(New) በአላህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩሕሩሕ
መንግስትም በአቋሙ እንደፀና ቀጥሏል፡፡ እኛም በአላህ እገዛ እስከመጨረሻው ድረስ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሟችንን እንቀጥላለን፡፡
ሙስሊሙ ሕዝብ በሆደ ሰፊነት የሕገ መንግስቱን ሥርዓት በማክበርና ለሠላም ተገዢ በመሆን ሕጉ በሚፈቅደው አካሄድ ተቃውሞውን ከማሰማት ውጭ ወደ ግጭት የሚያመራ ምንም ዓይነት ተግባር ከመፈፀምም ሆነ ትንኮሳ ከመጫር ተቆጥቦ ባለበት ሁኔታ፤ከዚህም በላይ ተቃውሞውን በሠላማዊ መንገድ በሚያሰማበት ጊዜ እየደረሰበት ያለውን ማስፈራራት፣ እገታ፣ ድብደባ፣ እስራትና ግድያ በመቋቋም በጠንካራ አቋሙ ላይ እንደፀና ባለበት ሁኔታ በተደጋጋሚ እያልነው እንደምንገኘው ሁሉ ያገኘነው ትርፍ ቢኖር ተጨማሪ ንቀትን፣ ምንም አያመጡም መባልን ብቻ መሆኑን በዓይናችን እያየን እንገኛለን፡፡ በትክክለኛ የዲሞክራሲ ሥርዓት መርህ የብዙኃኑ ድምፅ ይከበራል፡፡ ፍፁም ጨዋነት በተሞላበት አካሄድ ሕዝብ ተቃውሞውን እየገለጠ ባለበት አጋጣሚ ይቅርና ብዙኃን ተበደልን ባዮች ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ በመውጣት ሁከት የተቀላቀለበት ተቃውሞ ቢያሰሙ እንኳን በዲሞክራሲ መርህ መሠረት የብዙኃን ድምጽ ያለምንም ማቅማማት ተቀባይነት ያገኛል፡፡ በአገራችን በተጨባጭ የምናየው ነገር ግን የዲሞክራሲ ስርዓት ባሕሪ ቀጥተኛ ግልባጩን ነው፡፡ ብዙኃን ልክ አሁን በምናው ሁኔታ የሚጨቆኑበት፣ ድምፃቸው የሚታፈንበት፣ የሚንገላቱበት፣ የሚደበደቡበት፣ ሚታሠሩበት ብሎም የሚገደሉበት…
ሕዝበ ሙስሊሙ ወኪል የኃይማኖት ተቋሙን እየመሩት ያሉት አካላት እሱ የማያውቃቸው በመሆኑ እነኚህ አካላት ወርደው በምትካቸው እኔ የማምንባቸው ግለሰቦች ይመረጡ ሲል ያሰማውን ጠንካራ የተቃውሞ ድምፅ ተከትሎ ምርጫ ይካሄዳል መባሉ እሰዬው የሚያሰኝ ቢሆንም ሂደቱ ከመጀመሪያው አሁን እስከ ደረሰበት ደረጃ ድረስ የብዙኃኑን ድምጽ በወከለ መልኩ እየተካሄደ እንዳልሆነ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሙስሊም ሕዝበ በዚህ እንቆቅልሽ በሆነ የአሰራር ስርዓት ውስጥ ራሱን ተሳታፊ ከማድረግ ቆጥቦ ተቃውሞ ማሰማቱን ቢቀጥልም “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ታሳድራለች” እንዲሉ የመጅሊሱ ሕገ ወጥ አመራር አካላት ጉዳይ አስፈፃሚዎችና የመንግስት የፀጥታና ደሕንነት አካላት ሕዝቡን የሚያሸማቅቅና የሚያስፈራራ ተግባር እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡
በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ምርጫውን እንዲሳተፍ ጥሪ ቢያደርጉም የ “ምርጫው” አስፈፃሚ አካላት ሰሚ ጆሮ ማጣታቸው ሳያበሳጫቸው አልቀረም፡፡ ለሚዲያ እና ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ያውሏቸው ዘንድ በየቀበሌው እንዲመዘገቡ የመለመሏቸው እና ያሰለፏቸው ሰዎች እና ዘዴ የሚፈልጉትን ያክል ውጤት ሊያስመዘግብላቸውም አልቻለም፡፡ ህዝቡም ነቄ በማለቱ ከቤቱ ሳየወጣ ቀረ፣ ተቃውሞውንም እነሆ አጠናክሮ ቀጠለ፡፡ በሁኔታው ግራ የተጋቡት እነኚሁ አካላት ከፍተኛ ንቀትና ማን አለብኝነት በተሞላበት ሁኔታ ኮፊያ የለበሱ ግለሰቦች ከመንግስት ደሕንነትና ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በየመንደሩና በየቤቱ በስም ዝርዝር የተሞላ ወረቀት በማነብነብ “ተመዝግባችኋል?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡
ተቃውሞውን በአደባባይ በሠላማዊ መንገድ እያሰማ ለሚገኝ ማሕበረሰብ ቤቱ ድረስ በመሄድ “ተመዝግብሃል?” ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ምላሹ ምን እንዲሆን እንደተፈለገ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ተግባራቸው የተበሳጨ አካል ትንኮሳ እንደፈፀሙበት ተሰምቶት በስሜት ተነሳስቶ ጥቃት እንዲያደርስ መጋበዝ ሲሆን እጅግ የሚያስደንቀው ነገር ቢኖር ቤቱ ድረስ ቢሄዱበትም ሙስሊሙ ሕዝብ እያሳየው ያለው ግብረ መልስ እና እየሰጣቸው ያለው ምላሽ ነው፡፡ “አዎን ተመዝግበናል፣ እሺ እንመዘገባለን…” ይሏቸዋል የሆዳቸውን በሆዳቸው በመያዝ፡፡ “ምክንያቱ ደግሞ እነኚህ ሰዎች አላህን ሳይፈሩ በየቤታችን የሚመጡት እኛን በማሸማቀቅ የእነሱን ጉዳይ እንድናስፈጽምላቸው አሊያም በንዴት አላስፈላጊ እሰጣ አገባ ውስጥ እንድንገባ ለማድረግ ሲሆን ከዚህ የተለየ ምላሽ ከሰጠናቸው ደግሞ ያው የፈረደበትን ስያሜ ለጥፈውብን ሲበቁ ለማሰር እንደሆነ ገብቶናል ስለዚህ እና የምንሰራውን እናውቃለን፡፡ ብልጦች አይደለንም ብልጣ ብልጥ ነን ባዮች ግን አያታልሉንም” ሲሉ ምላሽ ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡
ይህ በሁሉም አካባቢዎች እንደ ጥሩ ተሞክሮ ሊወሰድና ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ በመታመኑ ምክንያት ለብዙኃኑ እንዲተላለፍ ሆኗል፡፡
መንግስት እስካሁን ባለው ተጨባጭ ምንም ዓይነት የአቋም ለውጥ ለማድረግ እንዳልተዘጋጀ የምናያቸው ተግባራት እያረጋገጡልን ይገኛሉ፡፡ የብዙኃን ድምፅ ተንቆ እና ሕዝቡም የአሸባሪነትና የፅንፈኝነት ታፔላ ተለጥፎበታል፣ ሕገ መንግስቱም በግልጽ እየተጣሰ ይገኛል፡፡
ከኛ ምን ይጠበቃል? እጃችንን ወደ አላህ ዘርግተን ስናበቃ የተለመደውን የጠነከረ ዱዓ ማድረግ እና በማንኛውም አካል አማካይነት የሚደርስብንን ትንኮሳ ወደ ጎን በመተው ተቃውሟችንን መቀጠል እና መቀጠል ከኛ ይጠበቃል፡፡
በታሪክ አይተነው የማናውቀውና ችሮታው ከአላህ እንደሆነ የሚገባን አንድነታችን ዛሬም እንደትላንቱ ታሪክ እንደሚሠራ ከቶም አንጠራጠርም፡፡እዚህ ደረጃ የደረሰው ፍፁም ሰላማዊ የሆነው ትግላችን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረን እናምናለን-ኢንሻ አላህ፡፡ ዛሬ ጡንቻቸውን(ማሰር መቻላቸውን፣መግደል መቻላቸውን) በመተማመን ጥቂቶች በብዙኃን ጫንቃ ላይ እንዳሻቸው ቢረማመዱም ዞሮ ዞሮ ብዙኃኑ ይመውዕ (ብዙኃኑ ያሸንፋል!) ነውና ነገሩ እኛ ሙስሊሞች እስከ መጨረሻው ድረስ እንገፋለን፡፡
ይህ ሁኔታ በዚህ መልኩ እንዲቀጥል መፈለጉ ለማንም እንደማይጠቅም እጅግ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ቢሆንም በአገራችን መልካም ገፅታ ላይ፣ አገራችን በታሪክ አይታው በማታውቀው የልማት እንቅስቃሴ ላይ እና የእድገት ጉዞ ላይ ምንም ዓይነት ሳንካ አይፈጥርም ማለት ሞኝነት ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ያለ መታደል ነው! የአገሪቱ ሕዝብ ግማሽ አካል የሆነው ዜጋ መብት በጥቂቶች ተረግጦ እና ሕዝቡም አኩርፎ የሚፈለገው ውጤት በልማት መለወጥ ከሆነ ተኝቶ ማለም ብቻ ከመሆን አይዘልም፡፡
እኛም ተቃውሟችንን በፅናት ለመቀጠል በአላህ ፈቃድ ቃል እንገባለን፡፡
አላሁ አዕለም

No comments:
Post a Comment