የሰላም አምባሳደሮቻችን በአፋጣኝ ይፈቱልን!
ኢስላም ‹‹ሰላም›› ከሚለው የአረብኛ ቃል ተመዝዞ የወጣ ሀረግ እንደሆነ ሙስሊም ምሁራን ደጋግመው ይናገራሉ፡፡ እጅግ ትክክልም ናቸው፡፡ ኢስላም የሰላምና የሰላማዊነት ተምሳሌት፣ የፍትህና ፍትሀዊነት ቀንዲል ነበር፤ ነውም፤ ይሆናልም! ይህን መሰረታዊ ባህሪውን በአማኞች ዘንድ ለማስረጽም ከእያንዳንዱ ሶላት በኋላ ‹‹አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ! የሰላምም ምንጭ ነህ! የልቅናና የቸርነት ጌታ ሆይ፤ የተባረክህ ነህ!›› ስንል ጌታችንን እንድናወድስ ያስተምረናል፡፡ የጀነት ሰዎች ሰላምታ ‹‹ሰላም›› የሚለው ቃል መሆኑን በመንገርም ወደሰላም እናይ ዘንድ ያጓጓናል፡፡
ምንም እንኳን ዛሬ ‹‹የሰላም አምባሳደሮቻችን!›› ስንል የመሰከርንላቸው ኮሚቴዎቻችን ‹‹አሸባሪ›› እና ‹‹ሁከት ቀስቃሽ›› ተብለው ዘብጥያ ቢወርዱም ያሳዩን የሰላማዊነት ተምሳሌት ከሚለጠፍባቸው የሃሰት ውንጀላ በላይ ደምቆ የሚታይ፣ ልቆ የሚወጣ እውነታ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እኒህ ለትግሉ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ምርጥ የኢስላም ልጆች በቅድመ ትግሉም ሆነ በድህረ ትግሉ ወቅት ሁሉ ሰላማውያን ነበሩ፡፡ ካሁን ቀደም በነበራቸው ህይወት በህብረተሰባቸው ውስጥ ሰላምና መቻቻልን ለማስፈን፣ አብሮ የመኖር ባህልን ለማዳበር ብዙ ለፍተዋል፡፡ ከውስጣቸው ጥቂት የማይባሉት ሰባክያን የነበሩ መሆናቸውም ይኸንን እውነታ ጎልቶ እንዲወጣ አመቻችቷል፡፡ ዛሬ ቀን ተቀይሮ የኮሚቴያችን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ‹‹አሸባሪ›› ተብሎ ሳይጠረጠር በፊት ብዙ ሺዎችን በሚሰጠው ኢስላማዊ ትምህርት ያቃና መምህር ነበር፡፡ ድንቅ የሰላም ሰው መሆኑን የሚመሰክሩለትን በርካታ የሲዲ እና የመስጊድ ሙሀደራ ዝግጅቶችን አቅርቧል፡፡ ስለሰላም ድንቅ እሳቤ ኢስላምን ወክሎ አብራርቷል - ያ ሳር ቅጠሉ የወደደው ዳኢ! በሚሳተፍባቸው ማህበራዊ ህይወቶች ሁሉ ለሚከሰቱ የሰላም እንከኖች ቀዳሚው የመፍትሄ አባል መሆኑን ወንጃዮቹም ያውቁታል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ደርሶ ልውጥውጥ ያለው መንግስታችን ዛሬ ‹‹ዳኢ ያሲን ኑሩ አሸባሪ ነው ብዬ ጠርጥሬያለሁ›› ብሎ ከፍርግርግ ኋላ አውሎታል፡፡ አስገራሚው እውነታ ግን የምንወደው ዳኢያችን እጅግ በጣፈጠው ምላሱ ስለሰላም የሰበከባቸው በርካታ የሲዲ ሙሀደራዎች በየቦታው ተንሰራፍተዋል፡፡ በትምህርቶቹ የብዙዎችን ደረት በሰላማዊ አስተሳሰብ አስፍቷል፡፡ ቂምና ቁርሾ ከማኅበረሰባዊ ኑሮ መነቀል ያለበት ሰንኮፍ ስለመሆኑ ሰብኳል፡፡ የሙስሊሙን ልብ ገዝቷል - የህዝብ ልብና ፍቅር በሰላም እንጂ በነውጠኝነት የሚገኝ እንዳልሆነ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
ስለ ሰላማዊነት እና መልካም ስነምግባር አንስቶ ከኮሚቴዎቻችን ጋር ‹‹በአሸባሪነት›› ተጠርጥሮ የታሰረውን ኢንጅነር በድሩ ሁሴንን መርሳት ጭራሽ የማይሆን ነገር ነው፡፡ ይህን ዳኢ በአሸባሪነት መፈረጅ ልብ እሺ ብሎ አይቀበለውም፡፡ የታላቁን ነቢይ አዛኝ ሩህሩህነት በየዋህ አንደበቱ ያስተማራቸው፣ ስለነቢዩ ሲያወጋ በሚያለቅሱ አይኖቹ እምባ አጅቦ ያስደመማቸው እልፍ አእላፍት ታዳሚዎች ሰላማዊነቱን ለመመስከር ከበቂ በላይ አይደሉምን? ሽብር እና ነውጠኝነት የተጠናወተው ሰው የሰላምን ታሪክ እንደምን ሲተርክ ይኖራል?
ዛሬ ቀን ተለወጠና የምንወደው የሚዲያ ባለሙያ ሐሰን አሊ ‹‹በአሸባሪነት ተጠርጥሮ›› እስር ቤት ተቆለፈበት! ይገርማል! ይህ ሰው ከማንም በፊት የዶክተር ዛኪርን በርካታ የሰላምና መቻቻል ሲዲዎች በመተርጎም የተሳሳቱ አመለካከቶችን ከህዝብ ላይ ሲያጸዳ የነበረ፣ በነዚሁ ሲዲዎችም አንድ ሙስሊም ከጽንፈኝነትና ከሽብርተኝነት መራቅ እንዳለበት ሲያስተምር የነበረ ሰው ነው፡፡ በአለም ዙሪያ የሰላም ጠበቃ መሆኑ ታውቆለት የተለያዩ አገራት መንግስታት ንግግር እንዲያደርግላቸው በተደጋጋሚ የሚጋብዙትን ምሁር በርካታ ሲዲዎች በመደዳ የተረጎመ ሰው ዛሬ ‹‹በሽብርተኝነት›› የተጠረጠረው በምን ስሌት ይሆን?
ዛሬ ቀን ተለወጠና በነጃሺ ጋዜጣ እና በሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጅነቱ የምናውቀው… የምናደንቀው ጉምቱው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ‹‹በአሸባሪነት ተጠርጥሮ›› ተከረቸመበት! ለረጅም አመታት ፍትሀዊነት እንዲሰፍን፣ መብት እንዲጠበቅ፣ ሰላምም በዘላቂ እና የማይነቃነቅ መሰረት ላይ እንዲያርፍ ተጽእኖን ሁሉ ተቋቁሞ ህዝብና መንግስትን የመከረና የዘከረ፣ ለህዝብ ከአንጀቱ የሰራ ጀግና ከቶ ስለምን ‹‹ሽብር ፈጣሪ›› ተብሎ ይጠረጠራል? በዙሪያችን ዝምብ እንኳ ሲገድሉ ያላየናቸው ጀግኖቻችን በህግ ፊት በድንገት ወደ ‹‹አደገኛ ወንጀለኛነት›› የተቀየሩት የሰላም ምንነት መለኪያ መስፈርቱ በመለወጡ ይሆን?
ዛሬ ቀን ተለወጠና የታሪክ ተመራማሪው፣ እንደአይናችን ብሌን የምንሳሳለት ጋዜጠኛና ጸሀፊ አህመዲን ጀበል ‹‹የሰላም ጸር›› ተሰኝቶ፣ በአሸባሪነት ተጠርጥሮ›› ከብረት በር ጀርባ ተቆልፎበታል! ይህ ጀግና የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ታሪክ ለሆዳቸው ያደሩ ጸሀፍት ከከመሩበት ቆሻሻ ለማጽዳት ከፍተኛ ጥናት ሲያደርግ የነበረና የተሳካለትም ወጣት ነው፡፡ በመጽሀፉ ያለፉ ግንኙነቶቻችንን ችግሩን አክመን፣ ጥንካሬውን አዳብረን እንቀጥል ዘንድ ‹‹ታሪክ የምንማረው ለቂምና ለቁርሾ ሳይሆን ለትምህርት ነው፤ በዳዩም ተበዳዩም አልፈዋልና የመበቃቀል አጀንዳ ቦታ የለውም›› ሲል በብርቱ የሞገተ ነበር፡፡ የመንግስት ማይክራፎን የሆነው ኢቲቪ እንኳ ስለሰላምና መቻቻል ቃለ መጠይቅ አድርጎ አቅርቦት ነበር - ‹‹አሸባሪ›› በመሆን ሳይጠረጠር በፊት!
ዛሬ ቀን ተለወጠና የህግ ባለሙያችን ካሚል ሸምሱ ‹‹አሸባሪ ነው›› በሚል ጥርጣሬ ፖሊስ ጣቢያ ከራረመ! ይህ ወጣት ገና ከጅምሩ ኮሚቴው የሚያደርገው እንቅስቃሴ እግር በእግር ሕግና ሕገ-መንግስቱን የተከተለ እንዲሆን፣ ሰላማዊነትን እንዲጎናጸፍ የማይናቀውን እና ዋነኛውን ሚና ሲወጣ የነበረ ነው - በግል ህይወቱም እጅግ ሰላማዊ ነበር፡፡ ‹‹ሕግን እናክብር›› በማለት የሚታወቅን ሰው ‹‹ሽብርተኛ›› የሚያደርገው ስሌት ከየት እንደሚመነጭ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
ዛሬ ቀን ተለወጠና ዳኢ አህመድ ሙስጠፋም ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል ጥርጣሬ ወህኒ ከወረደ ወራት ተቆጠሩ፡፡ ይህን ለሰው አዛኝ ወጣት በእርግጥም ያውቁታል፡፡ ለአመታት የዝቅተኛ ህብረተሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል በተለያዩ እርዳታ ድርጅቶች ላይ ታች ሲል የኖረ ነው፡፡ በዳኢነቱም ስለሰላም አውርቶ የማይጠግብ ነበር፡፡ የሙስሊም በአላት በደረሱ ቁጥር በኤፍ ኤም ሬዲዮኖች ተጋብዞ ያቀርባቸው የነበሩ የሃይማኖት መቻቻል ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች እስካሁንም በሺዎች ጆሮ ውስጥ ያቃጭላሉ፡፡ ሌላው ሁሉ ቢረሳ ፋና ላይ የቀረቡ ፕሮግራሞቹ ይረሳሉን?
ዛሬ ቀን ተለወጠና ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪም ‹‹ሽብርተኛ ነው›› በሚል ጥርጣሬ ዘብጥያ ወርዷል፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህ ወጣት የሰፈሩን ወጣቶች በማሰባሰብ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመፍታት ሁልጊዜም ፊት ተሰላፊ ነበር፡፡ በየጓዳ ጎድጓዳው ሲደግፏቸው የነበሩ አዛውንትና አረጋውያን፣ ሲረዷቸው የነበሩ ደጋፊ የለሽ ልጅ አሳዳጊዎች ለዚህ ወጣት ‹‹ሽብርተኛ›› አለመሆን ቋሚ ምስክሮች አይደሉምን? የሺዎችን ህይወት የሚለውጥ ሰው የሺዎችን ህይወት ወደሚያፈርስ ኹከት ፈጣሪነት በወራት ውስጥ መሸጋገሩን ሲነግሩን ትንሽ እፍረት አይሰማቸውም ይሆን?
ዛሬ ቀን ተለወጠና የምናከብራቸው ሸህ ሱልጣን ‹‹ሽብርተኛ›› ተሰኝተው ጭለማ ክፍል ተከተቱ፡፡ እኒህ ሰው ያለምንም ጥርጥር ትልቅ የሀገር ሀብት ናቸው - ህይወታቸውን ሙሉ ለሰብአዊ እርዳታ ያለመሳሳት ያዋሉ! የብዙሃንን ህይወት ነክተዋል፤ አሻሽለዋል፡፡ ከሺዎች ትከሻ ላይ ብዙ ሸክሞችን አቅልለዋል፡፡ ዘርና ጎሳ ሳይለዩ፣ ክልልና ጎጥ ሳይመርጡ ያደረጓቸው እርዳታዎች ፋናቸውን ያልተዉበት ክልል ከቶ የታለና? ለዚህ ኦሮሚያ ትመስክር… ለዚህ አማራ ክልል ይመስክር… ለዚህ ደቡብ ክልል ይመስክር… ለዚህ ትግራይ ክልል ትመስክር….! ሁሉም ቢጠየቁ ሸህ ሱልጣን የአገራችን እስላማዊ ሰብአዊ እርዳታ ዋልታና ማገር መሆናቸውን በመሰከሩ! እውነታው ለብዙሃን አለኝታ መሆናቸውን ሲናገር ዛሬ ደግሞ ዋሾ ድምጾች ‹‹እኒህ ሰው የሺዎችን ህይወት ሊቀጥፉ ያሴሩ አሸባሪ ናቸው ብለን ጠርጥረናል›› ሊሉን ዳዳቸው፡፡ ሺዎችን የማዳን እና ‹‹ሺዎችን የመቅጠፍ›› ሁለት የተራራቁ ራእዮች በአንድ ሰው ሰብእና ውስጥ ተስማምተው እንደምን እንደሚኖሩ ዋሾ ድምጾቹ ቢያብራሩልን ምንኛ በወደድን!!!
ዛሬ ቀን ተለወጠና ኡስታዝ ጀማል ያሲን ‹‹የሽብር ተጠርጣሪ›› ተብሎ ተከርቸም መግባቱ አስተዛዛቢነቱ በቀላሉ የማይገለፅ ነው፡፡ የተረጋጋና ለስላሳነት የተሞላበት ግላዊ ስብእናው ከሚሰብከው ሰላማዊነት በዘለለ አገልግሎት በሰጠባቸው መስኮች በሙሉ ከመነሻው እስከመድረሻው በሰላም አየር መካበቡን ስለምናውቅ የወንጃዮቹ በደል ምንኛ የከፋ እንደሆነ አይጠፋንም፡፡
ዛሬ ቀን ተለወጠና ሸህ መከተ ሙሄ ‹‹አሸባሪ›› በሚል ጥርጣሬ ወህኒ እንዲወርዱ ተደርጓል፡፡ ታሪካቸው ግን የሚነግረን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡ እኒህ ትልቅ አሊም በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለአመታት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ መዋቅሩን ለማስተካከል፣ ከመጅሊስ ብልሹ አሰራር የመነጩ የተቋሙን ችግሮች ለመፍታት ብዙ መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ በሙያቸው የሺዎችን የቤተሰብ ችግር አድምጠው ኢስላም ያስቀመጠውን መፍትሄ በመስጠት ማህበራዊ ችግሮችን ፈትተዋል፤ ቤተሰቦችን ከመፍረስ፣ የፈረሱ ትዳሮችንም ከኢ-ፍትሀዊነት ለመጠበቅ ተግተዋል፡፡ በጥቅሉ ለእልፍ አእላፍት ቤተሰቦች የስክነትና የሰላም፣ የፍትህም ሰበብ ነበሩ - ዛሬ ግን ‹‹በሽብርተኝነት›› ወንጀል… ሺህ ቤተሰቦችን ለማፍረስና ለመበጥበጥ ሰበብ በሚሆን የከፋ ወንጀል ‹‹ጠርጥሬያቸዋለሁ›› ተባለ!
የታሰሩብን ዳኢዎች፣ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ሁሉ ለሰላም ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ብንዘረዝር ምንኛ በወደድን! ሁሉም ቢሆን ድንቅ ልጆቻችን ነበሩ! የጋዜጠኛና አርቲስት አቡበከር አለሙን ጽሁፎችና የትርጉም ስራዎች፣ የምንወደውን መምህራችንን ኡስታዝ ባህሩ ኡመርን ጣፋጭ ትምህርቶች፣ የነሸኽ ጣሂርን የበሰለ ምክር፣ የነሷቢር ይርጉን የበሰለ አመራርና ብልሃት፣ የወጣት ሙባረክ አደምን ያለእድሜ የበሰለ ንግግር፣ የነዲኑ አሊን ምርጥ ድራማዎችና የቲቪ ዝግጅቶች ሁሉ ብንዘረዝራቸው ባልጨረስናቸው! ሁሉም ቢሆን ሰላም በዘላቂ የፍትህ መሰረት ላይ እንዲያርፍ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ የነበሩ፣ ለህዝብ ፍቅር ሟቾች ነበሩ - ዛሬ ጆሮዋችን አልገባ ያሉ ድምጾች ‹‹ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች… ኹከት ፈጣሪ ሽብርተኞች በመሆን ጠርጥረናቸዋል›› ቢሉንም!
የምንወዳቸውና የምናከብራቸው ኮሚቴዎቻችን ትግሉ ከተጀመረና ሰዉም ጥያቄያችንን ከዳር አድርሱልን ብሎ በህጋዊ መልኩ (በፔቲሽን) ከወከላቸው በኋላም ቢሆን ሰላማዊነታቸውን አጥብቀው ይዘዋል፡፡ ይህን በሶስት ማስረጃዎች ከፍለን ማየት እንችላለን፡-
1.ከትግሉ መጀመር አንስቶ ጀግኖቻችን ‹‹ጀግና ማለት ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በቁጣ ወቅት ራሱን መቆጣጠር የሚችል ነው›› የሚለውን መርህ መሰረት በማድረግ ስለሰላም አዘውትረው ሲሰብኩ ነበር፡፡ እንቅስቃሴው በምንም አይነት ሁኔታ ሃይልን የመጠቀም አዝማሚያ ማሳየት እንደሌለበት በግልጽና በመድረክ ላይ ህዝቡን አደራ ሲሉ ነበር፡፡
2.ለትግሉ ቃል ገብቶና ቀበቶውን አጥብቆ የተሰለፈውን ህዝብ ብዛት በማየት የመደፋፈር ወይም የስሜታዊነት (ነሻጣ) አዝማሚያ አልታየባቸውም፡፡ በኮሚቴዎቻችን ስር ለመታገል የተሰለፈው ህዝብ የዘመናት መንግስታት ሃይማኖታዊ በደል ያማረረው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው፣ ብልሃትና ብስለት የተዋሃደው እና ድፍረት ልቡን የሞላው ወጣትና ጎልማሳ የማህበረሰብ ክፍል ነው፡፡ ለተወካዮቹ የነበረው ፍቅርም ያዘዙትን ለመፈጸም ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ አድርጎታል፡፡ የተጠራቀመ በደል፣ ድፍረት፣ ብልሃትና ብዛት ያለውን ህዝብ ታዛዥነት ያገኘ መሪ ወደፈለገው ሊመራው ይችላል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ግን በስራቸው ያለው ህዝብ ብዛት ወደስሜታዊነት አልመራቸውም፡፡ የተንሰራፋው የኑሮ ውድነት እና የነጻነት እጦት ያንገበገበውን ሚሊዮን ህዝብ አሰልፈው ፖለቲካዊ ጥያቄ የማንሳት ሙሉ እድል የነበራቸው ቢሆንም ያንን አላደረጉም፤ አላማቸውም አልነበረም፡፡ ሶስቱን መሰረታዊ ጥያቄዎች የይዘትም ሆነ የብዛት ለውጥ ሳያደርጉ በጀመሩበት ሰላማዊ መንገድ ቀጥለዋል፡፡ ልብ ይበሉ! በአንዳንድ የአወሊያ የጁምኣ ስብሰባዎች ከ 800 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን የሚደርስ ህዝብ የሚገኝባቸው ጊዜያቶች ጥቂት አልነበሩም፡፡ የመንግስትን ተደጋጋሚ ዛቻ ከምንም ሳይቆጥር ለህጋዊ ተቃውሞ አደባባይ የዋለውን የመረረው ሙስሊም ማህበረሰብ ይዘው ወደሃይል የመጠቀም ስሜታዊነት ቢገቡ አገሪቱ ውስጥ ቀላል የማይባል ቀውስ ሊፈጠር ይችል ነበር፡፡ እውን ኮሚቴዎቻችን አሁን መንግስት ‹‹ጠረጠርኩ›› እንደሚለን ‹‹አሸባሪዎች›› ከነበሩ ለአንድ ‹‹አሸባሪ›› ከዚህ የበለጠ አገር የመበጥበጥ እድል ከወዴት ሊገኝ ይችል ነበር? ለምንስ በመቶ ሺህ የሚቆጠረውን አወሊያ የተሰበሰበውን ህዝብ ትእዛዝ ሰጥተው አገሪቱን አላበጣበጡም? ይህን ሊመልስልን የሚችል አለን? ለሰላማዊነታቸው ከዚህ የተሻለ ምሳሌ ማግኘት ይቻላልን? መቶ ሺዎችን አንድ ቦታ ሰብስቦ የመምራት እድል አግኝቶ ወደሰላማዊነት የሚጣራ ‹‹አሸባሪ›› እንደምን ሊኖር ይችላል?
3.የኮሚቴዎቻችንን ሰላማዊነት ሊካድ በማይችል ሁኔታ ካረጋገጡት ክስተቶች አንዱ ነገሮች እያመረሩ ሲመጡ እነሱ ግን ያንኑ ሰላማዊነታቸውን አጥብቀው ይዘው መቆየታቸው ነው፡፡ ሀምሌ 6 አወሊያ መስጊድ ውስጥ መንግስት የወሰደው ህገወጥ እርምጃ ወደስሜታዊነት ለመገፋፋት እድል የከፈተ ሆኖ ሳለ ኮሚቴዎቻችን ግን ሕዝቡን በበነጋታው አንዋር መስጊድ ላይ ሰብስበው ሲያረጋጉ፣ ሰላማዊነቱን አጥብቆ እንዲይዝ አደራ ሲሉ ነበር፡፡ ከሁለት ቀናት በኋላ በተደረገው የአንዋር መስጊዱ ታላቅ አገር አቀፍ የሰደቃ ፕሮግራም ላይም ህዝቡን እጅ ለእጅ እንዲያያዝ አድርገው በሰላማዊነት ላይ ቃል አስገብተዋል፡፡ ‹‹እኛ ልንታሰር፣ ልንደበደብ፣ ከዚያም የከፋ ሊደርስብን ይችላል፡፡ እናንተ አደራ በስሜት ተገፍታችሁ የሃይል እርምጃ እንዳትወስዱ!›› ሲሉም ለነገሩ ክብደት ለመስጠት በአላህ ስም ቃል አስገብተዋል፡፡ ይህን በቦታው የነበሩ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን በመስጊዱ ዙሪያ ተኮልኩለው የነበሩ የፖሊስ አባላት ጭምር በአይናቸው በብረቱ አይተዋል፤ ሰምተዋል! ዛሬ ኮሚቴዎቻችንን በእስር ቤት የቆለፉባቸው ‹‹ደህነቶችም›› ቢሆኑ እውነታውን አያጡትም! ‹‹ልታሰር ነውና ለኔ ስትሉ ሙቱልኝ፤ አገር ብጥብጡልኝ›› ሊል ይችል የነበረ የተቃውሞ መሪ ‹‹መንግስት ሊያስረኝ ስለሆነ ምንም ችግር እንዳትፈጥሩ›› ሲል ህዝቡን ቃል ሲያስገባ እያዩ ተመልክተው ‹‹አሸባሪ ነህ›› በሚል ‹‹ጥርጣሬ›› እስር ቤት የሚቆልፉት ልባቸው ምን ቢደነድን ይሆን?
የክቡር ኮሚቴዎቻችን እና ዳኢዎቻችን ሰላማዊነት ከዚህም በላይ በብዙ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ነው፡፡ ያም ቢሆን ግን ሰላማዊነታቸው ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ከመጠርጠርና አራት ወር ከመታሰር አላዳናቸውም፡፡ በነሱ መታሰር ቤተሰቦቻቸው ተጎድተዋል፡፡ አብረዋቸው የታሰሩት ብርቅዬ ዳኢዎቻችን፣ ጋዜጠኞቻችን፣ የአገር ሽማግሌዎቻችን፣ አርቲስቶቻችን እና ሌሎችም የደረሰባቸው እንግልት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በሁኔታው የተፈጠረው የህዝብ ቅያሜም እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል - ኢድ እና ጁምአን በመሳሰሉ አጋጣሚዎች በግልጽ ለአለም እስኪታይ ድረስ! መንግስት ‹‹ካፈርኩ አይመልሰኝ›› በሚል አጓጉል መርህ አሁንም በእኒህ ለአገራችን ስጦታና ተምሳሌት በሆኑ ስብእናዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ ብዙ ችግሮችን መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ እንሞክር፡-
1.እንዲህ በተደጋጋሚና በግልጽ ሰላማዊነትን በሚሰብኩ የመብት ታጋዮች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ለወደፊቱ የሰላምን በር መዝጋቱ አይቀርም፡፡ በሂደት ህዝቡ ‹‹መብቴ የሚከበርልኝ ሃይል ስጠቀም ብቻ ነው›› ወደሚል አቋም እንዳይገለበጥ መንግስት በሃላፊነት ስሜት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ መንግስት እንደግለሰቦች በእልህ እና በመሰል ስሜቶች ከመመራት ይልቅ ወደመብሰል እና ሆደ ሰፊነት መሸጋገር ነው የሚሻለው፡፡ ‹‹ኢህአዴግ እልኸኛ ነው›› ብለው የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር መብዛቱ ለአንድ አገር ለሚያስተዳድር የፖለቲካ ፓርቲ ማእረግ ወይም ሙገሳ አይደለም - በፍጥነት ሊታረም የሚገባው ግለሰባዊ ባህሪ እንጂ! ፖለቲካም ቢሆን ዘላቂ ጥቅም ከግምት የሚገባበት ሂደት እንጂ በእልህና በሌሎች ግለሰባዊ ባህሪዎች የሚመራ ነገር አይደለም፡፡ ‹‹በሃይል ካልሆነ መብቴ አይከበርም›› ብሎ የሚያስብ ህዝብ ደግሞ በአመታት ሂደት ምን አይነት መንገድ እንደሚከተል የአለማችን አብዮት ታሪኮች ይነግሩናል፡፡ ከሞላ ጎደል የኢህአዴግም ታሪክ ቢሆን ለዚህ ምስክር ነው፡፡
2.እንደኮሚቴዎቻችን ባሉ ሰላማዊያን ላይ የሚወሰድ እርምጃ ዴሞክራሲን ይንዳል፡፡ ወደድንም ጠላንም መንግስት ‹‹ዴሞክራሲ መስመሬ ነው›› ብሎ አገሪቱም ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ›› እስከተባለች ድረስ የዴሞክራሲያዊ መብት መጠየቂያ ሂደቶች መታፈን እና የመሪዎቻቸው መታሰር ያለጥርጥር ችግር ነው፡፡ ቢያንስ መንግስት ‹‹ዴሞክራሲን አውጄያለሁ›› ያለ በመሆኑ በግልጽ ዴሞክራሲን ሲያፈርስ መታየቱ ገጽታውን ይሰብረዋል፡፡ ወደተስፋ መቁረጥም ያመራል፡፡
3.የጀግኖቻችን መታሰር ከህዝቡ ሌላ በፖለቲካው መሪዎች ላይም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ጉዳት ያመጣል፡፡ ምክንያቱም በተወሰደው እና ወደፊትም ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ህዝቡ ማዘኑ፣ ልቡ መሰበሩ አይቀርም፡፡ ልቡ የተሰበረ ህዝብ ደግሞ ወደአምላኩ ይዋደቃል፤ ያለቅሳል፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያችን ያለች የአማኞች ምድር ውስጥ ህዝብን ደም የሚያስለቅሱ መሪዎች እንቅልፍ ያገኛሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ ህዝቡ የሚከፋበት መሪ በእንቅልፍ እና እርካታ እጦት ይታመሳል፡፡ በግል ህይወቱ ደስታን ሳያጣጥም የፖለቲካ ሰለባ እንደሆነ ይኖራል፡፡ ከዚያም ባለፈ ‹‹በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም›› እንደሚባለው የሴራ ፖለቲካ ሰለባ ይሆናል፡፡ ትናንት እንደልቡ ሲሆን ቆይቶ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ ሆኖ ሲዋረድ ያየነው ፖለቲከኛ የለምን? ትናንት ሺዎችን አርበድብዶ ዛሬ በተራው መሳለቂያ የሆነስ ስንቱ ነው?
በኮሚቴዎቻችን ላይ የሚወሰድ የክፋት እርምጃ ሌላም ሊፈጥራቸው የሚችሉ ችግሮችን ከግምት በማስገባት መንግስት ወደልቦናው ይመለስ ዘንድ አሁንም ‹‹ድምጻችን ይሰማ! መሪዎቻችን ይፈቱ!›› ስንል ድምጻችንን ማሰማታችን እንቀጥላለን፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!!!

No comments:
Post a Comment