Thursday, January 3, 2013

ጁመዓ የማይቀርበት ታሪካዊ ቀጠሮ አለን!

ጁመዓ የማይቀርበት ታሪካዊ ቀጠሮ አለን!

የኢስላም አስተምህሮ ከኛ ይደርስ ዘንድ የታለፈባቸው ወሳኝ መንገዶች እኛም እንድንጓዝባቸው የአላህ ፍላጎት መሆኑን እነሆ ተጨባጩ ያስረዳል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን ዲናቸውን በመጠበቅ የሰሩት አኩሪ ገድል በእኛም እንዲደገም ወቅቱ እየተጣራ ነው፡፡ የወቅቱንም ጥሪ በተግባር የሚመልሱ ሚሊዮን ቢላሎችና ሚሊዮን ሱመያዎችን በእርግጥም አይተናል፡፡ የቢላልና የሱመያን መንገድ ለመረጃ ፍጆታነት ሳይሆን ለህይወት መርህነት የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያኖችን አይናችን አይቷል፡፡ ታሪካችንም ዘግቦት እያለፈ ነው፡፡ ይህን በውስጣችን እያለ ሳናጤነው የኖርነው ትልቅ የአላህ ኒዕማን በገሃድ እንዲታይ ያደረገው ደግሞ ከአመታት በፊት በመንግስት ተመርጦልን ከ365 ቀናት በፊት ልንጠመቀው የተዘጋጀልን ‹‹ሙስሊሞችን ዳግም የማስለም›› ሃገራዊ ዘመቻ ነው፡፡ ይህንኑ ዘመቻ የሚመራው ደግሞ የመንግስትን ትከሻ ተደግፎ በመጅሊስ ስም የተሰባሰበው የካድሬዎች ቡድን ነው፡፡ የነዚህ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ ሁለት ሃይሎች የመጀመሪያ ሰለባ የነበረው ደግሞ ከነስያሜያቸው አፄ እና ወታደራዊ በመባል የሚታወቁ ሁለት መንግስታትን አሳልፎ ዴሞክራሲያዊ በሚል ስም በተሰየመው መንግስት ላይ የደረሰው የአወሊያ ተቋም ነው፡፡ የ365 ቀናት ጉዟችንም ከነዚህ ሶስት ነጥቦች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሶስቱ ነጥቦችም የነገሩ መነሻ እንዲሆኑ ያስቻለው ትልቁ ነጥብ ግን መንግስት ሃገር የሚተዳደርበትን ህገመንግስት በማንአለብኝነት በአደባባይ ደግሞ ደጋግሞ መጣሱ ነው፡፡

የትግላችን መነሾና የጥያቄዎቻችን እንድምታ

የትግላችን መነሾና የጥያቄዎቻችን እንድምታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡-
በአወሊያ ሙስሊም ሚሽን ት/ት ተማሪዎች የተጀመረውና ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ያደገው ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የኃይማኖት ነፃነት ጥያቄ እና የመንግስት ጣልቃ ገብነትና የመብት ጥሰት ተቃውሞ እነሆ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ በዚህም አመታዊ ጉዞው ውስጥ ከደርዘን በላይ ሙስሊሞች ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፤ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ 29 ሙስሊሞች ታስረዋል፤ በሽብርተኝነትም ተከሰዋል፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ሙስሊሞች በመላ ሀገሪቱ እስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ፤ ብዙ ምዕመናን አካላቸውን አጥተዋል፤ ብዙ ሙስሊሞች የሚወዷት ሀገራቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ትተው ተሰደዋል፤ ብዙ የሙስሊም ልማት ድርጅቶች፣ የገንዘብ፣ ኢኮኖሚና የንግድ ተቋማት፣ የየቲሞች መረዳጃና ማሳደጊያ ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት ተዘግተዋል፣ የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል፣ ገንዘባቸው ተወርሷል፤ የሙስሊም ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይመለሱ ተከርችመዋል፡፡ የእምነት ማዕከላትና መድረሳዎች ተዘግተዋል፤ መስጂዶች ፈርሰዋል፤ የግዳጅ ሰልፎች ተስተውለዋል፤ ሰላማዊ ትግሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር ሀገሪቱ ሰፍኗል፤ወዘተ...
የዚህ ምልከታ ዓላማም የትግሉን ጉዞ ሂደት ማለትም መነሻ ምክንያቶች፣ ስኬቶች፣ ድክመቶች፣ ስጋቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን ለመጠቆም ያለመ ነው፡፡

Uploaded videos (playlist)

Tuesday, January 1, 2013

Global Council for justice in Toronto Dec 30-2012

Global Council for justice in Toronto Dec 30-2012



የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ትግል የጀመሩበትን 1ኛ አመት ቶሮንቶ በሚገኘው ሳላህዲን እስላማዊ ማእከል ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን አከበሩ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አለማቀፍ ምክርቤታ የቶሮንቶ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው በዚህ አንደኛ አመት መታሰቢያ በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል።
በአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ፤ ከጀርመን ተጉዘው የመጡትና፤ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ሙስሊም ሀጂ መሀመድ አህመድ ልጅ፤ አቶ መሀመድ ሀሰን ስለሙስሊሞች ትግል ውጣውረድ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን እንዳቀደ የሚያሳይ ሰነድ ከእጃቸው እንደገባ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፤ ላለፉት 12 ወራት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርገው አፈና በዚህ ምስጢራዊ ሰነድ ውስጥ እንደተካተተ ተናግረዋል።
አተ መሀመድ ሀሰን የሙስሊሞችን የአንድ አመት ትግል ሂደት የሚያሳዩና ለትግሉ የተደረገውን አለማቀፍ ድጋፍ የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎችን ለተሰብሳቢዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ ተሰብሳቢዎቹ አቶ መሀመድ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ የአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የህገመንግስቱ አንቀጽ 27 እንዲከበር ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፤ “ድምጻችን ይሰማ፤ ሰላም አጣን ባገራችን፤ መንግስት የለም ወይ” የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል።
በዝግጅቱ ላይ በቶሮንቶ የሚገኙ አገር ወዳድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንም ተገኝተዋል።

Aschekuay አስቸኳይ የተላለፈ የመስጅዶቻችን እናድን ጥሪ

ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ - መስጊድ ነጠቃ!


ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ - መስጊድ ነጠቃ!

ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መሠረታዊ የእምነት ነፃነት መብታችን ተጥሶ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጣን ድፍን አንድ አመት ሞላን፡፡ ይህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን አንድ ላይ ያስተሳሰረ ተቃውሞ መነሻውም ሆነ መድረሻው የመንግስት በሐይማኖታችን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች በይፋ መጣሳቸው ነው፡፡ አሕባሽ የተሰኘውን አንጃ ከሊባኖስ በማስመጣት በሙስሊም ዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን የተደረገው ሙከራ ለዚህ የከፋ ድርጊት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡

አሕባሽ በከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ታጅቦ በመንግስት ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሊፈፅማቸው ያሰባቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ነበሩት፡፡ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአህባሽ የግዳጅ ጠመቃ ላይ በወጣው ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በአህባሽ የመጅሊስ አስተዳደር ጥብቅ ቁጥጥር ስር እንዲውል፣ ማንኛውም የመስጂድ ኢማምም ሆነ ዳዒ ይህንን የአሕባሽን ስልጠና እንዲሳተፍ፣ የአሕባሽን ስልጠና ያልወሰደ ማንኛውም ኢማም ማሰገድ እንደማይችልና ስልጠናውን ያልወሰደ ኢማም ቦታም ስልጠናውን በወሰደ ሌላ ሰው እንደሚተካ፣ የአህባሽን ስልጠና ያልወሰደ እና ከአህባሽ የመጅሊሱ አስተዳደር ሰርተፊኬት ያልተሰጠው ማንኛውም ዳዒ በየትኛውም መድረክ የኃይማኖት ትምህርት እንዳይሰጥ፣ በሕብረተሰቡ ጉልበት፣ ሀብትና ጥረት የተገነቡ ማንኛውም ኢስላማዊ ተቋማት ለአሕባሽ እንዲሰጡ… አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡