 ወራት የዘለቀ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ የእኛ ሀገር ታሪክ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ የህዝብ የሆነ ጥያቄ ይዞ ወጥቶ ህዝቡ ምንም ነገር ሳያደርግ እንዲመለሱ ያደረጉ ሰዎች ናቸው፡፡ እውነቱን ለመናገር የታሰሩት ሰዎች ሊመሰገኑ የሚገባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሊታሰሩ የሚገባቸው ሰዎች አይደሉም፡፡ ትልቅ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከአቃቤ ህግ ጋር የሚያደርጉት ክርክር አሸንፌ በእስር ላይ የሚገኙ ደንበኞቼን ነፃ አወጣቸዋለሁ ብለው ያስባሉ ?
ተማም አባ ቡልጉ :- በሙያዬ ባለፈው ልምድ ላይ ብቻ በመመስረት ትርጉም መውሰድ አልፈልግም፡፡ በምንም ነገር ተስፋ መቁረጥ አልፈልግም፡፡ እነሱን ደግሞ ተከራክሬ ነፃ አወጣቸዋለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ከቀረበው ማስረጃ አንፃር ሊከሰሱ የሚገባቸው እንዳልነበሩ ማስረጃው ያሳያል፡፡ የቀረቡት ማስረጃዎች በቀላሉ አይቅር በሚል ብቻ የቀረቡ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ንግግሮች እነሱን የሚያስጠይቁ አይደሉም፡፡ ሁሉም የተደረገው ነገር በዶክመንት የተያዘ ነው፡፡ እያንዳንዷ ነገር ማስረጃ አላት፡፡ ከዚህ አንፃር ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም እንደምናሸንፍ፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ለበርካታ ግዚያት ለጋዜጠኞች ጥብቅና ሲቆሙ ይታያሉ፡፡ ከምን አንፃር ነው ?
ተማም አባ ቡልጉ :- ለብዙ ጋዜጠኞች ጥብቅና በምቆምበት ጊዜ ደስ ይለኛል፡፡ ማንም ሰው ሃሳቡን በነፃነት የማቅረብ መብት አለው ብዬ አስባለሁ፡፡ ብትቀበለውም ፣ባትቀበለውም አንተ መናገር ካልቻልክ ሰው መሆን አትችልም፡፡ ሶቅራጥስ የተገደለው ለምን መናገር አትተውም ተብሎ ነው፡፡ “አለመናገር የማልችለው አንደኛ አማልክቶቹ ይቆጡኛል፣ ሁለተኛ ደግሞ የተፈጠርኩተ ለመናገር ነው ” ነበር ያለው፡፡ አየህ የምታድገውም ስትናገር ነው፣የምታውቀውም ስትናገር ነው፣ ስትናገር ነው ሰው መሆንህን የምታውቀው፡፡ ንግግር ክብርን ማሳያ ነው፡፡ ሰው መሆንህን ማሳያ ነው፡፡ ግልፅ ሆኜ መናገር ካልቻልኩ ላንተ ክብር የለኝም ማለት ነው ፡፡ ስለዚህ በጋዜጣና ከሰዎች ጋር መነጋገር መቻል ትልቅ ነገር ነው ፡፡ እኔም በጣም ደስ ይለኛል፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- አመሰግናለሁ ለቃለመጠይቁ፡፡
ተማም አባ ቡልጉ :- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

No comments:
Post a Comment