Tuesday, October 23, 2012

ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የአማርኛ ፓምፍሌት እና ኦዲዮ (ድምጽ)



ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የአማርኛ ፓምፍሌት እና ኦዲዮ (ድምጽ) ከታች በተቀመጡት ሊንኮች ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጁትን ፓምፍሎቶችና ድምጾችንም ከቆይታ በኋላ እናደርሳለን፡፡ እነዚህን የተዘጋጁ ፓምፍሌቶች ፕሪንት በማድረግ፣ በፎቶኮፒና በሌሎችም መንገዶች በማባዛት ለሁሉም ማደርስ ይኖርብናል፡፡ ኦዲዮውንም (ድምጹንም) በቀላሉ ወደ ኮምፒዩተራችንና ሞባይላችን ዳውንሎድ በማድረግ በአካባቢያችን ለሚገኙ ሙስሊሞች በተለይም ወደ ገጠር ለሚጓዙ በብሉቱዝ አማካኝነት ማስተላለፍ ይኖርብናል፡፡ ወደ ገጠር የምንጓዝ ሙስሊሞች ከሁሉም በተለየ መልኩ መረጃውን ገጠር ላሉ ወዳጅ ዘመዶች የማስተላለፍ ኋላፊነት አለብን፡፡ (ለኦዲዮው ለአማራጭነት ሁለት ሊንኮችን አስቀምጠናል) የአሌክትሪክ ኋይል ወደሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች የምንጓዝ የሞባይል ባትሪያችንን በመቆጠብ ገጠር ላሉ ሙስሊሞች ሁሉ መረጃውን እናድርስ፡፡

ትግሉ የሁላችንም ነው፡፡ ገጠርና ከተማን አይለይም፡፡ በእድሜ፣ በጾታ፣ በስራ ባህሪ፣ በማህበራዊ ደረጃ፣ ከባህር መለስ እና ከባህር ማዶ ተብሎ አይለይም፡፡ ሙስሊም የተባለን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ ትግሉም የሚጠይቀው የሁላችንንም አስተዋጽኦ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ያነሳናቸውን ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ እስኪመልስልን ድረስ በትግላችን በመጠናከር፣ ጥያቄያችን ላልገባቸው ወገኖች ጥያቄአችንን በማስረዳት፣ ከመንግስት አካላት የሚመጣብንን ግፊት በመቋቋምና ሰላምን መርህ በማድረግ በአላህም ዱዓእ በመታገዝ ወደ ፊት እንጓዝ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!

No comments:

Post a Comment