በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የኮሚቴዎቻችን፣ የትግሉ ሰማእታትና የጥቃት ሰለባዎች ሳምንት
365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት መርሃ ግብር (ሁለተኛ ሳምንት)
‹‹365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት›› በሚል መርህ በአራት ሳምንታት ተደልድሎ እየተዘከረ ያለው የአንድ አመት ጉዟችን እነሆ የመጀመሪያ ምዕራፉን አገባደደ፡፡ ባሳለፍነው ‹‹የአወሊያ ተማሪዎችና የጥያቄዎቻችን ሳምንት›› የጥያቄዎቻችንን መነሾና ሂደት፣ የአወሊያ ተማሪዎችን ገድልና ውለታ በጣም በአጭሩ ቃኝተናል፡፡ ያልተመለሱት ጥቂት ጥያቄዎቻችንንም ‹‹365 ቀናት ሳይመለሱ ዳግም የቀረቡ የህዝብ ጥያቄዎች›› ብለን በሚሊዮኖች ድምፅ አጅበን ካደባባይ ውለናል፡፡ ዛሬስ የጥያቄዎቻችን አግባብነት እንዲሁም የኛ እና የወኪሎቻችን ንፁህነት ተገልፆላቸው ይሆን? አዎን ብለን እንጠረጥራለን፡፡ ጥርጣሬያችንም ተግባራዊ ምላሽን እስኪወልድ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ስንል የተዘጉ በሮችን ሁሉ በርግዶ የመግባት አቅም ባለው በዚህ ባለዘርፈ ብዙ ትርጓሜ የትግላችንን አዋጅ እንለፍፋለን፡፡ አዎን ድምፃችን ይሰማ!!!
በመርሃ ግብራችን መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ያሉት ሰባት ቀናት ‹የኮሚቴዎቻችን፣ የትግሉ ሰማዕታትና የጥቃት ሰለባዎች ሳምንት› ስንል ሰይመነዋል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ዛሬ ከጥያቄዎቻችን አንዱ ሆኑ እንጂ መፍትሄ አፈላላጊ ብለን ስንወክላቸው ፊርማችንን ያኖርንበት ብዕር ቀለሙ ዛሬም ይሸተናል፡፡ በፈረመላቸው እጃችን መዳፍ ላይ ምስላቸው ይታየናል፡፡ ይኸው ፊርማችንን ነበር ሕጋዊ ኹነታችንን ለመፈጸም ስንጠቀም የቆየነው፡፡ ይህ ክቡር የህዝብ የውክልና ፊርማ የሚከበርበትና የሚናቅበት መስፈሪያውን ይነግሩን ይሆን? ስለ ሰላም አምባሳደሮቻችን ተቆጥረው ስለማይዘለቁ የተግባር ማንነቶቻቸው ብዙ ማለት መቻሉን ‹‹ያኛው›› ወገንም አይጠፋውም፡፡ የትግሉ ሰማእታት በመሰዋእትነት እርከን ከፍተኛ የሚባለውን ህይወታቸውን የሰጡን ናቸው፡፡ የትግል ምንነት በልባችን ጠልቆ እንዲሰማን ያስቻሉን እና በየእለቱ የምንከፍለውን ልክ የለሽ መሰዋእትነት ከምንም ሳንቆጥር እስከ ውጤት ለመጓዝ ወኔ የሆኑን ናቸው፡፡
በሃቅ ጉዳይ ከፊት የተሰለፉትን እነዚህን ወንድሞች ጀግንነታቸውን ለመረዳት ታሪካቸውን መፈተሸ ሳያስፈልገን በስራቸው መስክረናል፡፡ ይህ ያልገለፀው ተግባር በየትኛው ንግግርስ ሊገለፅ ይችላል? ከአያት ቅድመ አያቶቻችን በመሰዋእትነት የተረከብነውን እምነት መሰዋእት ከፍሎ ማስጠበቅ ግድ መሆኑን በሚሊዮኖች አእምሮና ልቦና የቀረፁ የዘመናችን ፋኖዎች ናቸው፡፡ በትግሉ የጥቃት ሰለባዎች ስንል ለአካላዊና አዕምሮአዊ ጥቃት የተጋለጡትን ማለታችን ነው፡፡ ሰለባ መባላቸው ግን ስቃይና መከራን የከፈሉለት አጀንዳ አንሶ ሳይሆን ይህን ያደርጋል ተብሎ በማይጠበቅ መንግስት፣ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ስራቸው ነው በተባለላቸው የፀጥታ ሃይሎች እና መፍትሄያቸው ቀላል ለሆኑት የመብት ጥያቄዎቻችን ተገቢ ባልሆነ አፀፋ ሰለባ መሆናቸውን ለማስረዳት ነው፡፡
በዚህ ሳምንት በልዩ ትኩረት የምናወሳው እነዚህን ጀግኖች ነው፡፡ ግድያ፣ ድብደባና እስር የሰዎችን ሞራል ለመስበር ሆን ተብለው እንደሚወሰድ አይጠፋንም፡፡ እኛ ግን የትግሉን የጥቃት ሰለባዎች የምናወሳው ከፊት ያስቀደሙትን የአላማ ትልቅነት ይበልጥ ለመረዳትና ከኋላቸው ትተውልን ያለፉትን የታሪክ አደራ ለማስጠበቅ ነው፡፡ ጀግኖቻችን ያለአላማ የተጎዱ፣ ወንጀለኛ ሁነው የተቀጡ፣ ረዳት አልባ ሁነው ለጉዳት የተጋለጡ፣ ወይንም ያለጥንቃቄ እራሳቸውን ለጉዳት አሳልፈው የሰጡ አይደሉም፡፡ ‹‹እምነቴን አትንኩ›› እና ‹‹ህገ-መንግስቱ ይከበር›› በማለታቸው የሰብአዊና የእምነት ነፃነት ማክበር የሚያስገድደውን ህገ-መንግስት ንቀው በረገጡ ህግ አላፊዎች እጅ ሰለባ የሆኑ እንጂ፡፡
መሰዋእትነት በበርካታ መልክ እና ደረጃ የሚገለፅ ቢሆንም የተከፈለለት አላማ ግን ሁሉንም ባንድ እንዲወሱ ያደርጋቸዋል፡፡ በከተማም ሆነ በገጠር፣ የተዘገቡና ያልተዘገቡ፣ የተሰሙና ያልተሰሙ ጉዳቶች በሙሉ ለዚህ ትግል የተከፈሉ በመሆኑ እኩል ሃገራዊ ታሪኮች ናቸው፡፡ ተመሳሳይ አላማን ከግብ ለማድረስ በአንድ ሃሳብና መንገድ በወጡ ሰዎች መካከል ከፊሉ በዘለፋ፣ አብዛኛው በእስር፣ ከፊሉ በድብደባ እንዲሁም ቀሪው በሞት ቢቀጣ እኛ ግን አላማቸውን ስናወሳ ሁሉንም በአንድነት እንዘክራቸዋለን፡፡ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ለጉዳቱ ስም ቢያወጡለትም የቀደሙትና የሚመጡት የትግሉ የጥቃት ሰለባዎች በሙሉ እኛን ባለእዳዎች ማድረጋቸውን አያስቀረውም፡፡
የዚህ ሳምንት መርሃግብር አላማ ጀግኖቻችንን ማውሳት ብቻ አይደለም፡፡ ሌላው አላማ ከእያንዳንዱ ጉዳት በስተጀርባ ከጥንስሱ እስከ ትግበራው ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱ የመንግስትና የመንግስት ብቻ መሆኑንም ለማሳየት ነው፡፡ ይህንንም እንደስከዛሬው በተጨባጭ ማስረጃዎች ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ መንገዶች ይፋ እናደርጋለን፡፡ ጉዳቶቹ የደረሱት አንድም በፀሎት ላይ ባሉ ምእመናን ላይ በተሰነዘረ ጥቃት፣ አንድም እጃቸውን አሳስረው ከእስራት ፍቱን ብለው በሚማጸኑ ንፁሃን ላይ፣ ከዚህ አለፍ ካለም በውል በሚታወቁ አብዛኞቹም ተቀርፀው በተቀመጡ መረጃዎች በተረጋገጡ የመንግስት ትንኮሳዎች የተነሱ ግርግሮችን ተስታኮ የተወሰዱ፤ አስቀድመውም የታቀዱ እርምጃዎች ምክንያት ነው፡፡
የዚህም ሙሉ ሃላፊነት የመንግስት መሆኑን ልናስረግጥ እንወዳለን፡፡ መንግስታት ሃገራችንን በተለያዩ የተሳሳቱ አቅጣጫዎች ሲንዷት ጥርሱን ነክሶ ሲገነባ የመጣን ህዝብ ሃገር በመናድ መጠርጠሩና ያለግብሩ መወገሩንም በፅኑ ለማውገዝ ነው፡፡ እንደ ሃገር መሪ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ የተጠና ሞትና ጉዳት እንዲሁም በቃላት የማይገለፅ የመብት ጥሰት እየቆጠሩ መኖር ምን ዓይነት ደንዳናነት ይሆን? ያስብላል፡፡ ጥያቄው የሚሊዮኖች መሆኑን ለማስተባበል የጥቂቶች በሚል ተለጣፊ ሲሰይሙት ‹‹አይ ፖለቲካ!›› ብለን ተገረምን፡፡ ግን ግን ለፍትህ ናፋቂዎች የተዘጋውን በራቸውን እያለፈ ከሚያገኙት መረጃ በእጆቻቸው የተሰዉ እና በተለያየ ደረጃ ጉዳት የደረሰባቸው ንፁሃን ወገኖች መበርከት የሚናገረው እውነት አጥንታቸውን ሰብሮ አይገባ ይሆን? መሰረታቸውን ሃሰት ያደረጉና ሚዛናቸው ለሃሰት ያጋደሉ ጥቂት መገናኛ ብዙሃን የነዚህን ወንድሞችና እህቶች ክቡር ነፍስ ለሁከት በሁከት ላይ ሳሉ የተከፈለ አድርገው ለመሳል ይጥራሉ፡፡ እኛም እንደኮሚቴዎቻችን ደግመን እንናገራለን ‹‹የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መደጋገም የመብት ጥያቄን ወንጀል አያሰኘውም›› የኛ ትግል ወንጀል አለመሆኑ በተቃራኒው የሚመሰክረውን እውነት ለነዚህ ሚዲያዎች ማስተዋሉ እንዴት ተሳናቸው?
በሳምንቱ መርሃግብራችን የጉዳቱ ሰለባዎችን መቁጠራችን ጉዳዩን መላመዳችንን ሳይሆን 365 ቀናት እንደተጣራነው ሁሉ ዛሬም ‹‹ይህ በደል ይብቃ›› እያልንም ጭምር ነው፡፡ የተጎጂ ቤተሰቦችን በጉዳታችሁ ‹‹ብቻችሁን አይደላችሁም›› ለማለት ይህንኑ ሳምንት በይበልጥ እንጠቀመዋለን፡፡ አጋርነታችን ያጧቸውን ባይተካላቸውም፣ ችግሮቻቸውን ባይፈታላቸውም ለኛ ግዴታችን ለነሱም መብታቸው በመሆኑ በዚህ ሳምንት በልዩ ትኩረት እንተገብረዋለን፡፡ የነሱ ቤተሰቦች ለኛ ግን የሞራል እና የትግል መምህሮቻችን መሆናቸውን ተገቢውን ክብር በመስጠት እናሳያቸዋለን፡፡ ቤተሰቦቻቸው መብት ከጠየቅህ ትሞታለህ ከሚል ጥቁር ውርስ፣ ይህ ጉዳይ መለወጥ የማይችል ነው ከሚል በዜግነት ተስፋ የመቁረጥን ልማድ፣ ጎመን በጤና ከሚል በዲን ላይ የተጋረጠን አደጋ ዝም ብሎ ከመመልከት ነፃ ወጥተው እነሱነታቸውን ሁነው የነሱነታቸውን አሻራም ለኛ አውርሰውን የሄዱ ባለታሪኮች ናቸው፡፡ እኛና ቤተሰቦቻቸው በጉዳታቸው እንዘን እንጂ መሰዋእት በከፈሉለት አላማ ግን እንደኮራን ነን፡፡ በአላህ ፍቃድም መሰዋእትነት የከፈሉለትን አላማ ከዳር እናደርሳለን፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment