Radio
Bilal Aug 28, 2012 አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 22/2004
- ባሳለፍነው ሳምንት በበደሌ ከተማ የተያዙት ሶስት ሰዎች በዋስ መለቀቃቸው ተሰማ
- በሚዛን ተፈሪ ካለ መጅሊስ ፈቃድ ቁርዓን አስቀርታችኋል በሚል ታስረው የነበሩ ግለሰቦች ተፈቱ
- ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በጋራ ድንበር ላይ ወንጀሎችን ለመከላለከል ስምምነት ላይ ደረሱ
- የፍትሕ ዋና አዘጋጅ ክስ ተቋረጠ
ባሳለፍነው ሳምንት በበደሌ ከተማ የተያዙት ሶስት ሰዎች በዋስ መለቀቃቸው
ተሰማ
አዲስ አበባ
ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 22/2004
ባሳለፍነው ሳምንት በበደሌ ከተማ የተያዙት ሶስት ሰዎች በዋስ
ተለቀቁ፡፡ 3ቱ ምዕመናን ባሳለፍነው ሳምንት አክራሪዎችን ትረዳላችሁ በማለት መጅሊስ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ስብሰባውን በትናችኋል
በሚል ሰበብ እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቃቢ ህግ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠይቆባቸው ፍርድ ቤት ለ7ቀን ቀጠሮ
በሠጠው መሠረት 3ቱ ምዕመናን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በ3 ሺ ብር ዋስ ተለቀዋል፡፡ በተሰጠው ቀጠሮ ላይ መርማሪ ፖሊስ ባለመገኘቱ
ፍረድ ቤቱ የዋስ መብታቸውን እንዳከበረላቸው ድምጻቸውን መቀረፅ ያልፈለጉ
እስረኛ ገልጸዋል፡፡
በሚዛን ተፈሪ ካለ መጅሊስ ፈቃድ ቁርዓን አስቀርታችኋል በሚል ታስረው
የነበሩ ግለሰቦች ተፈቱ
አዲስ አበባ
ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 22/2004
በሚዛን ተፈሪ ከመጅሊስ ፈቃድ ውጪ ቁርዓን አስቀርታኋል በሚል
ምክንያት ለ14 ቀናት ታስረው የነበሩ ግለሰቦች ተፈቱ፡፡ ሙሳፊሮች በከተማዋ ሲዛወሩ የነበሩ 8 ሙሳፊሮችም አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ
መደረጉነወ የአካባቢው ምንጮች አስረድተዋል፡፡
በሚዛን ተፈሪ
ቁርዓን ሲያስቀሩ የነቡሩ ሁለት ግለሰቦችን ጨምሮ ለቁርዓን መቅሪያ ቦታ የሰጡን ግለሰብ ከ14 ቀናት እስራት በኋላ መለቀቃቸውን
ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ሶስቱ ግለሰቦች ለፍርድ ቀርበው በድጋሚ በድጋሚ ዛሬ 3ሰዓት ላይ ተገኝተው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከተደመጡ
በኋላ በዋስ እንዲፈቱ ገልጸዋል፡፡ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በአንድ ሺ ብር ዋስ እንደተለቀቁም የአካባቢው የሬድዮ ቢላል ምንጭ አስረድተዋል፡፡
በተበ,መሳሳይ በሚዛን ተፈሪ ሲንቀሳቀሱ የነበረ 8 ሙሳፊሮች የእስር ቆይታ በኋላ ትላንት ሲፈቱ አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እንደተነገራቸውም
የአካባቢው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በጋራ ድንበር ላይ ወንጀሎችን ለመከላለከል ስምምነት ላይ ደረሱ
አዲስ አበባ
ሬዲዮ ቢላል ነሐሴ 22/2004
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን
ለመከላከል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡በጋራ ድንበራቸው ላይ የተረጋጋ ሰላም ለማስፈን ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የጋምቤላ
ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡
የክልሉ የደህንነትና የአስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ጎርደን ኮንግ የቀረበው
መረጃ እንደሚያመለክተው ድንበር እየተሸገሩ ጥቃት የሚሰነዝሩ ፀረ-ሰላም ቡድኖችን ለመከላከልና ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ባደረጉት
ስምምነት ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡በተጨባጭ ከተሳተፉትም መካከል ከደቡብ ሱዳን ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ በመግባት የግለሰቦችን
ንብረት ለማጋየት በተንቀሳቀሱ የደቡብ ሱዳን ፀረ ሰላም ቡድኖች ላይ ፑሊየትበተባለው የጋምበቤላ ክልላዊ ልዩ የፖለቲካ ቡድን በሰነዘረው
ጥቃት 15ታጣቂዎች መግደላቸው በዋናነት ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን መንግስት በጋምቤላ ዘልቀው በመግባት
ባለፈው ግንቦት ጥቃት ከሰነዘሩት ታጣቂዎች ውስጥ 15 የሚሆኑት ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም
በበኩሉ በደቡብ ሱዳን ወንጀል የፈፀሙ አምስት ታጣቂዎችን አሳልፎ መስጠቱን አስረድተዋል፡፡
የፍትሕ ዋና አዘጋጅ ክስ ተቋረጠ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 22/2004
የፌደራል ዓቃቤ
ሕግ በመሠረተበት ሦስት
ክሶች ምክንያት ነሐሴ
17 ቀን 2004 ዓ.ም. ዋስትና ተከልክሎ በማረሚያ ቤት እንዲቆይ የተደረገው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና
አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት
ክሱ እንዲቋረጥ ተደረገ፡፡ ክሱ እንዲቋረጥ ያዘዘው ከሳሹ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ
ሲሆን፣ ለክሱ መቋረጥ በምክንያትነት ያቀረበው ተጨማሪ ምርመራ አደርጋለሁ በማለቱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በጻፈው ደብዳቤ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸውን ክሶች ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ተመስገን በዛሬው ዕለት ከእስር እንደሚለቀቅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ የተመሠረተበት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ራሱ በዘገባቸውና በጋዜጣው ዓምደኞች በተዘገቡ አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉ ሦስት ጽሑፎች ሳቢያ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስር መለስ ዜናዊ ሕመም ጋር በተገናኘ ዘገባው ምክንያት ከታተመ በኋላ እንዳይሠራጭ በፍትሕ ሚኒስቴር መታገዱም ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም በማለቱ ምክንያት ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በጻፈው ደብዳቤ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸውን ክሶች ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ተመስገን በዛሬው ዕለት ከእስር እንደሚለቀቅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ የተመሠረተበት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ራሱ በዘገባቸውና በጋዜጣው ዓምደኞች በተዘገቡ አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉ ሦስት ጽሑፎች ሳቢያ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስር መለስ ዜናዊ ሕመም ጋር በተገናኘ ዘገባው ምክንያት ከታተመ በኋላ እንዳይሠራጭ በፍትሕ ሚኒስቴር መታገዱም ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም በማለቱ ምክንያት ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡
No comments:
Post a Comment