ምነው ጠቅላይ ሚኒስትር… ምነው ጥቂቶች እንዳልሆንን እያወቁ!?
ከሳምንት በፊት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አመራራቸውን እና አገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን አስመልክተው ከአል ጀዚራ የእንግሊዝኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ባለፈው ቅዳሜ ለእይታ በቅቷል፡፡ ቃለመጠይቁ ብዙዎችን ብዙ እያናገረም ይገኛል። እኛም የበኩላችንን ለማለት ወደድን።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሃይማኖታዊ ነጻነት ትግል የአል ጀዚራዋ ጋዜጠኛ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሳችው ጥያቄ ሁለተኛው መሆኑን ሁላችንም አስተውለናል። ጣቢያው የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለሚያደርገው ቃለ መጠይቅ የኛን ጥያቄ ትኩረት መስጠቱ በራሱ ጉዳዩ (ቢያንስ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች እይታ) አንገብጋቢ መሆኑን ይጠቁማል የሚል ግንዛቤ ልንወስድበት እንችላለን። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ‹‹መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቶ አህባሽን እየጫነብን ነውና ይቁምልን›› የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንና የመንግስት እርምጃም ከባድ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ጋዜጠኛይቱ ብትጠቅስም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰጡት መልስ ግን በጣም አሳዛኝ ነበር። ‹‹ይሄ የጥቂቶች ጥያቄ ይመስለኛል›› ሲሉ ነበር የጀመሩት። (‹‹ይመስለኛል›› ማለታቸው በራሱ የተናገሩትን እንደማያምኑበት አያሳይም ትላላችሁ?)
ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እዚህ ላይ የምናነሳው የመጀመሪያ ጥያቄ ‹‹ጥቂት ስንት ነው?›› የሚል ነው። ‹‹ጥቂት ስንት ነው?›› ከዚህ ባለፈ ደግሞ ‹‹ለመንግስት ጥቂት የሚባለው የህዝብ ቁጥር ስንት ነው?›› የሚል ጥያቄ እንጨምርልዎ። ዲሞክራሲ መርሃችን በመሆኑ ላይ እስከተስማማን ድረስ የሰለጠነውን አለም ፍቺ መጠቀም እንችላለን። በሰለጠነው አለም ለመንግስት ጥያቄ ያቀረቡ አንድ ሺህ ሰዎች እንኳ በጣም ብዙ ናቸው፤ በጣም ብዙ! አንድ ሺህ ሰዎች የፈረሙት ፔቲሽን በነሱ ዘንድ የብዙዎች እንጂ የጥቂቶች ድምጽ አይደለም። በጎ መሪ ባልታደለችው አገራችን ግን እስካሁንም ሚሊዮኖች ‹‹ጥቂት›› እየተባሉ አሉ።
ታዲያ እኛ ‹‹ጥቂቶች አይደለንም!›› የምንልዎ በሰለጠነው አለም የአንድ ሺ ሰዎች ጥያቄ ምዘና ላይ ተመስርተን አይደለም፤ ሚሊዮኖች ስለሆንን እንጂ! አዎን ሚሊዮኖች ነን! እርስዎም ይህ አይጠፋዎትም። ባይጠፋዎትም ግን ሚሊዮኖች ለመሆናችን ተጨባጭ ማስረጃዎች ጠቅሰን የንግግርዎን ሐሰትነት እናሳያለን። ይኸው፡-
አንድ፡- ብዙም ሳይርቅ ባሳለፍናቸው የኢድና የአረፋ ስግደቶቻችን ላይ ከአገሪቱ ጫፍ እስከጫፍ ድምጻችንን አሰምተናል፤ ብሶታችንን አቤት ብለናል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች በርካታ ከተሞች በተጥለቀለቀ ታላቅ ሰልፍ ‹‹እጃችሁን ከሃይማኖታችን ላይ ሰብስቡልን! መስጊዶቻችንን ለሼኾቻችን ተዉልን!›› ስንል ድምጻችንን አሰምተናል። በኢድ ሰላት የሰላማዊነታችንን ምልክት ነጭ ሪቫን፣ በአረፋ ደግሞ ማስጠንቀቂያውን ቢጫ ካርድ በሚሊዮኖች ክናድ አውለብልበንላችኋል። የሁለቱ ኢዶች ጎርፍ አልታየዎትም ነበርን? ፎቶውን፣ አልያም ቪዲዮውን አልተመለከቱም ይሆን? እሺ ይህም ይሁን! ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ከኢድ ሰላት በኋላ ልማታዊ ንግግር የሚያደርጉልን ከንቲባ እና ሌሎች ባለስልጣናት ወደ ኢዶቹ ሰላት ድርሽ ሳይሉ የቀሩት የጥቂቶችን ድምጽ ፈርተው ነበርን?... ነው ወይስ ከሚሊዮኖች የተባበረ የብሶት ጥሪ ለመሸሽ? ‹‹የጥቂቶች የሰለለ ጩኸት›› ይሆን ቀርተው ከማያውቁበት መድረክ እንዲህ በድንገት ያስጠፋቸው?
ሁለት፡- ጥቂቶች ሳንሆን በርካታ ሚሊዮኖች፣ ይልቁንም ‹‹ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች›› መሆናችንን ያለማወላወል ካሳየንባቸው አጋጣሚዎች አንዱና ዋነኛው በእርስዎ መንግስት አቀናባሪነት የተካሄደው የዘንድሮው የመጅሊስ ቅርጫ-ምርጫ ትርኢት ነው። በዚሁ ጉደኛ ምርጫ በየከተማው የተዘጋጁት የምዝገባ እና የምርጫ ጣቢያዎች ኦና ሁነው ውለዋል። መዝጋቢዎች የሚመዘገብ አጥተው በገጠር ያለውን በማዳበሪያ ና በስንት ጉዳዮች ሲያስፈራሩ በከተማ ያለውን ደግሞ በመኖሪያ ቤት እና በታክስ እያስፈራሩ በግልጽ ታይተዋል፡፡ ካድሬዎቹ የምርጫ መዝጋቢዎችና አስፈጻሚዎች ያለስራ ብቻቸውን ውለዋል። ደህንነትና ፖሊስ የአለቆቻቸውን ‹‹በወንፊት ውሃ ቅዱ›› ትእዛዝ ለማስፈጸም በየመንገዱ የሚያልፈውን ሙስሊም እየጎተቱና እየነዱ ያለምርጫው ወደምርጫ ጣቢያዎች አምጥተው ‹‹አስመርጠዋል!›› መራጭ ድርሽ አልል ሲል አስራ ምናምን ሰዎችን በየቀበሌው እየሰበሰቡ ‹‹እጅ አውጡ›› እያሉ አቦሰጥ ምርጫ አካሂደዋል። እመራዋለሁ የሚሉት መንግስትዎ ለዚህ ሁሉ ትዝብት የተጋለጠው እኛ ሚሊዮኖቹ ‹‹በቅርጫ ትርኢታችሁ አንሳተፍም!›› ብለን ስለተውናችሁ ነበር። አይደለምን? አይደለም ካሉ እስቲ ማስረጃዎን ወዲህ ይበሉ!
ሶስት፡- በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአገሪቱ በርካታ መስጊዶች በሚሰገዱት ሳምንታዊ የጁሙአ ሰላቶች ላይ ተቃውሟችንን እና የተባበረ ድምጻችንን በማሰማታችን፣ ለህገ መንግስታዊ መብታችን በመታገላችን ብቻ ራሳቸውን ‹‹ደህንነት›› ብለው የሚጠሩት ስርአት አልበኞች በየሳምንቱ ሺዎችን ሲያስፈራሩ፣ ሲያስሩ፣ ሲደበድቡ፣ ሲገርፉ፣ ሲገድሉ፣ ሲረሽኑም ቆይተዋል። አመት በሞላው ተቃውሞ ቢያንስ አንድ ጊዜ የመታሰር ወይም የመመታት፣ ወይም መስፈራራት እጣ ያልደረሰው ሙስሊም ወጣት የለም ማለት ይቻላል። አዛውንትና አሮጊቶች፣ ሴትና ህጻናቶች እንኳን መሬት ላይ ተጋድመው ተገርፈዋል። ይህ ሁሉ እስርና ድብደባ ‹‹ለጥቂቶች›› ጩኸት ነበር እንዴ? እንኳን ጥያቄውና ለጥያቄው ሲል የተጎዳው ሰው ቁጥር ራሱ ጥቂት አይደለም። ፌደራሎች የገደሉት ሰው ቁጥር እንኳ ጥቂት አይደለም - ‹‹ጥቂት›› የ‹‹ሚሊዮን›› ሁለተኛ ስሙ ነው ካላሉን በስተቀር!
ከኛ በኩል የሚጠቀሰውን መረጃ እዚህ ላይ ገታ አድርገን የርስዎ ጓደኞች እና የስራ ባልደረቦች እንኳን ሚሊዮኖች መሆናችንን ለማመን እየተገደዱ መምጣታቸውን ለምን አናሳይዎትም? በራስ ሲሆን ያምራል ይባላል!
አራት፡- በቅርቡ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት ውስጥ ከንቲባው አቶ ኩማ ደመቅሳ እርስዎ ‹‹የጥቂቶች›› ያሉትን ጥያቄ እና ያስከተለውን መዘዝ አስመልክተው በስብሰባ ንግግር ሲያደርጉ ‹‹ልማት ትተን እዚህ ጉዳይ ውስጥ ተዘፍቀናል፤ ቢዚ አደረገን፤ ስራ መስራት አልቻልንም›› ብለው ነበር። (ባለስልጣናት ቢሮዋቸውን እርግፍ አድርገው ትተው ‹‹መስጊድ መዋላቸው›› ከማንም በፊት ችግር የፈጠረው ለኛው ነው፤ ጥያቄያችን ‹‹ከመስጊዳችን ውጡልን!›› ሆኖ ሳለ ‹‹ቢዚ አደረጋችሁን›› መባሉ ምንኛ ምጸት ነው!?) ታዲያ አቶ ኩማ እንዳሉት እርስዎንና ባልንጀሮችዎን እንደዚህ በስራ የጠመደው ጉዳይ ‹‹የጥቂቶች›› ስለሆነ ይሆን? ችግሩ ሚሊዮኖችን ‹‹እኔ የመረጥኩላችሁን ሀይማኖት ካልተቀበላችሁ አሸባሪዎች ናችሁ›› እያለ ሰላም የነሳው የአህባሽ አጀንዳ ነው ወይስ ‹‹የጥቂቶቹ›› ድምጽ!?
አምስት፡- የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ሽመልስ ከማል ይህንኑ ‹‹የጥቂቶች›› ጉዳይ አስመልክቶ ከአለማቀፍ ሚዲያ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲመልሱ በቅርቡ የምላስ ወለምታ ገጥሟቸው ነበር። አልያም እውነታውን መካድ የማይችሉበት ቅርቃር ውስጥ ገብተውም እንደሆን እንጃ። ብቻ በተቃውሞ ሰልፎች ላይ ስለሚሳተፈው በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም ሲጠየቁ ‹‹አክራሪዎች አሳስተውት ነው›› ብለው አረፉ። ቢያንስ ብዛቱን ከሚክዱ መሳሳቱን ገልጸው መገላገላቸው ነበር። ባልታደለችው አገራችን ዛሬም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ድምጽ ከጥቂት ባለስልጣናት ድምጽ ያነሰ ዋጋ ነው ያለው! አንድ ባለስልጣን አንዳችም ሳይሳቀቅ ሚሊዮኖችን ‹‹እናንተ ተሳስታችኋል! ልክ እኔ ነኝ!›› ይልባታል - በምስኪኗ እናት አገራችን!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር! እርስዎ ዛሬ ደፍረው ‹‹ጥቂቶች ናችሁ›› ቢሉንም እኛ ቁጥራችንን በትክክል እናውቀዋለን። በቀናኢ ሐይማኖተኝነት ስምዎ በተደጋጋሚ የሚነሳ እንደመሆኑ እርስዎ ራስዎን ለትዝብት አጋለጡ እንጂ የትግል ስሜታችን በመሰል ንግግሮች እንደማይቀዘቅዝ እኛ ሚሊዮኖቹ እናውቃለን። ውሸት ከአገራችን ፖለቲካ የሚጠፋበትን ወቅትም በናፍቆት እንጠብቃለን። እድለኛ ሆነው በሰሞኑ ቃለ መጠይቅ ገራገር ቢጤ ጋዜጠኛ ስለገጠመዎ ፈጣሪዎን ያመስግኑ። ጋዜጠኛይቱ እጅግ አስደማሚው የኢድ ሰላት ተቃውሞ ላይ የተነሱ ፎቶዎችን አልያም የተቀረጹ ቪዲዮዎችን አሳይታ ጠይቃዎት ቢሆን ኖሮ መልስዎ ምን ይሆን እንደነበር ሁላችንም ብናውቅ ምንኛ ደስ ባለን!
አሁንም አንድ ነገር ባይረሳ ደስ ይለናል። የምንገኝበት ወቅት የኤሌክትሮኒክስ ዘመን ነው። ከሃያና ሰላሳ አመታት በፊት እንደነበረው ቪዲዮ ካሜራ ኢቲቪ ቅጥር ግቢ ውስጥ ብቻ አይደለም የሚገኘው። ይልቁንም በየሰዉ ሞባይል ላይ እንደልብ የሚገኝ ነገር ነው። በመሆኑም ሰዎች በዙሪያቸው የሚገጥማቸውን ያነሳሉ፤ ይቀርጻሉ። ያለፈው አንድ አመት ትግላችንም ሕዝባዊ እንደመሆኑ እስኪበቃው ተጸርጾዋል፤ ፎቶ ተነስቷል፤ ተመዝግቧል። በአል ጀዚራ በተደጋጋሚ ተዘግቧል፡፡ አንድ የፌስ ቡክ ግሩፕ ቢከፍቱ በመቶ የሚቆጠሩ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን ያገኛሉ። እነዚህ ሁሉ በርካታ ፎቶዎች የሚያሳዩዎት ደግሞ አንድና አንድ አውነታ ነው - ሚሊዮኖች እንጂ ጥቂቶች እንዳልሆንን! እርስዎ ዛሬ ‹‹ጥቂት ናችሁ›› ሲሉን ትንሽ ማጣራት ያደረገ ሰው ይታዘብዎታል።
ማረሚያ ቢጤ ይቀበሉንና የዛሬ ጽሁፋችንን እናብቃ፡- ‹‹ጥቂት›› እኛ ሳንሆን ‹‹ጥያቄያችን›› ነው! በእርግጥም ጥያቄያችን ጥቂት እና ቀላል ነው! እኛ ጠያቂዎቹ ደግሞ ሚሊዮኖች ነን! መንግስትዎን ወክለው ይህችን በልብዎ የሚያውቋትን እውነታ በአፍዎ አልያም በተግባርዎ አረጋግጠው ህገ መንግስቱ ያረጋገጠልንን መብት ባይነፍጉን ችግሩ ሁሉ ተፈታ ማለት ነው፤ በእርግጥም እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ከመግባት ጥቂቶቹን ጥያቄዎቻችንን መመለስ ይቀላልና! አይቀልምን?
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment