Radio
Bilal August 29, 2012 አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ
23/2004
- በደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ የታሰሩ ምዕመናን ለፍርድ እንዳልቀረቡ ተገለጸ
- ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲን ባለፈው ቅዳሜ በቤተ መንግስት ተገኝተው ሐዘናቸውን እንደገለፁ ተነገረ፡፡
- ተጠባባቂ ጠ/ሚ ለሁለቱ ሱዳኖች የሰላም ድርድር ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
- ግብፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ-ስርዓት ልዑክ እንደምትልክ ገለጸች
በደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ የታሰሩ ምዕመናን ለፍርድ
እንዳልቀረቡ ተገለጸ
አዲስ አበባ
ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 23/2004
በደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ በተፈጠረ
ግርግር የታሰሩ ምዕመናን ለፍርድ እንዳልቀረቡ ተገለጸ፡፡ በአረብ
ገንዳ መስጅድ ከታሰሩ በርካታ ሙስሊሞች መካከል 12ቱ ለትላንትና ቢቀጠሩም ባልታወቀ ምክንያት ለፍርድ እንዳልቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሺ የሚቆጠሩ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች
የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ከፍርድ ቤት በራፍ ላይ ቢጠብቁም እስረኞቹ እንዳልመጡ ተገልፆዋል፡፡ከፍርድ ቤት የወጣ መረጃ ባይኖርም
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሀዘን ተከትሎ እንደተራዘመ ህብረተሰቡ እየገለፀ ይገኛል፡፡
ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲን ባለፈው ቅዳሜ በቤተ
መንግስት ተገኝተው ሐዘናቸውን እንደገለፁ ተነገረ፡፡
አዲስ አበባ
ነሐሴ 23/2004
ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲን
ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 19 ብሄራዊ ቤተ-መንግስት በመገኘት በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ለቤተሰቦቻቸውና ለኢትዮጲያ
ህዝብ መግለፃቸው ተጠቆመ፡፡
ሼህ መሐመድ
ሁሴን አልአሙዲን ቅዳሜ ከሲዊድን በመምጣት እስከ እሁድ ድረስ በጠ/ሚ መኖሪያ በመገኘት ቤተሰቦቻቸውንና የቅርብ ወዳጆቻቸውን እንዳፅናኑ
ተናግረዋል፡፡
ጠ/ሚ መለስ
ዜናዊ የጀመሩት የልማት እንቅስቃሴ ያለምንም እንቅፋት እንደሚቀጥል የተናገሩት ሼህ አልአሙዲን በነገው ዕለት በብሄራዊ ቤተመንግስት
በመገኘት የሐዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተናግረዋል፡፡
ሼህ መሐመድ
ሁሴን አልአሙዲን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለጠ/ሚ ሐዘን ባለመገኘታቸውና በተለያዩ ሚዲያዎች ባለመታየታቸው ታመዋል የሚል ወሬ መናፈሱንም
የተለያዩ ምንጮች አመልክተዋል፡፡
ተጠባባቂ ጠ/ሚ ለሁለቱ ሱዳኖች የሰላም ድርድር ድጋፍ
እንዲያደርጉ ተጠየቀ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 23/2004
ተጠባባቂ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አቶ መለስ ዜናዊ እያሉ የተጀመረውን
ሰላም የማስፈን ድርድር እንዲቀጥሉ የደቡብ ሱዳን መንግስት ጠየቀ፡፡ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል በርካታ ውይይቶች በኢትዮጲያ አደራዳሪነት
ሲካሄድ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የጎላ ሚና መጫወታቸውን የደቡብ ሱዳን ዓለም ዓቀፍ ኮፕሬሽን ሚኒስትር ኒሀልዴንግ ገልፀዋል፡፡
በግዛቱ ሰላም
ለማስፈን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የማይናቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ተጠባባቂ ጠ/ሚ
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በበኩላቸው ኢትዮጲያ የሁለቱን ሱዳኖች ሰላም ለማስፈን ያላትን አቅም እንደምትጠቀም ተናግረዋል፡፡
ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትሩ
በአቶ መለስ የተጀመሩት ሰላም የማሰፈን ሂደቶችን ሀገሪቷ እንደምታስፈፅም
አመልክተዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት
መካከል በነሐሴ ወር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ቢታቀድም በረመዷን ወር ምክያት መራዘሙ ሲገለፅ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የጠቅላይ
ሚኒስትር ሞት ድርድሩን እንደማያደናቅፈው ተናግረዋል፡፡
ግብፅ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ-ስርዓት
ልዑክ እንደምትልክ ገለጸች
አዲስ አበባ
ነሐሴ 23/2004
በጠቅላይ ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ግብፅ ልዑክ እንደምትልክ የፕሬዝደንቱ
ቃል አቀባይ ዶክተር ያሲር ገለፁ፡፡
የግብፁ ፕሬዝደንት
መሀመድ ሙርሲ ከኢትዮጲያ አቻቸው ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጋር በስልክ እንደተነጋገሩና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት
እንዳሳዘናቸው፤ ለቤተሰቡና ለመላው የኢትዮጲያ ህዝቦች መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ
በአባይ ጉዳይ ላይ ከተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በአባይ ጉዳይ ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment