Friday, January 18, 2013

JEGNEWU YA JIMMA MUSLIM DEMSTE ZARW KALELA KEN BATALEYA





በለቅሶና በዱአ የታጀበው ታላቁ አገር አቀፍ የጁሙዓ ተቃውሞ!!!

‹‹አማኞች አንዱ ለአንዱ ልክ ግድግዳ ላይ እንደተደረደሩ ጡቦች ናቸው፤ አንደኛው ሌላውን ያጠናክረዋል!›› (ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ)

አላሁ አክበር! የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድነት ዛሬም ፍንክች የማይል ጠንካራ ግንብ መሆኑን አስመስክሮ ዋለ! መውሊድን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም እርስ በርስ ሙስሊሙን ለመከፋፈል እና ለማጣላት ያሰበው መንግጅሊስ ተንኮል ዛሬም በድጋሚ ፉርሽ ሆነ! በረዥሙ ትግላችን ያሳለፍናቸው በርካታ ጁሙአዎች በደመቀ ስነ ስርአት እየተከናወኑ ያለፉ ቢሆንም ጠለቅ ያለ ስሜት እና አንድነት የሚስተዋልባቸውና ከትውስታ እስከመጨረሻው የማይፋቁ ጁሙአዎች ደግሞ ከሌሎቹ ለየት ብለው ተንጸባርቀው ያልፋሉ፡፡ ትዝታቸውን ለረዥም ጊዜ ይጥላሉ፡፡ የዛሬዋ ጁሙአ ከመሰል ታዋሽ ጁሙአዎች አንዷ ነበረች፡፡

No comments:

Post a Comment