አገር በተቀነባበረ የሀሰት ድራማ አትመራም!
እውነትን ገድዬ ሀሰትን ላነግስ ነው - ኢ.ቴ.ቪ ማክሰኞ ጠብቁኝ ብሏል
ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሁለቱን ደማቅ ኢዶች ጨምሮ ባደረጋቸው የአደባባይ ተቃውሞዎች ሁሉ ኢ.ቴ.ቪን ሌባ ሲለው ነበር፡፡
ወትሮም እውነት መናገር የማይሆንለት ኢ.ቴ.ቪ ዛሬ ምሽት ላይ ለወራት ለመቀጣጠል ሲደክምበት የነበረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴያችንና ኮሚቴዎወቻችን ላይ ጥላሸት ለመቀባት ያለመ የሀሰት ‹‹ዶኩመንተ›› ፊልም ማክሰኞ ምሽት እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡ ይኸው ፊልም ከተሰራ ወራቶች ያለፉት ቢሆንም በተለያየ ጊዜ ባለስልጣኖች ጋር ለግምገማ ቀርቦ አሳማኝ ባለመሆኑ ተሻሽሎ እንዲፈበረክ ሲደረግ ከርሟል፡፡ ከተለቀቀው ማስታወቂያ መረዳት እንደሚቻለው ፊልሙ በዋነኛነት ሙስሊም ያልሆነው የህብረተሰብ ክፍል የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ጥያቄ እና እንቅስቃሴ በስጋት እንዲያየውና ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ወደ ግጭት እንዲያመራ ማድረግ ነው፡፡ ይህንኑ እኩይ ስራ መንግስት ከዚህ ቀደም በተለያየ መንገድ ሞክሮት የከሸፈበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በርካታ ክርስቲያን ወገኖቻችንም ይህንኑ ዓላማ ተረድተው በተለያየ ጊዜ መንግስት ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን በማፋጀት ዕድሜውን ለማራዘም የሚያደርገውን ሙከራ አውግዘዋል፡፡ በተግባርም ክርስቲያኑ ህብረተሰብ ለትግሉ ድጋፉን በተለያየ መልኩ ሲሠጥ ቆይቷል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትም በዚህ የክርስቲያኑ ህብረተሰብ ድጋፍ በመናደድ የምሬት መልሶች ለሚዲያዎች ሲሰጡም ጭምር ተሰምቷል፡፡
ሙስሊም ህብረተሰብ መሰረታዊ የእምነት ነጻነት መብቱን ለማስከበር ባለፈው ዓመት ያደረገው ትግል ሰላማዊ ለመሆኑና የትኛውንም የህብረተሰባችንን ክፍል ስጋት ውስጥ የማይከት ለመሆኑ የተለያዩ የውጪ አገር የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ካወጡት መግለጫ በላይ ‹‹ሊያርዱህ ተነስተውብሃል›› እያሉ ሲያስፈራሩት የነበረው ክርስቲያኑ ህብረተሰብ በየሰደቃ ፕሮግራሞቹ ላይ ያሳያቸው ትብብሮች ማረጋገጫ ናቸው፡፡ ኢ.ቴ.ቪ ዛሬ ይዞት ብቅ ያለው የተቀነባበር ድራማም ይህን በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መሃከል የተፈጠረውን መተማመን ለመናድ የተተኮሰ የመጨረሻ ጥይት ይመስላል፡፡ ኮሚቴዎቻችንና ዳዒዎቻችን በማዕከላዊ እስር ቤት ባሳለፏቸው የግፍ ወራት በአሰቃቂ እና ተከታታይ ቶርቾች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሁኔታ ውስጥ ሁነው በግድ እንዲናገሩ ያደረጉዋቸውንና በድብቅ ካሜራዎች የቀረጿቸውን ንግግሮች ቆርጦ በመቀጠልና በማቀናበር ‹‹ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ነበር የምንንቀሳቀሰው›› ብለዋል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞክር የሚመስለው ይኸው ፊልም ከዚህ ቀደም ሲወሩ የነበሩትን የተቀበረ መሳሪያ አወጣን ድራማዎችንም እንዳካተተ ማስታወቂያው ያሳያል፡፡ እነዚህ ሁሉ ኢ.ቴ.ቪ ከዚህ ቀደም በህብረተሰቡ ውስጥ ካገኘው አሉታዊ ስም ጋር ተዳምሮ የማንንም ቀልብ ሊገዛ እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡
መንግስት የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞን ለማዳፈን ከዛቻና ማስፈራሪያ ጀምሮ ቃታ እስከመሳብ የደረሱ እርምጃዎች ቢወስድም ጥያቄችን ፍትሃዊና እንደ ረፋድ ፀሃይ ውልል ያለ በመሆኑ አድማሱን እያሰፋ ከአንድ ዓመት በላይ በጽናት መቀጠል ችሏል፡፡ አሁንም ቢሆን ተቃውሟችን ሊፈታ የሚችለው በተቀነባበረ የሃሰት ድራማ ሳይሆን ጥያቄዎቻችን ፍትሃዊ መልስ ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡ ጥያቄው የመረጥናቸው ኮሚቴዎች ብቻ ሳይሆን የመላ ህብረተሰባችን ለመሆኑ ተቃውሟችን ኮሚቴዎቻችን ከታሰሩ በኋላም ከ 6 ወራት በላይ አንዳችም መቀዝቀዝ ሳያሳይ መቀጠሉ ብቻ በቂ መረጃ ነው፡፡ ህዝብን ለማታለል እና አንዱን ኢትዮጵያዊ የሌላው ጠላት አድርጎ ለመሳል ቀን ከሌሊት የሚባዝኑ መሰሪ አዕምሮዎችና ሃብቶች የህዝብን ችግር ለመፍታት ቢውሉ አገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ግን ለዚህ አልታደልንም፡፡
አመት የቆየውን ድምጻችን ይሰማም ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ይህን የሃሰት ድራማ ከንቱነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የተለያዩ የድምጽ ዘገባዎች ይዛ እንደምተቀርብ እያስታወቀች ሁላችንም ለቤተሰባችን፣ ለመድ አዝማዳችን እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮቻችን ጎረቤቶቻችንና ወዳጆቻችን እውነታውን በማስረዳት እንድንበረታ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ እውነትን ማንም አይጥላትም፡፡ አገር በተቀነባበረ የሀሰት ድራማ አትመራም፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment