ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ - መስጊድ ነጠቃ!
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መሠረታዊ የእምነት ነፃነት መብታችን ተጥሶ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጣን ድፍን አንድ አመት ሞላን፡፡ ይህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን አንድ ላይ ያስተሳሰረ ተቃውሞ መነሻውም ሆነ መድረሻው የመንግስት በሐይማኖታችን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች በይፋ መጣሳቸው ነው፡፡ አሕባሽ የተሰኘውን አንጃ ከሊባኖስ በማስመጣት በሙስሊም ዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን የተደረገው ሙከራ ለዚህ የከፋ ድርጊት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡
አሕባሽ በከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ታጅቦ በመንግስት ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሊፈፅማቸው ያሰባቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ነበሩት፡፡ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአህባሽ የግዳጅ ጠመቃ ላይ በወጣው ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በአህባሽ የመጅሊስ አስተዳደር ጥብቅ ቁጥጥር ስር እንዲውል፣ ማንኛውም የመስጂድ ኢማምም ሆነ ዳዒ ይህንን የአሕባሽን ስልጠና እንዲሳተፍ፣ የአሕባሽን ስልጠና ያልወሰደ ማንኛውም ኢማም ማሰገድ እንደማይችልና ስልጠናውን ያልወሰደ ኢማም ቦታም ስልጠናውን በወሰደ ሌላ ሰው እንደሚተካ፣ የአህባሽን ስልጠና ያልወሰደ እና ከአህባሽ የመጅሊሱ አስተዳደር ሰርተፊኬት ያልተሰጠው ማንኛውም ዳዒ በየትኛውም መድረክ የኃይማኖት ትምህርት እንዳይሰጥ፣ በሕብረተሰቡ ጉልበት፣ ሀብትና ጥረት የተገነቡ ማንኛውም ኢስላማዊ ተቋማት ለአሕባሽ እንዲሰጡ… አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡
ይህ አዋጅና በከፍተኛ የመንግስት ሁለንተናዊ እገዛ የተደረገው የአሕባሾች እንቅስቃሴ የህዝብን ቁጣ ቀስቅሶ እነሆ መብረጃ ወዳልተገኘለት ቀውስ ውሰጥ ገብቶ ይገኛል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ በወሰዳቸው ቆራጥ የተቃውሞ እርምጃዎች የአሕባሽ ፕሮጀክቶች አንድ ባንድ ተንኮታከተዋል፡፡ ዛሬ ስለ አህባሽና አደገኛ ሴራው ያልተረዳ እና ራሱንም ቤተሰቡንም ከአደጋው ያልጠበቀ ሙስሊም ግልሰብ ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ይሁንና መንግስት በዚህ ተፀፅቶ እርምት ሊወስድ ሲገባው አላስፈላጊ እልህ ውስጥ በመግባት እነሆ የብዙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እጣ ፋንታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት የአህባሽ ፕሮጀክት የመጨረሻ ተግባራትን የፖለቲካ ኃይሉን ተገን አድርጎ ለማስፈፀም እየተጋ ይገኛል፡፡
መንግስት ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ያደራጃቸውን ቡድኖች ስትራቴጂካዊ ቅርጫ በማድረግ ነባሩን የአሕባሽ አመራር በሌላ የአሕባሽ አመራር አካላት ተክቷል፡፡ ይህም ለቀጣይ የመጨረሻ የአህባሽ ፕሮጀክት አፈፃፀም እንደሚረዳው በመተማመን እነሆ በአሁኑ ሰዓት ይህንኑ ድፍረት የተሞላበትን እርምጃ መውሰድ ጀመሯል፡፡ በሕዝብ ንፁህ ሀብት፣ ጉልበት፣ ደምና መስዋዕትነት የተገነቡ ኢስላማዊ ተቋማትም ሆኑ መስጂዶች ለሙስሊሙ ሕዝብ ትርጉማቸው ከ‹‹ግንብ›› ከ‹‹ሕን›› በላይ ነው፡፡ አይደለም ዛሬ የመጣበትን አደጋ ለመከላከል እጅ ለእጅ ተሳስሮ አንድነቱን ይፋ ባደረገበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ይቅርና ያኔም በቀደመው ጊዜ በነኚህ ሀብቶቹ ላይ የመጣውን አካል ያለምንም ማቅማማት ሲጋፈጥ ቆይቷል - በዚህ ጉዳይ ተደራድሮም አያውቅም፡፡
ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይም እዚህ በመዲናችን አዲስ አበባ እና ደሴ ከተማ እየተደረገ ያለው አደገኛ አካሄድ አፀፋ ከማውገዝም በላይ ሊሆን እንደሚችል ማንም ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው የሚጠፋው አይደለም፡፡ ህዝብ ጥሮ ግሮ ያፈራቸውና ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን መስጂዶች በፖሊስና በወታደር ኃይል በማስፈራራት፣ በመከብበብና በማገት ለመንጠቅና እና ለአሕባሾች አሳልፎ ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በተለይም በደሴ ከተማ እየተስተዋለ ያለው ሁኔታ ትእግስትን የሚፈታተን ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው፡፡ የዚህ የመንግስት አካሄድም ተልዕኮውም ግልፅ ነው፤ ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት እልቂትና ፍጅትን መጋበዝ ነው፡፡ መስጂዶቻችንን መንጠቅ፣ ኢማሞቻችንን በማባረር በአሕባሾች መተካት በየትኛውም ሐይማኖት ተከታዮች ላይ ታስቦ እንኳን የማይታወቅ ድፍረት ነው፤ የዚህን ድርጊት መቀጠል ተከትሎ ለሚከሰተው ማንኛውም ጥፋት መንግስት ራሱ ተጠያቂ እንደሚሆን ቀድሞ ሊያምንበት ይገባል፡፡ መስጂዶቻችን የህልውናችን ጉዳዮች ናቸው፡፡
አሕባሾን ከማደራጀትና በሌላው ላይ በግድ ከመጫን ያልተቆጠበው መንግስት የህዝብ ንብረት በሆኑት መስጂዶቻችን ላይ ወረራ ከማካሄድ የራሳቸውን መስጂድ ሊገነባላቸው ይችላል፡፡ ከዚህ ቀደም በከሸፉት የአሕባሽ ፕሮጀክቶች፤ በተለይም ሕብረተሰቡ በአንድ ድምጽ የአሕባሽን አስተሳሰብ ከእውቀት በመነሳት አንቅሮ በመትፋቱ በመበሳጨትና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጦ ያለ የሌለ ሃይልን በመጠቀም በተጨባጭ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ መዘዙ የከፋ እና የአገራችንንም ገፅታ እስከመጨረሻው ድረስ ሊያበላሽ እንደሚችል ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም መቼም ቢሆን መስጂዶቹን አሳልፎ እንደማይሰጥ ቢታወቅም በተዘጋጀለት ወጥመድም ላይ እንደማይወድቅም ሊታወቅ ይገባል፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment