Tuesday, February 5, 2013

ETV mistakenly airs unedited interrogation video of Abubeker Ahmed | Feb...

እኛ ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ መንግስት ግን ዛሬም ስለ ሽብር ይናገራል
ኢቴቪና ብሔራዊ ፌዝ
‹‹ፊልሙ›› ላነሳቸው ሃሳቦች ምላሽ የሚሰጥ የድምጽ ማብራሪያ ነገ እንለቃለን
ዛሬ የመሪዎቻችንን ጉዳይ በሚያየው አራተኛ ወንጀል ችሎት እግድ ተሰጥቶበት የነበረው ‹‹ፊልም›› በሕግ ወጥ መንገድ በኢቴቪ ተላልፏል፡፡ ‹‹ፊልሙ›› እንደለመደው ላለፈው አንድ አመት መንግስት ሲያደረግ የነበረውን የሙስሊሙን ማህበረሰብ ሰላማዊ ትግል እና ተመራጭ የኮሚቴ አባላትን በሽብርተኝነት እና አክራሪነት የመወንጀል አባዜ በስፋት ሲያራምድ ነበር፡፡ ‹‹ፊልሙ›› ደጋግሞ የሙስሊሙን ማኅብረሰብ ጥያቄና የትግሉን መሪዎች ሽብርተኞች፣ የብዛ ሃይማኖቶችና ብሄሮች በሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚሹ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም ለማናጋት ተልእኮ የተሰጣቸው፣ ለዚህም ከውጪ ስልጠናዎችን ወስደዋል እና ሌሎችንም ሀረጎች በመጠቀም ሲወነጅላቸው አምሽቷል፡፡ የህግ የበላይነት ምሶሶ የሚባለው የተጠርጣሪዎችን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆኖ የመገመት (Presumption of innocence) መብትም ዛሬ በግልጽ ሲጣስ ተመልክተናል፡፡ ‹‹ተጠርጣሪ አሸባሪ›› የሚል የለበጣ ሀረግ በመጠቀም የመሪዎቻችን ሕገ መንግስታዊ፤ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20/3 ‹‹በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር፣ በምስክርነት እንዲቀርቡም ያለመገደድ መብት አላቸው፡፡›› የሚለውን አንቀጽ በመጣስ ጣቢያው ለሕግ ተገዢ እንዳልሆነ ምስክርነቱን በአደባባይ ሰጥቷል፡፡ የፍ/ቤቱንም እግድ እንዲሁ ያለ ከልካይ ጥሷል፡፡ በ‹‹ፊልሙ›› ከመንግስት በማይጠበቅ መልኩ ካሜራ በድብቅ በማስቀመጥ የሚፈልጉትን ቃላት መልቀም ያሳፍራል፡፡ ሰዎች የማይሹትን ነገር በግድ እንዲናዘዙ ማስገድ የህግ የበላይነትን ይንዳል፡፡ በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ንግግሮችን እየቆረጡና እየቀጠሉ (ያውም በቀሽም ቆርጦ ቀጣዮች) የተለየ መልእክት ለማስተላለፍ መሞከርም ከአንድ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ማየት በጣም ያሳዝነናል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ትላንትም ዛሬም ነገም የምናምናቸው ስለምናምናቸውም ፈርመን ውክልና የሰጠናቸው በመሆኑ መቼም ለእነሱ ያለን ታማኝነትና ክብር አይሸረሸርም፡፡ እንደዛሬው በመሪዎቻችን ላይ የሚሰራ ተራ ፕሮፖጋንዳ ፍጻሜው ውደቀት እንጂ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
በ‹‹ፊልሙ›› ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸው በስፋት ሲራገብ ነበር፤ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአገራችን በነጻነትና በተድላ እየኖርንም እንደሆነ ተነግሮናል:: ከዛሬ አንድ አመት በፊት በአወሊያ እና በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ሙስሊሞች የቀረቡ ሦስት መሰረታዊ የእምነት ጥያቄዎችን በተወካዮቻችን አማካኝነት ለመንግስት አቅርበን ነበር፡፡ ሶስቱም ጥያቄዎች ዛሬም ምላሽ አላገኙም፡፡ የመጅሊስ አመራርን ምርጫ መንግስት በሚፈልገው መልኩ ብቻ ለማካሄድ ስለ ፈለገ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከምርጫው ራሱን አገለለ፡፡ ምርጫውም ቅርጫ ሆኖ በጥቂት ግለሰቦች አስገቢ አስወጪነት ተካሄደ፡፡ በዚህ አይነት ድራማም ሙስሊሙ ሌላ መሪ በእጅ አዙር በመንግስት ተሾመለት፡፡ የአህባሽ አስተሳሰብ በግድ አይጫንብን ሲባል የተነሳው ሁለተኛ ጥያቄም ምላሽ ሊያገኝ ቀርቶ መንግስታዊ እስልምናን እንከተላለን ለሚሉ ጥቂት ካድሬ ኢማሞ አሳልፎ በመስጠት ሙስሊሙ ከራሱ መስጊድ ተገፍቶ እየወጣ ይገኛል፡፡ ባለፈው ወር ብቻ በመላዋ አገሪቱ ከ12 በላይ የመስጊድ ኢማሞችና የሰላት ጥሪ አድራጊዎች ከስራቸው በሀይል ተነስተው መንግስታዊ ኢማሞች በፖሊስ በመታገዝ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ አወሊያ ተቋም ከመጅሊስ እጅ ወጥቶ በነጻ ቦርድ ይተዳደር የሚለው ጥያቄ ዛሬም ምላሽ ሳያገኝ አሁንም ተቋሙ በመጅሊስ አመራር እጅ ውስጥ ይገኛል፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ መንግስት ምጸት ያወራል፡፡ ጥያቄውን መልሻለሁ ብሎ ሕዝብ ላይ ብሄራዊ ፌዝ ያሰማል፡፡
‹‹ፊልሙ›› ሙስሊሞች ዛሬ በኢትዮጵያ ነጻነታቸው ተጠብቆ እየኖሩ ነው ብሎ ነግሮናል፡፡ እስቲ እውነት ነው የሚል እጁን ያውጣ፡፡ ግን የዚህ ሀሳብ ምጸቱ የሚጀምረው የሙስሊሙን ህብረተሰብ መሪዎች በእስር እና ቶርች እያሰቃየ በሚያናዝ ፊልም ላይ መገለጹ ነው፡፡ ዛሬ በመላው አገሪቱ ሙስሊም መሆን ወንጀል ነው የተባለ ይመስል፤ ሙስሊሞች ለሰላት መስጊድ ሄደው በሰላም የማይመለሱበት ሁኔታ እያየን፣ የመብት ጥያቄን ያቀረቡ ሺዎች ተደብድበው ከፊሎችም ተገድለው እየተመለከትን፤ ሙስሊሞች በነጻነት እየኖሩ ነው ተብለናል፡፡ ሙስሊም ሴቶች መከናነቢያ ማድረግ ባልተከለከሉበት አገር የምን ጭቆና?ም ተብለን ተጠይቀናል፡፡ ዛሬ ይህ ‹‹ፊልም›› እየታየ ባለበት ሰዓት ግን ጥቂት በማይባሉ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች በመከናነቢያቸው ምክንያት፣ በእምነታቸው እና ጸሎት በማድረሳቸው ሳቢያ እየተገፉ እየወጡ ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞች ደህንነት እየተሰማቸው አይደለም፡፡ የሃይማኖት ነጻነት እንደቀልድ መገፈፈ፣ ወደ እስር ቤትም መወርወር ሙስሊሙ ላይ አይንን ከድኖ ከመግለጥ የበለጠ ቀላል ኖኗል፡፡ ግን ‹‹ፊልሙ›› ነጻነት አለ ይለናል፡፡
በአንዋር መስጊድ እና በሌሎችም አካባቢዎች ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› እያለ መፈክር የሚያሰማን ሰላማዊ ህዝብ እና የሶማሊያ ታጣቂዎችን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ብሎ ማቅረብም መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ ያለውን ንቀት ትንሽም ለመደበቅ አለመፈለጉን በግልጽ አሳይቶናል፡፡ ይህ በምንም መልኩ በዝምታ የሚታለፍ አይደለም፡፡ የዛሬው የኢቴቪና የመንግስት ድርጊት እጅግ አሳዝኖናል፤ አሳፍሮናል፡፡ እንደ ሕዝብ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የምንጠብቃቸው በርካታ በጎ ነገሮች ቢኖሩም በዚህ አይነት አሳፋሪ ስራ ውስጥ መንግስት ተጠምዶ ማየታችን ስለ አገራችን ዕጣ ፈንታ የምር እንድንጨነቅ ያደርገናል፡፡ የኛ ትግል ግን ነገም ከነገ ወዲያም ሚሊዮኖችን ከኋላው አስከትሎ ገና ይቀጥላል፡፡ ትግላችን በወሬ እና በሀሜት የሚፈታ ቢሆን ኖሮ ድሮ እናየው ነበር፡፡ የኛ ትግል ግን በሰላማዊነትና በሕዝቦች የአብሮነት መተሳሰብና የሃይማኖት ቀናኢነት ላይ የተገነባ በመሆኑ እስከጥያቄያችን መመለስ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ጥያቄዎቻችን ከማንኛውም የተለየ የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዱ፣ የሌሎችን እምነት እና መብት የማይጻረሩ ንጹሕ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥይቄዎች ናቸው፡፡ ኮሚቴዎቻችንም ሆነ ጥያቄዎቻችንን በየትኛውም መንገድ በመጠምዘዝ ከህዝብ ለማስጣል የሚደረገው ጥረት መቼም አይሳካም፡፡
በመጨረሻም ‹‹ፊልሙ›› ጠምዝዞና አወላግዶ የተለየ ውዥንብር ሊፈጥር ያደረገው ሙከራ፤ ሕዝቡ በሌላ አቅጣጫ መንግስት ሙስሊሙ ላይ እና ኮሚቴዎቹ ላይ የሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ምን ያህል መሰረተ ቢስ እንደሆነ የተረዳበት ነው ብለን እንገምታለን፡፡ በተለይም የሌላ እምነት ተከታዮች በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይም ሆነ በሰላማዊ እንቅስቃሴው ላይ የተለየ አሉታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የተደረገው ሙከራ እንደማይሳካ እንገምታለን፡፡ እኛም በነገው እለት ‹‹ፊልሙ›› ላነሳቸው ሃሳቦች ምላሽ የሚሰጥ የድምጽ ማብራሪያ ይዘን እንድምንቀርብ ቃል እንገባለን፡፡ በተለያዩ መንገዶችም ለሁሉም ለማዳረስ ዝግጅትና ጥረት እናድርግ፡፡


አላሁ አክበር

ታግዷል የተባለው ፊልም እንዳይታገድ የእጅ አዙር ድራማ ተሰራበት

ፍትህ ሆይ የት ነው ያለሽው?

ዛሬ ምሽት ኢቴቪ ያስተላልፈዋል ተብሎ የነበረውና ዛሬ በፍርድ ቤት እንዳይታይ እግድ የተጣለበት ፊልም በአስተዳደራዊ እርምጃ በሚመስል መልኩ በከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ ደብዳቤው ኢቴቪ መዝገብ ቤት ተፈርሞ ከገባ በኋላ ተስቦ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ጠበቆች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ቢሮ ቢሄዱም፤ ውሳኔውን ልናነበው እንፈልጋለን የሚል ምክንያት በመስጠት ጥቂት መስመሮች ያሉትን ደብዳቤ ለሰአታት ቢሮዋቸው ውስጥ ካስቀሩ በኋላ የስራ መውጫ ሰአት ሲደርስ ነገ ተመለሱ ዛሬ አላለቀም የሚል ምክንያት ሰጥተው ነገ ተመለሱ የሚል ምላሽ ለጠበቆቹ መስጠታቸው ታውቋል፡፡ ጠበቆች ፕሬዚዳንቱን ለማናገር ጥረት ቢያደርጉም ፕሬዝዳንቱ ማናገር አልችልም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ የፍ/ቤትን ውሳኔ በቀጭን የስልክ መስመር መሻር የሚቻልበት አሰራር በአገሪቱ ውስጥ ባይኖርም የፕሬዚዳንቱ ድርጊት ይኸው ነበር፡፡ ውሳኔው ዛሬ ተፈጻሚ መሆን ያለበት ዛሬ መሆኑ እየታወቀ በእጅ ጥምዘዛ የተፈጸመው ውሳኔውን ተፈጻሚ ያለማድረግ ድርጊት ስለ አገሪቱ የፍትህ ስርአት ፍትሃዊነት እና ታማኝነት ደጋግመን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ በዚህ ጉዳይም የህግ ባለሞያ አስተያየት ይዘን ለመቅረብ ጥረት እናደርጋለን፡፡

‹‹ፊልሙ›› እንደሚገመተው ዛሬ የመታየት እድሉ ሰፊ ነው - ፍ/ቤቱ እንዳይታይ ውሳኔ ቢያሳልፍበትም፡፡ ሆኖም የፍ/ቤቱም ቀዳሚው ውሳኔ መሪዎቻችን እየተካሄደባቸው ካለው አሳዛኝ የምስክርነት የችሎት ድራማ ጋር ተያይዞ ሙሉ እምነት የሚጣልበት አልነበረም፡፡ አንድ ሊታወቅ የሚገባው ቁም ነገር የ‹‹ፊልሙ›› መታየት ወይም አለመታየት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ትግል ላይም ሆነ በመሪዎቻችን ላይ የሚፈጥረው አንዳችም እክል እንደሌለ ነው፡፡ በተቃራኒው የ‹‹ፊልሙ›› መታየት ከሚጥሰው ሕግ በተለይም ዛሬ የተሰጠውን የፍ/ቤት ውሳኔና የተጠርጣሪዎችን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆኖ የመገመት (Presumption of innocence) መሰረታዊ የህግ መርህ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ትግል የበለጠ የሚያፋፍም መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከፊልሙ መታየት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ስሜታዊነት ሳይንጸባረቅበት የተለመደ ስክነቱን በማሳየት ቀጣይ ሂደቶችን እንዲጠብቅ እንጠይቃለን፡፡

አላሁ አክበር

Breaking News

Sunday, February 3, 2013

አገር በተቀነባበረ የሀሰት ድራማ አትመራም!


አገር በተቀነባበረ የሀሰት ድራማ አትመራም!

እውነትን ገድዬ ሀሰትን ላነግስ ነው - ኢ.ቴ.ቪ ማክሰኞ ጠብቁኝ ብሏል

ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሁለቱን ደማቅ ኢዶች ጨምሮ ባደረጋቸው የአደባባይ ተቃውሞዎች ሁሉ ኢ.ቴ.ቪን ሌባ ሲለው ነበር፡፡

ወትሮም እውነት መናገር የማይሆንለት ኢ.ቴ.ቪ ዛሬ ምሽት ላይ ለወራት ለመቀጣጠል ሲደክምበት የነበረውን ሰላማዊ እንቅስቃሴያችንና ኮሚቴዎወቻችን ላይ ጥላሸት ለመቀባት ያለመ የሀሰት ‹‹ዶኩመንተ›› ፊልም ማክሰኞ ምሽት እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡ ይኸው ፊልም ከተሰራ ወራቶች ያለፉት ቢሆንም በተለያየ ጊዜ ባለስልጣኖች ጋር ለግምገማ ቀርቦ አሳማኝ ባለመሆኑ ተሻሽሎ እንዲፈበረክ ሲደረግ ከርሟል፡፡ ከተለቀቀው ማስታወቂያ መረዳት እንደሚቻለው ፊልሙ በዋነኛነት ሙስሊም ያልሆነው የህብረተሰብ ክፍል የሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ጥያቄ እና እንቅስቃሴ በስጋት እንዲያየውና ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ወደ ግጭት እንዲያመራ ማድረግ ነው፡፡ ይህንኑ እኩይ ስራ መንግስት ከዚህ ቀደም በተለያየ መንገድ ሞክሮት የከሸፈበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በርካታ ክርስቲያን ወገኖቻችንም ይህንኑ ዓላማ ተረድተው በተለያየ ጊዜ መንግስት ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን በማፋጀት ዕድሜውን ለማራዘም የሚያደርገውን ሙከራ አውግዘዋል፡፡ በተግባርም ክርስቲያኑ ህብረተሰብ ለትግሉ ድጋፉን በተለያየ መልኩ ሲሠጥ ቆይቷል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትም በዚህ የክርስቲያኑ ህብረተሰብ ድጋፍ በመናደድ የምሬት መልሶች ለሚዲያዎች ሲሰጡም ጭምር ተሰምቷል፡፡

ሙስሊም ህብረተሰብ መሰረታዊ የእምነት ነጻነት መብቱን ለማስከበር ባለፈው ዓመት ያደረገው ትግል ሰላማዊ ለመሆኑና የትኛውንም የህብረተሰባችንን ክፍል ስጋት ውስጥ የማይከት ለመሆኑ የተለያዩ የውጪ አገር የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ካወጡት መግለጫ በላይ ‹‹ሊያርዱህ ተነስተውብሃል›› እያሉ ሲያስፈራሩት የነበረው ክርስቲያኑ ህብረተሰብ በየሰደቃ ፕሮግራሞቹ ላይ ያሳያቸው ትብብሮች ማረጋገጫ ናቸው፡፡ ኢ.ቴ.ቪ ዛሬ ይዞት ብቅ ያለው የተቀነባበር ድራማም ይህን በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መሃከል የተፈጠረውን መተማመን ለመናድ የተተኮሰ የመጨረሻ ጥይት ይመስላል፡፡ ኮሚቴዎቻችንና ዳዒዎቻችን በማዕከላዊ እስር ቤት ባሳለፏቸው የግፍ ወራት በአሰቃቂ እና ተከታታይ ቶርቾች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሁኔታ ውስጥ ሁነው በግድ እንዲናገሩ ያደረጉዋቸውንና በድብቅ ካሜራዎች የቀረጿቸውን ንግግሮች ቆርጦ በመቀጠልና በማቀናበር ‹‹ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ነበር የምንንቀሳቀሰው›› ብለዋል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞክር የሚመስለው ይኸው ፊልም ከዚህ ቀደም ሲወሩ የነበሩትን የተቀበረ መሳሪያ አወጣን ድራማዎችንም እንዳካተተ ማስታወቂያው ያሳያል፡፡ እነዚህ ሁሉ ኢ.ቴ.ቪ ከዚህ ቀደም በህብረተሰቡ ውስጥ ካገኘው አሉታዊ ስም ጋር ተዳምሮ የማንንም ቀልብ ሊገዛ እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡

መንግስት የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተቃውሞን ለማዳፈን ከዛቻና ማስፈራሪያ ጀምሮ ቃታ እስከመሳብ የደረሱ እርምጃዎች ቢወስድም ጥያቄችን ፍትሃዊና እንደ ረፋድ ፀሃይ ውልል ያለ በመሆኑ አድማሱን እያሰፋ ከአንድ ዓመት በላይ በጽናት መቀጠል ችሏል፡፡ አሁንም ቢሆን ተቃውሟችን ሊፈታ የሚችለው በተቀነባበረ የሃሰት ድራማ ሳይሆን ጥያቄዎቻችን ፍትሃዊ መልስ ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡ ጥያቄው የመረጥናቸው ኮሚቴዎች ብቻ ሳይሆን የመላ ህብረተሰባችን ለመሆኑ ተቃውሟችን ኮሚቴዎቻችን ከታሰሩ በኋላም ከ 6 ወራት በላይ አንዳችም መቀዝቀዝ ሳያሳይ መቀጠሉ ብቻ በቂ መረጃ ነው፡፡ ህዝብን ለማታለል እና አንዱን ኢትዮጵያዊ የሌላው ጠላት አድርጎ ለመሳል ቀን ከሌሊት የሚባዝኑ መሰሪ አዕምሮዎችና ሃብቶች የህዝብን ችግር ለመፍታት ቢውሉ አገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ግን ለዚህ አልታደልንም፡፡

አመት የቆየውን ድምጻችን ይሰማም ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ይህን የሃሰት ድራማ ከንቱነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የተለያዩ የድምጽ ዘገባዎች ይዛ እንደምተቀርብ እያስታወቀች ሁላችንም ለቤተሰባችን፣ ለመድ አዝማዳችን እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮቻችን ጎረቤቶቻችንና ወዳጆቻችን እውነታውን በማስረዳት እንድንበረታ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ እውነትን ማንም አይጥላትም፡፡ አገር በተቀነባበረ የሀሰት ድራማ አትመራም፡፡

አላሁ አክበር!

Friday, February 1, 2013

በስኬት የተጠናቀቀ ወር!

በስኬት የተጠናቀቀ ወር!
አመት የሞላውን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግል ለማሰብ ለአንድ ወር ሙሉ ስናካሂድ የነበረው መርሀ ግብር በአላህ ፍቃድ በስኬት ተጠናቋል። ሚሊዮኖች በአላማ ተዋህደው፣ ጥረታቸውን አዋድደው በጋራ ለፍተውበታል። በእርግጥም ውጤታማ ወር ነበር። በሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ በአገር ውስጥ ከ 35 በላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ትእይንቶች ተደርገዋል፤ በአማካይ ቢሰላ በቀን ከአንድ በላይ ተቃውሞ ተደርጓል እንደማለት ያክል ነው፡፡ በውጭ አገራት ደግሞ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአህጉረ አፍሪካ በርካታ የተቃውሞ ትእይንቶች እና ሴሚናሮች የተካሄዱ ሲሆን በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ ሚዲያዎች ለአመት መታሰቢያ ዝግጅቱ ሰፊ የዘገባ ሽፋን ሰጥተውታል።
በዚህ የመታሰቢያ ተቃውሟችን ምን ጥቅም ለማግኘት እንደቻልን የተወሰነ ትንተና መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ይታየናል። ምክንያቱም የስራችንን ውጤት ለመመዘን እና ድክመቶቻችንን ነቅሶ በማውጣት ለማሻሻል ይረዳናልና ነው። በመሆኑም ወር ከፈጀው ትግል የሰበሰብናቸውን ፋይዳዎች ጠቀስ ጠቀስ ለማድረግ እንሞክራለን።

Hijab for a day: Non-Muslim women who try the headscarf


Sarah Rhodes, with and without her hijab
Jess Rhodes, with and without her hijab
World Hijab Day calls on non-Muslim women to try out life under the traditional head scarf. Can it lead to more religious tolerance and understanding?
"Because I'm not very skilled I'm wearing what you could call a one-piece hijab - you just pull it over your head. But I've discovered the scope is endless. There are all sorts of options."
So says Jess Rhodes, 21, a student from Norwich in the UK. She had always wanted to try a headscarf but, as a non-Muslim, didn't think it an option. So, when given the opportunity by a friend to try wearing the scarf, she took it.
"She assured me that I didn't need to be Muslim, that it was just about modesty, although obviously linked to Islam, so I thought, 'why not?'"
Rhodes is one of hundreds of non-Muslims who will be wearing the headscarf as part of the first annual World Hijab Day on 1 February.
Read More