የህዝብ አለመረጋጋት ለአገር ዕድገት እንቅፋት ነው፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አሰልጣኞችን ከሊባኖስ አምጥቶና በይፋ በግዮን ሆቴል አሳውቆ ሙስሊሙን በአህባሽ የማጥመቅ ዘመቻ ከጀመረ አንድ ዐመት አለፈው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም መጤውን አስተሳሰብ አልቀበልም፤ በግድ ሊጫንብኝም ሆነ ተቋማቶቼን ሊነጥቀኝ አይገባም ብሎ እምነቱን የማስጠበቅ ትግል ከጀመረም እንዲሁ ዐመት ሊደፍን ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በመንግስት በኩል ለልማት ቢውል ኖሮ በኢኮኖሚ አቅሟ ከመጨረሻዎቹ ተርታ ለምትመደበው አገራችን ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የነበረ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ፣ በርካታ ረጃጅም ስብሰባዎች፣ ስልጠናዎች፣ የደህንነትና ፖሊስ ጉልበቶች ባክነዋል፡፡ በሙስሊሙ በኩልም ለስራና ልማት ቢውል ለአገራችን ዕድገት አስተዋጽኦ ሊያመጣ የሚችል የነበረ ቀላል የማይባል ጊዜና ጉልበት መስዋዕት ተደርጓል፡፡ አገራችን ከምንም ነገር በላይ ስለዕድገቷ የሚጨነቅላት ሃይል በምትፈልግበት በአሁኑ ወቅት እንደምን ሆኖ ይሆን ገንዘብና አቅም ሁሉ ወደ ሌላ አቅጣጫ እየፈሰሰ ያለው? ከማናችንም በላይ የአገራችን ዕድገት እንዲያሳስበው የሚጠበቀው መንግስታችን መቼም ይህ ጉዳይ አላሳሰበውም ለማለት ይቸግረናል፡፡ በርግጥ የዕድገት ፀር የሆነና ልማትን የሚያደናቅፍ አካል ካለ የዚህ ዐይነቱን አካል ቅድሚያ ሰጥቶ ማስወገድ እንደሚስፈልግ ሁላችንንም ያስማማናል፡፡ መንግስት ስለ ልማት እያሰበ በሌላ በኩል በአንዳንድ አገራት የምናየው ዐይነት ሰላምን የሚያናጉ የሽብር ተግባራት እየተፈጸሙ ቢሆን ኖሮ ፤ የተለያዩ ሃማኖቶችን አቅፋ በያዘችው አገራችን ያለውን ሁሉ አቀፍ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት በመናድ ሃይማኖታዊ መንግስት ህብረተሰቡ ላይ በጉልበት ለመጫን የሚታገል ሃይል ቢኖር ኖሮ አሁንም ቅድሚያ እነዚህን አካላት መዋጋት እንደሚያስፈልግ እናምናለን፡፡
ነገር ግን ኢትዮጲያ ውስጥ መሰል ተግባራት ወይም አስተሳሰቦች እንደ ህብረተሰብ በጭራሽ አልተንፀባረቁም፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከክርስቲያኑ ህብረተሰብ ጋር በጉርብትና በሰላም ሲኖር እንጂ አንዱ አንዱን ሲያጠቃ አላስተዋልንም፡፡ ህብረተሰባችን ከሌላው እምነት ተከታይ እኩል ተምሮ ለአገር እድገት እኩል አስተዋጽኦ ማድረግን እንጂ ሃማኖታዊ መንግስት የመመስረት ህልም አልሞም አያውቅም:: በርግጥ ከሙስሊሙም ይሁን ከክርስቲያኑ ህብረተሰብ በጣት የሚቆጠሩ ከህብረተሰቡ ወጣ ያለ አመላካከት ያላቸው ሰዎች የሉም ብሎ ማሰብ ያስቸግራል፡፡ በግለሰብ ደረጃ የሚፈጸሙ ጥፋቶችን በህግ አግባብ ማየትና እርምጃ መውሰድ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ ነገር ግን በሰላም የዕለት ኑሮውን ለማሳካት ደፋ ቃና እያለና አቅሙ በፈቀደ ልክ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ለመወጣት ሲጣጣር የነበረውን ህብረተሰብ በድንገት በማያውቀው ጉዳይ የመወንጀልና የማዋከብ እንዲሁም "የተሳሳቱ የተባሉትን" አስተሳሰቦቹን ለማቃናት በግዳጅ የሚሰጡት ስልጠናዎች ሰላሙን ከማወካቸውም በላይ በተረጋጋ ሁኔታ የዕለት ስራዎቹን እንዳያከናውን እንቅፋት ሆኖውበታል፡፡ አሸባሪነት ሳይሆን እምነቱ እንደተነካበት ስለተሰማውም ሆ! ብሎ በአንድነት እምነቱን ለማስጠበቅ ተነስቷል፡፡ ይህ ያለንበት መንግስትና ህዝብ መሐል የተፈጠረው ውጥረትና አለመተማመን ደግሞ ከምንም ነገር በላይ ለአገራችን ዕድገት እንቅፋት ነው፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንዲስተካከሉለት የጠየቃቸው ጥያቄዎች እጅግ ቀላል እና በምንም መንገድ መንግስትን የሚፈታተኑ ጥያቄዎች አልነበሩም፡፡ በግድ አህባሽን እንድንቀበል ጫና አይደረገብን፤ እራሳቸውን አቅለው እኛንም ያዋረዱን ሙሰኛ የመጅሊስ መሪዎች ህዝቡ በሚያምንባቸው መሪዎች ይተኩልን፤ የተወሰዱ ተቋማቶቻችን ይመለሱልን፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በፍጹም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች አልነበሩም፡፡ መንግስትም እነዚህን ጥያቄዎች መመለሱ ህብረተሰኑ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት የሚጨምሩ እንጂ በምንም ሂሳብ ክብሩን የሚነኩ አልነበሩም፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ እጅግ ሰላማዊና ምንም አይነት ፖለቲካዊ አጀንዳ እንደሌለው ባለፉት አስር ወራት ያሳያቸው ፍጹም ጨዋነትንና ሰላማዊነትን የተላበሱ ሂደቶች ለመንግሰት አሳይተዋል ብለን እናምናለን፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አንድ ቦታ ተሰብስበው አንዲት ጠጠር ሳይወረወርና ሰላም አስከባሪ ሃይል ሳያስፈልጋቸው ሃይማኖቴ አይነካብኝ የሚል ድምጽ ብቻ አሰምተው በሰላም ቤታቸው ሲገቡ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ከጀርባው ያለው ህዝብ ቢሆን ኖሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በዒድ ቀን በመላ አገሪቱ በእኩል ሰዓት ወጥቶ ምንም ሁከት ሳይፈጥር በእምነቴ አትምጡብኝ ብቻ ብሎ ሊመለስ አይታሰብም ነበር፡፡ ነገር የሙስሊሙ ጥያቄዎች ፍጹም ሃይማኖታዊ በመሆናቸው ሆኗል፡፡
አገራችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈት ምክኒያት በሃዘን ድባብና የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የስልጣን ሽግሽግ የማድረግ ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጥያቄዎቹን በድጋሚ አይተው የተሻለ ፍትሐዊ መልስ እንደሚሰጡት ተስፋ ባለመቁረጥ በሰላም ሲጠባበቅ የቆየ ቢሆንም ጥያቄያችንን በድጋሚ ከማየታቸው በፊት ሞት በመቅደሙ ከፍተኛ ሐዘን ይሰማናል፡፡ አሁን ስልጣኑን ለሚረከቡት መሪም የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄዎች የመጀመሪያ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚታዩ ጉዳዮች እንደሚሆንና ፍትሐዊ መልስ እንደምናገኝ ተስፋችን የላቀ ነው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተብ ካለው ሃይማኖት ወዳድነት የተነሳ እምነቱን የማስጠበቅ ፍላጎት እንጂ ምንም ዐይነት ፖለቲካዊ ጥያቄ እንደሌለው በአዲሱ መንግስት በድጋሚ እንዲጤንም በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በሙስሊሙ ጥያቄ ተሸፍኖ ፖለቲካዊ አጀንዳ ማራመድ የሚፈልግ አካል አለ የሚል ጥርጣሬ ካለም የጥያቆዎቻችን መመለስ እነዚህ አካላት ፍንትው ብለው እንዲወጡ ለማድረግ ይረዳል ብለን እናምናለን፡፡ ጥያቄያችን ተመልሶ መንግስትና ህዝብ መሐል የተፈጠረው አለመተማመን ተሰብሮ በጋራ ለአገራችን ዕድገት መስራትን ከልብ እንመኛለን፡፡ አዲሱ መንግስትም ጥያቄዎቻችን በተረጋጋ መንፈስ ለማየት ያመቸው ዘንድም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሲያደርግ የነበረውን የዐርብ የተቃውሞ ሂደት ለጊዜው ማቆሙ ለሰላም ያለውን ፅኑ ፍላጉት አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ከመንግስት በኩልም ጥያቄዎቹ በቀናነት ታይተው ፍትሐዊ መልስ የምናገኝበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

No comments:
Post a Comment