Friday, December 21, 2012

ፍትህ የናፈቀው የደሴ ሙስሊም ዛሬም በድጋሚ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ


ፍትህ የናፈቀው የደሴ ሙስሊም ዛሬም በድጋሚ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ!!

አዎ! ፍትህ ናፍቆናል!! በሃገራችን ፍትህ ተጠምተናል!! የኮሚቴዎቻችንን ስቃይ ማየት አልቻልንም!! ይህ ነበር የዛሬው ድምፅ፡፡ ዛሬ ደሴ ሙስሊም ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት ነበር፤ በኮሚቴዎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሁሉንም ልብ ሰብሯል፡፡ ለህዝብ ሲሉ ተሰቃይተዋል፣ ሙስሊሙ ሲሉ ጊዜያቸውን ሰውተዋል፣ ለዲናቸው ብለው ህይወታቸውን ለግሰዋል፤ ውድ ኮሚቴዎቻችን፡፡

ዛሬም የደሴ ሙስሊም የነሱ ስቃይ ምን ያህል እንደተሰማው አሳይቷል፣ በኮሚቴዎቻችን ላይ የሚፈፀመውን ግፍ አውግዟል፡፡ በዛሬው ደማቅ ተቃውሞ ላይ ኮሚቴዎቻችን ለሙስሊሙ ከምንም በላይ እንደሆኑ ድምፃችንን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡
“ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!” ፣ “በሀገራችን ሰላም አጣን!” ፣ “ፍትህ ናፈቀን” ፣ “መንግስት የለም ወይ?” በዛሬው ደማቅ ተቃውሞ ላይ የተሰሙት መፈክሮች ነበሩ፡፡

የደሴ ህዝብ ዛሬ ኮሚቴዎቻችን ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፅሙትን የሽፍታ ጥርቅሞች መቼም ይሁን እንደሚፋረዳቸው አሳውቋል፡፡ የዛሬው ደማቅ ተቃውሞም በሰላም ተጠናቋል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ ከማንኛችንም ልብ ውስጥ የሚወጣ አይደለም!! ግፈኞቹንም በህግ እንፋረዳለን!!

ድል ለኢትዮጵያ ሙሊሞች!
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment