ጥቂት ማለት ስንት ነው? ብሎ የጠየቀው የዛሬ የተቃውሞ ውሎ
ተቃውሞው በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች በተወከሉ ከተሞች ተከናውኗል
የመንግስት ፖሊሶች ሴቶችን መደብደብና ማሰር ልምድ አድርገውታል
ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ ላይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአልጀዚራ እንግሊዝኛ ክፍል ሰጥተውት በነበረው ቃለ መጠይቅ ቅዋሜ የሚያነሱት ሙስሊሞች ቁጥር በጣም አናሳና ጥቂት ናቸው ብለው ተናግረው ነበር፡፡ እኛም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ ቁጥራችንን እያወቁት? ስንል በወቅቱ ጠይቀናቸዋል፡፡ ለነገሩ የመንግስት ባላስልጣናት አንድ ጊዜ ጥቂቶች ናቸው፣ ሌላ ወቅት አሸባሪዎች ናቸው፣ አንድ አንዴም ሳት እያላቸው በጥቂቶች የተሳሳቱ ብዙሀን ብለው የሚጣረሱ መግልጫዎች ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ይሄ ሁሉ ከእውነት እና ከሐቅ ሽሽት መሆኑ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥራችንም ሆነ በጥያቄዎቻችን ሕጋዊነት ላይ ጥርጣሬ ካላቸው ይኸው ዛሬም አደባባይ ወጥተን፣ በታላቅ ሕዝባዊ ማእበል አጅበን በተመረጡ የአገሪቱ ከተሞች ጥያቄዎቻችንን ዳግም ለሚመለከተው አካል አቅርበናል፡፡
አዎ! አንደኛ አመቱን ሊጨርስና ወደ ቀጣዩ የትግል ዓመት ሊሸጋገር የቀናት እድሜ ብቻ የቀሩት ሰላማዊ ትግላችን ዛሬም ኢትዮጵያን በፍትህ ፈላጊዎች ድምጽ ሲንጣት ውሏል፡፡ መሐል አገር አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች የሚገኙ ከተሞች ተቃውሞአቸውን በተሳካ መልኩ ያደረግንበት የዛሬው ውሎ በአይነቱ ለየት ያለና ሚሊዮኖችን ያሳተፈም ጭምር ነበር፡፡ በመሀል አገር አዲስ አበባ አንዋር መስጊድ፣ በምስራቅ ሀረር ከተማ፣ በሰሜን ደሴ ከተማ፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጅማ፣ በወልቅጤና መቱ ከተሞች ደማቅ ተቃውሞዎች ተካሄዶባቸዋል፡፡
ይህ ቀን ለኛ የመጀመሪያችን ባይሆንም የዛሬው ተቃውሞአችን ልዩ የሚያደርገው ከኢድ አል አድሀ አገር አቀፍ ተቃውሞ በኋላ የመጀመሪያው የተባለ ሰፊ ሕዝብ የተገኘበት እና ከፍተኛ ድምቀት የነበረው መሆኑ ነው፡፡ ይህም ትግላችን እያበበ እና እየጋመ መሄዱን አመላካች ከመሆኑም በላይ ያነሳናቸው ሕገ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስም የጀመርነውን ሰላማዊ ትግል አጠናክረን እንደምንዘልቅ ያረጋገጥንበትም ጭምር ነው፡፡
በታላቁ አንዋር መስጊድ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተገኝቶ የነበረው ሕዝብ እጅግ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን በሕዝቡ ገጽታ ላይም ወኔና ቁጭት አይሎ ታይቷል፡፡ ‹‹እኛ… ሚሊዮኞች ነን›› በሚል አብይ የተቃውሞ ርዕስ የተሰባሰበው ሙስሊም ሕብረተሰብ የጁምዓ ሰላት እንደተጠናቀቀ የተቃውሞውን ድምጽ ማሰማት የጀመረ ሲሆን ተክቢራ፣ ‹‹እኛ….. ሚሊዮኖች ነን››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ››፣ ‹‹ምርጫው…… ሕገ ወጥ››፣ ‹‹ሕጉ ይከበር›› እና ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የሚሉ መፈክሮችን ያሰማ ሲሆን፤ እንዚሁ ሀሳቦች የሰፈሩባቸው መፈክሮችንም በእጁ ከፍ አድርጎ በመያዝ አሳይቷል፡፡
እንደ አዲስ አበባው ሁሉ ታላቅ ተቃውሞ የተደረገባት የምስራቋ ሐረርም ኢማን መስጊድን (አራተኛ መስጊድ) ጨምሮ በአምስት መስጊዶች ዛሬ ደማቅ ተቃውሞ አስተናግዳለች፡፡ በዚህ በአይነቱ ልዩ በተባለለት ተቃውሞ የተገኘው ሕዝብ በርካታ የነበረ ሲሆን፤ የሕዝቡን ብዛት ተከትሎም ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በከተማዋ ተከስቶ ውሏል፡፡ በዛሬው ልዩ ተቃውሞ የታሰሩት ይፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ እና ሚሊዮኖች ነን የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡
በደሴ ሸዋ በር መስጊድ፣ በወልቂጤ ረቢዕ መስጊድ፣ በመቱ ነጃሺ መስጊድ እንዲሁም በጅማ ራሕማ መስጊዶች ዛሬ የተሰሙት የተቃውሞ ድምጾች ትግላችን፣ አንድነታችን፣ ለመብቶቻችን መከበር ያለንን ቁርጠኝነት፣ ሰላማዊነታችንነ እና አገር ወዳድ ዜጎች መሆናችንን ጭምር ያሳየንበት ታሪካዊ ቀንም ጭምር ነው፡፡
ይህ ያልተዋጠላቸው የመንግስት ፖሊሶች ዛሬ የተለመደውን ትንኮሳ በሴት እህቶቻችን ላይ በመፈጸም አሰቃቅ ድብደባ በሴት እህቶቻችን ላይ ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ ሁሌም ግርግርና ሁከት ለመፍጠር ዝግጁ የሆኑት ፖሊሶች ባልተለመደ መልኩ አሁን አሁን ሴቶች እህቶቻችን ላይ የሚወስዱት የድብደባና የእስር እርምጃ እየተባባሰ መጥቷል፡፡ ከሴት ማህጸን የወጡ የማይመስላቸው የፖሊስ አባላት ዛሬም በአንዋር መስጊድ መውጫ በሮች አካባቢ በእህቶቻችን እና እናቶቻችን ላይ ጸያፍ ድብደባ ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ ጥቂት የማይባሉ እህቶቻችንንም በመጫን በሙስሊም እስረኞች ወደተሞላው አራተኛ ጣቢያ አጉዘዋል፡፡ ይህ ድምጽን ለማፈን የሚደረግ ጥረት ግን ፈጽሞ ሊሳካላቸው እንደማይችል ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን፡፡
ያሰማነው ድምጽና ቁጥራችንን እንዲሁም ጥያቄያችንን የምርም ያልተረዱና ያልገባቸው የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ዛሬም በቂ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ እኛ ሰላማዊነታችንን ጠብቀን መብታችን እንዲከበርልን እየጠየቅን ያለነው መንግስት ከሕግ አግባብ ውጪ ሃይማኖታችን ውስጥ ጣልቃ እየገባ በመሆኑ፣ የማንፈልገውን እምነት እየጫነብን በመሆኑ፣ የኢሕአዴግ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ መ/ቤትን አመራሮች በራሱ መርጦ ማስቀመጡ፣ የሰላም አምባሳደር መሪዎቻችንን በማሰር በወህኒ እያንገላታ በመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ ምድር ሙስሊም መሆን ወንጀል ነው የተባለ እስኪመስል ድረስ ሙስሊሞች ከገጠር እስከከተማ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው በመሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ከህገ መንግስቱ ያፈነገጡ ድርጊቶች እስካልተስተካከሉና እስካልታረሙ ድረስ ትግላችን ተራራ እና ሸንተረሮች ሳያግዱት በአገረ ኢትዮጵያ ሁሉም አቅጣጫዎች መናኘቱን ይቀጥላል፡፡ የእልፍ አእላፎች ዝማሬ የሆነው ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› መፈክራችን ገና ከፍ ብሎ ይሰማል፣ ድላችን ቀርቧል፤ የድል ወጋገን ጎላ ብሎ እየታየን ነው፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment