Friday, January 18, 2013


ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት መንግስትንና አጫፋሪዎቹን ያንበረከከ በአይነቱ ልዩ የሆነ ተቃውሞ በደሴ!!

ዛሬ በደሴ ከተማ ሙስሊሙ መንግስት ኢማም የመደበባቸውን መስጂዶች ባዶ በማድረግና ሌሎች መስጂድ ሂዶ በመስገድ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ የመንግስት ቅጥረኛ የሆኑት ኢማሞች ከጥቂት ግለሰቦች በስተቀር በመስጂዱ ውስጥ ብቻቸውን ሰግደዋል፡፡ ሌሎች መስጂዶችም የሚሰግድባቸው ጠፍቶ ተቆልፈው እንደዋሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዛሬ ፔፕሲ፣ አሬራ፣ ሜጠሮ ጎሮ እና ጦለሃ መስጂድ እጅግ በጣም ብዙ ሰው የተገኘባቸው ሲሆን አረብ ገንዳ፣ ሸዋበር፣ ፉርቃን እና ዳዌ መስጂዶች በሰው እጦት ባዷቸውን ውለዋል፡፡ በዳዌ ሜዳ(አራዶ) መስጂድ እነዚህ የመንግስት ሹሞች በቅሬ ሁሉም ሰው መስጂድ እንዲመጣ ትእዛዝ በማስተላለፍ ቢያስፈራሩም መስጂዱ ውስጥ ከአስር ያልበለጠ ሰው ብቻ እንደተገኘ ታውቋል፡፡ ፉርቃን መስጂድ እና ቄራ መስጂድም እንደዚሁ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ሰግደው ተመልሰዋል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዛሬ ልዩ የሆነ ተቃውሞውን አህባሾች በተመደቡበት መስጂድ ባለመስገድ ልዩ የሆነ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

ሙስሊሙን ለመረበሽና የንፁሃንን ደም ለመጠጣት የሚሯሯጡት የመንግስት ኃይሎች ከመቼውም በላይ ዛሬ በሙስሊሙ ላይ ጥቃት ለማድረስ ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን እነሱ ያሰቡት ሳይሆን በአላህ ፈቃድ ጭራቃዊ ተግባራቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ገና ከጧት ጀምረው በሸዋበር መስጂድ አካባቢ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች ቦታውን ሲቃኙ የነበረ ሲሆን ረፋዱ ላይ ጭንብል የለበሱ አድማ በታኞችንና እጅግ በጣም በርካታ ፖሊሶችን በሸዋበር መድረሳ ውስጥ እንዲቀመጡ አድረገዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ተክቢራ ይደረጋል ብለው ሲጠብቁ ልዩ በሆነ መልኩ ሙስሊሙ ለመንግስት ቅጥረኛ ለሆኑት ኢማሞች ጀርባውን በመስጠትና ጆሮውን በመያዝ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ትላንት ፀጥታ ዘርፍ ቢሮ ስብሰባ አድርገው የነበረ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ለሶላት ሲቆም በተሰማው የጭብጨባ ድምፅ እርምጃ ባለመወሰዱ በቦታው ተመድበው ለነበሩት የፌደራለ አዛዦች ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ዛሬ በሸዋበር መስጂድ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ሲቪል በመልበስ መስጂድ ውስጥ የገቡ ሲሆን ሙስሊሙ መስጂዱን ባዶ በማድረጉ እነርሱ ለመደቧቸው ኢማሞች አጃቢ ሁነው ውለዋል፡፡

እኛ ሙስሊሞች ብንደበደብም፣ ብንታሰርም ብሎም ቢገድሉን ጥያቄያችን እስካልተመለሱ ድረስ ሰላማዊ ተቃውሟችንን በምንም አይነት መልኩ አናቆምም! የተቃውሞ ሂደቱን እየቀያየርን እስከመጨረሻው ድረስ እንጓዛለን!
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment