Tuesday, January 29, 2013

የሐሰት ምስክርነቱ አሁንም ቀጥሏል!


የሐሰት ምስክርነቱ አሁንም ቀጥሏል!

በአቃቤ ህግ እና በዳኛ መካከል ለውጥ ጨርሶ ጠፍቷል!

ድምጻችንን ያሰሙልን ዘንድ መርጠን የላክናቸው መሪዎቻችን እና አጋሮቻቸው ከረጅም ጊዜ የእስር ቤት ቆይታና ድብደባ በኋላ የተመሰረተባቸው ኢ-ፍትሀዊ ክስ በእርግጥም ፍትህ የተጓደለበት መሆኑን ካሁኑ እያረጋገጥን ነው፡፡ ገና የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ አንስቶ ብዙ መድልዎ ሲካሄድ እንደቆየ ሁላችንም እናስታውሳለን፡፡ ክሱ ኢ-ህገመንግስታዊ ይዘት የነበረውና የህግ አተረጓጎም ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መተላለፍ ሲገባው ተከሳሾች እንዲከላከሉ የተደረገ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ይህም ሳያንስ መሪዎቻችንን በሞራል ከሚደግፋቸው ህዝብ አይን ለማራቅ የክሱ ቦታ ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት አቅራቢያ ተዛውሯል፡፡ ይህም ግን አልበቃቸውም፡፡ መሪዎቻችንን ለመክሰስ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው ብቸኛው ነገር የሐሰት ምስክርነት ብቻ መሆኑን በመገመት በማእከላዊ የምርመራ ጣቢያ የሀሰት ምስክሮች በፕሮጀክተር የታገዘ ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡት እኒህ የሀሰት ምስክሮች ይህንን ከባድ ወንጀል ለመስራት የተስማሙት ያላዩትንና ያልሰሙትን፣ በጭራሽ ያልተፈጸሙ ክስተቶችን ሁሉ እንዳዩና እንደሰሙ አድርገው ለመመስከር ነው፡፡ እያደረጉትም ይገኛሉ፡፡

(Must Watch) Best Nasheed " USTAZZEE" አዲሱ ነሺዳ ፡ ኡስታዜ

Thursday, January 24, 2013

የመጅሊሱ ቁማርተኞች (ክፍል አንድ)


የመጅሊሱ ቁማርተኞች (ክፍል አንድ)
ሰሞኑን እዚህ ቦታ ልገልፀው በማልፈልገው ቤተሰባዊ ጉዳይ (ለደህንነቴ ስል ነው የማልገልፀው)፣ ለሳምንት ያህል ከአዲስ አበባ ራቅ ወዳለች ከተማ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ወደዚህች ከተማ የወሰደኝ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ሁሌም የዲኔ ጉዳይ ያሳስበኛልና ስለሙስሊሙ ወቅታዊ እንቅስቃሴ በዚህች ከተማ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ ጉጉት ነበረኝና በምችለው አቅም ለማወቅ ጥረት አደርግ ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ እኔና ሌሎች 3 የቅርብ ዘመዶች ያረፍንበት ቤት አንዱ ጎረቤት ሰውዬ በዛው አካባቢ የሚገኝ አንድ መስጂድ ኢማም ናቸው፡፡ ኢማሙ ያሳረፈን ግለሰብ አባት ናቸው፡፡ ካለኝ ልምድ የትም ቦታ ብሄድ የአካባቢውን ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከማጥናት ውጭ ስለራሴ መግለፅ ብዙም ፍላጎት የለኝምና በዛች ቤት ውስጥ ከወሰደኝ ጉዳይ ውጭ ስለምንም ነገር ትንፍሽም አላልኩም፡፡ ወደዛች ከተማ የሄድኩበት ጉዳይ ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ሲቀረኝ ግን ድንገት ካስጠጉኝ ሰዎች ጋር የመወያየት እድል ገጠመኝ፡፡ ወቅቱም የነቢያችን (ሰዐወ)መውሊድ ሊከበር ሳምንት ያህል ጊዜ ቀርቶታልና ወሬው ስለ በአሉ ሆነ፡፡
ኢማሙ ወደኔ እያዩ ፡- “ለምን መውሊድን ከኛ ዘንድ አክብረህ አትመለስም?” ጠየቁኝ፡፡ አስተያየታቸው የቆቅ ነው፡፡ በአይናቸው አይኔን ሰርስረው ለመግባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ከሁኔታቸው ስረዳ ማንነቴንም ለማወቅ የፈለጉ ይመስላሉ፡፡ እድሜያቸው ወደ 60ዎቹ ገደማ ይሆናሉ፡፡ ስለኔ ለማወቅ ጭንቅላታቸውን ክፉኛ እያስጨነቁት እንደሆነ ከሁኔታቸው ተረዳሁ፡፡ከተቃዋሚዎቹ ወገን ይሆን ወይስ ከየትኞቹ ይሆን ? የሚል ጉጉት ይታይባቸወል፡፡ ሳቅ ብዬ ዝም አልኩ፡፡ አባት የሚላቀቁ አይነት አይደሉም፡፡ ደግመው ጠየቁኝ፡፡

Tuesday, January 22, 2013

south africa Ethio Muslim S.Africa show their solidarity to the DimTsachin Yisema movement

አዲስ አበባ ሬድዮ ቢላል ጥር 14/2005 Jan 22, 2013



በሐረር በአረፋ በዓል ወቅት የተያዙ ሙስሊሞች እስካሁን ፍትህ አለማግኘታቸው ጠቆሙ
አዲስ አበባ ሬድዮ ቢላል ጥር 14/2005

በሐረር ከታሰሩ አራት ወራትን ያስቆጠሩት ሙስሊም ወጣቶች እስካሁን ፍትህ ሳያገኙ እየተስተጓጎሉ እንደሚገኙ  ተጠቆመ፡፡ ጥቆማውን ያደረሱን የሐረር ነዋሪዎች እንደገለፁት ለወራት ጉዳያቸውን በሐረር ፍርድ ቤት ቢከታተሉም ያለምንም ፍትህ በእስራት ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል  ፡፡
ታስረው የሚገኙት ሰባት ሙስሊሞች በትላንትናው እለትም ፍርድ ቤት ቀርበው ለፊታችን ጥር 20 2005 ቀጠሮ ተይዞላቸዋል ፡፡
ለቀጠሮ ዋነኛ ምክንያት የመንግስት አቃቢ ህግ መረጃ አላጠናከርኩም በማለቱ እንደሆነ ፍርድ ቤት የተገኙት ነዋሪዎች ለሬድዮ ቢላል አስረድተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በሐረር ከሁለት ሳምንት በፊት የአካባቢው ህዝበ ሙስሊም አንደኛ ዓመት የህዝበ ሙሰሊም ተቃውሞ በተካሄደበት ወቅት ተቃውሞውን መርታችኋል ተብለው በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት 21 ሙስሊም ወጣቶች በዛሬው ዕለት ፈርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
-----------------------------------------------
መፍትሄ ያጡት የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆናቸውን ገለፁ
አዲስ አበባ ሬድዮ ቢላል ጥር 14/2005
ለረጅም ጊዜ መፍትሔ ሲጠይቁ የነበሩት የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለትምህርት ቤት አስተዳደር የመስገጃ ቦታ ይዘጋጅልን ፣የጀምዐ ሰላት ይፈቀድልን ፣ የሂጃብ እና የኒቃም ጉዳይ ላይ የወጣው የመተዳደሪያ ደንብ ይስተካከል ብለው ቢጠይቁም ምላሽ ሰጪ አካል አጥተው ዩኚቨርስቲውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል፡፡
እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል በመሰብሰብ እና በተወካዮቻቸው አማካኝነት ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎች እንደገለፁት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ  በተካያሄደው ስብሰባ ወቅት የቀረበው ህግ እና ደንብ ሙስሊም ተማሪዎች ክፉኛ እንደሚበድል  መጥቀሳቸውን አስታውሰዋል ፡፡
በዛሬው ዕለት ቁጥራቸው ከ300 የሚበልጡ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንደወጡ ጠቅሰዋል ፡፡
በባህር ዳር አራቱም ካምፓሶች የሚገኙ ሙስሊሞች መልቀቃቸውን መንግስት እና የሚመለከተው አካል ዝምታን መምረጣቸው ከበስተጀርባው ምን ዓይነት መልዕክት እንዳለው ለመረዳት እንደቻሉ ጠቅሰዋል፡፡
በመጨረሻም እንደተማሪዎቹ ገለፃ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰው ያለው በደል በመላው ሃገሪቱ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ሳይዘምት መቆም እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
------------------------------------------
በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ማውገዛቸው ተገለፀ
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች የመስገጃ ቦታና የጀመዐ ሰላት መከልከል እንዲሁም ኒቃምና ጅልባብ መልበስ  መከልከል ተከትሎ በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ጉዳዩን በመቃወም ዱዐ በማድረግና ፆም በመፆም ማሳለፋቸውን ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በባህርዳር ዩኚቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎች ሰሚ ማጣት እንዳሳሰባቸውና ይህንንም  ጉዳይ ፒቲሽን በማሰማሰባሰብ ለዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ማስገባታቸውን ምላሹንም በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ለሬዲዮ ቢላል ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም የጂጂጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ምግብ አንመገብም በማለት ፆማቸውን ያፈጠሩት በአካባቢው ከሚገኝ አንድ መስጂድ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡  

Saturday, January 19, 2013

Radio Bilal Jan 19,2013 የእለተ ቅዳሜ የራዲዮ ቢላል ስርጭት Jan 19 , 2013

Radio Bilal Jan 19,2013 የእለተ ቅዳሜ የራዲዮ ቢላል ስርጭት Jan 19 , 2013
ዳውንሎድ ለማድረግ ይሄን ይክፈቱ በብሉትዝ በማስተላለፍ ኢስለማዊ ግዴታዎን ይወጡ፤
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
1-> http://goo.gl/wYUzG

 
= 2-> http://goo.gl/6A7Q5
 
3-> http://goo.gl/0a4Wf
 
4-> http://goo.gl/rILWt
 
= 5-> http://goo.gl/ZtG2O
 

ኦሮምኛ ስርጭት(Afan Oromo)
1-> http://goo.gl/rJzsh
 
= 2-> http://goo.gl/EFVKS
 
= 3-> http://goo.gl/qnz9c
 
= 4-> http://goo.gl/v4kPJ
 

Radio Bilal has Customized Its Services For Mobile Users, As well. Thus, The Mobile-Based Listeners Can Download On The Cell Phone And Share via BLUETOOTH daily Radio Bilal programs

Friday, January 18, 2013

የኢህአዲግን ከንቱ ፕሮፖጋንዳ ባዶ ያስቀረ የቪኦኤ ዘገባ

Bemelawu Ethiopia Yetederegewu teqawumo mulu Video 18-1-2012

Radio Bilal Jan 18,2013

Radio Bilal Jan 18,2013 የእለተ አርብ የራዲዮ ቢላል  ስርጭት
ዳውንሎድ ለማድረግ ይሄን ይክፈቱ በብሉትዝ በማስተላለፍ ኢስለማዊ ግዴታዎን ይወጡ፤
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
= http://goo.gl/C2lz1 =
= http://goo.gl/XgTyZ =
= http://goo.gl/RHlMC =
= http://goo.gl/SWrPk =
ኦሮምኛ ስርጭት(Afan Oromo)
http://goo.gl/Xvwft =
http://goo.gl/lCC1R =
http://goo.gl/xPa5t =
Radio Bilal has Customized Its Services For Mobile Users, As well. Thus, The Mobile-Based Listeners Can Download On The Cell Phone And Share via BLUETOOTH daily programs

በአዲስ አበባ የህዝበ ሙስሊም ተቃውሞ በአንጋፋው ኑር መስጂድ ተከያሄደ

 በአዲስ አበባ የህዝበ ሙስሊም ተቃውሞ በአንጋፋው ኑር መስጂድ ተከያሄደ


JEGNEWU YA JIMMA MUSLIM DEMSTE ZARW KALELA KEN BATALEYA





በለቅሶና በዱአ የታጀበው ታላቁ አገር አቀፍ የጁሙዓ ተቃውሞ!!!

‹‹አማኞች አንዱ ለአንዱ ልክ ግድግዳ ላይ እንደተደረደሩ ጡቦች ናቸው፤ አንደኛው ሌላውን ያጠናክረዋል!›› (ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ)

አላሁ አክበር! የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድነት ዛሬም ፍንክች የማይል ጠንካራ ግንብ መሆኑን አስመስክሮ ዋለ! መውሊድን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም እርስ በርስ ሙስሊሙን ለመከፋፈል እና ለማጣላት ያሰበው መንግጅሊስ ተንኮል ዛሬም በድጋሚ ፉርሽ ሆነ! በረዥሙ ትግላችን ያሳለፍናቸው በርካታ ጁሙአዎች በደመቀ ስነ ስርአት እየተከናወኑ ያለፉ ቢሆንም ጠለቅ ያለ ስሜት እና አንድነት የሚስተዋልባቸውና ከትውስታ እስከመጨረሻው የማይፋቁ ጁሙአዎች ደግሞ ከሌሎቹ ለየት ብለው ተንጸባርቀው ያልፋሉ፡፡ ትዝታቸውን ለረዥም ጊዜ ይጥላሉ፡፡ የዛሬዋ ጁሙአ ከመሰል ታዋሽ ጁሙአዎች አንዷ ነበረች፡፡

መንፈሳዊነት ልቆ የታየበት ጁምዓ!


በለቅሶና በዱአ የታጀበው ታላቁ አገር አቀፍ የጁሙዓ ተቃውሞ!!!

‹‹አማኞች አንዱ ለአንዱ ልክ ግድግዳ ላይ እንደተደረደሩ ጡቦች ናቸው፤ አንደኛው ሌላውን ያጠናክረዋል!›› (ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ)

አላሁ አክበር! የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድነት ዛሬም ፍንክች የማይል ጠንካራ ግንብ መሆኑን አስመስክሮ ዋለ! መውሊድን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም እርስ በርስ ሙስሊሙን ለመከፋፈል እና ለማጣላት ያሰበው መንግጅሊስ ተንኮል ዛሬም በድጋሚ ፉርሽ ሆነ! በረዥሙ ትግላችን ያሳለፍናቸው በርካታ ጁሙአዎች በደመቀ ስነ ስርአት እየተከናወኑ ያለፉ ቢሆንም ጠለቅ ያለ ስሜት እና አንድነት የሚስተዋልባቸውና ከትውስታ እስከመጨረሻው የማይፋቁ ጁሙአዎች ደግሞ ከሌሎቹ ለየት ብለው ተንጸባርቀው ያልፋሉ፡፡ ትዝታቸውን ለረዥም ጊዜ ይጥላሉ፡፡ የዛሬዋ ጁሙአ ከመሰል ታዋሽ ጁሙአዎች አንዷ ነበረች፡፡

ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት መንግስትንና አጫፋሪዎቹን ያንበረከከ በአይነቱ ልዩ የሆነ ተቃውሞ በደሴ!!

ዛሬ በደሴ ከተማ ሙስሊሙ መንግስት ኢማም የመደበባቸውን መስጂዶች ባዶ በማድረግና ሌሎች መስጂድ ሂዶ በመስገድ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ የመንግስት ቅጥረኛ የሆኑት ኢማሞች ከጥቂት ግለሰቦች በስተቀር በመስጂዱ ውስጥ ብቻቸውን ሰግደዋል፡፡ ሌሎች መስጂዶችም የሚሰግድባቸው ጠፍቶ ተቆልፈው እንደዋሉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዛሬ ፔፕሲ፣ አሬራ፣ ሜጠሮ ጎሮ እና ጦለሃ መስጂድ እጅግ በጣም ብዙ ሰው የተገኘባቸው ሲሆን አረብ ገንዳ፣ ሸዋበር፣ ፉርቃን እና ዳዌ መስጂዶች በሰው እጦት ባዷቸውን ውለዋል፡፡ በዳዌ ሜዳ(አራዶ) መስጂድ እነዚህ የመንግስት ሹሞች በቅሬ ሁሉም ሰው መስጂድ እንዲመጣ ትእዛዝ በማስተላለፍ ቢያስፈራሩም መስጂዱ ውስጥ ከአስር ያልበለጠ ሰው ብቻ እንደተገኘ ታውቋል፡፡ ፉርቃን መስጂድ እና ቄራ መስጂድም እንደዚሁ ከአምስት ያልበለጡ ሰዎች ሰግደው ተመልሰዋል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ዛሬ ልዩ የሆነ ተቃውሞውን አህባሾች በተመደቡበት መስጂድ ባለመስገድ ልዩ የሆነ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

ሙስሊሙን ለመረበሽና የንፁሃንን ደም ለመጠጣት የሚሯሯጡት የመንግስት ኃይሎች ከመቼውም በላይ ዛሬ በሙስሊሙ ላይ ጥቃት ለማድረስ ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን እነሱ ያሰቡት ሳይሆን በአላህ ፈቃድ ጭራቃዊ ተግባራቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ገና ከጧት ጀምረው በሸዋበር መስጂድ አካባቢ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የፌደራል ፖሊስ አዛዦች ቦታውን ሲቃኙ የነበረ ሲሆን ረፋዱ ላይ ጭንብል የለበሱ አድማ በታኞችንና እጅግ በጣም በርካታ ፖሊሶችን በሸዋበር መድረሳ ውስጥ እንዲቀመጡ አድረገዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ተክቢራ ይደረጋል ብለው ሲጠብቁ ልዩ በሆነ መልኩ ሙስሊሙ ለመንግስት ቅጥረኛ ለሆኑት ኢማሞች ጀርባውን በመስጠትና ጆሮውን በመያዝ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ትላንት ፀጥታ ዘርፍ ቢሮ ስብሰባ አድርገው የነበረ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ለሶላት ሲቆም በተሰማው የጭብጨባ ድምፅ እርምጃ ባለመወሰዱ በቦታው ተመድበው ለነበሩት የፌደራለ አዛዦች ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ዛሬ በሸዋበር መስጂድ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ሲቪል በመልበስ መስጂድ ውስጥ የገቡ ሲሆን ሙስሊሙ መስጂዱን ባዶ በማድረጉ እነርሱ ለመደቧቸው ኢማሞች አጃቢ ሁነው ውለዋል፡፡

እኛ ሙስሊሞች ብንደበደብም፣ ብንታሰርም ብሎም ቢገድሉን ጥያቄያችን እስካልተመለሱ ድረስ ሰላማዊ ተቃውሟችንን በምንም አይነት መልኩ አናቆምም! የተቃውሞ ሂደቱን እየቀያየርን እስከመጨረሻው ድረስ እንጓዛለን!
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!
አላሁ አክበር!

Thursday, January 17, 2013

Radio Bilal Jan 17,2013 የእለተ የራዲዮ ቢላል ስርጭት


Radio Bilal Jan 17,2013 የእለተ የራዲዮ ቢላል ስርጭት
Radio Bilal has Customized Its Services For Mobile Users, As well. Thus, The Mobile-Based Listeners Can Download On The Cell Phone And Share via BLUETOOTH daily programs
ዳውንሎድ ለማድረግ ይሄን ይክፈቱ በብሉትዝ በማስተላለፍ ኢስለማዊ ግዴታዎን ይወጡ፤
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
= http://goo.gl/oZD6q =
= http://goo.gl/j6QsP =
ኦሮምኛ ስርጭት(Afan Oromo)
= http://goo.gl/N1kFo =
= http://goo.gl/srbeK =

Radio Bilal Jan 17,2013 የእለተ የራዲዮ ቢላል ስርጭት 
Radio Bilal has Customized Its Services For Mobile Users, As well. Thus, The Mobile-Based Listeners Can Download On The Cell Phone And Share via BLUETOOTH daily programs
ዳውንሎድ ለማድረግ ይሄን ይክፈቱ በብሉትዝ በማስተላለፍ ኢስለማዊ ግዴታዎን ይወጡ፤
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
= http://goo.gl/oZD6q =
= http://goo.gl/j6QsP =
ኦሮምኛ ስርጭት(Afan Oromo)
= http://goo.gl/N1kFo =
= http://goo.gl/srbeK =

መንግስት በምስክር እጦት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል


ሰበር ዜና


መንግስት በምስክር እጦት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል፡፡


የብዙዎች ምላሽ ‹‹በሐሰት አንመሰክርም›› የሚል ሆኗል፡፡


በእስር ላይ የሚገኙ መሪዎቻችን እና ሌሎች ወንድሞቻችንን በአሸባሪነት ከስሶ ሲያንገላታ የቆየው መንግስት በምስክር እጦት ችግር ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ መንግስት ኮሚቴዎቻችን ላይ በመሰረተው ክስ በሐሰት ሊያስመሰክራቸው ያዘጋጃቸው 197 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት) ሰዎች መኖራቸውን ለፍርድ ቤት ቢያሳውቅም የተገለጸውን ቁጥር ያህል ምስክሮች ማግኘት አልቻለም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ለምስክርነት የታሰቡት ብዙዎቹ ግለሰቦች ምስክር ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡ መሪዎቻችን ባልዋሉበት እና በማያውቁት ወንጀል የከሰሳቸው መንግስት በየአካባቢው ‹‹ድጋፍ ይሰጡኛል፤ እተማመንባቸዋለሁ›› የሚላቸውን ግለሰቦች ለምስክርነት ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርግላቸውም በሐሰት አንመሰክርም የሚል ቆራጥ አቋም ማሳየታቸው ተሰምቷል፡፡

Share via BLUETOOTH daily Radio Bilal programs

Radio Bilal has Customized Its Services For Mobile Users, As well. Thus, The Mobile-Based Listeners Can Download On The Cell Phone And Share via BLUETOOTH daily Radio Bilal programs
Radio Bilal Jan16,2013 የእለተ የራዲዮ ቢላል ስርጭት ዳውንሎድ ለማድረግ ይሄን ይክፈቱ በብሉትዝ በማስተላለፍ ኢስለማዊ ግዴታዎን ይወጡ፤
የአማርኛ ስርጭት (Amharic)
=1= http://goo.gl/ZyzQu ==
=2= http://goo.gl/0KVqq ==
ኦሮምኛ ስርጭት(Afan Oromo)
=1= http://goo.gl/Fo8Vf ==
=2= http://goo.gl/EufuQ ==

Wednesday, January 16, 2013

365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት - 3 ሳምንት

365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት - ሶስተኛ ሳምንት
የአንድነትና የሰደቃ ሳምንት
በዳዮችን ያንቀጠቀጠው መሳሪያ ዛሬም በጃችን ነው!

አንድነት ለድል ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ተበዳዮች በደልን ከጫንቃቸው ሊያወርዱ የሚቻላቸው በአንድነት ሲቆሙ ነው፡፡ በአንድነት የፀና ህዝብ በበዳዮች ተንኮል በቀላሉ እንደማይፈታ ታሪክ ያስተምረናል፡፡ አንድነቱ እውነተኛ ሲሆን ደግሞ በደልን መሻገር ብቻ ሳይሆን ዘመን ተሸጋሪ ታሪክን መስራትም ያስችላል፡፡ በሌላ በኩል በደልን በሰወኛ ትግል ብቻ ሳይሆን ሌላ ማስወገጃ መንገድም ኢስላም ቀይሶልናል፡፡ ሰደቃ (ምፅዋት)፡፡ በእምነታችን አስተምህሮ መሰረት ሰደቃ በላዕን እና ፈተናን ይመልሳል፡፡ ይህን ደግሞ በታሪካችን በተለያዩ አጋጣሚዎች በተግባር አይተነዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደሃር ሃይማኖተኛ በመሆኗ ይህን እውነት መላው ዜጎቿ ይረዱታል፡፡ መሪዎቹም ይህን ብርቱ ሃይል ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ማወቅ ብቻም ሳይሆን አደጋውን በብርቱ ይፈሩታል፡፡

በአንድ አመቱ ሰላማዊ ጉዟችን የታለፉብን ህጎች

ድምፃችን ይሰማ
በአንድ አመቱ ሰላማዊ ጉዟችን የታለፉብን ህጎች
ክፍል አንድ
ከአንድ አመት በፊት የተጀመረው የህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በሁሉም እርምጃዎቹ ህጋዊ የሚባሉ አማራጮችን ብቻ ሲከተል ቆይቷል፡፡ ጥያቄዎቻችን ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች፤ ያቀረብንበት መንገድና ወኪሎቻችን የመረጥንበት አካሄድም ፍፁም ህገ-መንግስታዊ ናቸው፡፡ ይህንን የህዝብ ጥያቄ በህግ አግባብ ሊመልስ የሚገደደው አካል ግን አክብሮ ሊያስከብራቸው የሚጠበቅበትን ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችና ድንጋጌዎች ክፉኛ ለአደጋ አጋልጧቸዋል፡፡ እኛም በተከታታይ ክፍሎች የመብት ጥያቄዎቻችንን ተከትሎ የተጣሱ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በጥቂቱ ለማየት እንሞክራለን፡፡
‹‹ሕገ-መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡›› ይህንን በህገ-መንግስቱ አንቀፅ ዘጠኝ ላይ ሰፍሮ ያገኙታል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነትን በመከላከል ሽፋን በመንግስት እንደተረቀቀ የሚነገርለት ‹‹የሃይማኖት አክራሪነትና የህዳሴያችን ጉዞ›› ሰነድ የሙስሊሞችን የሃይማኖት እንቅስቃሴ በአክራሪነት ሽፋን ሙሉ ለሙሉ የሚገድብ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ህገ-መንግስቱን የሚፃረሩ የሃይማኖት መብት እቀባ አቅጣጫዎችና ዕቅዶች ገና ከህዝብ እንደደረሱ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠሟቸዋል፡፡

Thursday, January 10, 2013

ዚያራ

ዚያራ

ኢስላም እንደ እምነት የህይወት መርህ ሆኖ ለሰው ዘር የተበረከተ ፀጋ ነው፡፡ በውስጡም የዚህ ፀጋ አካል ሆነው የተሰደሩ በርካታ ተግባር ተኮር እሴቶች አሉት፡፡ አብዛኛዎቹ ተግባራት እውን ሲሆኑ መጨረሻቸው የሙስሊሙን ወንድማማችነትና አንድነት ጠንካራ በሆነ ገመድ ማስተሳሰር ይሆናል፡፡ ዘር፣ ቋንቋ፣ ቀለም፣ ብሔርና መሰል ልዩነቶች ደምቀው የማንነት መለያ እና መተዋወቂያ ይሆናሉ፡፡

የሰው ልጅ በተፈጥሮው አብሮነትን፣ ጓደኝነትን፣ ቅርርብን፣ መወዳጀትን ይወዳል፡፡ ኢስላም እንደ እምነት የአብሮነት፣ የፍቅር እና የሰላም መንገድ እንደመሆኑ መጠን ማሕበራዊ ግንኙነቶችንና በሰዎች መካከል ቤተሰባዊነትን የአስትምህሮቱ መሰረታዊ አካል በማድረግ ያስቀምጣል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ብቻውን መሆን ከሚያበዛ ሰው ሰዎች ጋር የሚቀላቀልን ሰው ይወዳሉ፡፡ ኢብን ማጃህ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ማለታቸው ተጠቅሷል ‹‹በሰዎች መሀል አብሮ የሚሆንና ችግራቸውን የሚካፈል አማኝ ብቻውን ከሚሆን፣ የሰዎችን ጉዳትም ከማይካፈል አማኝ የተሻለ ነው፡፡››

Wednesday, January 9, 2013

የኮሚቴዎቻችን፣ የትግሉ ሰማእታትና የጥቃት ሰለባዎች ሳምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

የኮሚቴዎቻችን፣ የትግሉ ሰማእታትና የጥቃት ሰለባዎች ሳምንት

365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት መርሃ ግብር (ሁለተኛ ሳምንት)

‹‹365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት›› በሚል መርህ በአራት ሳምንታት ተደልድሎ እየተዘከረ ያለው የአንድ አመት ጉዟችን እነሆ የመጀመሪያ ምዕራፉን አገባደደ፡፡ ባሳለፍነው ‹‹የአወሊያ ተማሪዎችና የጥያቄዎቻችን ሳምንት›› የጥያቄዎቻችንን መነሾና ሂደት፣ የአወሊያ ተማሪዎችን ገድልና ውለታ በጣም በአጭሩ ቃኝተናል፡፡ ያልተመለሱት ጥቂት ጥያቄዎቻችንንም ‹‹365 ቀናት ሳይመለሱ ዳግም የቀረቡ የህዝብ ጥያቄዎች›› ብለን በሚሊዮኖች ድምፅ አጅበን ካደባባይ ውለናል፡፡ ዛሬስ የጥያቄዎቻችን አግባብነት እንዲሁም የኛ እና የወኪሎቻችን ንፁህነት ተገልፆላቸው ይሆን? አዎን ብለን እንጠረጥራለን፡፡ ጥርጣሬያችንም ተግባራዊ ምላሽን እስኪወልድ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ስንል የተዘጉ በሮችን ሁሉ በርግዶ የመግባት አቅም ባለው በዚህ ባለዘርፈ ብዙ ትርጓሜ የትግላችንን አዋጅ እንለፍፋለን፡፡ አዎን ድምፃችን ይሰማ!!!

Tuesday, January 8, 2013

Ethiopia hold Tunisia to draw in friendly - News - Kick Off

Saladin Seid
Ethiopia served notice of their potential to cause an upset at the Africa Cup of Nations by holding Tunisia to 1-1 draw in their friendly in Doha on Monday.

Ethiopia came from behind to equalise in the 64th minute through Saladin Seid after Tunisia had taken a fourth minute lead from a penalty converted by their Swiss-based attacking midfielder Oussama Darragi.
The draw in a warm-up international in Qatar came after success for Ethiopia last week at home against Niger, another of the sides who will be competing in this month’s continental championship in South Africa.
Ethiopia are playing at the Nations Cup for the first time in more than 30 years and remain something of an unknown quantity. They compete in Group B with defending champions Zambia, Nigeria and Burkina Faso.
Tunisia are in Group D with Algeria, Togo and the much fancied Ivory Coast.
The tournament starts on January 19.

Sunday, January 6, 2013

የጁሙዓ ውሎ በሐረር ኢማን መስጅድ

Bilal Ibn Rebah
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
part 1
የጁሙዓ ውሎ በሐረር ኢማን መስጅድ ትንሽ ልበላችሁ………
እኔ ከሐረር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ከምትርቅ ከተማ ላይ ነው የምኖረው።
ገና በጠዋቱ እየገሠገስኩ ነው ከመኖሪያ ክልሌ ለቅቄ የወጣሁት። ምክንያቱም ሁሌም ጁምዓ ጁምዓ ቀን ቀጠሮዬ ሐረር ኢማን መስጅድ ነውና! ልክ 5:00 ሰዓት ሲሆን ወደ መስጅዱ አመራሁ። ወደ መስጅዱ ግቢ ስገባ ከሌላው ግዜ በተለየ ሁኔታ ሕዝቡ መስጅዱን ሞልቶታል። ማሻ አላህ! ውስጤን ሀሴት ተሠማኝ። ውዱዕ አድርጌ 2 ረከዓ ከሰገድኩ በኋላ የሰውን ስሜት ለመመልከት አንገቴን ዞር ዞር አደረኩ ገሚሱ ቁርዓንን በተመሥጦ ይቀራል፣ገሚሡ በዱዓና በዚክር ተጠምዷል። ትንሽ እንደቆየን አንዱ ሼኻችን (ዳኢ)በተቅዋ ዙርያ ዳእዋ ማድረግ ጀመረ ።ማሻ አላህ ብዙ ጉዳዮችን
ዳሰሰልን! በመቀጠልም የጁምዓን ሷላት የሚያሠግዱት ተረኛው ተወዳጁ ኢማማችን ቦታውን ተረከቡ። ሱብሃን አላህ! ፈገግታቸው እንዴት ያምራል መሰላችሁ። ሕዝቡ ለሳቸዉ የተለየ ፍቅር አለው። ምክንያቱም ሐቅን አይፈሩም፣ስለሐቅ የሚሠብኩ፣ለሐቅ የሚሞቱ፣ሐቅን የማይደባብቁ ትልቅ ኢማም ናቸው። ይሔንን ስል ሌሎቹ ከዚህ የተለዩ ናቸው ማለቴ አይደለም። ኢማማችን እስላማዊውን ሰላምታ ካቀረቡልን በኋላ ወደ እለታዊው ፕሮግራም ማለትም ለቁርዓን ተሕፊዝ ለሚሠራው ህንፃ ግንባታ መዋጮ ሕዝቡ እንዲያዋጣ ትእዛዝ ካስተላለፋ በኋላ ወደ ምክርና ዱዓ ገቡ። እንዲህ እያለ…………… የኹጥባው ሰዓት ደረሰና ሚንበራቸው ላይ ወጡ። አዛን ተብሎም ኹጥባ መናገር ጀመሩ። ታዲያ ገና ግማሽ ገፅ የሚያክል እንኳን ሳያነቡ ሕዝቡ በለቅሶ ከሣቸው ጋር ማንባት ጀመረ። የኹጥባው ርእስ ሐይለኝነት እንዴት ያስፈራ ነበር? አላህ.……………..……!
እሳቸው ወረቀቱን መያዝ አቃታቸው፣የሕዝቡ የለቅሶ ጩኸት ከመስጅዱ አልፎ ውጪውን አናጋው።

Thursday, January 3, 2013

ጁመዓ የማይቀርበት ታሪካዊ ቀጠሮ አለን!

ጁመዓ የማይቀርበት ታሪካዊ ቀጠሮ አለን!

የኢስላም አስተምህሮ ከኛ ይደርስ ዘንድ የታለፈባቸው ወሳኝ መንገዶች እኛም እንድንጓዝባቸው የአላህ ፍላጎት መሆኑን እነሆ ተጨባጩ ያስረዳል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን ዲናቸውን በመጠበቅ የሰሩት አኩሪ ገድል በእኛም እንዲደገም ወቅቱ እየተጣራ ነው፡፡ የወቅቱንም ጥሪ በተግባር የሚመልሱ ሚሊዮን ቢላሎችና ሚሊዮን ሱመያዎችን በእርግጥም አይተናል፡፡ የቢላልና የሱመያን መንገድ ለመረጃ ፍጆታነት ሳይሆን ለህይወት መርህነት የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያኖችን አይናችን አይቷል፡፡ ታሪካችንም ዘግቦት እያለፈ ነው፡፡ ይህን በውስጣችን እያለ ሳናጤነው የኖርነው ትልቅ የአላህ ኒዕማን በገሃድ እንዲታይ ያደረገው ደግሞ ከአመታት በፊት በመንግስት ተመርጦልን ከ365 ቀናት በፊት ልንጠመቀው የተዘጋጀልን ‹‹ሙስሊሞችን ዳግም የማስለም›› ሃገራዊ ዘመቻ ነው፡፡ ይህንኑ ዘመቻ የሚመራው ደግሞ የመንግስትን ትከሻ ተደግፎ በመጅሊስ ስም የተሰባሰበው የካድሬዎች ቡድን ነው፡፡ የነዚህ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡ ሁለት ሃይሎች የመጀመሪያ ሰለባ የነበረው ደግሞ ከነስያሜያቸው አፄ እና ወታደራዊ በመባል የሚታወቁ ሁለት መንግስታትን አሳልፎ ዴሞክራሲያዊ በሚል ስም በተሰየመው መንግስት ላይ የደረሰው የአወሊያ ተቋም ነው፡፡ የ365 ቀናት ጉዟችንም ከነዚህ ሶስት ነጥቦች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሶስቱ ነጥቦችም የነገሩ መነሻ እንዲሆኑ ያስቻለው ትልቁ ነጥብ ግን መንግስት ሃገር የሚተዳደርበትን ህገመንግስት በማንአለብኝነት በአደባባይ ደግሞ ደጋግሞ መጣሱ ነው፡፡

የትግላችን መነሾና የጥያቄዎቻችን እንድምታ

የትግላችን መነሾና የጥያቄዎቻችን እንድምታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡-
በአወሊያ ሙስሊም ሚሽን ት/ት ተማሪዎች የተጀመረውና ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ያደገው ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የኃይማኖት ነፃነት ጥያቄ እና የመንግስት ጣልቃ ገብነትና የመብት ጥሰት ተቃውሞ እነሆ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ በዚህም አመታዊ ጉዞው ውስጥ ከደርዘን በላይ ሙስሊሞች ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፤ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ 29 ሙስሊሞች ታስረዋል፤ በሽብርተኝነትም ተከሰዋል፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ሙስሊሞች በመላ ሀገሪቱ እስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ፤ ብዙ ምዕመናን አካላቸውን አጥተዋል፤ ብዙ ሙስሊሞች የሚወዷት ሀገራቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ትተው ተሰደዋል፤ ብዙ የሙስሊም ልማት ድርጅቶች፣ የገንዘብ፣ ኢኮኖሚና የንግድ ተቋማት፣ የየቲሞች መረዳጃና ማሳደጊያ ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላት ተዘግተዋል፣ የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል፣ ገንዘባቸው ተወርሷል፤ የሙስሊም ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይመለሱ ተከርችመዋል፡፡ የእምነት ማዕከላትና መድረሳዎች ተዘግተዋል፤ መስጂዶች ፈርሰዋል፤ የግዳጅ ሰልፎች ተስተውለዋል፤ ሰላማዊ ትግሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀያየር ሀገሪቱ ሰፍኗል፤ወዘተ...
የዚህ ምልከታ ዓላማም የትግሉን ጉዞ ሂደት ማለትም መነሻ ምክንያቶች፣ ስኬቶች፣ ድክመቶች፣ ስጋቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን ለመጠቆም ያለመ ነው፡፡

Uploaded videos (playlist)

Tuesday, January 1, 2013

Global Council for justice in Toronto Dec 30-2012

Global Council for justice in Toronto Dec 30-2012



የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ትግል የጀመሩበትን 1ኛ አመት ቶሮንቶ በሚገኘው ሳላህዲን እስላማዊ ማእከል ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን አከበሩ።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አለማቀፍ ምክርቤታ የቶሮንቶ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው በዚህ አንደኛ አመት መታሰቢያ በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል።
በአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ፤ ከጀርመን ተጉዘው የመጡትና፤ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ሙስሊም ሀጂ መሀመድ አህመድ ልጅ፤ አቶ መሀመድ ሀሰን ስለሙስሊሞች ትግል ውጣውረድ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።
ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን እንዳቀደ የሚያሳይ ሰነድ ከእጃቸው እንደገባ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፤ ላለፉት 12 ወራት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርገው አፈና በዚህ ምስጢራዊ ሰነድ ውስጥ እንደተካተተ ተናግረዋል።
አተ መሀመድ ሀሰን የሙስሊሞችን የአንድ አመት ትግል ሂደት የሚያሳዩና ለትግሉ የተደረገውን አለማቀፍ ድጋፍ የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎችን ለተሰብሳቢዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ ተሰብሳቢዎቹ አቶ መሀመድ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ የአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የህገመንግስቱ አንቀጽ 27 እንዲከበር ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፤ “ድምጻችን ይሰማ፤ ሰላም አጣን ባገራችን፤ መንግስት የለም ወይ” የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል።
በዝግጅቱ ላይ በቶሮንቶ የሚገኙ አገር ወዳድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንም ተገኝተዋል።

Aschekuay አስቸኳይ የተላለፈ የመስጅዶቻችን እናድን ጥሪ

ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ - መስጊድ ነጠቃ!


ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ - መስጊድ ነጠቃ!

ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መሠረታዊ የእምነት ነፃነት መብታችን ተጥሶ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጣን ድፍን አንድ አመት ሞላን፡፡ ይህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን አንድ ላይ ያስተሳሰረ ተቃውሞ መነሻውም ሆነ መድረሻው የመንግስት በሐይማኖታችን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች በይፋ መጣሳቸው ነው፡፡ አሕባሽ የተሰኘውን አንጃ ከሊባኖስ በማስመጣት በሙስሊም ዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን የተደረገው ሙከራ ለዚህ የከፋ ድርጊት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡

አሕባሽ በከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ታጅቦ በመንግስት ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሊፈፅማቸው ያሰባቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ነበሩት፡፡ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአህባሽ የግዳጅ ጠመቃ ላይ በወጣው ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በአህባሽ የመጅሊስ አስተዳደር ጥብቅ ቁጥጥር ስር እንዲውል፣ ማንኛውም የመስጂድ ኢማምም ሆነ ዳዒ ይህንን የአሕባሽን ስልጠና እንዲሳተፍ፣ የአሕባሽን ስልጠና ያልወሰደ ማንኛውም ኢማም ማሰገድ እንደማይችልና ስልጠናውን ያልወሰደ ኢማም ቦታም ስልጠናውን በወሰደ ሌላ ሰው እንደሚተካ፣ የአህባሽን ስልጠና ያልወሰደ እና ከአህባሽ የመጅሊሱ አስተዳደር ሰርተፊኬት ያልተሰጠው ማንኛውም ዳዒ በየትኛውም መድረክ የኃይማኖት ትምህርት እንዳይሰጥ፣ በሕብረተሰቡ ጉልበት፣ ሀብትና ጥረት የተገነቡ ማንኛውም ኢስላማዊ ተቋማት ለአሕባሽ እንዲሰጡ… አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡