ጁመዓ የማይቀርበት ታሪካዊ ቀጠሮ አለን!
የኢስላም አስተምህሮ ከኛ ይደርስ ዘንድ የታለፈባቸው ወሳኝ መንገዶች እኛም እንድንጓዝባቸው የአላህ ፍላጎት መሆኑን እነሆ ተጨባጩ ያስረዳል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን ዲናቸውን በመጠበቅ የሰሩት አኩሪ ገድል በእኛም እንዲደገም ወቅቱ እየተጣራ ነው፡፡ የወቅቱንም ጥሪ በተግባር የሚመልሱ ሚሊዮን ቢላሎችና ሚሊዮን ሱመያዎችን በእርግጥም አይተናል፡፡ የቢላልና የሱመያን መንገድ ለመረጃ ፍጆታነት ሳይሆን ለህይወት መርህነት የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያኖችን አይናችን አይቷል፡፡ ታሪካችንም ዘግቦት እያለፈ ነው፡፡ ይህን በውስጣችን እያለ ሳናጤነው የኖርነው ትልቅ የአላህ ኒዕማን በገሃድ እንዲታይ ያደረገው ደግሞ ከአመታት በፊት በመንግስት ተመርጦልን ከ365 ቀናት በፊት ልንጠመቀው የተዘጋጀልን ‹‹ሙስሊሞችን ዳግም የማስለም›› ሃገራዊ ዘመቻ ነው፡፡ ይህንኑ ዘመቻ የሚመራው ደግሞ የመንግስትን ትከሻ ተደግፎ በመጅሊስ ስም የተሰባሰበው የካድሬዎች ቡድን ነው፡፡ የነዚህ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ ሁለት ሃይሎች የመጀመሪያ ሰለባ የነበረው ደግሞ ከነስያሜያቸው አፄ እና ወታደራዊ በመባል የሚታወቁ ሁለት መንግስታትን አሳልፎ ዴሞክራሲያዊ በሚል ስም በተሰየመው መንግስት ላይ የደረሰው የአወሊያ ተቋም ነው፡፡ የ365 ቀናት ጉዟችንም ከነዚህ ሶስት ነጥቦች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሶስቱ ነጥቦችም የነገሩ መነሻ እንዲሆኑ ያስቻለው ትልቁ ነጥብ ግን መንግስት ሃገር የሚተዳደርበትን ህገመንግስት በማንአለብኝነት በአደባባይ ደግሞ ደጋግሞ መጣሱ ነው፡፡
የእምነት ነፃነታችንን ለማስከበር ባሳለፍነው ድፍን አንድ አመት ስለተጎናፀፍናቸው ድሎችና ስላስተናገድናቸው በደሎች ዛሬ ላይ አናትትም፡፡ ለአመታት እንደተሴረብንና የሃገር አንጡራ ሃብትንና ሙሉ የፖለቲካ አደረጃጀት በመጠቀም እንደተዘመተብን ቢሆን ኖሮ ግን የዛሬው እኛነታችንን ለማየት ባልቻልን ነበር፡፡ በጉያችን የታቀፍነው ‹‹ዘመድ ›› ጠላትነቱንም ሳናውቅ ገዝግዞ በጣለን ነበር፡፡ ቤተሰቦቻችንን ሳናውቅ ከጃችን ባመለጡን ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን ሃያሉ አምላካችን አላህ(ሱ.ወ) ታላቅ ፀጋውን በኛ ላይ ዋለ፡፡ አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን፡፡ እናታችን አዒሻ እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሚያስደስታቸውን ነገር ባዩ ሰአት ለአለማቱ ጌታ ምስጋና ይገባው ጸጋዎች እና መልካም ነገሮች ሁሉ በእርሱ ሙሉ የሚሆኑት፡ የሚያስከፋቸው ነገር ሲያጋጥማቸው ደግሞ በማንኛውም ሰአት ምስጋና ለአላህ ይገባው ይሉ ነበር፡፡ ኢማም አልቲርሚዚ እና ኢብን ማጃህ ከነብያችን በሰነዳቸው እንደ ዘገቡት "በላጩ ዚክር ላኢላሀ አለላህ በላጩ ዱአዕ አልሀምዱሊላህ " ብለዋል፡፡ አላህን ማመስገን ደግሞ ተጨማሪ ፀጋን ለማግኘት ያመላክታል፡፡ ባሳለፍናቸው ፈታኝ የ 12 ወራት የትግል ጉዞ ያጣናቸውንም ነገር አልሃምዱሊላህ ከማለት ውጭ የምንገልፅበት ቃላት አይኖረንም፡፡ አቢ ሙሳ አልአሽአሪ ከአላህ መልእክተኛ በዘገቡትና አንድ ልጁን በሞት ሲነጠቅ ‹‹አልሃምዱሊላሂ›› እና ‹‹ኢና ሊላሂ ወኢና ኢላሂ ራጂኡን›› ስላለ ሰው ሲናገሩ፤ ጌታችን ለመላኢኮቹ እንዲህ ይላቸዋል በጀነት ውስጥ ቤት ገንቡለት የቤቱንም ስም የምስጋና ቤት በሉት ይላቸዋል፡፡ አልሃምዱሊላህ!
365 ቀናትን በአንድነትና ዲንን በመጠበቅ ወኔ ከተሻገርን በኋላ እነሆ ነገ የመጀመሪያዋን የጁመዓ እለት ልናገኝ ነው፡፡ ለአንድ አመት ምላሽ የተነፈጋቸውን ጥቂት ጥያቄዎቻችንን በሁለተኛው አመትም በዚህ እለት በመላ ሃገሪቱ ሚሊዮኖች ሁነን በአደባባይ ይዘናቸው እንቀርባለን፡፡ ጥያቄዎቻችን የሁሉም ሙስሊም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንም በተግባር ዳግም እናሳያለን፡፡ ህፃናትና አዛውንት ሳንለይ የ365 ቀናት የመብት ጥሰት እንዳልፈታን ፅናታችንን እናውጅበታለን፡፡ የድል ባለቤት የሆነው አምላካችን ያማረ መጠጊያችን መሆኑንና በርሱም ለድል እንደምንበቃ በአንድነት ‹‹ሃስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል›› ስንል እለቱን እናደምቀዋለን፡፡ ሃስቡነላህ ወኒዕመ አልወኪል የሚለው ታልቅ ስንቅ ነው፡፡ ነብዩላህ ኢብራሁም(ዐ.ሰ) ወደ እሳት በተጣሉ ሰአት፣ ነብዩ ሙሀመድም (ሰዐ.ወ) ሰዎች ለእናንተ ተሰብስበውባችኋል በተባሉ ጊዜ ‹ሃስቡነላህ ወኒዕመ አልወኪል› ነበር ያሉት፡፡ የነቢዮ ሙሀመድ ሰሀቦች ከኡሁድ ጠርነት በኃላ በሀምራኢል አሰድ ጦርነት ጊዜ የመካ ሙሽሪኮች ስለ መካው ሰራዊት ብዛት ሀይል ሲነገራቸው መልሳቸው ‹ሀስቡነላሁ ወኒዕመ አልወኪል› ነበር መልሳቸው፡፡ አላህም ይህንን በሱረት አል ዒምራን እንዲህ ሲል ገልፆታል (እነዚያ ለአላህ እና ለመልክተኛው የታዘዙ ችግር እና መከራ ከደረሰባቸው በኃላ እና መልካምን ለሰሩ አላህንም ለፈሩት ታላቅ ምንዳ አላቸው፡ እነዚያ ለምእመናን ሰዎች ለናንተ ሀይልን ሰብስበውላቹሀል ፍሯቸው ሲባሉ ለእነርሱ ኢማንን ጨመረላቸው እንዲህም ብለው አሉ አላህ በቂያችን ነው በሱም መመካት ምንኛ አማረ፡ በአላህ በሆነ ትሩፋት እና ጸጋ ተመለሱ ምንም መጥፎ ነገር አልነካቸውም፤ የአላህንም ውዴታ ተከተሉ፤ አላህ የታላቅ ትሩፋት ባለቤት ነው)፡፡
እናም የነገውን ጁመዓ የአላህን ፀጋ እያመሰገንን እና በመንገዱ ለምናደርገው ትግል ድልን እየጠየቅን አዲስ ታሪክ መስራት እንጀምራለን፡፡ ጥቂቶች ብለው ለተሳለቁብንም ሆነ ተሰላችተው ይተዉታል ሲሉ ለገመቱን ሚሊዮኖች ሁነን ፅናታችንን እንሳያለን፡፡ በዚህ የከፈትነው ሁለተኛው የትግል አመት ድሉ በጣሙን የቀረበ እንደሆነ በኣምላከችን አንጠራጠርም፡፡ የእለቱ መርሃግብርን በተመለከተም በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ የጁመዓ ሰላት ተሰግዶ እንዳበቃ
• በሃያልነቱ የጠላትን ልብ የሚያርድልንን አምላካችንን እናተልቃለን፡፡ ለ3 ደቂቃዎች እጃችንን በመያያዝ ‹አላሁ አክበር› በማለት፡፡
• ለዋለልን ታላቅ ኒዕማ በአንድነት ሁነን እናመሰግነዋለን፡፡ ለ3 ደቂቃዎች እጃችንን በመያያዝ ‹አልሃምዱሊላህ› በማለት፡፡
• 365 ቀናት ምላሽ የተነፈጉ ጥያቄዎቻችንን እና እየደረሰብን ያለውን የመብት ጥሰት አመት ሙሉ ባቀረብንበት ወኔና ይዘት ለሁለተኛው አመት መባቻም እንደግማቸዋለን፡፡ ለ 3 ደቂቃዎች ‹ድምፃችን ይሰማ› በማለት፡፡
• 365 ቀናትን በበደል ላይ ፀንተን በእምነታችን መርህና በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት እንድንዘልቅ ቃል ያስገቡንንና በእስር የተቀማናቸውን የሰላም አምባሰደሮቻችንን እንዲሁም በርካታ ወንድሞቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱልን እናሳስባለን፡፡ ለ 3 ደቂቃዎች ‹ኮሚቴው ይፈታ› በማለት፡፡
• ከላይ እንዳየነው ነቢያት ፣ሰሀቦች፣የአላህ ወዳጆች ችግር፣ መከራና የአምባገነኖች ጫና በሚደርስባቸው ሰአት ከአፋቸው የማይለየውን ታላቁን ስንቅ ከፍ አድርገን እናስተጋባለን፡፡ ለ 3 ደቂቃዎች ‹ሃስቡነላህ ወኒዕመል ወኪል› በማለት፡፡
• በስተመጨረሻም ለራሳችን፣ ለመንግስት፣ ለመላው ህዝባችንና ለአለም ማህበረሰብ በሙሉ ታላቅ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ ምናልባት በአለም ላይ ቀላል የመብት ጥያቄዎችን ለ‹ዴሞክራሲያዊ› መንግስት አቅርቦ ምላሹ የ 365 ቀናት እስር፣ ድበደባ እና እንግልት የሆነበት ብቸኛ ህዝብ መሆናችንን፡፡ ከዚህም ጋር 365 ቀናት አላማውንና መንገዱን ሳይስት በፅናት የቆየ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እኛው መሆናችንን፡፡ ሁለተኛ አመቱን የጀመረው ጉዟችን ንፁህ የሃይማኖት መብትን የማስከበር ጉዞ መሆኑን ፅፈን እናስነብባቸዋለን፡፡ በነፍስ ወከፍ አዘጋጅተን የምንመጣውን ‹365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት› የሚል ጽሁፍ ለ 3 ደቂቃዎች ባለንበት በዝምታ ቆመን ከፍ አድርገን እናሳያለን፡፡ ይህም የእለቱ ፕሮግራማችን ፍፃሜ ይሆናል፡፡
ከላይ የተቀመጡት መርሃ ግብሮች በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩ ሲሆን በአዲስ አበባ ደረጃ ሙሉ መርሃግብሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ መረጃዎችን ዘግየት ብለን የምናሳውቅ ስለሚሆን ፔጁን በመከታተል ላልሰሙት እንድታስተላልፉ እንጠይቃለን፡፡
ማስታወሻ፡- ሁላችንም ‹365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት› የሚል ፅሁፍ አዘጋጅተን ከቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችን ጋር መምጣታችንን አንዘንጋ፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment