Monday, December 17, 2012

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ክስ ያየው ፍርድ ቤ ት 2ኛውን ክስ ውድቅ አደረገ በአንደኛው ክስ ላይ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ለጥር 14 እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ

ሰበር ዜና

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ክስ ያየው ፍርድ ቤ ት 2ኛውን ክስ ውድቅ አደረገ በአንደኛው ክስ ላይ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ለጥር 14 እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ


ዛሬ ታህሳስ 8/2005 ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛወንጀል ችሎት ቀደም ሲል በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቆች በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ያቀረቡትን መቃወሚያ እና አቃቤ ህግ ያቀረበው የመቃወሚያ መቃወሚያ ካስታወሰ በዃላ የሚከተሉትን ብይን ሰጥቷል፡-.


1. ጠበቆቹ ያቀረቡት 1ኛ መቃወሚያ የፀረሽ ብር ህጉ ህገመንግስቱን የጣሰ ነው የሚለውን ፍርድ ቤቱ አልተቀበልኩም ብሏል፡፡

2. ተከሳሾች በጸረሽብር አዋጅ አንቀጽ 3 (በ

ቀጥታ የሽብር ተግባር መፈጸም) እና አንቀጽ 4 (የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም ማነሳሳት) በአንድነት መከሰሳቸው አግባብ ስላልሆነ በአንድ ድርጊት 2 ጊዜ እንዲከሰሱ የተደረገው ቀርቶ በፀረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 3 (በቀጥታ የሽብር ተግባር መፈጸም) ብቻ ክሱ እንዲቀጥል ብሏል፡፡

3. ህገመንግስት በሀይል ለማፍረስ ማሴር የሚለው ክስም ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

4. 23ኛ ተከሳሽ አብዱረዛቅ አክመል የአዕምሮ ሁኔታው ከአማኑዌል ሆስፒታል እንዲቀረብ ፍርድ ቤቱ አዟል ይህ እስኪሆን የሌሎች የክስ ሂደት እንዳይራዘም የእሱ ጉዳይ ለብቻው እንዲታይ ተነጥሎ ይቅረብ በማለት ለአቃቤ ህግ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

5. የ28ኛ ተከሳሽ ወሮ ሀቢባ ክስ ተነጥሎ እንዲታይ በጠበቃቸው አማካኝነት የቀረበውን መቃወሚያም ፍርድ ቤቱ አልተቀበልኩም ብሏል፡፡

ከዚህ በዃላ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል ወዲያው እንዲሰማ ቢጠይቅም ጠበቆቹ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ የለወጠውን እና ያሻሻላቸውን ነገሮች አለመረዳታቸውን ነግረውናል እንድናስረዳቸው እድል ይሰጠን ብለው ስለጠየቁ የ15 ደቂቃ እድል ተሰጥቷቸው ለተከሳሾች አስረድተዋል፡፡ በዚህ መሀል ጋዜጠኞች እርስበርሳቸው እና የአሜሪካ እና የካናዳ ዲፕሎማቶች (ከአስተርጓሚዎቻቸው ጋር) እንዲሁም ቤተሰቦች እና ብዛት ያላቸው ‘ደህንነቶች’ ፍርድ ቤቱ ስለሰጠው ብይን ፋታ አግኝው ተወያይተዋል፡፡

የ15 ደቂቃው የማስረዳት ጊዜ ጠበቆቹ እንዳጠናቀቁ ደንበኞቻችን የእምነት ክህደት ቃሉን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው በማለታቸው በየተራ ፍርድ ቤቱ “የተከሰስክበትን ድርጊት ፈጽመሀል? ጥፋተኛ ነህ ? ” በማለት ለጠየቃቸው ጥያቄ ፡-

- ድርጊቱን አልፈጸምኩም ጥፈተኛ አይደለሁም፤

- ወንጀል አፈጸምኩም ወንጀል ግን ተፈጽሞብኛል ጥፋተኛ አይደለሁም፤

- በህገመንግስት የተሰጠኝን መብት ነው የጠየቅኩት ወንጀል አልፈጸምኩም፤

- ወንጀል አልፈጸምኩም ንጹህ ኢትዮጲያዊ ነኝ፤

- ወንጀል ፈጽመሀል የተባልኩት ከእውነት የራቀ ነው ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም፤

- ወንጀል ተፈጸመብኝ እንጂ ወንጀል አልፈጸምኩም፤

- በፍጹም ወንጀል አልፈጸምኩም መቼም ወንጀል አልፈጽምም፡፡

እና የመሳሰሉትን በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


ፍርድ ቤቱም ጥር 14/2005 ጀምሮ ለ አስር ተከታታይ የስራ ቀናት አቃቤ ህግ አለኝ ያለውን ምስክሮችና ማስረጃዎች እንዲያቀርብ አዟል፡

No comments:

Post a Comment