Friday, November 30, 2012

በመሪዎቻችን ላይ የተመሰረተው ህገ ወጥ ክስ ህዝብን የማሸበር አይነተኛ መገለጫ ነው!!

በመሪዎቻችን ላይ የተመሰረተው ህገ ወጥ ክስ ህዝብን የማሸበር አይነተኛ መገለጫ ነው!!

እነሆ በሀይማኖታችን ላይ የተፈፀሙብንን የመብት ጥሰቶች በግላጭ ወጥተን ‹‹የፍትህ ያለህ›› ስንል 11 የተቃውሞ ወራት አለፉ፡፡ በእዚህ ሁሉ ግዚያት የሙስሊሙ ህብረተሰብ እጅግ አስደማሚ የሰላማዊ ትግልን ባህል በአንድ በኩል በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ሰርፆ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን በሌላ በኩል መንግስት በተከተለው እጅግ የተወላገደ አረዳድ የወሰዳቸው ሀላፊነት የጎደለው እርምጃዎች ከህዝብ ልብ ከነ አካቴው እንዲወጣ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ህዳር 21 የጀርመን ሬዲዩ የዘገበው ዘገባ ሰለ ኮሚቴዎቻችን



የአቃቤ ሕግን የመቃወሚያ ምላሽ ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍ/ቤት ለሚቀጥለው ሳምንት ኅዳር 27 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የችሎቱን ውሎ ቆየት ብለን እናቀርባለን፡፡ በአካባቢው የምንገኝ ሁሉ መሪዎቻችን ጊቢውን ሲለቁ እኛም ወደየአካባቢያችን እንበተናለን፡፡

 ድምፃችን ይሰማ


ታሳሪዎቹ ከመንግስት ጋር በአንድ ጠረፔዛ ተቀምጠው ሲወያዩ የነበሩ ናቸው

“ታሳሪዎቹ ከመንግስት ጋር በአንድ ጠረፔዛ ተቀምጠው ሲወያዩ የነበሩ ናቸው” አቶ ተማም አባ ቡልጉ የኮሚቴዎቹ ዋና ጠበቃ ትላንት ማክሰኞ በወጣችው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ላይ የሰጡት ሙሉ ቃለ መጠይቅ፡፡
ኢትዮ -ምህዳር :- ሃሙስ ህዳር 13\2005 የኢትዮፕያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የጊዜ ቀጠሮ ነበራቸው የችሎቱ ውሎ እንዴት ነበር ?
ተማም አባ ቡልጉ :- በእለቱ ደንበኞቻችን ላይ የቀረበው ክስ ተነቧል፡፡ 23 ገፅ ክስ ነው፡፡ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ የመጀመሪያው የፍርድ ቤት ቀነ ቀጠሮ ክሱና ማስረጃ ተብሎ የቀረበው ሰነድ ብዙ ስለነበር በአግባቡ ለይተን እንድንመጣ 19 ቀን ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቶን ስለነበር እሱን ለይተን የክስ መቃወሚያ በንባብ አቀረብን፡፡ ዐቃቤ ህግ የመቃወሚያ መቃወሚያ ለማቅረብ ለመጪው አርብ ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቶናል፡፡

Wednesday, November 28, 2012

አገር በሀሰተኛ የሰልፍ ድራማ አትመራም፡፡



ዛሬ በገርባ ከተማ መንግስት የግዳጅ ሰልፍ ማስወጣቱ ተሰማ


በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በገርባ ከተማ መንግስት የአካባቢውን ህዝብ በማስገደድ ዛሬ ሰልፍ ሲያስወጣ ውሏል፡፡ በሰልፉ ላይ ህዝቡ እንዲሳተፍ የአካባቢው ሹማምንትና ካድሬዎች ማስፈራሪያ የታከለባቸው ከፍተኛ የቤት ለቤት ቅስቀሳዎች ሲያካሄዱ የከረሙ ቢሆንም፤ መንግስት የሰልፈኛው ቁጥር ጥቂት ይሆናል በሚል ሥጋት ሰልፉ የሚካሄድበትን ቀን የከተማዋ የገበያ ቀን እንዲሆን በማድረግ፤ ለገበያ የወጣውን ህዝብ በማስገደድ ወደ ሰልፉ እንዲጓዝ አድርጓል፡፡ መንግስት ለሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እንዲመቸው በማድረግ ህዝቡን ‹‹አክራሪነትን እንቃወማለን፣ በሃይማኖት ሽፋን አድርገው የግል የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን እንቃወማለን፣ መንግስት በመላ ሃገሪቱ አክራሪነትን እና ሽብርተኝነትን ለማጥፋት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን፣ በከተማችን መንግስት አክራሪዎች ላይ እየወሰደው እርምጃ ተገቢ ነው፣ የጀመርነው ልማት በአክራሪዎች አይደናቀፍም›› የሚሉ እና በከተማው አስተዳደር የተዘጋጁ መፈክሮችን በእጁ እንዲይዝና በተደጋጋሚም በድምጹ እንዲያሰማ ሲያስገድዱት ውለዋል፡፡

Monday, November 26, 2012

በመሪዎቻችን ላይ የተመሰረተው ህገ ወጥ ክስ ህዝብን የማሸበር አይነተኛ መገለጫ ነው!!


በመሪዎቻችን ላይ የተመሰረተው ህገ ወጥ ክስ ህዝብን የማሸበር አይነተኛ መገለጫ ነው!!

እነሆ በሀይማኖታችን ላይ የተፈፀሙብንን የመብት ጥሰቶች በግላጭ ወጥተን ‹‹የፍትህ ያለህ›› ስንል 11 የተቃውሞ ወራት አለፉ፡፡ በእዚህ ሁሉ ግዚያት የሙስሊሙ ህብረተሰብ እጅግ አስደማሚ የሰላማዊ ትግልን ባህል በአንድ በኩል በሁሉም ህብረተሰብ ዘንድ ሰርፆ እንዲገባ ያስቻለ ሲሆን በሌላ በኩል መንግስት በተከተለው እጅግ የተወላገደ አረዳድ የወሰዳቸው ሀላፊነት የጎደለው እርምጃዎች ከህዝብ ልብ ከነ አካቴው እንዲወጣ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

Sunday, November 25, 2012

አባይና የኢትዩጲያ ሙስሊም

አባይና የኢትዩጲያ ሙስሊም

(በኢትዮ-አልሀበሺ)
መቼም የአባ ጉዳይ የኢትዩጲያና የተፋሰሱ ሀገራት የልብ ትርታ መሆን ከጀመረ ዘመናት አልፈዋል፡፡ የአባይ ግድብ ጉዳይ ደግሞ ትርታውን በይዘትም በፍጥነትም አሙቆታል፡፡ የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉ የዘርፉ ምሁራን ሠላማዊ የመሠለው የአባይ ግድብ ግንባታ ሂደት እንደሚታሠበው አልያም እንዲታሠብ እንደተፈለገው ፍፁም ሠላማዊ እንዳልሆነ መግለፅ ጀምረዋል፡፡ ከባቢውም ከአደጋ አልፀዳም፤ እንደውም የቁርሾ እና በጎሪጥ የመተያየት ጉም ማንዣበብ ስለመጀመሩ አንዳንድ ምልክቶች እየተስተዋሉ እንደሆነ አሁን አሁን መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዩጲያን ፖለቲካና ወቅታዊ የሙስሊሞችን ጉዳይ ካሠብነው በላይ ሠፋ ባለ መልኩ የቃኘው የቀድሞ የኢህአዴግ አባል አብደላህ አደም ተኪ ዝርዝር ፅሁፍም በተወሠነ መልኩ ከመጋረጃው ጀርባ ያሉ ድብቅ ተልዕኮዎችን ዳሷል፡፡ የመለስ ኢትዩጲያ (እዚህ ላይ እኛ በሀገርነቷ የምንኮራባት፤ እትብታችንን የቀበርንባት እና ልንዋደቅላት ተፈጥሮአዊ ቃልኪዳን የገባንላት ውዷ ኢትዩጲያችን ሳትሆን፡ የእግር እሳት ሆና ዕምነታችሁን ቀይሩ እስከማለት የዘመተችብንን ኢትዩጲያ ለመግባባት ያክል “የመለስ ኢትዩጲያ” ለማለት መርጫለሁ፡፡) አህባሽን ለማጥመቅ ስትሠናዳ እና በህዝብ የተተፋውን የኤልያስ REDMAN መጅሊስ ለህዝብ ያሠቡ በማስመሠል እጅግ በተጠና መልኩ ማንነታቸው የማይታወቅ፤ ሲያዩአቸው ግን እስላማዊ ቁመና ያላቸው የሚመስሉ አህባሽ አመራሮችን ከያሉበት ለቅመው በሲስተም ሲያሰርጉ፡ ቀጣይ ጥንስሶችንም በአህመዲን አብዱላሂ ያልበሠለ ካቢኔ እንጭጭ አዕምሮ ሊታሰብ ከሚችለው በላይ በተጠና አኳኋን አላህ እስካጋለጠው ድረስ ውስጥ ውስጡን ማስፈፀም የጀመሩበት አካሄድ እንደሚታሠበው ከአንድ እና ሁለት ሠው ውሳኔ የዘለለ ውስብስብ የፖለቲካ ሴራ ነበር፡፡