Tuesday, November 20, 2012

A Must Watch Video !! TPLFites are being Terrified!


በምስራቅ ኢትዮጲያ በኦጋዴን አከባቢ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ሰብስበው ገለፃ ያደረጉት የፌደራል ፖሊስ ሃላፊ ፖሊሶች እየከዱ ማስቸገራቸውን ገልፀዋል። ለሰባት ዓመታት ለማገልገል የገቡትን ሥምምነት ጥሰው በመኮብለላቸው እየያዝን ጅጅጋ እስር ቤት እንከታቸዋለን ሲሉ አሳስበዋል። በምስራቅ ካለው ይልቅ የሰሜኑ ችግር የሰፋ መሆኑን በሁመራና በመተማ ዘወትር ግጭት በመታየት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።
በደቡብ ወሎ ሙስሊም መሆን ወንጀል ሆኗል!

መንግስት ምን እየሰራ ነው?

የኢህአዴግ መንግስት ‹‹አክራሪነትን ለመግታት›› በሚል የሀሰት ምክንያት የአህባሽን አንጃ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ለመጫን ሙከራ ማድረግ ከጀመረበት ካለፈው አመት ጀምሮ ታላቅ ብሄራዊ ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወቃል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ዲኔን አላስነካም›› በሚል ስሜት የተሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከት ባደረገው እጅግ ሰላማዊ ትግልም በርካታ ድሎችን ሲጎናጸፍ ቆይቷል፤ መንግስትም በበኩሉ ሰላማዊውን ትግል ለማስቆም በወሰዳቸው ኢሰብአዊ እርምጃዎች ህዝበ ሙስሊሙ ይህ ነው የማይባል መስዋእትነትን ለመክፈል እንደተገደደው ሁሉ!

በዚሁ ታሪካዊ ሰላማዊ ትግል በከፍተኛ የተቆርቋሪነት ስሜት የመንግስትን ውስብስብ ሴራ መና ሲያስቀሩ ከነበሩ ጠንካራ ክልላዊ ተቃውሞዎች አንዱ በወሎ ክልል የነበረው ተጠቃሽ ነው፡፡ በተለይ በደቡብ ወሎ ክልል በሰደቃና በአንድነት ፕሮግራሞች የተደረገው ህዝባዊ ንቅናቄ እና የመጅሊሱን ምርጫ መና ያስቀረው የህዝብ አንድነት ያበሳጨው መንግስት የጭካኔ እርምጃዎችን ጭምር በመውሰድ ለማስቆም ጥረት አድርጓል፡፡ የደቡብ ወሎ እምብርት በሆነችው በደሴ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው የፈደራል ፖሊሶች ጥቃት ሳይሽር የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ባሉ ከተሞች ላይ የሚፈጽሙትን ህገ ወጥ ጥቃት ቀጥለዋል፡፡ ይህ የመንግስት ህገ ወጥ አካሄድ ከሞላ ጎደል ምን ይመስል እንደነበር በመጠኑ ለማየት እንሞክር፡፡

Monday, November 19, 2012

Jewish Rabbi says Islam is religion of future

ታላቁ ታሪካዊ የዚያራ ፕሮግራም በ ጀርመን ራዲዮ

High time to support Ethiopian Muslims

High time to support Ethiopian Muslims

by Abebe Gellaw
Ethiopian Muslims are waging their struggle in a religious contextFor the last two decades, nonviolent struggle, or civil resistance, appeared to be highly misunderstood and confused in Ethiopia. The resultant effect of this confusion is that so many opportune moments to build a movement for change have been wasted. In fact, a number of leaders failed to provide the necessary leadership to mobilize the oppressed people of Ethiopia to confront their oppressors.
Though Ethiopian Muslims are waging their struggle in a religious context, they are showing us that nonviolent struggle is not “impossible” but a “force more powerful” to crack, stress out and eventually dismantle the tyrannical TPLF regime. While the regime has left no stone unturned to isolate the struggle of Muslims through its confusing and divisive propaganda, the movement is gaining momentum and getting smarter. It now stands out that the movement has reached a critical stage. Despite its best efforts, TPLF has failed to put the genie back into the bottle as the movement has already become irrepressible.

የመራኑ ሃቢብቲ የቃሊቲ የዚያራ ትረካ



የመራኑ ሃቢብቲ የቃሊቲ የዚያራ ትረካ

"ስለፌዴራል ፖሊሶች ግን ባላወራ ይቀለኛል፡፡ ቅንነት የሚባል ነገር
አልፈጠረባቸውም፡፡ ህዝቡ የሚደናበር መስሏቸው እስከ አፍንጫቸው ታጥቀው በህዝቡ መሃል በመኪና አስሬ ይመላለሳሉ፡፡ ግብር ከፍሎ በሚያስተዳድራቸው ወንድሞቻቸው መሃል ሳይሆን በሃገሪቱ ላይ የሆነ የጠላት ጦር ወረራ ፈፅሞ ለግዳጅ የተሰማሩ ነበር የሚመስሉት፡፡ የአሜሪካን ጦር አባላት እጅግ በሚያስፈራው የአፍጋኒስታን የቶራ ቦራ ተራራ አካባቢ ሲሰማሩ እንኳ እንደዚህም የታጠቁ አይመስለኝም፡፡ ፌዴራል ፖሊሶቹ ክላሻቸውን ወደ ሰላማዊው ህዝብ ደግነው በፓትሮል ወዲህ ወዲያ ይላሉ፡፡ እብዛኛው የፌዴራል ፖሊሶቹ አባላት ከታጠቁት ትጥቅ በተጨማሪ ደረታቸውን ያሳበጠ የደረት መከላከያም አድርገዋል፡፡"

ቃሊቲ አቅሏን ሳተች
ወደዳችሁም ጠላችሁ ግርማ ሞገሱ ከሩቅ ይስባችኋል፡፡ በነጭ ጀለቢያ ተውቦ ፍፁም ርጋታ በተላበሰ ሁኔታ ሊዘይሩት የመጡትን ጠያቂዎች በአይኑም፣በፈገግታውም፣ ጭንቅላቱንም ጭምር በመነቅነቅ ምስጋናውን ይገልፃል፡፡ ይህ ሁኔታ ለረጅም ሰዐት የዘለቀ ቢሆንም እሱና ጓደኞቹ ያለምንም ድካም ጠያቂዎቻቸውን(ዘያሪዎቻቸውን) ተቀብለው እያስተናገዱ ነው፡፡ ጠያቂዎችም ያለምንም ፋታ መፍሰሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ ልክ የአባይ ዉሃ አገር አቆራርጦ እየፈሰሰ ከግብፁ አስዋን ግድብ እንደሚጨመረው አይነት ጠያቂዎችም በረጅሙ እየፈሰሱ ከዚህ ቆፍጣናና ልበ ሙሉ ወጣት አጠገብ ሲደርሱ ከንግግግር ይልቅ እንባ ይተናነቃቸዋል፡፡ ይህ ወጣት በቅርቡ ወደዚህች አለም ከመጣች ሳምንት ያልሆናት የሱመያ አባት የሆነው አህመዲን ጀበል ነበር፡፡
ውድ አንባቢያን ከሰላምታዬ አስቀድሜ በቀጥታ ወደቃሊቲ እስር ቤት ያስገባሁህ ወድጄ እንዳይመስልህ ናፍቆት ነበረብኝና ነው፡፡ የቃሊቲ ትርክቴን ያቋረጥኩት የአንተን ልብ ለማንጠልጠልም አይደለም፡፡እመለሳለሁ፡፡ ናፍቆቴን ላጣጥም ብዬ እንጂ፡፡

Sunday, November 18, 2012

ትግሉ ዛሬም በሌላ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡

ድምፃችን ይሰማ
የዛሬው የዚያራ መርሐ ግብር ሪፖርታዥ

ትግሉ ዛሬም በሌላ ምዕራፍ ላይ ነው፡፡

ዛሬ በስኬት የተጠናቀቀው የጉዞ ቃሊቲ የዚያራ መርሐ ግብራችን ይፋ ከተደረገበት ሐሙስ ምሽት ጀምሮ ነበር በርካታ ሕዝብ ሂደቱን በስኬት ጀምሮ በስኬት ለማጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የጀመረው፡፡ በሁሉም አካባቢዎች በተደረገው የተቀናጀ አንቅስቃሴ ሁሉንም መዳረሻ መንገዶች ያካተተ ሰፊ የቅስቀሳ ስራ ተሰርቷል፡፡ በመርሐ ግብሩ እቅድ ላይ መንግስት ያሰማራቸው አካላት ትእይንተ ዚያራውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊለውጡት ይችሉ ይሆናል የሚል ስጋት የነበረ ቢሆንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ባካበተው እና ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ባሳያቸው ሰላምን እሰከመጨረሻው የመጠበቅ
ስልት በመተማመን መርሐ ግብሩ በታቀደለት መልኩ ሊሄድ ችሏል፡፡

 
በበርካታ አካባቢዎች የሚኖሩ ሙስሊሞች የቃሊቲ ጉዞአቸውን የጀመሩት ገና ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ ነበር፡፡ እለቱ እሁድ በመሆኑ ችግሩን አቃለለው እንጂ በሕዝቡ ብዛት የተነሳ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ገና ከማለዳው ጀምሮ ተፈጥሮ ነበር፡፡ ሆኖም የተገኘውን የግልም ሆነ የሕዝብ ትራንስፖርት እንዲሁም በእግርም ጭምር በመጓዝ ቃሊቲ የደረሰው ሕዝበ ሙስሊም በደቂቃዎች ጊዜ ነበር የአካባቢውን ነፋስ የለወጠው፡፡ ቃሊቲ በውስጡ እንደያዛቸው ንጹሐን መሪዎቻችን እና ‹‹እንደ ሕዝብ ታስረናል›› የሚል መልዕክት በሚያስተላልፉ ሙስሊሞች ተሞላ፡፡ ቃሊቲና አካባቢው እየጠበበ፣ የሰው ቁጥር ግን እያየለ መጣ፡፡ የህዝቡ ወረፋ ሶስት ረድፍ ሰርቶ መንደሮችን እያቆራራጠ ነጎደ፡፡ ሳይታሰብ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የቃሊቲ አውራ ጎዳና አፋፍ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹ሰልፉ ወደ ጎዳና መውጣቱ ብዛቱን ያሳብቃል›› የሚል ስጋት የገባቸው የጸጥታ አካላት ሰልፉ ወደ ሌሎች አጎራባች መንደሮች እንዲቀጥል ቢያደርጉም መንደሮቹ እየሞሉ በርካታ ሕዝብ ዋናው ጎዳና ላይ ፈስሶ ታይቷል፡፡

ዘግይቶ ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ በር ለጎብኚዎች ክፍት ሲደረግ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በተሠጠው መመሪያ መሰረት በእርጋታ ያለ ምንም ግፊያ ወደ ውስጥ መግባት ጀመረ፡፡ በማረሚያ ቤቱ የነበረው ፍተሻ ከወትሮው የተለየና ጫማን እስከማስወለቅ የደረሰ ነበር፡፡ ሕዝቡ በሌሊት ከቤቱ በመውጣትና ይሄንን አስቸጋሪ የቃሊቲ ረጀም መንገድ በመጓዝ (በአማካይ ለትራንስፖርት እስከ 12 ብር ድረስ በመክፈል) ለሰዓታትም በቃሊቲ በር ላይ ለመጠበቅ የተገደደው ሕዝብ ፍተሻውን አልፎ የናፈቃቸውን መሪዎች ሲያገኝ እንባውን መዝራት ይጀምራል፡፡ ሕጻን፣ አዋቂ፣ ሴት፣ ወንድ፣ ጎልማሳ፣ አረጋዊ ሳይል መሪዎቹን የሚቀበለው አንዳንዱ በለቅሶ፣ ሌላው ሀዘን ባጠላበት ፊት! የኅሊና እስረኞቹ መሪዎቻችን ዘወትር እንደሚደርጉት የሚያለቅሰውን ሕዝብ ከሽቦው አጥር ጀርባ ሆነው ያባብላሉ፡፡ ይህን ትእይንት የተመለከተ ታሳሪዎቹ ሕዝቡ እንጂ መሪዎቹ አይመስለውም፡፡ ለነገሩ ሕዝቡም በፍትህ እጦት ‹‹ኢትዮጵያ በምትባል ትልቅ እስር ቤት ታስሬያለሁ›› የሚል መልዕክት ለማስተላለፍም ጭምር ነበር የዚያራ ፕሮግራሙን ያካሄደው፡፡ ሕዝቡ ከኋላ ለተሰለፉት መቶ ሺዎች እድል ለመስጠት ሲል በመከራ ያገኘውን ቃሊቲ የመግባት እድል ለቅጽበት ያህል በመጠቀም ለተረኛው ሙስሊም ይሰጥ ነበር፡፡

የእድል ነገር ሆኖ ከኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋና ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው በስተቀር ሁሉም የኅሊና እስረኞቻችን አንድ ላይ ነበሩ፡፡ ዞን ሶስት ላይ ተደርድረው የቆሙት ቀሪዎቹ 27 የኅሊና እስረኞች ከማለዳው ጀምሮ አስከ ቀትር ድረስ ያለምንም እረፍት ሊጎበኛቸው የመጣውን ሕዝብ ሲቀበሉ፣ ሲያበረታቱ፣ ሲመክሩ እና ዱአ ሲጠይቁ ውለዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ሊዘይራቸው ከመጣው ሕዝብ እድሉን አግኝቶ በአይን የተያያቸው ሩብ ያህሉ እንኳ አይሞላም፡፡ የማለዳውን ብርድ እና የረፋዱን ጸሐይ ተቋቁሞ በትእግስት ሲጠብቅ የነበረው በቁጥር የሚበዛው ሙስሊም የመግባት እድሉን እንደማያገኝ እያወቀም ቢሆን የዚያራ ፕሮግራሙን ለማሳካት ሲል በሰልፍ ተሰድሮ ነበር፡፡ የሰልፉን ጫፍ ለማግኘት የዚህ ሪፖርታዥ አዘጋጆች ሰልፉን ተከትለው ቢጓዙም በሰልፉ ርዝማኔ የተነሳ ጫፉን ለማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ይሄ ሁሉ ሕዝብ ግን መሪዎቹንም ሆነ የመንግስትን ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት አስመልክቶ ያለውን አቋም በማያሻሙ ቃላት ዛሬም በድጋሚ ለመንግስት በማረጋገጥ ወደ ቤቱ በሰላም መመለስ ጀምሯል፡፡

በሰላም ተጠናቅቋል ሲባል የነበረውን ሰላም ለማደፍረስ ጥረቶች አልተደረጉም ማለት አይደለም፡፡ ሰላማዊውን ሕዝብ ከማመናጨቅ አንስቶ የበርካታ ሙስሊሞችን የመኪና ታርጋ እስከ መፍታት የደረሰ ትንኮሳ በጸጥታ አካላትና በትራፊክ ፖሊሶች ተፈጽሟል፡፡ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ የፌዴራል ፖሊስ ኃይሎች በልዩ መለዮዋቸው ነገር ፍለጋ በሚመስል መልኩ ተደጋጋሚ ከበባ በተሸከርካሪዎች በመታገዝ በሙስሊሙ ላይ ቢያደርጉም ሕዝቡ ያለ ምንም መሳቀቅ ሙከራውን አክሽፎታል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ‹‹በሞባይል ሲቀርጹ ነበር›› የተባሉ 5 የሚደርሱ ወጣቶች በፖሊሶች ታፍነው ተወስደዋል፡፡ ይሄም የትንኮሳው አካል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ዚያራውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ይሄዱ የነበሩ ሙስሊሞች ሳሪስ ቀለበት መንገድ አካባቢ በፖሊስ ትንኮሳ ሲደረግባቸው የነበረ ቢሆንም ሁኔታውን ሕዝቡ በሰላም ለማሳለፍ ያደረገው ጥረት ተሳክቶ ያለምንም ችግር በሰላም ተጠናቅቋል፡፡

ለመርሐ ግብራችን ስኬት የሙስሊሙ መኅበረሰብ ሰላም ወዳድነት አብዩን ሚና የተጫወተ ቢሆንም የሌላ እምነት ተከታዮች በተለይም ክርስቲያን ወገኖቻችን ዚያራው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለይም በቃሊቲና አካባቢው የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሚናቸው የጎላ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሙስሊሞች ወደየቤታቸው የተመለሱትም ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ባገኙት ነጻ ትራንስፖርት (ሊፍት) ነው፡፡ ይህ አጋርነትና ትብብር ወሳኝ በሆኑ አገራዊና ብሄራዊ አጀንዳዎች ላይ ተጠናቅሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የዛሬው ትዕይንተ ዚያራችን ወህኒ ቤት የሚገኙ መሪዎቻችንንና ውድ ወንድሞቻችንን ልእልና አጉልቶ እና ጎዳናዎችን አጥለቅልቆ በሰላማዊ ትግላችን ጉዞ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ አክሎበታል፡፡ ትግላችንም ቀሪውን ትውልድ አስተማሪ ሆኖ እየዘለቀ ነው፡፡ ለሁከትና ግርግር በተመቹ ቦታዎችና በተጋበዝንባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ሰላምን መምረጣችን አስተውሎት ላልተሳናቸው ሁሉ በውስጡ ጥልቅ ትምህርት አለው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!