ዘመን ተሸጋሪ ድንቅ ውለታ (እውነተኛ መጣጥፍ)
ክፍል አንድ፡-
ሀምሌ 7 2004 እለተ ቅዳሜ ታላቁ አንዋር መስጂድ ከወትሮ በተለየ እልህና ቁጭት ምሬት ጭምር የተናነቀው ከልጅ
እስከ ሽማግሌ ሴቷም ሆነች የቤት እመቤቷ ፍፁም ከልብ በሆነ ወኔ እና ሃይል አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ
አክበር ……. በሚሉ ሰዎች ተሞልቷል;;ሐምሌ 6 2004 አርብ ምሽት ከሁሉም ሙስሊም ልብ የማይጠፋ ዘግናኝ
ኢ-ሰብአዊ የጭቆናና የግፍ ድርጊት በ አወሊያ ለአንድነት ዝግጅት ስራ ለመስራትና በመስራት ላይ በተገኙ እናቶቻችንና
እህቶቻችን ላይ ይህ ነው ተብሎ ሊገለፅ በሚከብድ መልኩ አይደለም ለመመታት ለማውራት እንኳን በሚከብድ መልኩ
የድብደባና የስቃይ ውርጅብኝ ዘንቦ ግርፋቱ ሳያባራ ነበር እለተ ቅዳሜ ሐምሌ 7 2004 በጠዋት በታላቁ አንዋር
መስጂድ ህዝበ ሙስሊሙ የተሰበሰበው;;የወንድሞቻችን ነገር ከአላህ እዝነት ካልሆነ በስተቀር በምንም ሊለወጥ በማይችል
መልኩ ከሞት ተርፈው የሞት ኑሮ በህይወት ይኖሩ እንደሆን እንጂ እንዲህ ነው ተብሎ መገለፅ በሚችል ሁኔታ ውስጥ
አልነበሩም፡፡አንዱ ወንድሜ ሞቷል ሲል አንዷ ደግሞ ወንድሜ ሚተርፍ አይመስለኝም እናት የልጄ ስልክ ቁጥር ይህ ነው
እባካችሁ ደውሉለት ማታ እንደወጣ አልተመለሰም ፖሊስ ጣብያ ሁሉ ፈለኩ ላገኘው አልቻልኩም ሆስፒታሎችን አሰስኩ ከዛም
አልተገኘ ልጄ ምን ሆኖ ይሆን እባካችሁ ልጄን ያገኛችሁ እባካችሁን ወንድማችሁን ፈልጉት ግማሹ በለቅሶ የጠፉት
ሚመለሱ እየመሰለው ግድብ በሌላቸው የወንድ አይኖቹ ሲያነባ ገሚሱ በእልህና በቁጭት ወንድሜ ተጎድቶ እንዴት እኔ
ተረፍኩ ይላል የወንድሙን ስቃይ እሱ አለመካፈሉ እጅግ እያበሳጨው ሌላው በብስጭት ቀሪውም በቁጭት ...
……
.አቤት
የጭንቅ አይነቶች እዋይ የስቃይ ብዛት፡፡እልህና ቁጭት የፍትህ መጓደል እርር ድብን ያደረገው ሰላም ናፋቂ ፍትህ
ፈላጊ ህዝበ ሙስሊም አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር ….ይላል፡፡ምን እንደሚያደርግ ከምንና ምንን ከምን
እንደሚጀምር መሪ ፍለጋ አሚሮቹን የሞትን ሽረት ያህል በጣር በምጥ በጉጉት ሲጠብቅ ለነበረው በታላቁ በአንዋር
መስጂድ ለተሰበሰበው ለተጨነቀው ህዝበ ሙስሊም አለሁላችሁ ሲል ጭንቀታችሁን በአላህ ላይ ጣሉት አላህ ከታጋሾች ጋር
ነው እያለ ሲያስተምረን የነበረው ውለታውን በቃላት መግለፅ ሳይሆን በቃላት ለማስቀመጥ ሀሳቡ እንኳን የሚከብደው
ያስተማረንን የዲን ትምህርት ተግብሮ ያሳየን ከሁሉም ሙስሊም ልብ መቼም የማይጠፋው የሰላም አምባሳደር የማይገልፀው
ሰላም ቀማሪው የኢስላም ልጅ ያ በኩር የወጣቶች ሞዴል የዘመኑ አርአያ ተምሳሌት ዳኢ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ መጣ መጥቶም
ያን ሁሉ ጭንቀት እና ስጋት አላህ በሰጠው ፀጋ ወደማረጋጋት ለወጠው ያሁሉ ሺህ ህዝብ ከልቡ አደመጠው፡፡አቤት
የዛን ቀን ኢትዮጵያን ምን ሊውጣት ነበር??? ሙስሊሞች አሚር መርጠን አሚር ባይኖረን ኖሮ ሙስሊም ሆነን አሚር
መከተል ራህመቱን ሊልአለሚን የሆኑት ረሱል ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)ባያስተምሩን ኖሮ አንድን ነብስ ማጥፋት
የአለምን ህዝብ ነብስ ማጥፋት እንደሆነ ቅዱስ ቁርዓን ባይነግረን ኖሮ አቤት ኢትዮጵያ እስከወዲያኛው ትሆን ነበር
እሮሮ በእሮሮ ግን ይህ ሁሉ እንዳይሆን መናገር ጀመረ ያሲን ኑሩ በአንዋር ተገኝቶ መቼም ማንረሳውን ታሪክ
ተንተርሶ፡፡ታሪኩ እንዲህ ነው ከሱ ከሰማሁት እኔ ላካፍላችሁ፡፡ይቀጥላል…..
No comments:
Post a Comment