Thursday, December 13, 2012

የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን ትላንት ኢትዮጵያ ገቡ

ሰበር ዜና

የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን ትላንት ኢትዮጵያ ገቡ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ መንግስት አማካኝነት እየተፈጸመባቸው ያለውን ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመተቸት መግለጫ ያወጣው የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን አባላት ትላንት ኢትዮጵያ መግባታቸው ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ኮሚሽኑ አውጥቶት በነበረው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በኢስላማዊ የሃይማኖት ተቋም (መጅሊስ) ውስጣዊ አመራር ውስጥ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት ማሳየቱ፣ አዲስ አስተሳሰብ (አሕባሽ) በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ ለመጫን መሞከሩ፣ በርካታ ኢማሞችም በዚሁ ሰበብ ከኢማምነት መነሳታቸው፣ መንግስት በአዲሱ የመጅሊስ ምርጫ ላይ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት መፈጸሙን አስረግጦ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ወቅቶች የመንግስት ወታደሮች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት፣ በኮሚቴ አባላት እና በሌሎች ሙስሊሞች ላይ የተመሰረተውን የሽብርተኝነት ክስ በማውገዝ የታሰሩ የሙስሊሙ ኅብረተሰብ አመራሮችን በሙሉ መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔት እንዲፈታ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡ የዚሁ ተቋም ኋላፊዎች አሁን ያለውን ተጨባብ ሁኔት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ይህንኑ ተግባራቸውንም ለመፈጸም አሁን አዲስ አበባ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ የልኡካኑ አባላት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ከመንግስት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ የሚጠበቅ ሲሆን ቃሊቲ በመሄድም በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮቻችንን እንደሚያነጋግሩ ተሰምቷል፡፡ ይህ ተቋም በአሜሪካ መንግስት ትልቅ ተሰሚነት ያለው ከመሆኑም በላይ የተቋሙ ሀላፊም የሚሾሙት በአሜሪካ ፕሬዚዳንት አማካኝነት ነው፡፡

ከዚህ በፊት ገልጸነው እንደነበረው የጉዳዩ አንኳር ነጥብም ሆነ እኛ ልንገነዘበው የሚገባው ያነሳናቸው የመብት ጥያቄዎችም ሆኑ ሰላማዊ ትግላችን ሕጋዊና ዓለም አቀፍ ተቀባይነትም ማግኘታቸውን ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የያዘው አቋም በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ነው፡፡ ሐቁ ይህ ቢሆንም መንግስት ‹‹አክራሪነትን እዋጋለሁ›› በሚል ሰበብ በገጠር ከተማ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የሚፈጽመውን በደል አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ግለሰቦች አሕባሽ አይደላችሁም እየተባሉ ከፍተኛ ጫና፣ እንግልት፣ ድብደባ እና ግድይ ጭምር እየተፈጸመባቸው ሲሆን መስጊዶችን ለመንግስታዊው መጅሊስ አስረክቡ እየተባሉም እንደሚገደዱ በየዕለቱ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በመሪዎቻችን ላይ የተመሰረተው ክስ እና በወህኒ ቤት የተፈጸሙባቸው አሳፋሪ ድርጊቶች የዚህ ከልክ ያለፈን አሳፋሪ ከሕግ የበላይ የመሆን ድርጊት የሚያሳዩም ሲሆን የመጅሊሱንም አመራር መንግስት ያለ ሙስሊሙ ሕዝብ ይሁንታ በራሱ መልኩ መርጦ ማጠናቀቁም አለም ያወቀው ተግባር ነው፡፡ እኛም በጀመርነው ፍጹም ሰላማዊ ተቃውሞአችን በመቀጠል መንግስት እየሰራቸው ያሉትን ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ ተግባራትን እንዲያቆም በተደጋጋሚ በመጠየቅ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ተቃውሞአችን እና ሂደታችን ጥይቄዎቻችን እስኪመለሱ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፤ በተቃውሞአችን ሂደት ላነሳነው የመብት ጥያቄ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሰጡ የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ለመሰሉ ተቋማት አውንታዊ ምላሽ መስጠታችንንም እንቀጥላለን፡፡ በቀጣይ ቀናቶች በምናደርጋቸው ተቃውሞዎችም የጥያቄያችንን መንፈስ እና ሰላማዊነታችንን የሚያንጸባርቅ ትዕይንት እናሳያለን፡፡ ለዓለም ሕዝብም ምስክርነቱን በድጋሚ እንሰጣለን፡፡ ይህ እስከጥያቄያችን መመለስ ድረስ ዘላቂ መሆኑን ለማስረገጥ እንወዳለን፡፡

ከዚህ በታች የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ሰጥቶት የነበረውን መግለጫ ለግንዛቤ እንዲረዳ በድጋሚ ለጥፈነዋል፡፡

11/8/2012
ከአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ

‹‹በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሃይማኖት ነጻነት መብት ጥሰት ያሳስበናል››

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ከቀን ወደቀን እየጨመረ የመጣው የሃይማኖት ነጻነት መብት ጥሰት ድርጅታችንን (የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን) በጣም ከሚያሳስቡት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ከጁላይ 2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አስቀድሞ የነበረውን የሃይማኖት አንጃ ለመቀየር የጣረ ሲሆን ሂደቱን የተቃወሙ የሃይማኖት አባቶችን እና ሰባኪዎችንም እየቀጣ ይገኛል፡፡ በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተሳተፉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሲታሰሩ ቆይተዋል፡፡ በ 29 ኦክቶበር 2012 መንግስት ሃይ ዘጠኝ ያህል ተቃዋሚዎችን በሽብርተኝነት እና ኢስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ሙከራ በማድረግ ወንጀል ከሷቸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ አንድን የሃይማኖት አንጃ በግድ በመጫን ሃይማኖታዊ አተገባበሮችን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት ያስነሳበትን ተቃውሞ ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግስት ካደረጋቸው ሙከራዎች ውስጥ ይህኛው በጣም አሳሳቢው ነው›› ይላሉ የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ኮሚሽነር አዚዛ አል ሂብሪ፡፡ ‹‹የተከሰሱት ግለሰቦች ህገ-መንግስታዊ እና በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን የሃይማኖት ነጻነት መርሆዎች መጣስ በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ከነበሩ አስር ሺዎች መካከል አባል የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሞች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን አቁሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና በአስቸኳይ ያላግባብ የተከሰሱትን ግለሰቦች ሊፈታ ይገባል›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በአብዛኛው የሱፊ መስመር ተከታይ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ካለፈው ጁላይ 2011 ጀምሮ አል አህባሽ የተባለውን የሃይማኖት አንጃ በግድ ለመጫን ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫንም ራሱ በሚፈልገው መልኩ አካሂዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር የዋለ እንደሆነ ተደርጎም ይታሰባል፡፡ በመንግስት እየተፈጸመ ያለው እስራት፣ የሽብርተኝነት ክስ እና የመጅሊስ ምርጫ ቁጥጥር ማስረጃ ሆኖ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ነጻነት አደጋ ውስጥ መግባቱንና መንግስትም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የመቆጣጠር ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን ነው፡፡

‹‹የአሜሪካ መንግስት ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጠውን የአገሪቱን ህገ መንግስት እና አለምአቀፍ ድንጋጌዎች ማክበር እንዳለበት ለአዲሱ የኢትዮጵያ አስተዳደር ማስገንዘብ ይኖርበታል፡፡ የአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን አክራሪነትን በመዋጋት ስም ሃይማኖታዊ ጭቆና ማድረስ የበለጠ ወደአክራሪነት የሚገፋ፣ አለመረጋጋትን የሚፈጥር እና ወደብጥብጥም የሚመራ መሆኑን ይረዳል›› የሚሉት ደግሞ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ካትሪና ላንቶስ ስዌት ናቸው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካላት ጂኦ ፖለቲካዊ አስፈላጊነት እና ሙስሊሞችም ከአገሪቱ ጠቅላላ ህዝብ ከአንድ ሶስተኛ በላይ እንደመሆናቸው መንግስት የሃይማኖት መብት ጥሰቱን አቁሞ ሃይማኖታቸውን በሚፈልጉት መልኩ እንዲተገብሩ ሊፈቅድላቸው ይገባል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ለአደጋ ተጋላጭ የሆነው ይኸው ክልል ወደበለጠ አለመረጋጋት የሚሸጋገርበት እድል ሰፊ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የጉዳዩ የኋላ ታሪክ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአብዛኛው የሚተገበረው የሱፊ እስልምና መስመር መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 27 ደግሞ ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጥ ሲሆን መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንዳይገባ ይደነግጋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አገሪቱ ውስጥ ‹‹ወሀቢዝም›› እየተስፋፋ መጥቷል በሚል እሳቤ ከሊባኖስ የሃይማኖት ምሁራንና ኢማሞችን በማምጣት ለተማሪዎቻችው እና ተከታዮቻቸው ያስተምሩ ዘንድ ለኢትዮጵያውያን ኢማሞች እና መምህራን ስልጠና እንዲሰጡ አድርጓል፡፡ ስልጠናውን ለመውሰድና ለማስተማር ያልፈቀዱ ኢማሞችን ከስራቸው ያባረረ ሲሆን መስጊዶችንና ትምህርት ቤቶችንም ዘግቷል፡፡ ይህንን በመቃወም ነው እንግዲህ በየአርብ ስግደቶቹ ላይ በተለያዩ መስጊዶች ሰላማዊ ተቃውሞ ሲደረግ የቆየው፡፡ ተቃውሞዎቹ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄዱ የቆዩ ቢሆንም ማእከል ያደረጉት ግን የአዲስ አበባውን አወሊያ ትምህርት ቤት እና መስጊድ ነበር፡፡

ተቃውሞዎቹ ሲቀጥሉ ባለፈው ጸደይ ህዝቡ 17 ታዋቂ ግለሰቦችን በአስታራቂነት (በመፍትሄ አፈላላጊነት) በመምረጥ ከመንግስት ጋር ድርድር እንዲያደርጉ ልኳል፡፡ ድርድሩም በሚከተሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ነበር፡-
1. መንግስት ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ የሚሰጠውን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ እንዲያከብር
2. መንግስት አል አህባሽ የተባለውን አንጃ በሙስሊሙ ላይ በግድ መጫኑን እንዲያቆምና አህባሽ እንደማንኛውም ሃይማኖት በራሱ ብቻ እንዲንቀሳቀስ
3. የተዘጉ መስጊዶችና ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ዱሮ ለነበሩት ኢማሞችና አመራሮች እንዲመለሱ
4. ለመጅሊስ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድና የሚካሄድበት ቦታም የመራጩን ህዝብ ውሳኔ ለማክበር ሲባል በመስጊዶች እንዲሆን

ሆኖም ድርድሩ ሳይሳካ በመቅረቱ ተቃውሞዎቹ በመጠንና በተደጋጋሚነት ጨምረው ነበር፡፡ በምላሹ የኢትዮጵያ መንግስት የታጠቁ ሃይሎችን አሰማርቶ ከበባ በማድረግ እና ቤት ለቤት ፍተሻዎችን በማካሄድ ሰላማዊ ሙስሊሞችን ለማስፈራራት ሲሞክር ቆይቷል፡፡ መንግስት ከጁላይ 13 እስከ 21 የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና በትንሹ ሰባ ያህል ተቃዋሚዎችን ማሰሩን የገለጸ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን የታሰሩት ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠር መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ሂደትም ሆነ በእስር ቆይታቸው ወቅት ፖሊስ ትርፍ ሃይል መጠቀሙንም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩት ብዙዎቹ በአሁኑ ወቅት ተለቀዋል፡፡ ዘጠኝ የኮሚቴው አባላት ግን አሁንም በእስር ላይ ነው የሚገኙት፡፡

በኦክቶበር 29 መንግስት በተቃዋሚዎቹ እና በዘጠኝ የኮሚቴው አባላት ላይ ያቀረበው ክስ የመጀመሪያው ሲሆን ግለሰቦቹ ሲታሰሩ የተወሰዱትም የፖለቲካ እስረኞች ወደሚታሰሩበት እና ተደጋጋሚ ቶርቸር ወደሚፈጸምበት የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ማእከላዊ ነው፡፡ የተከሰሱትም ሽብርተኝነትን ከመከላከል ይልቅ ተቃውሞን ለመደፍጠጥ ጥቅም ላይ ሲውል በቆየው የጸረ ሽብር ህግ ነው፡፡

ተቃዋሚዎቹ ቢጫ እና ነጭ ካርዶችን በማሳየት ሰላማዊነታቸውን እንዲሁም እስራትና ክሱን መቃወማቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡ በጥቅሉ ተቃውሞዎቹ በአብዛኛው ሰላማዊ ነበሩ ሲሆኑ በአንዳንድ ቦታዎች ግን ሰላም አደፍራሽ ክስተቶች ታይተዋል፡፡ በኦክቶበር 21/2011 ተቃዋሚዎችን ከፖሊስ ጣቢያ ለማስፈታት በተደረገ ሙከራ 4 ያህል ሰዎች ሲገደሉ በአፕሪል 2012 ደግሞ ‹‹አህባሽን አላቀነቅንም›› ያለ ኢማም በመባረሩ ምክንያት በተነሳ ተቃውሞ 5 ያህል ሰዎች ተገድለዋል፡፡

የድርጅቱን ኮሚሽነር ቃለ መጠይቅ ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻ ይጠቀሙ፡- Samantha Schnitzer at sschnitzer@uscirf.gov or (20

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment