Monday, September 17, 2012

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች የፊታችን መስከረም 27 ይካሄዳል የተባለዉን ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ,,,,,,,,,


በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊሞች የፊታችን መስከረም 27 ይካሄዳል የተባለዉን ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ እንደማይሳተፍ በየወረዳዉ ለሚገኙ ለመንግስት አስተዳደር አካላት በፊርማ የተደገፈ የተቃዉሞ ደብዳቤ እያስገቡ መሆናቸዉን ምንጮቻችን አስታወቁ::ይህ ደብዳቤ ህዝበ ሙስሊሙ በምርጫዉ የማይሳተፍበትን ምክንያት የዘረዘሩ ሲሆን ህዝቡ በጠየቀዉ መልኩ ምርጫዉ ካልተካሄደ መቼም ቢሆን እንደማይሳተፍ አቖማቸዉን እየገለፁ ይገኛሉ:: ህዝበ ሙስሊሙ በየወረዳዉ እያስገባ የሚገኘዉ የደብዳቤ ይዘት ከታች የተቀመጠ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ይህን መሰል ስራ እየሰራ መገኘቱ እጅግ የሚደነቅ እና የሚበረታታ መሆኑን እንገልፃለን:: በምርጫዉ ህዝበ ሙስሊሙ እንደማይሳተፍ ለየወረዳዉ የመንግስት አስተዳደር ቀድሞ በፅሁፍ ማሳወቅ መጀመሩ ምርጫዉ ቢካሄድ እንኮን ህዝቡ ተቃዉሞዉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ተቃዉመሞዉን አጠናክሮ ለመቀጠል አይነተኛ ምክንያት እንደሚሆን አመላካች መሆኑን እንገልፃለን:: ይህንን ደብዳቤ ያላስገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ከወዲሁ በየአካባቢዉ ባሉ መስጂዶች ፊርማዉን በማሰባሰብ በየአቅራቢያዉ ላሉ የወረዳ አስተዳደሮች በማስገባት በምርጫዉ እንደማይሳተፍ ማሳወቅ እንደሚኖርባቸዉና ሌሎች ወረዳዎች እንዳደረጉት በማድረግ አንድነታችንን እንድናሳይ እናሳስባለን:: የጁምአ ቀንም በርካታ ሙስሊም ለሰላት በየመሳጂዱ ስለሚገኝ ፊርማ የማሰባሰቡን ስራ በዕለቱ ማከነወን እንደምንችል እንገልፃለን:: በዚሁ አጋጣሚ የምርጫ ካርድ ፈፅሞ ሙስሊሙ መዉሰድ እንደሌለበት በጥብቅ እናሳስባለን!!! ከዚህ በታች የተቀመጠዉ ህዝበ ሙስሊሙ በየወረዳዉ ፈርሞ እያስገባዉ የሚገኙዉ ደብዳቤ ስለሆነ በየወረዳችን ፈርመን ያላስገባን ሰዎች ይዘቱን በማስተካከል ፕሪንት በማድረግ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን:: ለዚህ ስራ ተግባራዊነት ሁላችንም ፊርማዉን በማሰባሰብ የበኩላችንን አስተዎፅኦ በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታችንን እንወጣ!!!,
ለ --------------------­-
ርዕስ፡- የማናውቃቸው ግለሰቦች የሚያስፈጽሙትን የሀጥማኖታችን የመጅሊስ ምርጫ እንደማንሳተፍ ስለማሳወቅ ይሆናል
እኛ የ ----------- ክ/ከተማ የ -------- ወረዳ ነዋሪዎች ስንሆን ከዚህ ቀደም የመጅሊስ ምርጫ ይካሄድልን በማለት ለወረዳችን በፊርሚያችን ጉዳያችንን በዝርዝር ጠቅሰን ማስገባታችን ይታወቃል ፡፡ ከጠየቅናቸው ነጥቦች ውስጥ አንዱ በቅድሚያ የምርጫ አስፈጻሚዎች ነጻና ገለልተኛ በሆነ መልኩ በህዝብ ተመርጠው፡ እነሱ የአስመራጭን፤ የመራጭንና የተመራጭን መስፈርት አውጥተው የምርጫውን የግዜ ሰሌዳ ለህዝብ አሳውቀው ነው ምርጫው መካሄድ ያለበት የሚል ነበር፡፡ አሁን ግን በመንግስት ሚድያ እየሰማን ያለነው እኛ ካመለከትነው ውጭ በማነውቀው አካል እንደሚካሄድና ቀነ ቀጠሮም እንደተያዘለት ነው፡፡ ስለዚህ መስከረም 27/2005 ይካሄዳል የተባለውን የመጅሊስ ምርጫ በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ምክንያት የማንሳተፍ መሆኑን እናሳውቃለን ፡-
1- የምርጫ አስፈፃሚዎች በህዝብ የተሰየሙ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን የምንቃወማቸው በመሆኑ፡፡
2- አሁን የምርጫ አስፈጻሚ ነን ባዮች ከአመት በላይ በሀይል አይጫንብን እያልን ስንቃወመው የነበረውን የአህባሽን አመለካከት ስሙን (አህለሱና ወለጀማ ሱፍያ) ብለው ቀይረው ተደራጅተው በሀይል በህዝቡ ላይ ለመጫን ቀን ማታ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ፡፡
3- የመራጮችና ተመራጮች መስፈርት የተዘጋጀው ሙስሊሙ አይወክሉንም በድለውናል ለፍርድ ይቅረቡልን እያል ለቡዙ አመታት ሲከሳቸው በነበሩት ያልተመረጡ የመጅሊስ አመራሮች በመሆኑና በመስፈርቱም የማናምንበት በመሆኑ
4- የምርጫ ቦታና ግዜው ሙስሊሙ ባላመነበትና ብሎም በሚቃወምበት ቦታበመሆኑ ፡፡
5- ይህንኑ ህጋዊ የመብት ጥያቄያችንን ለመንግሰት እንዲያቀርቡልን የወከልናቸው ወንድሞቻችን ባላወቅነው ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ መሆናቸው ሞራለችንን የጎዳው በመሆኑና መሰል ችግሮች ምክንያት ምርጫው የማይመለከተን መሆኑን እየገለጽን፡ ከዚህ ቀደም ባመለከትነው መሰረት የመጅሊሳችንን አመራሮች ነጻና ገለልተኛ በሆኑ የመላው ህዝበ ሙስሊም እውቅና ባላቸው የምርጫ አስፈጻሚዎች፡ የሀገራችን ህገ መንግሰት በሰጠን መብት እንዲሁም እምነታችን በሚያዘው መሰረት ብቻ እንድናካሄድ እድሉ እንዲሰጠን ስንል በተለመደው ፊርሚያችን በአክብሮት እንጠይቃለን ፡፡

No comments:

Post a Comment