Monday, October 8, 2012

የመንግስትን ምርጫ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባ ውሎ

የመንግስትን ምርጫ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባ ውሎ
የተለያዩ መንግስታት በመርህ ደረጃ ሴኩላር ሆነውም በሃይማኖቶች ላይ ግን ድብቅ እጆች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በኛ ተጨባጭ የታየው ግን መንግስት የሃይማኖት ስራን በብቸኝነት ከባለቤቶቹ ነጥቆ ሲፈነጭ ነው፡፡ ያለማወቅ የሚፈነጭ ደግሞ ሂደቱም ጎርባጣ ፍፃሜውም ውድቀት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ሰዎች ጉዱን እንዳያወጡት በዝግ ሞባይልና ካሜራ ታግዶ የታደሙበት የመንግስት አርቲስቶች ከመድረክ በውርደት የተሸኙበት አሳፋሪ የምርጫ ቲያትርም በመንፈሳውያን ላይ የተሰነዘሩ የክፋት እጆች ወይ ጉም ዘግኖ መመለስ አልያም መቆረጥ እንደሆነ ያረጋገጠ ነበር፡፡ 



በዚህ የማፈሪያ ስራ እንደ መንግስት ምርጫ ካድሬዎች አንድ ለአምስት አደረጃጀት በመፍጠር ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በየቤቱ በመዞር የቦኖ ውሃ እናቋርጥባችኋለን፤ ከቀበሌ ቤት ትወጣላችሁ፤ በቫት እናሰቃያችኋለን፤ የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት አይሰጥም፤ እና መሰል በየትኛውም መስፈርት ለማስፈራሪያነት ሊቀርቡ በማይገባ ጉዳዮች ሰውን እያሸማቀቁ ሲቀሰቅሱ አረፈዱ፡፡ ይህም ሆኖ በጣቢያቸው ውስጥ አስቀድመው ሹመቱን ከሰጧቸው የአህባሽ ቅጥረኞችና አጋፋሪ ካድሬዎች እንዲሁም በጣት የሚቆጠሩ ‹‹ተገዳጅ መራጮች›› ውጪ ዝር የሚል ባለመገኘቱ ጭርታው ሲያሰቃያቸው ተስተውሏል፡፡ ይህ ጉድ በሌላው ህብረተሰብ ሳይጋለጥባቸው በፊት ከዚህ በፊት የምርጫ ካርድ ባትወስዱም ዛሬ መውሰድ ትችላላችሁ እባካችሁ ኑ በሚል ተማፅኖ በበርካታ የወረዳና የቀበሌ ፅ/ቤት ውስጥ ቁርዓን በስፒከር በመክፈት፤ የምግብና የቡና ስነስርአት በማዘጋጀት፤ ከዚህም አልፈው የመስጂድ ማይክራፎንን በመጠቀም ያለወቅቱ የአዛን ጥሪና እባካችሁ ለምርጫ ኑ በሚል በመማፀን፤ ሽማግሌዎችን በመለመን፤ የመምረጥ እድሜ ላይ ያልደረሱትን በመሰብሰብ፤ እድርተኞችን ብር ትቀጣላችሁ በሚል በማስፈራራት፤ ጀናዛ ይዘው የተገኙ ለቀስተኞችን ከነጀናዛቸው ወደቀበሌ በማስገባት ለማስመረጥ ቢጥሩም በተለያዩ ክልሎች በራሳቸው የሃፍረት ማቅ ተከናንበው ሁሉም ጥረታቸው በዜሮ ተባዝቶ ተመልሰዋል፡፡ በዚህ መልኩ ሰው ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከንቱ ህልም እንደሆነ ሲረዱ ለምርጫ ጣቢያው አስቀድመው የተሾሙ ግለሰቦችን አንዳንዶቹ በሌሉበትና ማንም በማያውቃቸው ሁኔታ ስም ዝርዝር በማንበብ ብቻ አፅድቀው ‹እቃቃው አለቀ› አይነት ጨዋታ ‹‹ምርጫው አልቋል›› እያሉ ተመልሰዋል፡፡ ይህን መሰል አሳፋሪ ውሎን ነው እንግዲህ የሚሊዮኖች እንባ ሳይገደው ለናሙናነት በሞላቸው አዳራሾች በመኮፈስ ሰባት ሚሊዮን ሰዎችን ለምርጫ አሳተፍኩ ያለን፡፡ መደበኛ የመንግስት ምርጫ ውጤት እንኳን በዚህ ፍጥነት መዘገብ የሚያስችል አደረጃጀት በሃገራችን አለመኖሩ ይታወቃል፡፡ ሃገር አቀፍ መዋቅርና አለምአቀፍ ድጋፍ ያለው በባለሙያዎችና ጠንካራ የቁስ አቅም በመታገዝ የሚንቀሳቀሰው የምርጫ ቦርድ እንኳን የሃገር አቀፉን ምርጫ ውጤቶች ከመላሃገሪቱ ጣቢያዎች ሰብስቦ ለማቅረብ ቀናት ይፈጁበታል፡፡ የመንግጅሊስን ምርጫ ግን በተጀመረ በጥቂት ሰአታት ከተመዘገቡት 7 ሚሊየን መራጮች 95 በመቶ መርጠዋል የሚል ወሬ ነዝተው ሃገራችን በገጠር መንገድ በቅጡ ሳትተሳሰር በዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች ምቾት የተጥለቀለች የሚያስመስል ፈጣን የመረጃ ፍሰት ባለቤት አድርገዋት አረፉ፡፡ ያሳፍራል፡፡
ከዚህ ዘገባቸው አስቀድሞ ግን ለዚህ የማይናድ ህዝባዊ አንድነት ላይ ያደረሰን የመረጃ ትስስራችን ዋልታ የሆኑት ምንጮቻችን እንደዘገቡልን በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር በሙሉ ገጠር ቀበሌዎች ምርጫውን ህዝቡ ሙሉ በሙሉ አስቁመውታል፤ በጅማ፤ በሰበታ፤ በሱሉልታ፤ በዱከም፤ በሞጆ በአርሲና ባሌ፤ እንዲሁም በበርካታ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች ምርጫው ሙሉ ለሙሉ ከሽፏል፡፡ በደቡብ ክልል በከፋ፤ ቦንጋ፤ ዲላ፤ ወልቂጤና ዙሪያዋ፤ ጉራጌ ዞን ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ወረዳዎች የምርጫውን ከንቱነት በተግባር አሳይተዋል፡፡ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ቢቸና፤ ቻግኒ፤ በደሴ፤ በገርባ፤ በደጋን፤ በከሚሴ፤ እና ሌሎች በቦታ ውስንነት ባልገለፅናቸው ከተሞች የምርጫው ውሎ ከሃገራችን አስቀያሚ ታሪኮች ሆኖ ተመዝግቦ አልፏል፡፡ አፋር፤ ጂጂጋ፤ ሃረርና ድሬዳዋ በፍላጎታችን ካልኖርን ሃገራችሁ አይደለምና ውጡ በሉን በሚያስብል አስለቃሽ ትዕይንት የተሞላ ውሎ አልፏል፡፡ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች ምርጫ እንዲህ ነው እንዴ የሚያስብል የለቅሶ ቤት ድባባ ተስተውሏል፡፡ የመጣበትን ታሪክ የዘነጋው መንግስታችን ግን የህዝብን ዳኝነት ንቆ የህዝብን አይን በካሜራው አይን ለማስተባበል ሲንከላወስ ለተመለከተ ታዛቢ ለካስ የመንግስት መደበኛ ምርጫም በዚህ መልኩ የተካሄደ ነው የሚል ታሪካዊ ጥያቄ እንዲያነሳ አስገድዶታል፡፡

1 comment:

  1. asafari ena tarikawi ken alefe mechem yaltederege beyetegnawem sereat malet yechalal. yohanes, menelik, tewodros, haileselase ena mengestu enkuan endih ayenet asafari getseta aleneberachewem menem enkuan ye muslim telat bihonu ahun yalen mengest eko achefenu enamognachehu honeben manen yezo guzo mehonum yastezazebal gen lemen?? ene kalnorku yalechewen aheya yasmeselal yewedefit wudketu bitayew eko haimanoten tegen bemareg becha meerabun alem mastegat ayechalem bichalem selam sinor new lemegezatem yemichalew be enchechu mekechet alebet silu yeneberut eko yemecheresha kalachew hone lemen anemarem????

    ReplyDelete