የትግላችን መነሾና የጥያቄዎቻችን እንድምታ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡-
በአወሊያ ሙስሊም ሚሽን ት/ት ተማሪዎች የተጀመረውና ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ያደገው ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የኃይማኖት ነፃነት ጥያቄ እና የመንግስት ጣልቃ ገብነትና የመብት ጥሰት ተቃውሞ እነሆ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ በዚህም አመታዊ ጉዞው ውስጥ ከደርዘን በላይ ሙስሊሞች ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፤ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ 29 ሙስሊሞች ታስረዋል፤ በሽብርተኝነትም ተከሰዋል፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ሙስሊሞች በመላ ሀገሪቱ እስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ፤ ብዙ ምዕመናን አካላቸውን አጥተዋል፤ ብዙ ሙስሊሞች የሚወዷት ሀገራቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ትተው ተሰደዋል፤ ብዙ የሙስሊም ልማት ድርጅቶች፣ የገንዘብ፣ ኢኮኖሚና የንግድ ተቋማት፣ የየቲሞች መረዳጃና ማሳደጊያ ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት ተዘግተዋል፣ የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል፣ ገንዘባቸው ተወርሷል፤ የሙስሊም ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይመለሱ ተከርችመዋል፡፡ የእምነት ማዕከላትና መድረሳዎች ተዘግተዋል፤ መስጂዶች ፈርሰዋል፤ የግዳጅ ሰልፎች ተስተውለዋል፤ ሰላማዊ ትግሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር ሀገሪቱ ሰፍኗል፤ወዘተ...
የዚህ ምልከታ ዓላማም የትግሉን ጉዞ ሂደት ማለትም መነሻ ምክንያቶች፣ ስኬቶች፣ ድክመቶች፣ ስጋቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን ለመጠቆም ያለመ ነው፡፡ የችግሩ ቁልፍ መነሻ
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከ1987ቱ የአንዋር መስጅድ ጭፍጨፋ በኋላ ከመጅሊስ እጁን አንስቶ ባያውቅም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ይፋዊ የሆነ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ አልጀመረም ነበር፡፡ ከሀምሌ ወር 2003 ጀምሮ ግን አዲስ ጥፋት ተጀመረ፡፡ መንግስት በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በኩል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ካደረገ በኋላ በዚሁ ወር በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሀረር ካምፓስ ውስጥ በ1980ዎቹ አካባቢ በሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት እንደተጀመረ የሚነገርለት አል-አህባሽ የሚባል እምነት በመንግስትና በመጅሊሱ ቅንጅት ከሊባኖስ በመጡ 200 መምህራን በይፋ ማጥመቅ ተጀመረ፡፡ በዚህም 1300 አካባቢ የሚሆኑ የፌደራልና የክልል የመጀሊስ ቢሮዎች አባላት ተካፋይ ሆነዋል፡፡ ከዚህ በኋላም በተከታታይ ቀጥሎ የነበረው የአስገዳጅ ስልጠና በየአካባቢው መሰጠቱ ሲቀጥል፣ ስልጠናውን የተቃወሙ ሙስሊሞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ የአሸባሪነት ስያሜም እየተሰጣቸው ለማሸማቀቅ ተሞክሯል፡፡ እንዲሁም ሁሉም የመስጂድ ኢማሞችና ሙዓዚኖች በአህባሾች አቀንቃኞች እንዲቀየሩ፣ ሁሉም የሙስሊም ትምህርት ቤቶችና ማዕከላት በአህባሽ አስተምህሮ እንዲቀየሩ ካልሆነም እንዲዘጉ በሚለው የመንግስት ዕቅድ መሰረት ብቸኛው የሙስሊሞች ኮሌጅ የሆነው አወሊያም እጣው ደርሶት በ2004 ታህሳስ 21 ቀን የኮሌጁ 50 የአርብኛ መምህራን እና የመስጂዱ ኢማምና ምክትላቸውን ጨምሮ በመጅሊሱ ቀጭን ትዕዛዝ በአንድ ሌሊት እንዲባረሩ ተደረገ፤ በዚህ ምክንያት ኮሌጆም ተዘጋ፡፡ ይህ ያስቆጣቸው የአወሊያ ኮሌጅና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ታህሳስ 24 ቀን ‹‹ኢማሙና መምህራኖች ይመለሱልን፣ ኮሌጁም ይከፈት!›› በማለት የተቀውሞ ድምጽ ማሰማት ጀመሩ፡፡ ይህ ችግር በቀላሉ ሳይፈታ ቀርቶ ወደ ሀገራዊ አጀንዳነት በማደጉ ‹‹የመጅሊስ አመራሮች ይውረዱ!›› የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡ የችግሩ ቁልፍ መነሻ የኃይማኖትና እምነት ነፃነት በሚፃረር፣ የኢትዮጲያን ህገ-መንግስታዊ አንቀፅ 27 እንዲሁም የዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን በሚጥስ ሁኔታ መንግስት በኃይማኖት ጉዳዩች ጣልቃ መግባቱና አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ መጀመሩ ነበር፡፡ ነውም፡፡
የሰላማዊ ትግሉ ህጋዊ አካሄድ
ይህ የተማሪዎች ጥያቄ ወደ ሀገራዊ አጀንዳነት ከተቀየረ በኋላ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት ሲጀምሮ ህገ-መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ጥር 11 ቀን ወኪሎችን በመምረጥ 17 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቀረ፡፡ ይህ ኮሚቴም ዘርፈ-ብዙ ከሆኑት ከህዝቡ ከተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ውስጥ ሶስት ጥያቄዎችን ብቻ በመለየት ለመንግስት ለማቅረብ ተሰናዳ፡፡ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ከህዝብ ከቀረቡ ጥያቄዎች እነዚህ ሶስቱ ሲመረጡ በርካታ ነጥቦችን ከግንዛቤ በማስገባት ነበር፡፡ በቀጥታ ተቃውሞው እንዲነሳ ምክንያት የሆኑት ላይ ብቻ በማተኮር፣ ከእምነት ነፃነትና የህገመንግስታዊ መርህን ሙሉ ድጋፍ የሚያገኙትን፣ በሃይማኖታችንና በመንፈሳዊ ተቋማችን ብቻ የታጠሩትን፣ መንግስት ከመመለስ ውጭ ምክንያት ሊያቀርብ እድል የማያሰጡትን፣ በፅንሰ ሃሳብና አሻሚ በሆኑ ነገሮች ላይ የተገነቡ ሳይሆን ግልፅና በተግባር መመለሳቸው ሊረጋግጥ የሚችሉ፣ ቀላሎቹን፣ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሹትን፣ ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያሳምኑትን፣ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ባህሪ ያላቸውን፣ 3 ጥያቄዎችን በመለየት ነበር የመንግስት ባለስልጣናትን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማፈላለግ ስራውን የጀመረው፡፡
ሦስቱ መሰረታዊ የትግሉ ጥያቄዎችም፡-
1. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አመራሮች በሙሉ የሕዝበ ሙስሊሙ ውክልና የሌላቸው በመሆኑ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ በነጻነት በሚመረጡ አመራሮች ይተኩልን
2. በመጅሊሱ አማካኝነት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ በግድ እየተጫነ ያለው የአሕባሽ የማጥመቅ ዘመቻ ይቁምልን እና
3. አወሊያ የህዝበ ሙስሊሙ ነጻ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል መጅሊስ እጁን ከአወሊያ ያንሳ የሚሉ ነበሩ፡፡
በዚህም መሰረት የሰላማዊ ትግሉ ዓላማና ግብ ከመንግስትና መጅሊስ እጅ ነፃ የሆነና ህትሃዊ ምርጫ ይካሄድ፤ እንዲሁም ሙስሊሙ ተቋማት በራሱ በሙስሊሙ ፍላጎት ይመሩ የሚል ማለትም የኃይማኖታዊ ተቋማትን የማደራጀት፣ ኃይማኖታዊ የመምረጥና የመመረጥ መብቶች መከበር ላይ የሚያተኩር ነበር፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻው ይቁም ሲል የኃይማኖት፣ የእምነትና የአስተሳሰብ መብትና ነፃነት ይከበር፣ መንግስት እጅህን አንሳልን የሚል ትልቅ እንድምታ ያለው ነበር፡፡ የትግሉም ውጤትና ስኬት የሚለካው ከዚሁ ዓላማና ግብ አንፃር ነው፡፡
ኮሚቴውም እነዚህን ጥያቄዎች ይዞ ከመንግስት አካል ከሆነው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር ባደረገው ከሶስት ያላነሱ ውይይቶች መሰረት የካቲት 26 መንግስት ‹‹መልሴ ነው›› ያለውን የመጨረሻ አቋሙን እንደሚከተለው አሳወቀ፡-
1. የመጅሊስ ምርጫ በቅርቡ ይካሄዳል፤ እንዴት በማንና በምን መስፈርት የሚሉት ግን ዝግ ነበሩ
2. አወሊያና መሰል የሙስሊሙ ማዕከላት በመጅሊሱ በሚመረጥ ቦርድ ይመራሉ እና
3. የአህባሽ ስልጠናም ይቀጥላል የሚሉ ነበሩ፡፡
ምንም እንኳን ጥያቄዎቹ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት፣ በዓለማቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በግልፅና በማያሻማ መልኩ የተቀመጡ ቢሆንም የመንግስት ምላሽ ግን ሰብዓዊነትን የሚጋፋ፣ የኃይማኖት ነፃነት መብትን በእጅጉ የሚጥስና ኢትዮጲያ የፈረመቻቸውን ዓለማቀፋዊ ስምምነቶች በሙሉ ቅርቃር ውስጥ የሚከት ነበር፡፡ ኮሚቴውም ሰላማዊነትንና ህጋዊነትን ብቻ በመላበስ የፌደራል ጉዳዮች የሰጠው ምላሽ ትክክለኛና ጥያቄዎቹን በደንብ ያላገናዘበ መሆኑን በፅሁፍ ጭምር በማሳወቅ ወደ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ድረስ በደብዳቤ በማስረዳት እንዲሁም ለውይይት በመጋበዝ ብዙ የተጓዘ ቢሆንም ሳይሳካና ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
ከየካቲት 26ቱ ምላሽ በኋላ መንግስት በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን ሰላማዊ ትግሉንና ጥያቄውን በአክራሪነትና በአሸባሪነት በመፈረጅ የማጠልሸት ፕሮፓጋንዳውን በይበልጥ ተያያዘው፡፡ ኮሚቴውም ለወቅታዊ ክስተቶች ማብራሪያዎችን እየሰጠ እንዲሁም በየክልሉ የትግሉንና የጥያቄዎቹን ምንነት በህዝብ ዘንድ ለማስረፅ እንዲሁም የህዝብን አንድነትና ሰላማዊ አካሄድ ብቻ ለማስረፅ ብዙ ተጉዟል፡፡ መንግስት የመጅሊስ አመራሮችን ለመቀየር ቢፈልግም ምርጫወውን ግን ለራሱ ቁጥጥር በሚያመቸው መልኩ በመንግስት አስተዳደራዊ ቦታዎች ማለትም በቀበሌ እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት ህዝበ-ሙስሊሙ ‹‹ምርጫችን በመስጅዳችን›› እያለ ቢቃወምም በእምቢተኝነት ህዝብ ያልተሳተፈበት የምርጫ ድራማ በመስከረም ወር አድርጎ በአዲስ የመንግስት ካድሬዎች ተክቷል፡፡ እስካሁንም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን መስጅዶችና መድረሳዎች በመጅሊሱ ቁጥጥር ስር ለማስገባት ሩጫውን እንደቀጠለ ነው፡፡ የተቃወሙትን እስር ቤቶች በማጎር ላይ ይገኛል፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ከ 365 ቀን በኋላ ዛሬም ፍትሓዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ መስማት የነበረባቸው አካላት ጆሮ ዳባ ልበስ ቢሉም ለመስማት እስኪገደዱና መልስ እሰከሚያገኝ ድረስ ያለ መሰልቸት ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፡፡ ድካሙም ከንቱ እንደማይቀር በአላህ ላይ ሙሉ እምነት ጥሎ ወደፊት ይጓዛል፡፡ መሰረታዊ መብቱ እየተጣሰ እንዳላየ ሆኖ ዝም የሚልበት ጊዜ በአላህ ፈቃድ ላይመለስ ተሸኝቷል፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment