ግፍ በተመላበት ሴራ ትግላችን አይቆምም!
ራሳቸውን ‹‹የህዝብ ደህንነት ጠባቂ›› ሲሉ በሰየሙ አካላት ኮሚቴዎቻችን እና ብርቅዬ ልጆቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የመብት ጥሰት ግቡን ሊመታ የማይችል መሆኑን ደግመን ደጋግመን ስንገልጽ መቆየታችን ይታወሳል። አዎን! ከቀን ወደቀን እያደገ የሚመጣ የመብት ጥሰት የትግልን ስሜትና አመክንዮ ቢያሳድግ እንጂ በጭራሽ አይቀንስም። በመሆኑም ‹‹ግፍ በተመላበት ሴራ ሰላማዊ ትግላችን አይቆምም!›› የሚል መልእክት በስልጣን ርክክብ ላይ ላለው መንግስት ለማስተላለፍ እንወዳለን። ይህን የምንልባቸውም ሶስት ምክንያቶች አሉን፡-
(1) ኮሚቴዎቻችን፣ ዳኢዎቻችን፣ ጋዜጠኞቻችንና አርቲስቶቻችን በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው እስር ቤት ቢቀሩ እንኳ የእውነት ሽብርተኞች መሆናቸውን አምኖ የሚቀበል ማህበረሰብ የለም። በኢቲቪና በአዲስ ዘመን የሀሰት ዘገባዎችና ድራማዎች እጅግ የተሰላቸው ሙስሊሙ ማህበረሰብና የሌላ ሃይማኖት ተከታይ አጋሮቹ መሰል ያፈጠጡ ፕሮፓጋንዳዎችን አምነው የሚቀበሉበት ክፍተት የለም። ለመንግስት ሕጋዊ ህልውና ብቸኛውን መሠረት ሊጥል የሚችለው ሰፊው ህዝብ ያላመነበት ክስ እና ፍርድ ደግሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴያችንን ሊያጠለሽ አይችልም። አንድ ‹‹ከምንም በላይ የምደነቅበት ባህሪዬ ሕዝባዊነቴ ነው›› ሲል ደጋግሞ የሚናገር መንግስት የሚወስዳቸው እርምጃዎች በህዝቡ ዘንድ ተአማኒነት ከሌላቸው ምንስ ያህል ዘላቂ ዋጋ ይኖረዋል?
(2) በኮሚቴዎቻችን ላይ ሊወሰድ የሚችለው ማናቸውም አይነት እርምጃ (በሽምግልና መፍታትም ሆነ በሽብር ወንጅሎ ለአመታት ማሰር) ግለሰቦችን ከመጉዳት ባለፈ ትግሉን ሊያስቆመው አይችልም። መንግስት ግን እዚህ ላይ የተሳሳተ ሂሳብ ሲጠቀም ይታያል።፡ ይህ ስህተት ደግሞ ‹‹እንቅስቃሴውን የፈጠሩት ኮሚቴዎቹ ናቸው›› የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ነው። ይህ ግን ትልቅ ስህተት ነው። ለአመታት የተጠራቀመ በደልና የአዲሱ ‹‹አህባሽ›› የተባለ ሃይማኖት በአፈሙዝ ታጅቦ መምጣት የፈጠረው ህዝባዊ ተቃውሞ ኮሚቴዎቹን ፈጠረ እንጂ ኮሚቴዎቹ ቁጣውን አልፈጠሩትም። ህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ጥያቄያችንን ለመንግስት አድርሱልን›› ሲል በዳእዋ የሚያውቃቸውን አስተማሪዎቹን መረጠ እንጂ አስተማሪዎቹ ጥያቄውን አልፈጠሩም። በመሆኑም እነሱ ላይ የሚደርስ ጉዳት ተጨማሪ ጥያቄ እና የትግል ፍላጎት ከመፍጠር ውጭ ትግሉን ሊያደበዝዘው አይችልም። ኮሚቴዎቹም ያልፈጠሩትን ህዝባዊ ተቃውሞ ሊያስቆሙ አይችሉም። ይህ በተግባር ተከስቶ ያየነው ነው። ኮሚቴዎቻችን እና ዳኢዎቻችን ከታሰሩ ሁለት ወር ቢሞላቸውም የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ላይ ‹‹ይፈቱልን!›› ከሚል አራተኛ ጥያቄ መጨመር በቀር የተከሰተ ነገር የለም። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ እስከ የካቲት 26 ድረስ መንግስት ‹‹ተገቢና ህገ መንግስታዊ ናቸው›› ሲል ያሞካሻቸው ሶስቱ የመብት ጥያቄዎች ገና ባለመመለሳቸው ነው። የህዝብ ተወካይነት ጥያቄ የተነሳበት መጅሊስ አሁንም ድረስ በስልጣኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይደረጋል በተባለው ምርጫም መንግስት ‹‹እኔ በምፈልገው መልኩ በቀበሌ ብቻ ነው የሚካሄደው›› በሚል አስቸጋሪ አቋሙ ቀጥሎበታል። በግድ ሲጫን የነበረው አዲሱ ‹‹መንግስታዊ እስልምና (አህባሽ)›› መሳጂዶቻችንን መረበሹን የቀጠለ ሲሆን አህባሽ ያልሆኑ ኢማሞች እየተባረሩ በሌሎች መተካታቸው ቀጥሏል። የአወሊያ ትምህርት ቤትም አሁንም ድረስ የሚገኘው በህገ ወጡ መጅሊስ እጅ ነው። ይልቁንም ከ12 የማያንሱ ኢስላማዊ የእርዳታ ድርጅቶች ባንክ ሂሳብ መታገዱ፣ ወለድ አልባ ባንክ ከተፈቀደ በኋላ መከልከሉ እና ሌሎችም ተጨማሪ የመብት ጥሰቶች መፈጸማቸው የትግሉን ‹‹የህልውና ጉዳይነት›› አጉልቶታል። በመሆኑም ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ ኮሚቴዎቻችን መታሰራቸው ሕዝበ ሙስሊሙ አዳዲስ ህቡእም ሆነ ግልጽ አመራሮችን እንዲፈጥር ከማድረግ ባለፈ ትግሉን የማቆም እድሉ እጅግ ደካማ ነው።
(3) በመሪዎቻችን ላይ እስካሁን የተፈጸመውም ሆነ ሊፈጸም የታሰበው ህገ ወጥ ሴራ ‹‹ተሳክቶ ተቃውሞውን ያቆመዋል›› የሚል እጅግ የራቀ ግምት ብንወስድ እንኳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በልባቸው ከፍተኛ ቂም እና ቁርሾ በመንግስት ላይ መያዛቸው አይቀሬ ነው። በየትኛውም አይነት የፖለቲካ ቀመር ይህ ለመንግስት አዋጭ ሊሆን አይችልም። በተለይ ደግሞ ለበርካታ አመታት በስልጣን ላይ ለመቆየት ለሚያስበው የኢህአዴግ መንግስት! በህዝበ ሙስሊሙ እና በመንግስት መካከል ቅያሜ መኖሩ ደግሞ በሚቀጥሉት ጊዜያት ለመንግስት የሚፈጥረው ኪሳራ ቀላል አይሆንም። ካለፉት የአፄዎችና የደርግ ሃይማኖታዊ ጭቆና አንጻር ለተሰጡት ሽርፍራፊ መብቶች ምስጋናውን ሲያሳይ የቆየው እና ከፖለቲካዊ ተሳትፎ ለዘመናት ርቆ የቆየው ህዝበ ሙስሊም ወደ ተቃዋሚው ፖለቲካ ጎራ በመቀላቀል የፖለቲካ ተሳትፎውን የሚጀምርበት እድል ሰፊ ነው። ካለፈው አመት ጀምሮ ሲያሳየው ከቆየው የሰላማዊ ተቃውሞ ብቃትና እምቅ ሃይል አንጻር አሰናስለን ስናስበው ደግሞ ኪሳራው ለመንግስት ቀላል እንደማይሆን ግልጽ ነው። በሚቀጥሉት አገራዊ ምርጫዎች ላይ ይህ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ እንደሚሆንም ሳይታለም የተፈታ ነው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ አገራችን የአማኝ ህብረተሰብ አገር ናት። አማኞች ሲበደሉ ደግሞ ወደየፈጣሪያቸው አቤት ይላሉ! የየትኛውም እምነት ተከታይ ቢሆኑ እንኳ የተበደሉ ሰዎችን ዱዓ የሚሰማው ጌታ ደግሞ አያሳፍራቸውም። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቹ ወደፈጣሪያቸው እምባቸውን የሚያዘሩበት መንግስት በስልጣን የመቆየት እድሉ ምን ያህል ይሆን?
መደምደሚያ
ህዝብና ፈቃደኝነቱ የአንድ መንግስት ህጋዊ ህልውና የሚገነባበት ብቸኛ መሰረት ነው። ‹‹ዴሞክራሲያዊ ነኝ!›› የሚል መንግስት ደግሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ተቃውሞ የዴሞክራሲ ባህል የሚዳብርበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠንቅቆ መረዳት ይኖርበታል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊም ዜጎቹ ያቀረቡለትን ንጹህ ሃይማኖታዊ ጥያቄ መመለስም ‹‹ህዝባዊ ነኝ!›› ለሚል መንግስት ሽንፈት አይደለም፤ ይልቁንም የህዝብን ጥያቄ እሺ ማለት ትህትናንና አዳማጭነትን፣ ህዝባዊነትን የሚያሳይ አኩሪ ባህል ነው። በተቃራኒው ደግሞ ‹‹እልኸኛ›› መሆን፣ ‹‹ተደፈርኩ!›› ባይነት እና ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ እልኽ ትግል እንዲገጥሙ ማድረግ ከአንድ መንግስት የሚጠበቅ ሆደ ሰፊነትን ይቃረናል። የመንግስትን የህልውና መሰረትም ይነቀንቃል።
እስካሁን በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተፈጸሙትን በደሎች ለመካስና ለመታረቅ አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም። የሙስሊሙን ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ሁሉም በእርቅ ስሜት ወደወትሮው ልማት እና አገር ግንባታ መመለስ የሚችለልበት እድል ሰፊ ነው - መንግስት ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ! በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ አለም በሞት መለየት የተፈጠረውን ክፍተት በሰላማዊ ሽግግር ለመሙላት እየጣረ ያለው አዲሱ አስተዳደር ይህንን ለማድረግ ሙሉ እድል አለውና ይጠቀምበት እንላለን! እኛ ሙስሊሞች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከ‹‹ምእራፍ መጽሄት›› ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ‹‹ሰላምና በረከት ለዚህች አገር እንዲበዛ እጸልያለሁ፡፡ ለመሪዎቿ፣ ለመንግስት ባለስልጣናት ጥበብና ማስተዋልን እንዲሰጥ እጸልያለሁ፡፡ ሁሉም ሃይማኖቶች ያለ አድልዎ እና ልዩነት በእኩልነት እና በመቻቻል እንዲኖሩ እመኛለሁ›› ሲሉ የገቡት ቃልና ምኞት ይፈጸምልን ዘንድ ድምጻችንን ከፍ አድርገን እያሰማን እንገኛለን። በአላህ ፈቃድም ይሳካልናል፤ አላህ ጌታችን አዛኝ ነውና!

No comments:
Post a Comment