Wednesday, November 28, 2012

አገር በሀሰተኛ የሰልፍ ድራማ አትመራም፡፡



ዛሬ በገርባ ከተማ መንግስት የግዳጅ ሰልፍ ማስወጣቱ ተሰማ


በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በገርባ ከተማ መንግስት የአካባቢውን ህዝብ በማስገደድ ዛሬ ሰልፍ ሲያስወጣ ውሏል፡፡ በሰልፉ ላይ ህዝቡ እንዲሳተፍ የአካባቢው ሹማምንትና ካድሬዎች ማስፈራሪያ የታከለባቸው ከፍተኛ የቤት ለቤት ቅስቀሳዎች ሲያካሄዱ የከረሙ ቢሆንም፤ መንግስት የሰልፈኛው ቁጥር ጥቂት ይሆናል በሚል ሥጋት ሰልፉ የሚካሄድበትን ቀን የከተማዋ የገበያ ቀን እንዲሆን በማድረግ፤ ለገበያ የወጣውን ህዝብ በማስገደድ ወደ ሰልፉ እንዲጓዝ አድርጓል፡፡ መንግስት ለሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እንዲመቸው በማድረግ ህዝቡን ‹‹አክራሪነትን እንቃወማለን፣ በሃይማኖት ሽፋን አድርገው የግል የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን እንቃወማለን፣ መንግስት በመላ ሃገሪቱ አክራሪነትን እና ሽብርተኝነትን ለማጥፋት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን፣ በከተማችን መንግስት አክራሪዎች ላይ እየወሰደው እርምጃ ተገቢ ነው፣ የጀመርነው ልማት በአክራሪዎች አይደናቀፍም›› የሚሉ እና በከተማው አስተዳደር የተዘጋጁ መፈክሮችን በእጁ እንዲይዝና በተደጋጋሚም በድምጹ እንዲያሰማ ሲያስገድዱት ውለዋል፡፡

የተለያዩ የመንግስት ካድሬዎችም የከተማውን ሙስሊሞች አቋም የሚወክል ንግግር በማስመሰል ለኢቴቪ አስተያየታቸውን ሲገልፁ እንደነበር ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡ መንግስት በየቦታው እየፈፀመ የሚገኘውን ኢ-ሰብአዊ እና ፀረ-ህገ-መንግስታዊ ድርጊቶች ህዝቡን ሰልፍ በግዳጅ በማሶጣት ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት በህዝብ ዘንድ ጥርስ አንዲነከስበት ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡

መንግስት በቅርቡ የገርባ ከተማ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችን እና የመንግስት ሰራተኞችን በመሰብሰብ ከገርባ ከተማ የተሰደዱ ሙስሊሞች ‹‹ወደቤታቸው እንዲመለሱ አድርጉ›› በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ‹‹በከተማው ሙሰሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ እስካልቆመ ድረስ መኖሪያቸውን ለቀው የተሰደዱ ሙስሊሞች ሊመለሱ አይችሉም›› በማለት የከተማው ሙስሊሞች አቋማቸውን በስብሰባው ላይ አስረግጠው በመግለጻቸው ስብሰባው ያለ ውጤት መጠናቀቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በዛሬውም ሰልፍ ሕዝቡ በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ቤተሰቡን እና ጎረቤቱን ማጣቱ ሳያንሰው፣ በስደትም ብዙ የገርባን ነዋሪዎች በሰቀቀን መሰናበቱ ሳያንሰው አብረውት የኖሩትን ወንድሞቹን እና አባቶቹን ‹‹አሸባሪዎች ናቸው ብለህ ሰልፍ ውጣ›› መባሉ መንግስት የደረሰበትን የሞራል አዘቅትና ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ አገር በሀሰተኛ የሰልፍ ድራማ አትመራም፡፡

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment