ፍትህ የናፈቃቸው ጥሪዎች ዛሬም በሐበሻ ምድር ተስተጋቡ!
አመቱን ሙሉ ሲስተጋባ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገ መንግስታዊ መብት የማስከበር ትግል ዛሬም የአገሪቱን አራት ክልልች በተቃውሞ አድምቆ ዋለ፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሐረር ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተመረጡ መስጊዶች እጅግ በደመቀ ስነስርአት የተተገበረው ተቃውሞ ዛሬም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሷቸውን የሃይማኖት ጥያቄዎች ሳያስመልሱ እና በግፍ የታሰሩ መሪዎቻቸውን ነጻ ሳያወጡ ወደኋላ እንደማይሉ ለሚመለከታቸው አካላት ያለጥርጥር ያረጋገጠ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡
በደሴ ከተማ በተካሄደው ታላቅ ተቃውሞ የደሴ አፋፍ ላይ የምትገኘው የሸዋበር መስጊድ በሺዎች ተሞልታ የነበረ ሲሆን ከጁምአ ስግደት በኋላ በደሴ ፋኖዎች የተባበረ ድምጽ ተንጣለች፡፡ ‹‹በአገራችን ሰላም አጣን! ፍትሕ ናፈቀን! ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!›› ሲሉም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማስተጋባት፣ ወረቀቶችንም በማውለብለብ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
የረዥም ኢስላማዊ ታሪክ ባለቤት በሆነችው በምስራቋ የሐረር ከተማ በኢማን መስጊድ የተካሄደው ተቃውሞም እንዲሁ በሰላም ተጠናቅቋል፡፡ የህዝብን ድምጽ በመስማትና ከስህተቱ በመማር ፋንታ ያሻውን ብቻ እያደረገ የሚገኘው መንግስት ተቃውሞው ገና ከመጀመሩ መሳሪያ እስካፍንጫቸው በታጠቁ ፖሊሶችና ወታደሮች መስጊዱን በመክበብ ሰላማዊውን ሙስሊም ህብረተሰብ ለማስፈራራት እና ለመተንኮስ ቢሞክርም ሙስሊሙ ተረጋገቶ በደቂቃዎች ውስጥ ተቃውሞውን አጠናቅቆ በሰላም ሊበተን ችሏል፡፡ ከተቃውሞው በኋላ የተወሰኑ ሙስሊሞች እንደተለመደው ታስረዋል፡፡ ሰላም እና ሰላማዊነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ለእስር በሚያበቃባት አገራችን ምን እየተካሄደ እንደሆነ አሁንም ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡
በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ነጃሺ መስጊድና በደቡብ ክልል በምትገኘው ወልቂጤ ከተማ ረቢእ መስጊድ ታላላቅ ተቃውሞዎች ተደርገው ውለዋል፡፡ በሁለቱም ተቃውሞዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የከተሞቹ ሙስሊሞች ወጣት አዛውንት፣ ሴት ወንድ ሳይሉ የጋራ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ያነሳውን ጥያቄ በሙሉ የሚጋሩ መሆኑን፣ ኮሚቴዎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ በአስገምጋሚ ድምጻቸው እና በአስደማሚ አንድነታቸው አሳይተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹ በፍጹም ሰላም ተጠናቅቀውም ህዝበ ሙስሊሙ ወደየቤቱ ተመልሷል፡፡ በአዲስ አበባ ደረጃ ቀድሞ በተቀመጠው መርሐ ግብር ምንም አይነት ተቃውሞ እንደማይደረግ በመገለጹ ምንም አይነት ተቃውሞ አልተደረገም፡፡
ዛሬም ‹‹አላሁ አክበር!›› እንላለን! አልሐምዱሊላህ አለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ እስካሁን ድረስ ሳይፈታና ሳይገታ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ መስዋእትነት እየከፈለ ላቀረባቸው ጥያቄዎች እና በሂደቱ ግፍ ለተፈጸመባቸው ኮሚቴዎቹ ያለውን ታማኝነት በተደጋጋሚ ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ‹‹ህዝበ ሙስሊሙ ካሁን አሁን ተሰላችቶ ተቃውሞውን ይተዋል›› በሚል አጉል ተስፋ በደሉን እያራዘሙ የሚገኙት የመንግስት አካላት ግን ተቃውሞው እየተሟሟቀ እንጂ እየተዳፈነ እንደማይሄድ መረዳት ተስኗቸው ባሉበት እየረገጡ ናቸው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ በበኩሉ ቁርጠኝነቱ ከቀን ወደቀን፣ ከሳምንት ወደሳምንት እየጨመረ መሄዱን፣ የሚፈጸምበት ማንኛውም በደልም ትግሉን ለመቀጠል ተጨማሪ ምክንያት እንደሚሆነው፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ከአላህ እዝነት እና ድል ተስፋ ሊቆርጥ እንደማይችልም ጭምር በተደጋጋሚ እያረጋገጠ ነው፡፡
(በዚህ አጋጣሚ የትግላችን እድሜ አንድ አመት የመሙላቱን አጋጣሚ ምክንያት በማድረግ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ እያሰባሰብን የምንገኘው አስተያየት እና ግምገማ መስጫ ጊዜ የሚያበቃው በነገው ምሽት በመሆኑ እስካሁን አስተያየታችሁን ያላደረሳችሁን እስከነገ ምሽት ድረስ ኢንቦክስ (Message) እንድታደርጉልን በአላህ ስም እንጠይቃለን!)
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment