Wednesday, October 31, 2012

9 የሙስሊሙን ኅብረተሰብ አመራር ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሙስሊም አረጋውያንን......

9 የሙስሊሙን ኅብረተሰብ አመራር ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሙስሊም አረጋውያንን፣ የምግባረ ሰናይ ድርጅት ሐላፊዎችን፣ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሃይማኖታዊና ሞራላዊ ትምህርት ሲሠጡ የቆዩ ሰባኪያንን እና ለበቀሉበት ኅብረተሰብ ሞያዊ ግልጋሎት ይሰጡ የነበሩ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞችን በጥቅሉ 29 የሚደርሱ ግለሰቦችን ባለፈው ሰኞ የፌደራል አቃቤ ሕግ አሸባሪዎች ናቸው ብሎ መክሰሱ ይታወሳል፡፡ የክሱ ይዘት እጅግ አሳፋሪና አገርን ከሚመራ የመንግስት አካል ፈጽሞ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ በክሱ ላይ መንግስት ሕገ መንግስቱን በመጻረር ጭምር በርካታ ጤናማ ሃይማኖታዊ ተግባራትን ወንጀል አድርጎ አቅርቧል፡፡ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የክሱን ዝርዝር እንዳለ አቅርበነዋል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት

አዲስ አበባ

Tuesday, October 30, 2012

ታላቅ የዳዕዋ እና የግብዣ ፕሮግራም በጂማ ዩቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ተካሄደ!!


ታላቅ የዳዕዋ እና የግብዣ ፕሮግራም በጂማ ዩቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ተካሄደ!!

እሁድ ማለትም ጥቅምት 18-02-2005 በግዙፉ የጂማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ (JUMJ) Main Campus አንድ ታሪካዊና አስገራሚ ክስተት ተፈጠረ፡፡ ጀማዓው አራት ቅርንጫፎች አሉት፡፡ የዓረፋ በዓል ጥቂት ቀናት እንደቀሩት ነበር ‹‹ለምን አራቱንም ቅርንጫፎች የሚያገናኝ የጀመዓዎቹን መሰረታዊ የዓላማ አንድነት የሚያሳይ የዳዕዋና የምሳ ፕሮግራም አይዘጋጅም?›› የሚለው ሀሳብ የተፀነሰው፡፡ በዓረፋ በዓል ቀን ጀመዓው ሌላ ዝግጅት የነበረው በመሆኑ የምሳ ፕሮግራሙ እሁድ ተደረገ፡፡ ግብዣው የአራቱ ግቢ ጀማዓዎች (ማለትም Main campus, Business and Economics College, Agricultural And Veterinary Medicine, and Institute of technology(JiT)) ተማሪዎች፣ የጂማ ከተማ ወጣት ጀመዓዎችና ተጋባዥ እንግዶችን ያካተተ ነበር፡፡

ከ40,000.00 ብር (አርባ ሺህ ብር) በላይ እንደወጣበት እና 20 በጎች እንደታረዱበት የተነገረለት ይህ ዝግጅት በጀመዓው ድንቅና ብርቅዬ ወንድምና እህት አባላት ንቁ ተሳትፎ ያለ ምንም ቅሬታ ተካሂዷል፡፡ በእለቱ ሙስሊሙ ተማሪ አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበትና የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመዓዎች ዓላማ ትምህርትንና ሀይማኖትን ጎን ለጎን በማስኬድ ጥሩ ዓለማዊ ዕውቀት ያለው ሀይማኖተኛ ሙስሊም ዜጋ ማምረት በመሆኑ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ሲመረቁ እንደ ዓለማዊ ትምህርቱ ሁሉ ዲናቸውን ጠበቅ ማድረግ እንዳለባቸው የተነገረ ሲሆን ፕሮግራሙ ላይ በአንድ ወንድም የተነበበው ግጥም ታዳሚውን ለለቅሶ የጋበዘና ያስለቀሰም ጭምር ነበር፡፡

የኮሚቴዎቻችን የልደታ ፍርድቤት ውሎ ዝርዝር!!!

የኮሚቴዎቻችን የልደታ ፍርድቤት ውሎ ዝርዝር!!!

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት ከጧቱ 4፡30 ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ብርቅዬ ዱአቶች፣ኡለማዎች፣አርቲሰቶች እና ሙሰሊም ጋዜጠኞች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ተምልክቷል።

ብርሀኑ ወንድማገኘሁ ፣ ዘረሰናይ ምስግናው እና ቴዎድሮስ ባህሩ አቃቢ ህጎች ሆነው የቀረቡ ሲሆን ለተከሳሾች ማለትም ለ29 ግለሰቦችና ሁለት ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠበቃ ሆነው የቀረቡት ደግሞ አቶ ተማም አባቡልጋ፣ አቶ ብርሀኑ ፣ አቶ ሞሀመድ አብደላና ናቸው።

የፌደራል ከፍ
ተኛው ፍርድ ቤት ከቀኑ 4፤30 ላይ ዘግይቶ የጀመረ ሲሆን የ31 ሙስሊም ተከሳሾችን ማየት ሲጀምር አቃቢ ህግ የክስ ፋይሉ ማህተም ይቀረዋል በማለቱ ችሎቱ ለ40 ዲቂቃ ተቋርጦ የክስ ፋይሉ ከመጣ በሁዋላ እንደገና ተሰይሟል።

መሪዎቻችንን ‹‹አሸባሪ›› ማለት ሕዝባችንን አሸባሪ ማለት ነው፡፡




መሪዎቻችንን ‹‹አሸባሪ›› ማለት ሕዝባችንን አሸባሪ ማለት ነው፡፡

አሁን ነገሮች ሁሉ ጥርት ብለው ወጥተዋል፡፡ እውነቱ እንደ ረፋድ ጸሐይ ፈክቷል፡፡ ቀዳሚው የአቶ መለስ አስተዳደርም ሆነ የአሁኑ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ፣ አለፍ ሲልም የአስልምና ሃይማኖት ላይ የሚከተለው ፖሊሲ አዎንታዊ ነው ብለው ያምኑ ለነበሩ ወገኖች የትላንቱ የልደታ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት ውሎ ‹‹ተሳስታችኋል›› የሚል በእብሪት የታጀበ መልስ ሰጥቷል፡፡ ለሶስት ወራት ተኩል ያህል በማዕከላዊ ወህኒ ቤት ታስረው የነበሩ 9 የሙስሊሙ አመራር ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሙስሊም አረጋውያንን፣ የምግባረ ሰናይ ድርጅት ሐላፊዎችን፣ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሃይማኖታዊና ሞራላዊ ትምህርት ሲሠጡ የቆዩ ሰባኪያንን እና ለበቀሉበት ኅብረተሰብ ሞያዊ ግልጋሎት ይሰጡ የነበሩ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞችን በጥቅሉ 29 የሚደርሱ ግለሰቦችን የፌደራል አቃቤ ሕግ አሸባሪዎች ናቸው ብሎ ከሷቸዋል፡፡ ከመሪዎቻችን ጋርም ምንም ግንኙነት የሌላቸው እንስትም ከኮሚቴዎቻችን ጋር በጋራ ተከሰዋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ኢስላማዊ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችንም መንግስት በተመሳሳይ ወንጀል ከሷቸዋል፡፡

Monday, October 29, 2012

“ድንቅ ስብዕናዎች...ኮሚቴዎቻችን”

“ድንቅ ስብዕናዎች...ኮሚቴዎቻችን”

በዚህች ምድር ላይ ከሚያስደስቱ ነገሮች አንዱ ከራሳቸው አልፈው ለህዝብ የሚኖሩ ሰዎችን ማየት ነው።ራሳቸውን ሁነው ቤተሰባቸውን በፍቅርና በስነ-ልቦና ገንብተው ለህዝብ ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ “ጀግኖችን” እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም። እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ብዙዎች ያፈቅሯቸዋል።ብዙዎች ስለ እነርሱ መስወዓት መሆንን ይመኙላቸዋል። ስለነርሱ መልካምነት ይዘክሯቸዋል። ብቻ ሳር ቅጠሉ ሳይቀር ስለነሱ የሚያስብ ይመስላል። ትንሽ ትልቁ፡ሴት ወንዱ፡ ወዳጅ ጠላቱ የሚያወራው ስለነርሱ ነው። አዎን! ግልፅ የሆነ የህይወት ግብን አስቀምጦ ለርሱ ኖሮና በርሱ ኖሮ ለዚሁ ግብ ሲሉ መክፈል የሚገባውን መስዋዕትነት ሁሉ መክፈል ሃሴትን ያሰገኛል። በዚሁ ግብ ላይ መሞትም ህያውነት ነው።ሁልጊዜ በሰዎች ልብ ውስጥ መታወስ ነውና። አዎን! የህዝብን ልብ መግዛት የሚቻለው በወሬና በፕሮፖጋንዳ አይደለም- ይልቁንስ ሆኖ በመገኘት እንጂ። በጠመንጃም አይደለም- በመልካም ስነ-ምግባር እንጂ። እንደ አንዳንድ ሗላ ቀርና ተምረው ያልተማሩ የስነምግባር ችግር ያለባቸው ባለስልጣናት ሰውን በሃይልና በሞት በማሰፈራራት የሚገኝ ታዛኝነት የለም-ውርደት እንጂ። ለእንደነዚህ አይነቶቹ ሰዎች የምንላቸው ነገር ቢኖር ስው እንዴት መፈቀር እንደሚችል ከ “እኛ ጀግኖች” ተማሩ ነው። የሰውን ልጅ ልብ እንዴት መግዛት እንደሚቻል ከ “እኛ ጀግኖች” ኮርጁ አይጎዳችሁም። ማንነታችሁን መጀመሪያ ፈልጉና አግኙት እንደኛው “ጅግኖች”።ለእራስ ሳይሆኑ -ለሃገርም ለህዝብም መሆን አይቻልምና!!!።

Yesumeya Terii " Atenesam Woy " የሱመያ ጥሪ " አትነሳም ወይ ! "

Ethiopia charges 29 Muslims under anti-terror law

Ethiopia charges 29 Muslims under anti-terror law

Sunday, October 28, 2012

Ethiopian government’s meddling in religious affairs upsets Muslims

Ethiopian government’s meddling in religious affairs upsets Muslims

On the Current Muslim Protests in Ethiopia: A Conversation between Jenny Vaughan of AFP & Alemayehu Fenatw of the LBJ School of Public Affairs, University of Texas


Jenny Vaughan:       What does the government's response to the Muslim protests tell you about religious tolerance among the ruling regime in Ethiopia?
Alemayehu Fentaw: What's going on in Ethiopia is a reflection of what's happening in the West. Fears of terrorism in the West have deteriorated into an irrational suspicion of Muslims, which will continue until the West turns its critical eye inwards. Since Ethiopia is a critical partner in the US war on terror, its government thinks it helps to appear terrified by the prospect of the rise of Islamism and an improbable takeover of governmental power by political Islam. That way, Ethiopia hopes to keep Western aid flowing into the country.

( Must Listen ) Ye Shehidoch Enat Enkwan Des Yalesh Nasheed

ቢጫው የዒድ ተቃውሞ እና ከፊል አንድምታው

ቢጫው የዒድ ተቃውሞ እና ከፊል አንድምታው

በ2005 የዒድ አል-ዓድሃ (አረፋ) በዓል ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ለአስራ አንድ ወራት መቋጫ ያላገኘውን የመብት ጥያቄዎች እና መንግስት ለመመለስ ፈቃደኝነት አለማሳየቱ የወለደውን ቅያሜ በሚሊዮኖች ቁጣ አጅቦ ከአደባባይ ውሏል፡፡ ሃገር አቀፉ የዒድ አደባባይ ተቃውሞ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችንን እና እነሱን ተከትለው የደረሱብን የመብት ጥሰቶችን እንዲሁም የኮሚቴዎቻችን መታሰር ያሳደረብንን መጥፎ ስሜት ዛሬም መንግስት እንዲያውቀው ዋነኛ አላማው ቢያደርግም እንድምታው ግን ከዛም ያለፈ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዒዱ ቢጫ ተቃውሞ እውነትና እውነተኞች ጎልተው የወጡበትና ሀሰትና የሃሰት ጭፍሮች ደግሞ በዚህ ዘመን እያበሉ መኖር እንደማይቻላቸው በተግባር የተረዱበት ዕለት ነበር፡፡ ይህ ባለቤቱ ህዝብ የሆነው ትዕይንት ማስተዋል ላልተሳነው በሙሉ ከባድ መልእክትም ያዘለ ነበር፡፡ ከአደባባይ መዋል መደበኛ የህይወታችን ክፍል ሆኗልና የዒዱ ውሎ በመርህ ደረጃ ከቀደሙት ባይለይም በይዘቱ፣ ግዝፈቱ እና ሃገራዊ መልዕክቱ አኳያ ግን ሁሉም አካላት የመልእክቱን ጥልቀት ሊረዱት ግድ ይላል፡፡

የዒዱ ተቃውሞ በሁሉም ህዝብ የነፍስ ወከፍ ተሳትፎ የደመቀ ነበር፡፡ ከመብት ትግላችን መባቻ አንስቶ ኮሚቴዎቻችንን መምረጡና አጠቃላይ ሂደቱ የህዝብ የነቃ ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ባለቤትነትም በተግባር የታየበት ትግልም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ጠንሳሹም-ሕዝበ፤ አራማጁም-ሕዝበ፤ ተሳታፊውና ባለቤቱም ህዝብ በሆነው የመብት ማስከበር ትግል በመላ ሃገሪቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አስተባባሪዎችና መሪዎች እየተባሉ ታስረዋል፡፡ የመብት ማስከበር ትግላችን ይበልጥ እየጠነከረ እና ሃገራዊ ገጽታውም እያደገ መምጣቱን አመላካች ነው፡፡ ሕዝቡም ለእስር እና እንግልት መቼም ቢሆን እጅ እንደማይሰጥ ያረጋገጠበት የተግባር ምስክር ነው፡፡

Saturday, October 27, 2012

አዲስ አበባ-የኢድ አል አድሐ በዓልና ተቃዉሞ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን የዘንድሮዉን በዓል ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ አንዳድ ሥፍራ ደግሞ ግጭትና እስራት አጥልቶበት እንደዋለ አንዳድ ዘገባዎች ጠቁመዋል።ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በዓሉ በየዓመቱ እንደሚደረገዉ ስታዲዮም በተካሔደ ሥግደት ቢከበርም መንግሥት በሐይማኖታዊ ነፃነታችንን አፍኗል፥ መሪዎቻችንን አስሯል፥ ሐባሽ የተሰኘዉን ሐራጥቃ ይደግፋል፥ የሚሉ ምዕመናን   ተቃዉሟቸዉን አሰምተዉበታል።ምዕመኑ ከስግደቱ በሕዋላ በተለይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያን ከብቦ ተቃዉሞን ሲያሰማ ነበር።አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ደግሞ ምዕመናኑ ከታላቁ አንዋር መስጊድ አጠገብ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ በመሰለፍ መንግሥት ያሰራቸዉን የሙስሊም ተወካዮች እንዲፈታና ሐይማኖታዊ ነፃነታቸዉን እንዲያከብር ጠይቀዋል።ሌሎች ምንጮች እንዳስታወቁት፥ ናዝሬትና ጂማን በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ሙስሊም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አዉግዟል።በምዕመናኑና በፖሊስ መካካል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች መጎዳት፥ መቁሰላቸዉ ተገዝግቧል።ዶቸ ቬለ  ዘገባዉን ከነፃ ምንጭ አላረጋገጠም።
የኢድ አልአድሃ አከባበርና ተቃውሞ
አስተያየት ከአዲስ አበባና ከደሴ

1433 EID ሃይማኖት መንካት እሳት መንካት ነው፡፡ መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ?

Friday, October 26, 2012

አልጀዚራ የኢደል አድሀ ቢጫ ተቃውሞውን ዘገበው

Ethiopia’s Muslims accuse government of religious meddling

Jenny Vaughan (AFP)|FRIDAY, OCTOBER 26, 2012
ADDIS ABABA-WITH hands clasped together as a symbol of unity, lines of Muslims gather under the beating sun outside Addis Ababa’s Anwar mosque after Friday prayers chanting “Amin, Amin,” or “thanks to God.”
They gather – as they have all this year – to protest what they call unconstitutional government interference in religious affairs, heightened by the election of Muslim leaders this month the protesters say were not free or fair

“We have requested an election, a peaceful one, a democratic one, and we didn’t get (it),” said Zeinu Lopiso, 26, a merchant near Anwar mosque, speaking at a recent demonstration where hundreds took part.
Zeinu, like many other protesters, refused to cast a ballot in the October 7 elections to appoint the leaders of the Supreme Council on Islamic Affairs, the community’s main representative body.
Zeinu opposed holding elections in government offices instead of mosques, complaining the government handpicked candidates after 17 Muslim leaders were jailed during protests in July, prompting accusations of a police crackdown.

Kennaa IIdaa Nashiidaa bareedaa Afaan oromootiinነሽዳ በኦሮሚኛ

የህዝብ ድምፅ ይሰማ!!!

የኢድ ተቃውሞ በአጭሩ በፎቶ ብቻ

( Must Watch ) Nation Wide Protest Against Ethiopian Government After 20...

የአገር አቀፉ የኢደል አድሐ ቢጫ ተቃውሞ ሙሉ ዘገባ

በመላዋ ኢትዮጵያ ዛሬ የሚከበረውን የኢደል አድሐ በዓል ተንተርሶ የተካሄደው አገር አቀፍ የቢጫ ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል፡፡

የአገር አቀፉ የኢደል አድሐ ቢጫ ተቃውሞ ሙሉ ዘገባ

ህዝበ ሙስሊሙ ዛሬም በከባድ ቁጣ ታጅቦ በመላው ሃገሪቱ በዒድ አደባባዮች ተቃውሞውን ሲያሰማ ዋለ፡፡ ይህ በሃገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ህዝባዊ ተቃውሞ አካል የሆነው የኢዱል አድሃ የቢጫ ማእበል ‹‹ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ቆም ብለው እንዲያስቡ›› በሚል የቢጫ ተቃውሟችንን ደጋግመን እንደምናሰማ በተገለፀው መሰረት በመላ ሃገሪቱ በሚሊዮኖች ከጫፍ እስከ ጫፍ ተካሂዷል፡፡ (የቢጫው ተቃውሞን ትርጉምና ዓላማ ለመረዳት በድምጻችን ይሰማ ላይ የተስተናገደውን ‹‹የቢጫው ተቃውሞና አገራዊ መልእክቱ›› የሚለውን ጽሑፍ ይመልከቱ) ሚሊዮኖች በተሳተፉበት በዛሬው ቢጫ ተቃውሞ ከዚህ በፊት በሰፊው ይባሉ ከነበሩት ‹‹ድምፃችን ይሰማ! ኮሚቴው ይፈታ! የታሰሩት ይፈቱ! እና ምርጫችን በመስጂዳችን!›› ከሚሉ የድምፅ መፈክሮች በተጨማሪ በርካታ አዳዲስ መፈክሮችን ህዝቡ አሰምቷል፡፡ ‹‹የህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ይተግበር! መብታችን ይከበር! ጭቆናው በቃን! ማስገደድ በቃን!›› እና ሌሎችም በእለቱ ከተስተጋቡ መፈክሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የመብት ጥያቄያችንን አስመልክተው የሚነዙ ፕሮፖጋንዳዎች ከመንግስት ሚዲያና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፍጆታነት ውጭ ከንቱ መሆናቸውን ዳግም በገሃድ ያሳየም ነበር፡፡

በአዲስ አበባ በመቶ ሺዎች የደመቀው የተቃውሞ ትእይንት በከተማው በሁሉም አቅጣጫዎች በቢጫ ማእበል የተዋጠ ነበር፡፡ በስታዲየም ውስጥ፣ በአብዮት አደባባይ፣ በኢቲቪ ህንፃ፣ በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት የተለየ ቁጣ አዘል ተቃውሞ ተስተጋብቷል፡፡ እስከአሁን ባሰባሰብነው መረጃ ከምስራቁ የሃገራችን ክፍል በሃረር ኢማም አህመድ ስታዲየም፣ ከዛም አልፎ እስከ ጀጎል የሞላው ህዝብ ደማቅ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን ‹‹ክርስቲያኖች ወንድሞቻቸን ናቸው›› ሲሉም ሃገራዊ ፍቅራቸውን ገልፀዋል፡፡

በአዳማ የመብት ጥሰቱ ድንበር ማለፉን በከባድ ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን ከጅምሩ እስከ ማብቂያው ሙሉ ከተማው በቢጫ የደመቀ ህገወጥ ምርጫንና የመሪዎቻችንን መታሰር ያወገዘ የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡ በድሬዳዋ እና በአፋር ሚሌም የታሰሩትን አላህ እንዲያስፈታቸው በኢድ አደባባይ ዱዓ ተደርጓል፡፡ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በደሴ ‹‹በአህባሽ ኢማም አንሰግድም›› በሚል ህዝቡ በራሱ ኢማም በመስገድ ታሪካዊውን ቢጫ ተቃውሞ በተለመደው ጀግንነቱ አስተጋብቷል፡፡ በከሚሴም ከእስከዛሬዉ ለየት ባለ ሁኔታ ወደ 80 ሺ የሚጠጋ ህዝብ በአአካባቢው ከሚገኙ 7 ቀበሌዎች እና ከከሚሴ ከተማም ጭምር በመውጣት ትላልቅ ባነሮችና መፈክሮች በመያዝ በቢጫ የታጀበ ከፍተኛ የተቃዉሞ ድምፅ አሰምተዋል፡፡ በባቲ፣ በመርሳ፣ በወልዲያ እና ሌሎች ከተሞችም ሃገራዊ ተቃውሞው የሁሉም መሆኑን በድምቀት አውጀዋል፡፡ በሰንበቴም ከ5 ሺህ በላይ ህዝብ በኢድ ሰላት ላይ ደመቀ ተቃውሞ አሰምቷል፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ አንዳንድ ከተሞች ህዝበ ሙስሊሙ እቤት በመቅረት መቃወሙን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ በምእራቡ የሃገራችን ክፍልም በጅማ ከሰላት በፊት የተጀመረው ከባድ ቁጣና ተቃውሞ ህዝቡ በሚሰማቸው ዳዒዎች መስመር እንዲይዝ የተደረገ ሲሆን ህዝቡም ለሚያምነው የተገራ፣ በመብቱም የማይደራደር መሆኑን አሳይቷል፡፡ በበደሌም ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡ በኢሊባቡር ከመቱ 42 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው አልጌሳቻ ወረዳ ሙሉ የከተማውና የገጠሩ ማህበረሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝ ምርጫው እንደማይወክላቸው በመግለፅ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!›› በሚል ተቃውመዋል፡፡ በደቡብ የሃገራችን ክፍል ከዚህ በፊት በጉራጌና ስልጤ ዞኖች፣ እንዲሁም በዲላ የተካሄዱት አይነት መሰል ተቃውሞ እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን ምንጮቻችን እንዳደረሱን እንዘግባለን፡፡ ወራቤ ላይ የመንግስት ተወካዮች ንግግር ለማድረግ በሞከሩበት ሰአት በተቃውሞ ሲያስቆሙት በወሊሶ እቤት በመቅረት ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡ ከጁምኣ ሰላት በኋላ ግን በመስጊዶቻቸው እጅግ በርካታ ህዝብ በተገኘበት ተደርጓል፡፡ በሻሸመኔም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ አሰምቷል፡፡ እስከአሁን ባለው መረጃ ብቻ በመላ ሃገሪቱ በአራቱም አቅጣጫዎች ህዝብ ‹‹መብቴ ይከበርልኝ! ወኪሎቼ ይፈቱ!›› በማለት የአላማ ፅናቱን ያሳየ ሲሆን ለህገወጥ ምርጫና ለህገወጥ ተመራጭ ምንም እውቅና እንደማይሰጥ በማያዳግም ሁኔታ አቋሙን ገልጧል፡፡

በአጠቃላይ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማ ለመላው ሙስሊሞች ‹‹ምርጫውን በፈለጋችሁት መሰረት በሰላም በማከናወናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!›› ሲሉ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙሃኑ መደሰቱን በገለጹበት ማግስት መላው የሃገራችን ሙስሊም ‹‹ምርጫው አይወክለኝም!›› በሚል መቃወሙ መንግስት እየተከተለው ያለው አካሄድ ከህዝብ ልቦና የሚያርቀው መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ‹‹ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!›› ሲል በፊርማው የወከላቸው መሪዎቹ ለእስር ተዳርገው የሚያስቆም ህሊና እንደሌለው መላው ሙሰሊም ህዝብ ተአምር በሚያስብል ፅናት እየገለጸ መሪዎቻችንን ከህዝቡ በመነጠል የተለየ አጀንዳ ያነገቡ ለማስመሰል የሚደረገው ሩጫ ውሃ የማይቋጥርና የማይሳካ መሆኑን መስማት ለሚችል ሁሉ አስተጋብቷል፡፡ ህዝብ መብቱን ለማስከበር ሊከተል የሚገባውን ትልቁን ሰላማዊ አካሄድ እያደረገ ባለበት ሁኔታ መንግስት ሊወጣ የሚገባውን ሃላፊነት መዘንጋት እንደሃገር የመልካም ነገር መገለጫ አይደለም፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ወትሮ የሚያቀርበውን የቀጥታ ስርጭት ማቅረብ ባይሳካለት አንኳ እስከ 8 ሰአት ድረስ ዜና መዘገብ አለመቻሉ የመንግስትን የአፈና አካሄድ ህዝባዊ ድጋፍ እንዳለው አድርጎ የማቅረቢያ ጠባብ አማራጭ እንኳን ማጣቱን ያመላክታል፡፡ በዚህም ህዝባዊ ተቃውሞው የመላው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ መሆኑን መንግስትም ሆነ ኢቲቪ በተዘዋዋሪ መንገድ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ቅጥፈት የማይሰለቸው ኢቲቪ ግን በ 8 ሰአት የዜና እወጃው ይህን በሚሊዮኖች የሚቆጠር መብት ጠያቂና ሌሎች ሚሊዮኖች ታዛቢዎችን ‹‹አይናችሁ በትክክል አላየም›› ለማለት በሚመስል ሁኔታ ‹‹አንዳንድ ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ግለሰቦች ይለቀቁ ሲሉ ጠይቀዋል›› ሲል ውሸት እንዲሰለቸን ባደረገው መስኮቱ ብቅ ብሎ የተለመደ ተግባሩን ፈፅሟል፡፡
ምንም አንኳን ህዝበ ሙስሊሙ የመበት ትግሉ እልህ አስጨራሽ ሊሆን እንደሚችል በማመን በሰላማዊነቱ መፅናትን ቢመርጥም ዛሬም የተለያዩ ትንኮሳዎች ሊፈፅሙበት ተሞክረዋል፡፡ በተለይ በአዳማ መደበኛው የዒድ ተቃውሞ ከተጠናቀቀ በኋላ ሆን ተብሎ በተፈጠረ ትንኮሳ ግርግር በመከሰቱ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውና መደብደባቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡ በተለይም የፌዴራል ፖሊስ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባና እስር ያካሄዱ ሲሆን ህዝቡ ግን መሰል ስቃይ ከመብት ትግል ሂደቱ እንደማይገታው በተግባር አሳይቷል፡፡ በአዲስ አበባ ሰላትን አስቀድሞ በመስገድ፣ የድምፅ ማጉያውን በስታዲየም ውስጥና በተወሰነ መልኩ በሴቶች አካባቢ እንዲሰማ ብቻ በማድረግ፣ ፖሊሶች በመገናኛ ሬዲዮ ‹‹ሃይል ይጨመርልን›› በሚል ህዝብ ውስጥ ፍርሃትን ለመልቀቅ በመሞከር የህዝቡን የጋራ ተቃውሞ አንድነትና ውበት ለማሳጣት ቢሞክሩም ደማቁን ተቃውሞ ግን ለደማቅ ታሪክነት ከመብቃት አላገዱትም፡፡

በመጨረሻም ለዲን ባለው ንፁህ ተቆርቋሪነትና ለወከላቸው ንፁህ መሪዎቹ ያለውን አጋርነት ለህይወቱ እንኳን ሳይሳሳ በፅናት እየገለፀ ያለው መላው ህዝባችን ዛሬም ሆነ መቼ ወደር ለማይገኝለት ድንቅ ታሪኩ አላህ ምንዳውን እንዲከፍለው እንለምናለን፡፡ በሰላማዊ ትግል መንገድ ላይ አቀበት መብዛቱን ተረድቶ እየተበደለም በሰላም በመፅናት በተለይም በዛሬው ውሎ በወጣው መርሃግብር ተቃውሞውን በማሰማትና ከፀጥታ ሃይሎች ጋርም ለሰላም በመተባበር ላሳየው አገራዊ ሃላፊነት ምስጋና ሊቸረው ይገባል፡፡ የመንግስት አካላትም መብትን መጠየቅ የዴሞክራሲ አንዱ መገለጫ ነውና በዛሬ ውሎ ያሳያችሁን አንፃራዊ በጎ የሃላፊነት ስሜት እሰየው የሚያስብል ሲሆን የተጠየቀን ጥያቄ መመለስም ሃላፊነታችሁ መሆኑን ልናስታውስ እንወዳለን፡፡ ድምፃችን ይሰማ ገጽ የዒዱን ተቃውሞ የቀጥታ ዘገባ (Live blog) መስራቷ ለህዝበ ሙስሊሙ ትክክለኛውን መረጃና ከአሚሮቻችን የሚሰጥን አቅጣጫ ለማስተላለፍ ያላትን ቃል ዳግም ያረጋገጠችበት ሆኖም ቀኑ አልፏል፡፡ ዛሬም በህዝቡ መሰል ቁርጠኝነት እና ፅኑ አቋም የትግል ጉዟችንን ዳር እናደርሳለን፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!


Thursday, October 25, 2012

የመሪዎቻችን መፈታት አለመፈታትን አስመልክቶ አንድ አንድ መረጃዎች


አንድ አንድ መረጃዎች

የኮሚቴዎቻችንና የሌሎችም ታሳሪዎቻችን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለትላንት ጥቅምት 14 እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የትላንቱ ቀጠሮ የመጨረሻቸው የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት መሪዎቻችን ትላንት ፍርድ ቤት ሳቀርቡ ቀርተዋል፡፡ ከመሪዎቻችን ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት አጭር ቃለ መጠይቅ የምርመራ ፋይሉ መዘጋቱን ገልጸው ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎም በመላው ዓለም መሪዎቻችን መፈታታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች ተናፍሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ መረጃዎች ኮሚቴዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን የሚገልጹ የነበረ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ዛሬ በእርግጠኝነት እንደሚፈቱ የሚያሳዩ ነበሩ፡፡

አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ
የዒድ የተቃውሞ ፕሮግራማችን ወጥነት እንዲኖረውና ሁሉም ሰው ፕሮግራሙን በቅደም ተከተል ያውቀው ዘንድ ዝርዝር ፕሮግራሙን በቀላሉ አባዝቶ ለማከፋፈል በሚመች መልክ ስለተቀመጠ አትመን ላልደረሳቸው ሰዎች እናከፋፍል፡፡

https://docs.google.com/open?id=0B_rPqOvDYoWseWxfeEE5cGV1SkU

Wednesday, October 24, 2012

የቢጫው ተቃውሞና አገራዊ መልእክቱ

የቢጫው ተቃውሞና አገራዊ መልእክቱ

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊና ህገ-መንግስታዊ መብታችን መጣሱን በመቃወም የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ትግልን የህይወታችን አንዱና ዋነኛው ክፍል አድርገን መጓዝ ከጀመርን እነሆ አንድ አመት ሊሞላን ነው፡፡ በዚህም የትግል ሂደት መንግስትና አጋሮቹ ለአመታት የተዘጋጁበትን በሚስጥር ዶልተው በተናጠል ሊወስዱብን ያሰቡትን የእምነትና የመብት ነጠቃ ዘመቻ ቀድመን በመረዳት ትግሉን ለነሱ ፈታኝ በሆነው የሰላማዊ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› ሜዳ ዉስጥ በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡ በዚህም ጠያቂው ጥያቄዉን በሰላም የመጠየቅ፣ መላሹም ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ መስጠት መቻል አለመቻሉ በብዙሃን ዳኝነት የሚታይበት ብቻ ሳይሆን ማን ‹‹አሸባሪ›› ማንስ ‹‹ተሸባሪ›› መሆኑ በግልጽ የሚታወቅበት ሁኔታ ጭምር ተከስቷል፡፡ ሂደቱም እነሱ እንዲፈጠር ከተመኙት ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ በመልካም አስተሳሰብ የበላይነትንና እውነተኛ ሀገር ወዳድነታችንን በተግባር ማሳየት ያስቻለ እድል ሆኗል፡፡ ዳሩ ግን የፈለጉት አልሰምር፤ ያሰቡት አልሳካ ሲላቸው በግልፅ በጠራራ ፀሃይ በመላው ዓለም እና በሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ህግንና ህገ-መንግስትን በጣሰ መልኩ ፤ ተጠያቂነትና ኃላፊነት ፍጹም የሌሉ በሚመስሉበት ሁኔታ ንፁሃን አማኞችን እምነታቸንን በማዋረድ መስጂዶቻችንን (የእምነት ቦታዎቻችንን) በመድፈር፤ ሽማግሌዎቻችንን (ኮሚቴዎቻችንን)ና ሺዎችን በማሰር ፤ ደማችንን በማፍሰስ ሽንፈታቸውን እያሳዩን ይገኛሉ ፡፡ ይህ በሚስጥር የተዶለተው ፖለቲካዊ ሴራ መክሸፍና በጠራራ ፀሃይ የሚፈፀም መንግስታዊ እብሪት ማሳያ በመሆኑም ሳይወዱ በግዳቸው ፍላጎታቸውና ማንነታቸው እርቃኑን ቀርቷል፡፡ ሙስሊሙን ለሀገር ስጋት አስመስለው በመሳል በፖለቲካው ሜዳ አሸንፈው ለእርድ እያዘጋጁት የነበረ ቢሆንም ከነሱ በተሻለ ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ስለሀገሪቱ ሰላም ዘብ የቆመ መሆኑን በታሪክ ላይረሳ በደሙ እያስከተበ ይገኛል፡፡ ትናንት ሰላማዊ የነበርን ህዝቦች በመሆናችን ዛሬ ላይ ሰላማዊ መሆን ሳይቸግረን በሰላማዊነታችን የሚደርስብንን መከራ ሁሉ በትእግስት በመቀበል ላይ ጸንተን እንገኛለን ፡፡

ድምጻችን ይሰማ በስልጥኛ " ጠንቤነ የሰመ ትልብልነ ዮል ሀኩ 10 ወሪ አቴለቅናን፡፡"

ድምጻችን ይሰማ በስልጥኛ   
https://goo.gl/b6nLF
 

የትግላችንን ጥሪ በሁሉም ቋንቋዎች ለማዳረስ የምናደርገበት ጥረት አካል የሆነውና ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የስልጥኛ ፓምፍሌት ጽሁፍና ኦዲዮ (ድምጽ) ከታች በተቀመጠው ሊንክ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጁትን ፓምፍሎቶችና ድምጾችንም ከቆይታ በኋላ እናደርሳለን፡፡ እነዚህን የተዘጋጁ ፓምፍሌቶች ፕሪንት በማድረግ፣ በፎቶኮፒና በሌሎችም መንገዶች በማባዛት ለሁሉም ማደርስ ይኖርብናል፡፡ ኦዲዮውንም (ድምጹንም) በቀላሉ ወደ ኮምፒዩተራችንና ሞባይላችን ዳውንሎድ በማድረግ በአካባቢያችን ለሚገኙ ሙስሊሞች በተለይም ወደ ገጠር ለሚጓዙ በብሉቱዝ አማካኝነት ማስተላለፍ ይኖርብናል፡፡ ወደ ገጠር የምንጓዝ ሙስሊሞች ከሁሉም በተለየ መልኩ መረጃውን ገጠር ላሉ ወዳጅ ዘመዶች የማስተላለፍ ኋላፊነት አለብን፡፡ የአሌክትሪክ ኋይል ወደሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች የምንጓዝ የሞባይል ባትሪያችንን በመቆጠብ ገጠር ላሉ ሙስሊሞች ሁሉ መረጃውን እናድርስ፡፡

ትግሉ የሁላችንም ነው፡፡ ገጠርና ከተማን አይለይም፡፡ በእድሜ፣ በጾታ፣ በስራ ባህሪ፣ በማህበራዊ ደረጃ፣ ከባህር መለስ እና ከባህር ማዶ ተብሎ አይለይም፡፡ ሙስሊም የተባለን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ ትግሉም የሚጠይቀው የሁላችንንም አስተዋጽኦ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ያነሳናቸውን ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ እስኪመልስልን ድረስ በትግላችን በመጠናከር፣ ጥያቄያችን ላልገባቸው ወገኖች ጥያቄአችንን በማስረዳት፣ ከመንግስት አካላት የሚመጣብንን ግፊት በመቋቋምና ሰላምን መርህ በማድረግ በአላህም ዱዓእ በመታገዝ ወደ ፊት እንጓዝ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

ጠንቤነ የሰመ ትልብልነ ዮል ሀኩ 10 ወሪ አቴለቅናን፡፡

ኢኘ ሙስሊምቻ በባድነ በኢትዮጲያ ትልነብርነ ተቀደ ጀመራኔ አላህ ያበነይ ዲን ባማንዋ ቦገሬት ኤንዜን ለልነብርነ በለ ያትማላን ጊዝቸ ቲተርሰቡን ነበርናን፡፡ ሂታይንገ ሊሊ ቀደ የሉክተኛይ (ሰ.ዓ.ወ) ሙአዚን በናረይ ቢላል (ረ.ዐ) ባድ አላህ ቢመኖትከ ቢቾ የጄጄቢ መርከ ዋ ታኣብ የቴክሰናን፡፡ ቢላል ባላህ ቢምኖትከ ቢቾ በያቀትላንይ በላ ለንበሮት ግድ ሆነቢያን፡፡ ቢላል እስሊሚንክ ሊያተጌፍሩይ በአረብ ባድ በጉት ማልት በነደደይ አይር ቢማግዳን ኡን ደረ አቲኑ ወቁያን፡፡ በደርክ አያቀትላነይ ኡን አጤወሩ ቲስቃይን ነበራን፡፡ ኡሃ ግን ኢክነብላን የናረይ ‹‹ አሃዱን ኣሃድ ›› ኢላነኒ ቢቾ፡፡

ሂታይ በአረቢያ ደች ሃድ ባለ የጀመረይ የኢትዮጲያ ሙሰሊመቸ ሲቃይ አውጄ ዘማን አለፋኔ በኛም ጄጃን፡፡ ተቀደ ጀመራኔ ቢንደት ባድነ ሙስሊም በውኖትነ ቢቾ ኢጄጅቢናነይ ሲቃይ አውጄም ኡፍተክ ኤገነ መጣኔ ያንዥነያን፡፡ ቢሃዲግ ኢትመራነይ መንግስት ‹‹አክራሪነትን ኢትጋደላው ›› ቢላነይ የኪዝብ ዡቦ ሙስሊም ኡኖትነ ወነጀልን ባለ ነቃኔ የኛነይ ሲቃይ ያበዝቢናነን አለ፡፡ ዲነነ ላፊቶት ዋ ላቅሮት በአቦነ ሀጅ መሀመድ ሳኒ ሱር የትጀመረይ መጅሊስ ለሙስሊሚ አድም ኢድገላን ጊዝ ሊያኝ ቀራኔ ኢስልምናይ ሊያጠፎነይ ሰበቸ ቀኚት ኢንጅ ሆናን፡፡መጅሊስ ቢተዳደርቢያነይ ደንብ መሰረት ኢመሮነይ ሰብቸ በ5 አይዶ በዲሞክራሲ ኡንጋ በሙስሊሚ በገጊኑም ኢትሜጠሮነረኮ ቢያዋለክም ሃኩ ጂንጌ ለ13 አይዶ ሃድም ምርጫ ተያሲ ፍቃድ ቤለይሙ ሰብቻ ቲጠፈ ነበራን፡፡ሂ ህገ ወጥ ሹምቸ የዲንም ሆነ የዱንያ ዒልም ተይነብረይሙየባደይ ሙስሊም ኡመት ቲቀትሉይ ነበሮን፡፡ ዪቲታይ ሰብቸ ሀለትኑም ኡንካን ሃድን ዲን ያላን ጊዝ ሊመሩ ቀራኔ ቢነብሩቢያን ቡርደ ተይቅረ ሱመቦዝ በውኖትኑምን እቻሎን፡፡መጅሊስ ቀደ ቲጅምሩይ ሙሰሊም ዮነይ ሁል ሃደ አሻኔ ሉሌነት ተይነብር ሊመርነ ናረ፡፡ ኢትራነይ ግን በረከረበይ ኡንጋ ሁል የሙስሊምነ ሀድነት ቲያጠፈን፡፡

መጀሊስነ ኢመሮን ሰብቸ ሙሰሊመይ ኡመት ሃደይ ሱፊ ገናይ ወሀቢይ ገናም ገናም ባሉ በሙስሊሚ ጉት ተዋድዶት ዋ ሃድነት አይነብራነኮ ቲለፉነበሮን፡፡ በመስጂድነ ሙሃባ ዋ ኢስላማዊ ሃድንት ለያቀርቡይ ገግ ተገግ ቲየሻኑ ዋ አያም ታያም ሰቢ ገግ ተገግከ ጎሜ ሊቲነዛዝ ጃድ ቲሊ አንዤናን፡፡መጀሊስ ሙስሊመይ ኡመት የዲነክ አሳዋ ሊያቅር ዋ በዲንከ ኢመጭቢያነይ ሁሉ ጊዝ ፈየ አሻን ቻላኔ እመረያን ኡመት ላቅኖት ቢጀምሩይም ኡሀንገ ሂነይ አደጋኔ ለዲን ኢለፎን ዋ ኢትመረሮን ሰብቸ ቲረክብ ኡሁነ ላጥፎት ደረ ኮሎ ቲልን ነበራን፡፡ ሂታይ ለዲን ያሻው ኢላነይ መጀሊስ በኡምረክ በኢትዮጲያ ደች ሀድም መሰጂድ አትቄነ ኢለችል፡፡ ሂ መጅሊስ ባይዶ አይዶ ሀጅዋ ኡመራ ኢሊሃው ባላኔ ተሰብ በሚሊዮን ኢቴለቃን ዲነትቲስበስበ ቢነብርም ሂታይ ዲነት ኤበሎ በልባሉይሙ ሰብቸእንጅ ሊገባነኮ ሙስሊሚ ኡመት ሃድም የዲን መድረሳ ታይነብረይ ነበራን፡፡ሙስሊሚ ኡመት የገነ ዲን ሰበቸኮ ትምህርተ ጋር፣ ሃኪም ጋር፣ ዩንቨርሲቲ ዋ ገነገናም ጊዝ ያተኬሹይ ናረ፡፡ ሂነይ ሁል ጊዝ ሊየሽ ቆት የናረይ መጀሊስ ሀድም ጊዝ አላሻን፡፡

ቢጲታይ ሁል ቦዝ ጊዘቸ ተትበተበ የነበረይ መጀሊስ አሸ አተሪሾት አበደየኔ ሂነይ ሁልም ሊያቀነ ኡፍተ ኮሎ ኢላነይ ሰብ አክራሪዋ አሸባሪ ባላኔ በወህኒ ጋር ቲያገባሙ ነበራን፡፡ ሂነይ ሱል ኢነቅላን ሰብ በትረከበቢ ኤት ኢታገዳን፣ ኢቶቃን፣ ያትፈራሩያን፡፡
ሂነይ ሁልም በላ ቲያመጫነይ መጀሊሰነዋ ሹማመቸከ ሙሰሊሚ ኡመት 17 አይዶ ጂንጌ ሃድ ግዝ ቢትቃቄርም ሃድም ሉሌ ጊዝ አላነዣን፡፡ ኡሃን ቲሊ ቢስልምና ደር ቦዝ ጊዝ ቲያሽ ተነበረይ መነግስት ባድ ተለፈቃኔ ተዲን ዮጠይ አህባሽነ በልቲቄበልኩም ባለ ቲያቻክ ኢትራን፡፡ አህባሽነ በግድ በሰቢ ለጣኖት መጀሊስ ተመነግስተ ተለፈቃኔ ተ ሓምሌ 2003 ጀመራኔ ዘመቻ ወጣን፡፡ ሂነይ ብልኑም የቻለይ ሙሰሊሚ ኡመት ኢለውቲቄበል ባለ ተቃውሞት ጀመረ፡፡ መንግስት ህገ መንጊስተይ ሬር አፎኛኔ በዲን ጉት ገበ ነቃኔ የከሼይ ሰብ ቲሾም የከሼይ ቲያውርደ ነበረ፡፡ ሃኩመ ሃነኩነ ኢነብሬን፡፡

ሂታይ ሁል የመንግስት ዙልም ያጬጠይ የኢትዮጲያ ሙሰሊም ተጥር 2004 ጀመራኔ 3 ሱልቸ ነቀለ ተሳላን፡፡ ሂነሚ ሱል የመንግስት ኤት ያጄጎንኮ ሁልምነ ባለነቢ 17 ሰብቸ ሜጠሪ አቀረቢ፡፡ሂታይ ሰብቻ ተመንግስተ ሰብቸ ተጎበሉ አሳዋ ቢሉም ሃድም ኢትረከባን ጊዝ ቀበጢ፡፡ ሙስሊሚ ሂነይ ያነዤ ግን በስላማዊ ኡንጋ ጠነቤክ ቲየሴማ ዮል ሃኩ 10 ውሪ ሆነያን፡፡ ሂነሚ ያቴርቢያን ያድነትዋ የ ሰደቃ ሊቃ አቀነ ሰበይ በሞላምከ ሃድ አሼይ፡፡ ሂነይ ተባድ ባድ ሰበይ ሃድ የሼይ የቆምሳን ብል ሊያቃን በኦሮሚያ-አሳሳ፣ በአማራ-ደሴ፣በአዲሰ አባባ-ባወሊያዋ አንዋር በቁርቢንገ ባማራ ክልል ግረባዋ ደጋን ሰበይ ቲቀትልዋ ቲያተቤችን አለ፡፡ የሜጠርንይሙ ስበቸዋ ኡስታዝቸ፣ ጋዜጠኛ ገን ገናም ስብ አገድቡናን፡፡ ሃድመ ተያሱ አላህ ሃድነ ለባሉ ኤት በቸ ታገዶን፡፡ የኛነይ ሱል ልሳሉ ኤት አሸ ባሪ ባሉይማን፡፡ ተጋርኑም እንደት ተላሉ፣ ቶልዲኑም ልይተልፍቁ፣ አባዴኑም ለየንዙ አሱይማን፡፡ ግን ብለ ያወለኩያን ጊዘ ቢነብርመ ሁለክ ባድ ጊነ አዋለኪ ኢለፍዲ፡፡
አኩ መንግስት የጀመረይ ሙሰሊምን የጥፎት ዘመቸ መች ያቃናንኮ አልቻሌን፡፡ መስጂድቸ በፖሊስ ትድፍሮን፣ ኢማምቸ ታገዶን፣ መድርሰ ቶነጣን፣ በቁርቢ ያነዤነይ የ ዘምዘም ባንክን አኝዤሞም፡፡ ሂነይ ሁል ቲጦቅሲ መንግስት አምቤው በባለ ስቢ ፈየክ ተጥናከረ ሊነቅ ተዝጋጃን፡፡ ሱሊ ኪመባዬ ሊረክብ ጂንጌ ቲግሊ እለቃን፡፡ ጌሰም ሴስተም ታላሃ ግነ ኢጦኝናን፡፡ ሂታይ መርከ የዲንነ ዡቦ ባሊቅ ሰቢይ ተይብል፤ አባች ኢንዳች ተይብል፣ ከተማ የጌ ተይብሊ ሁልምነ ባድ የንቂነ፡፡ ኢመጫነሚ በላ አዴኛም የክኒብሊ፡፡ዱዓ ያሲ በቀሬይ አላህ ያቀናያን ፡፡ የዱአን ወቅት ዱ ያሲ

ነስሪ የኛት
አላሁ አክበር

https://goo.gl/b6nLF
 

Tuesday, October 23, 2012

ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የአማርኛ ፓምፍሌት እና ኦዲዮ (ድምጽ)


ድምጻችን ይሰማ እያልን 10 ወራት ተቆጠሩ፡፡

ድምፃችን ይሰማ
ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀው የአማርኛ ፓምፍሌት


ድምጻችን ይሰማ እያልን 10 ወራት ተቆጠሩ፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከጥንትም ጀምሮ በእስልምናችን በሰላም እና በክብር እንዳንኖር አያሌ አጥፊ ተግባሮች ሲፈጸሙብን ቆይቷል፡፡ ይህ በነብዩ ሙአዚን አያታችን ቢላል ላይ የደረሰውን ስቃይ እና እንግልት ያስታውሰናል፡፡ ቢላል በአላህ በማመኑ ብቻ ሕይወቱን በስቃይ እንዲመራ ተገዷል፡፡ ቢላል እስልምናውን እንዲለቅ የአረቢያ የበረሐ አሸዋ ላይ በጠራራ ጸሐይ እንዲተኛ ተደርጎ ተገርፏል፡፡ ጀርባው ላይ ድንጋይ ተጭኖበት የስቃይን ጣሪያ ተመልክቷል፡፡ የአባታችን ቢላል ምላሽ ግን ‹‹አሀዱን አሀድ›› ብቻ የሚል ነበር፡፡

ይህ በአረቢያ ምድር በቢላል ላይ የተጀመረው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስቃይ ዘመናትን ተሻግሮ ዛሬም ደርሷል፡፡ በየዘመኑ
በእናት አገራችን ሙስሊም በመሆናችን ብቻ ይፈጸምብን የነበረው የመብት ጥሰት ዛሬም መልኩን ቀይሮ እየተመለከትነው
ነው፡፡ ኢሕአዴግ መራሹ መንግስት ‹‹አክራሪነትን እዋጋለሁ›› በሚል የሐሰት ሽፋን ሙስሊም መሆንን ከወንጀል በመቁጠር
ስቃያችንን እያበዛው ነው፡፡ ዲናችንን ለማስፋፋት እና ለማስተማር በውድ አባቶቻችን በእነ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ የተቋቋመው መጅሊስ ለእኛ ለሙስሊሞች አንዳች ኽይር ነገር ከማከናወን ይልቅ በጸረ እስልምና እንቅስቃሴ ውስጥ ዋነኛ ኃይል ሆኗል፡፡ መጅሊስ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት አመራሮቹ በየአምስት አመቱ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሕዝበ ሙስሊሙ እንዲመረጡ ቢደነገግም ለ13 ዓመታት ያህል ምንም ኣይነት ምርጫ ሳይደረግ ተቋሙ በሕገ ወጥ አመራሮች ሲበዘበዝ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ሕገ ወጥ አመራሮች በቂ የአካዳሚክም ሆነ የዲን እውቀት ሳይኖራቸው ሕዝበ ሙስሊሙን በዲኑም በዱንያውም ሲበድሉት ኖረዋል፡፡ የእነዚህ አመራሮች ግላዊ ስብእናም አንድ የሃይማኖት ተቋም አመራር ሊኖረው የሚገባውን የሞራል ብቃት ሊይዙ ቀርቶ ብዙዎቹ
በማኅበረሰባችን ውስጥ መልካም ባልሆነ ስም የሚታወቁ ናቸው፡፡

ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የአማርኛ ፓምፍሌት እና ኦዲዮ (ድምጽ)



ዒድን አስመልክቶ ወደ ገጠር ለሚሄዱ ወገኖቻችን የተዘጋጀውን የአማርኛ ፓምፍሌት እና ኦዲዮ (ድምጽ) ከታች በተቀመጡት ሊንኮች ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጁትን ፓምፍሎቶችና ድምጾችንም ከቆይታ በኋላ እናደርሳለን፡፡ እነዚህን የተዘጋጁ ፓምፍሌቶች ፕሪንት በማድረግ፣ በፎቶኮፒና በሌሎችም መንገዶች በማባዛት ለሁሉም ማደርስ ይኖርብናል፡፡ ኦዲዮውንም (ድምጹንም) በቀላሉ ወደ ኮምፒዩተራችንና ሞባይላችን ዳውንሎድ በማድረግ በአካባቢያችን ለሚገኙ ሙስሊሞች በተለይም ወደ ገጠር ለሚጓዙ በብሉቱዝ አማካኝነት ማስተላለፍ ይኖርብናል፡፡ ወደ ገጠር የምንጓዝ ሙስሊሞች ከሁሉም በተለየ መልኩ መረጃውን ገጠር ላሉ ወዳጅ ዘመዶች የማስተላለፍ ኋላፊነት አለብን፡፡ (ለኦዲዮው ለአማራጭነት ሁለት ሊንኮችን አስቀምጠናል) የአሌክትሪክ ኋይል ወደሌለባቸው የገጠር አካባቢዎች የምንጓዝ የሞባይል ባትሪያችንን በመቆጠብ ገጠር ላሉ ሙስሊሞች ሁሉ መረጃውን እናድርስ፡፡

ትግሉ የሁላችንም ነው፡፡ ገጠርና ከተማን አይለይም፡፡ በእድሜ፣ በጾታ፣ በስራ ባህሪ፣ በማህበራዊ ደረጃ፣ ከባህር መለስ እና ከባህር ማዶ ተብሎ አይለይም፡፡ ሙስሊም የተባለን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ ትግሉም የሚጠይቀው የሁላችንንም አስተዋጽኦ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ያነሳናቸውን ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ እስኪመልስልን ድረስ በትግላችን በመጠናከር፣ ጥያቄያችን ላልገባቸው ወገኖች ጥያቄአችንን በማስረዳት፣ ከመንግስት አካላት የሚመጣብንን ግፊት በመቋቋምና ሰላምን መርህ በማድረግ በአላህም ዱዓእ በመታገዝ ወደ ፊት እንጓዝ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!

የሰላም አምባሳደሮቻችን በአፋጣኝ ይፈቱልን!

 
የሰላም አምባሳደሮቻችን በአፋጣኝ ይፈቱልን!

ኢስላም ‹‹ሰላም›› ከሚለው የአረብኛ ቃል ተመዝዞ የወጣ ሀረግ እንደሆነ ሙስሊም ምሁራን ደጋግመው ይናገራሉ፡፡ እጅግ ትክክልም ናቸው፡፡ ኢስላም የሰላምና የሰላማዊነት ተምሳሌት፣ የፍትህና ፍትሀዊነት ቀንዲል ነበር፤ ነውም፤ ይሆናልም! ይህን መሰረታዊ ባህሪውን በአማኞች ዘንድ ለማስረጽም ከእያንዳንዱ ሶላት በኋላ ‹‹አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ! የሰላምም ምንጭ ነህ! የልቅናና የቸርነት ጌታ ሆይ፤ የተባረክህ ነህ!›› ስንል ጌታችንን እንድናወድስ ያስተምረናል፡፡ የጀነት ሰዎች ሰላምታ ‹‹ሰላም›› የሚለው ቃል መሆኑን በመንገርም ወደሰላም እናይ ዘንድ ያጓጓናል፡፡

ምንም እንኳን ዛሬ ‹‹የሰላም አምባሳደሮቻችን!›› ስንል የመሰከርንላቸው ኮሚቴዎቻችን ‹‹አሸባሪ›› እና ‹‹ሁከት ቀስቃሽ›› ተብለው ዘብጥያ ቢወርዱም ያሳዩን የሰላማዊነት ተምሳሌት ከሚለጠፍባቸው የሃሰት ውንጀላ በላይ ደምቆ የሚታይ፣ ልቆ የሚወጣ እውነታ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እኒህ ለትግሉ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ምርጥ የኢስላም ልጆች በቅድመ ትግሉም ሆነ በድህረ ትግሉ ወቅት ሁሉ ሰላማውያን ነበሩ፡፡ ካሁን ቀደም በነበራቸው ህይወት በህብረተሰባቸው ውስጥ ሰላምና መቻቻልን ለማስፈን፣ አብሮ የመኖር ባህልን ለማዳበር ብዙ ለፍተዋል፡፡ ከውስጣቸው ጥቂት የማይባሉት ሰባክያን የነበሩ መሆናቸውም ይኸንን እውነታ ጎልቶ እንዲወጣ አመቻችቷል፡፡

እንዲህ ናቸው የኛ ጀግኖች (ክፍል 1)

 ድምፃችን ይሰማ
እንዲህ ናቸው የኛ ጀግኖች (ክፍል 1)

የጠራው የእስልምና መንገድ ከኛ ለመድረስ በርካቶች ብርቱ ትግል አድርገዋል፡፡ ሕይወታቸውንም መሰዋእት አድርገው አቅርበዋል፡፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን ወቅቱ የሚጠይቀውን የትግል አማራጮች አሟጠው በመጠቀም ታላቅ ጀብዱ ፈፅመው ሙስሊም ሆኖ በኢትዮጵያዊነት መኖር ያሳፍር የነበረበትን ዘመን ላይመለስ ሸኝተውታል፡፡ አሁን የምንገኝበት ትውልድ ደግሞ ወቅቱ የሚጠይቀውን የትግል ዘዬ በመከተል ንቁ ሙስሊም በመሆንና በኢትዮጵያዊነት መካከል ግርዶሽ ለማበጀት የሚያሴሩ ሃይሎችን ‹‹አይሳካላችሁም›› ሲል በአደባባይ አንገታቸውን አስደፍቷቸዋል፡፡ የቀዳሚው ዘመን ጀግኖችን የመሩ ድንቅ ስብእናዎች ብዙዎችን
እንደማረኩ ሁሉ የኛን ትውልድ የህልውና ትግል የመሩት ድንቅ ስብእናዎችን መላው ህዝባችን ‹‹እንዲህ ናቸው የኛ ጀግኖች›› እንዲል የኩራትን አክሊል ደፍቶላቸዋል፡፡

የኛ ጀግኖች ብዙ ሁነው እንደ አንድ የቆሙ፣ አንድ አካል ሁነው ለወገን የበቁ፣ ተገደው የገቡበትን የመሪነት ሚና አፍቅረው የሚሰሩ፤ እራሳቸውን ለህዝብ የሰጡ ናቸውና ለነሱ ያለንን የጠለቀ ፍቅር ሁሌም እንዘክራለን፡፡ ኮሚቴዎቻችን ከእስር በፊት በነበራቸው የአብሮነት ቆይታ በተግባር ያሳዩንን ሰናይ ነገር ሁሉ ዘርዝረን ባንዘልቀውም በፈለጋቸው ፀንተን መቆማችንን ለማውሳት በጥቂቱ ‹‹እንዲህ ናቸው የኛ ጀግኖች›› ስንል በተከታታይ ክፍሎች በመልካም እናወሳቸዋለን፡፡

የኛ ጀግኖች ነፍሳቸውን በአላህ ፍራቻ የገሩ ለአምላካቸውና ለሰው ልጆች ጥልቅ ፍቅር የሰጡ ናቸው፡፡ ለሚያፈቅሩት ሲሉ ሁሉ ነገራቸውን የሰጡ፣ ቃላቸውን የሞሉ ታማኝ መሪዎቻችን ናቸው፡፡ ያደርጓቸው በነበሩ እያንዳንዷ እንቅስቃሴ በህዝብ የስሜት ግለት እና በጠላት ተንኮል መክሸፍ ሳይኩራሩ ሁሌም የአላህን እገዛ ተደፍተው የሚማፀኑ ነበሩ፡፡ ሹራዎቻቸው በኢስላማዊ አደብ ከመቃኘታቸው በላይ ከውሳኔ በፊት ከልብ ተጨንቀው በዚክር እና በዱዓ ታግዘው ነበር የሚወስኑት፡፡ በትግሉ ሂደት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ወንድሞችና እህቶች የሚያፈልቋቸው አማራጭ ሃሳቦች ሁሌም በጸሎት እንዲታገዙ ይሹ ነበር፡፡ በየሹራቸው እለት ከአባላቱ ቢያንስ የተወሰኑቱ ቀኑን በፆም ያሳልፉ ነበር፡፡ ከፊሎቹ በሹራዎች መሃል ምላሳቸውና ቀልባቸው በዚክር ተሰብስቦ የሌላ አለም ሰው እስኪመስሉ እሩቅ ይጓዙ ነበር፡፡ ውሳኔያቸው ከምንም በላይ አላህን እንዳያስከፋ በመቀጠልም ለሙስሊሙ ኡማ የተሻለ ነገር እንዲያመጣ ሁሌም ይጨነቁ ነበር፡፡ ወጣቶቹ በእድሜ ለገፉት ያደርጓቸው የነበሩ መተናነሶች በእድሜ የገፉት ለወጣቶቹ ያሳዩት የነበረውን ፍቅር የወለደው አክብሮት በመመልከት የአብሮነት መስተጋብራቸውን በአላህ የተመራ ብለን እንድንደመድም በሩን ይከፍትልናል፡፡

የኛ ጀግኖች አላህ በምድር ላይ ሳሉ ያስቀመጠባቸውን ሃላፊነት ተወጥተው ጌታቸውን መገናኘት የሚመኙ ባላደራ መሪዎች ናቸው፡፡ ከሚጋፈጡት ታላቅ ጠላት ግዝፈት ይልቅ የሚረዳቸው አላህን እገዛና ቅርበት በፅኑ ያምናሉ፡፡ በጌታቸው ላይ ያላቸውን ፅኑ እምነት በመመካት ለአንድ አፍታ እንኳ ተስፋ መቁረጥ ታይቶባቸው አይውቅም፡፡ በተለይ በግፍ ወደ እስር ሊወረወሩ ቀናትና ሰአታትን እየቆጠሩ በነበሩባቸው ግዜያት ያሳለፏቸው የአብሮነት ጊዜያት እራሳቸውን ይበልጥ ወደ አላህ ያቃረቡበት፣ የተጣለባቸውን ሕዝባዊ ሃላፊነት ከተወጡት አላህ እንዲመድባቸው ጽኑ ዱዓእ ያደረጉበት፣ የጀመርነው የመብት ማስከበር ትግል መርህ ባደረገው እውነተኝነት (ሲድቅ) እና ሰላማዊነቱ ፀንቶ እንዲቀጥል የአደራ መልእክት ያስተላለፉበት፣ ከምንም በላይ ደግሞ ከፊት ለፊታቸው የሚታያቸውን ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ በስነ ልቦና ዝግጁ የሆኑበትና መስዋእትነት የከፈሉለት ህዝብ አላህ ድልን አጎናጽፎት የደስታውን እለት እንዲያሳያቸው የተመኙበት ወቅት ነበር፡፡

እኛም የተጫነንን ቀንበር ከጫንቃችን ሳናነሳ ወደ ቤታችን እንደማንመለስ እስከአሁን እያስመሰከርን እንገኛለን፡፡ ለመሪዎቻችን ያለን ጥልቅ ፍቅር ለአላማችን ካለን ፅናት ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ሁለቱን ለይተን ማየት አንችልም፡፡ የጥያቄዎቻችንን መመለስ እስክናረጋግጥ ከኛ ጀግኖች ጋር ቃል በተጋባነው ሰላማዊ አማራጭ እንደምንፀና ሁሉ፤ ውድ መሪዎቻችንን ዳግም ከማግኘት የሚያግደንን መሰናክል ሁሉ በማለፍና መክፈል የሚገባንን መሰዋእትነት ሁሉ በመክፈል የድል ማማ ላይ እንደምንወጣ ዳግም ቃላችንን እንሰጣለን፡፡ በእነዚህ ቅን የአላህ ባሮች ላይ የምትሰነዘር ትንሿ የቅጣት ጅራፍ ዞሮ ዞሮ ሰንዛሪውን ትገርፋለች፡፡ ፀቡም ከአላህ ጋር በመሆኑ አመፀኞች የታሪክ መማሪያ ይሆኑ ዘንድ የእጃቸውን ያገኛሉ፡፡ ይህ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ ክበር!

Detail Report of Radio Bilal & VOA on The Gerba Massacre by The Ethio. F...

Monday, October 22, 2012

leyu getem sele comitewochachen

ከቀናቶች ሁሉ በላጭ በሆኑት ቀናቶች በላጭ የሆነ ዒባዳ!


ከቀናቶች ሁሉ በላጭ በሆኑት ቀናቶች በላጭ የሆነ ዒባዳ!

የዙልሒጃ ወር አስሩ የመጀመሪያ ቀናት ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡ በነዚሁ ቀናት የሚሰሩ የአምልኮ ተግባራት (ዒባዳዎች) በሌሎች ቀናት ከሚሰሩት ሁሉ በላጭ መሆናቸውን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናግረዋል፡፡ አቅሙ ለቻለ ሰው ሐጅና ዑምራ ማድረግ በነዚህ ቀናት ውስጥ ሊሰሩ ከሚችሉ የአምልኮ ተግባራት ሁሉ በላጩ ነው፡፡ ጾም መጾም፣ አላህን በብዛት ማወደስ፣ ተክቢራ ማለት፣ ቁርአንን ማንበብ፣ በጥቅሉ መልካም የተባሉ ተግባራትን ሁሉ በነዚህ ቀናት መፈጸም እጥፍ ድርብ ምንዳ ያስገኛል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘጠነኛውን ቀን (የፊታችን ሐሙስ) መጾምን አስመልክተው ‹‹ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል›› ብለዋል፡፡ በላጭ የሆኑ ዒባዳዎችን መርጦ በነዚህ በላጭ በሆኑ ቀናት መፈጸም ብልህነት ነው፡፡

The First Hijrah Foundation Press Release

The First Hijrah Foundation Press Release

ሠላማዊ ትግላችን አሁንም አይቀለበስም!!

ሠላማዊ ትግላችን አሁንም አይቀለበስም!!

ትግላችን ወንድሞቻችንን በመግደል አይገታም!!!

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ወሎ በደጋን እና ገርባ ከተማዎች የተፈፀመው ጥቃት ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እና ለበርካታ ወራት ይዘን የዘለቅነው ፍፁም ሠላማዊውን የመብት ጥያቄ በምንም መልኩ ወደ ሌላ አቅጣጫ አይቀለብሰውም፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድነት ስሜት ህገ መንግስትዊ ስርዓቱን ባከበረ መልኩ ያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ያገኙ ዘንድ ለተቃውሞ አደባባይ ላይ በዋለባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ሂደቱ መልኩን ቀይሮ ኹከትን እንዲላበስ ብሎም ወደ ብጥብጥ እንዲያመራ ተከታታይ ሙከራዎች ተደርገውበት አልፏል፡፡ በእነዚህ ሙከራዎቻቸው ዛቻ፣ ድብደባ፣ እስራት እና የህይወት መስዋዕትነትን ከፍለናል፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ እያለ ያለ ምንም የአቋም መዋዠቅ ትገሉ ሠላማዊነቱን ጠብቆ እንዲዘልቅ ሙስሊሙ ኡማ ያላሰለሰ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በመስከረም 27 ምርጫ እንኳን እነሱ ያለ ከልካይ በሕገ ወጥ ድርጊታቸው እንዳሻቸው ሲፈነጥዙ ሙስሊሙ ፍፁም ሠላማዊነቱን አስመስክሯል፡፡ በደቡብ ወሎ ደጋን እና ገርባ አካባቢዎች በትናንትናው ዕለት የተስተዋለውም የመንግስት ጸብ አጫሪነት የዚሁ የትንኮሳ እና ጸረ ሕዝብነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ክስተቱ የመላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ሰላማዊ የመብት ማስከበር ትግል አቅጣጫ በማስቀየር ወደ ብጥብጥ እና ኹከት በመለወጥ ብሎም ሙስሊሞች በዚህ ሂደት ተደናግጠው ከመታሰር፣ ከመደብደብ ብሎም ከመሞት አርፎ መቀመጥን እንዲመርጡ ከያዙትም አቋም እንዲያፈገፍጉ የታለመ መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን፡፡

በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች ሙስሊሙ ከምርጫ ራሱን እንዳገለለ ሁሉ የደጋንና ገርባ አካባቢ ሙስሊሞችም በገቡት ቃል መሰረት በአካባቢያቸው ምርጫ አልተካሄደም፡፡ በዚህ የተበሳጩት የመንግስት አካላት ትናንት የተፈጠረው አደጋ እንዲከሰት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ከርመዋል፡፡ ዕለቱ መልካም አጋጣሚ እንሚሆንላቸው በመገመት እቅዳቸውን ለማሳካት ተንቀሳቀሱ፡፡ የመንግስት የደህንነት አካላት ወደ አካባቢው በማቅናት ከደሴ-ሰመራ መተላለፊያ የሆነውን መንገድ ሕዝቡ በድንጋይ እንዲያጥር ከፍተኛ የማነሳሳት ስራ አከናወኑ ፤ በመቀጠልም ሕዝቡን በቀጥታ ወደ ረብሻ እና ሁከት ማስገባት እንዲያስችላቸው ይህንን ወሬ በማራገብ ከ 10 የማያንሱ የአካባቢውን ታዋቂ ግለሰቦች ከህግ አግባብ ውጪ በሆነ አካሄድ ለማፈን ሙከራ አደረጉ፡፡ የአካባበቢው ህብረተሰብ ይህንን ህገወጥ አፈና ለመቃወም ባደረገው ሙከራና ተቃውሞ የተሰጠው ምላሽም ጥይት ሆኖ የለየለት ኹከት እንዲፈጠር ደህንነቶች ክፉኛ ተሯሯጡ፡፡

በዚህ ሁኔታም የዝሁርን ሶላት ለማከናወን ወደ መስጊድ የገባውን ሰላማዊውን ሕዝብ ከመሬት ተነስተው መደብደብ፣ ማሰር እና በጥይት መቁላት ጀመሩ፡፡ ይሁንና የአካባቢው ነዋሪ በከፍተኛ ብስለት ሁኔታው የባሰ እልቂት እንዳያስከትል የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ተረባረበ፡፡ ይህ የተጠና ሴራ በአርሲ አሳሳ ከተፈፀመው ጋር ተመሳሳይ መሆኑ መንግስት ያዘለውን ተንኮል ይበልጥ እንድንረዳ፣ ወደፊትም ከመሰል ድርጊቱ ሊቆጠብ ዝግጁ ያለመሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡ ሰላማዊ እና ንፁኃን ዜጎችን በመደብደብ፣ በማቁሰል እና በጭካኔ በመግደል ‹‹የቆሰሉትና የተገደሉት አክራሪዎች ናቸው›› ይለናል፡፡ በገርባ እና በደጋን የሆነውም የዚህ ትክክለኛ መገለጫ ነው፡፡ በአካባቢው መንግስት ራሱ ሆን ብሎ የፈጠረው ትንኮሳና ያነሳሳው ረብሻ የዜጎችን ጉዳት አስከትሏል- የንፁኃንን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ የተገደሉት ንፁኃን ዜጎች አክራሪዎች ናቸው ይለናል፡፡ ኢትዮጵያችን ውስጥ የመብት ጥያቄ በማንሳት ሠላማዊ የመብት ትግል እያካሄደ የሚገኝ ዜጋ በሙሉ አክራሪና አሸባሪ የሚል ተቀፅላ ይወጣለታል፡፡

ይህ ፅሁፍ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ከአስር በላይ ወገኖች ቆስለው በደሴና በአካባቢው በሚገኙ የሕክምና ማዕከላት እርዳታ እያገኙ ሲሆን አራት የሚሆኑቱ ደግሞ ሸሂድ መሆናቸውን ድምፃችን ይሰማ አረጋግጣለች፡፡ መንግስት ‹‹አንድ ፖሊስ ተገድሏል›› ብሎ ቢገልጽም እስከአሁን ለዚህ ማረጋገጫ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ከዚህ ቀደም በአሳሳ ተከስቶ በነበረው ኹከት መንግስት ‹‹ፖሊስ ተገድሏል›› ብሎ መግለጫ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ሐሰት ሆኖ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ መንግስት ዛሬም ተመሳሳይ ድራማ እየፈጸመ እንደሆነና የአሁኑም ክስተት ሕዝቡንም ሰላም አልባ አድርጎ ለመሳል እያደረገ ያለው ጥረት አንድ አካል እንደሆነ እናስባለን፡፡ ይህ አገርንና ህዝብን ከሚመራ መንግስት ፈጽሞ የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር በመሆኑ ሊወገዝ ይገባዋል፡፡ ይህ ሕገ ወጥና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ሰላማዊ መብት የማስከበር ትግል አቅጣጫ ወደ ብጥብጥ እና ኹከት በመለወጥ ሙስሊሞች በዚህ ተደናግጠው ከያዙት አቋም እንዲያፈገፍጉ እና ከመታሰር፣ ከመደብደብ ብሎም ከመሞት አርፎ መቀመጥን እንዲመርጡ ለማስፈራራት የታለመ፣ ጭንቀት የወለደው ርካሽ ተግባር ከመሆን የዘለለ አይደለም፡፡

ሁኔታዎች ሳይፈለጉ በግድ መልካቸውን እንዲለውጡ እየተደረገበት ባለበት በዚህ ሰዓት ለመንግስት እና ለመላ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የሚከተለውን እውነታ በድጋሜ ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ መላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላለፉት አስር ወራት ይዘውት የዘለቁት የመብታችን ይከበር ጥያቄ በይዘቱ እጅግ ቀላል፣ ግልፅና ፍፁም ሃይማኖታዊ፣ እንዲሁም ከተለጠፈበት የሙስሊም ዜጎችን የአኗኗር ባሕል ግምት ውስጥ ያላስገባ አጓጉል ታፔላ የራቀ መሆኑን ኢትዮጵያዊያን እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን፡፡ መንግስት ጥያቄዎቹን ከጥያቄው ባለቤት ጋር በግልፅ መድረክ በመገኘት እና መፍትሔ በመፈለግ አደባባይ የወጣውን እና ያኮረፈውን የአገሪቱን ግማሽ አካል ህዝብ ቤቱ እንዲመለስ ከማድረግ ይልቅ ህጋዊ ኮሚቴዎቻችንን ማሰር፣ ታዋቂ ዳዒዎቻችንን እና ግለሰቦችን ማሰር እና ክፋት የተሞላባቸውን ከኃላፊነት የራቁ ተግባራት መፈፀምን መርጦ እነሆ ይህንኑ እየተገበረ ይገኛል፡፡

ሙስሊሙ ሕዝብ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ይሟሉና ሃይማኖታዊ፣ ፍትሐዊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይካሄድ›› ቢልም፣ ይህ ባለመሆኑም የተነሳ ሕዝቡ ተአቅቦ ቢያደርግም የመንግስት ካድሬዎች በየግለሰቡ ቤት ሁሉ በመግባትና በማስፈራራት ያልተሳካ ጥረታቸውን አድርገው በሚዲያቸው ‹‹ምርጫ አድርገናል›› ብለውናል፡፡ ህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲህ እንዲህ እያለ በሕጋዊነት ሽፋን ቢገፋም የፈጠረው አዲስ ነገር ግን የለም፡፡ ይልቁንም የሙስሊሙን ሕዝብ ንቃት እና ብስለት ይበልጥ እያሳደገው መሄዱ እሙን ሆኗል፣ በሰላማዊ የመብት ትግል ሂደቱም እንዲገፋበት ሆኗል፡፡ ሆኖም ይህ ሃይማኖት ነው:: ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንደመሆናችን መጠን ያገራችንን እና የሕዝቦቿን ሰላም በመጠበቅ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅድልን መርሕ መሠረት ሠላማዊ ትግሉ የሚጠይቀውን ሁሉ በመክፈል እስከመጨረሻው የስኬት ማማ ለመድረስ ዳገቱን በጥፍራችንም ቢሆን እየቧጠጥን እልህ አስጨራሹን ጉዟችንን እንቀጥላለን፡፡

በዚህ ከፍተኛ ፅናትን በሚጠይቅ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ ሂደትን ብቻ በመከተል ለመታገል ቁርጠኛነታችንን ስንገልፅ መሠል አስደንጋጭ መሰናክሎችን ማለፍ ግድ እንደሚለን ትምህርት እየወሰድን ታሪክ መስራታችንን እንደጀመርን እንጨርሳለን - ኢንሻአላህ! የአሚሮቻችንን መታሰር የሚያክል የከፋ በደል ተፈፅሞብን እያለ አዲስ አበባን በሚያክል ሰፊ እና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባለበት ከተማ ምን ሊፈጠር ይችል እንደነበር መገመት ከባድ የነበረ ባይሆንም ኮሽታ ሳይፈጠር ሰላማዊ ትግላችን ቀጥሏል፡፡ ከዚያም በኋላ ቢሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰላማዊ ትግላችንን እና ሰላማችንን የሚያደፈርሱ የመንግስት ትንኮሳዎችን በተደጋጋሚ አስተናግደን አልፈናል፡፡ እንደ መንግስት እና የደህንነት አካላት ምኞት ቢሆንማ ኖሮ ሚሊዮኖች ለተቃውሞ አደባባይ በወጡበት አጋጣሚ መቶዎችንነና ሺዎችን በጨረሱ ነበር፡፡ ሆኖም የሙስሊሙ ሕዝብ በሣል እና ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ቀዳዳዎችን ሁሉ ያጠበበ መሆኑ ረፍት ነስቷቸዋል፡፡ እስካሁን ያስመዘገብናቸው ድሎች አያሌ ከመሆናቸውም በላይ በሰላማዊነታችን ብቻ ላይ ፀንተን ወደፊት እንድንቀጥል ያገኘነውን ትምህርት ተጠቅመን ታሪክ መስራታችንን እንደጀመርን እንድንጨርስ ግድ ይሉናል-ኢንሻ አላህ፡፡ ሂደታችን ረጅምም በመሆኑና ስር ነቀል ለውጥ የሚጠይቅ በመሆኑ አቋራጭ ኹከት ቀስቃሽ መንገዶች ተመራጭ መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሕዝቡም ይህንን እውነታ ተረድቶ ላለፉት አስር ወራት የመንግስት የደህነነትና የፀጥታ አካላት ሲያደርጉ የነበሩትን ርካሽ ተግባር የማስቆም ስራዎቻችንንም አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡ ይህ ከፍተኛ ትዕግስትን የሚጠይቅ መሆኑ በበደል ላይ እያለን ከመሆኑ ጋር በጣም ከባድ ቢሆንም ያስመዘገብነውን ድል ጠብቀን የተሻለ ተጨማሪ ድል ባለቤት ለመሆን ይህንን በብለሃት ማለፍ ይጠበቅብናል፡፡

በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ፍፁም ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማት መብታቸውን ለማስከበር በሚያደርጉት ትግል መስዋዕት የሆኑትን የእምነት ወንድሞቻችንን አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በሸሂድነት እንዲመዘግባቸው ዱዓችን ነው፤ አላህ ይቀበለን

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

Sunday, October 21, 2012

Two Muslims Confirmed Dead, Several Wounded in Gerba


News Update!!

Two Muslims Confirmed Dead, Several Wounded in Gerba

Two Muslims were killed and several others were seriously injured by police in Gerba town, Qallu Woreda, South Wollo Zone of the Amhara Regional State, local sources said. Gerba is 403-km east of the capital Addis Ababa.

State-run Ethiopian Television confirmed the killing of the two Muslims. The report described the slain Muslims “extremists.” The state-run TV also reported one police officer was killed, while another was wounded.

Ethiopian Muslims across the nation have been staging peaceful protests against government interference in religious affairs since December 2011.

The latest killing in Gerba raises the number of Muslims killed by government security forces to six. on May 4, Federal Police forces killed four Muslims in Asasa town, Arsi Zone of the Oromia Regional State.

Ethiopian Muslims have been sternly opposing an attempt made by the government, in collaboration with the unelected leadership of the Supreme Council of Islamic Affairs, to impose a Lebanese-born sect called al-Ahbash on the country’s Muslims.

Despite the determined opposition of the country’s Muslims against the government’s unconstitutional moves, now in its eleventh month, the government seemed obstinate to address the legitimate concerns of the Muslim communities.

In July, the government arrested members of a Committee elected by the country’s Muslims to present their plights to the government, as well as Muslim community members, journalists and artistes. All Muslim media outlets have also been banned since July.
Ethiopian Muslims Continue Protests, as New PM Continues the Legacy of Defiance

A couple of days after Ethiopia’ new Prime Minister Hailemariam Desalegn voiced his government’s stubborn stance towards the legitimate demands of the country’s Muslims, the faithful continued their nationwide protests against government interference in religious affairs.
ድምፃችን ይሰማ


በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በጉባ ላፍቶ ወረዳ በተካሄደው “የመንግጀሊሰ” ምርጫ ፣ በሳንቃ ቀበሌ የተመረጡት የቀበሌው የመጅሊሰ ሰብሳቢ፣ ዋና ጸሀፊውና ሌሎች ተመራጮች የአህባሽን አስተምህሮ ይቃወማሉ፣ አህባሽን አይቀበሉም እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ተቃውሞ ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል ምክንያት አሸናፊነታቸው ተሰርዞ በምትኩ ሌላ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑን ምንጮች አስታወቁ፡፡ የምርጫው ውጤት እንዲታገድ ትእዛዙን ያስተላለፉት የወረዳው አስተዳዳሪ ሲሆኑ፣ እንዲታገዱ የተደረጉትም የሳንቃ ቀበሌ መጅሊስ ሰብሳቢ ሼክ አህመድ ያሲን፣ ዋና ጸሀፊው አቶ ሙሀመድ ሞላ፣ የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አቶ ኢብራሂም ሁሴንና ሼህ አሰፋ ይማም ናቸው። በአካባቢው 25 ሰዎች ተመርጠው አምስቱ ስራ አስፈጻሚ፣ 20 ዎቹ ደግሞ የምክር ቤት አባላት የሆኑ ሲሆን፣ለወረዳ ምርጫ እርሳቸውና ጸሀፊያቸው ተመርጠው እንደተላኩ ታውቋል። በተሰረዙት ሰዎች ምትክ በቀበሌው አዲስ ምርጫ ሊደረግ እንደሆነም ታውቋል፡፡

ድምፃችን ይሰማ

ማሳሰቢያ
በአማራ ክልል አንድ አንድ አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂ ሐይሎች በሙስሊሙ ላይ እየወሰዱት ያለውን ሕገ ወጥ እርምጃ በተለይም በርካታ ሙስሊም ወጣቶችን ወደ ወህኒ በመጋዝ የአካባቢውን ሙስሊም ኅብረተሰብ ወደ ሐይል እርምጃ እንዲገባ ግፊት እያደረጉበት ይገኛል፡፡ ገርባን በመሳሰሉ አካባቢዎችም ግጭቶች እየተከሰቱ እንደሆነና ይህም ወደሌሎች አጎራባች ክልልች እየተዛመተ እንደሆነ ከአካባቢው የሚወጡት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ከመሰል የጸጥታ ችግሮች በመራቅ ሁኔታውን በትእግስትና እስከአሁን ሲያሳይ በነበረው ኢስላማዊ አደብ እንዲያሳልፈው እየጠየቅን እነዚህ የመንግስት የጸጥታ ሐይሎች እየወሰዱት ያለው እርምጃም አገሪቷን ወደ ከፋ ብጥብጥ የሚከታት መሆኑን አውቀው ከየትኛውም የሐይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አበክረን እንገልጻለን፡፡

ድምፃችን ይሰማ
ሰበር ዜና!!
በዛሬዉ እለት እሁድ በአማራ ክልል በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያሰሙይገኛሉ፡፡ የዚህ ምክንያትም አብዱ አህመድ የተባለ መምህርን የመንግስት ሃይሎች በማፈን ሊወስዱት ስላሉ እንደሆነ በቦታው ያሉ ሰዎች ገልፀዋል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ባሳየው ቆራጥ አቋም ወንድማችን ሊለቀቅ ችሏል፡፡ የታላቁ መስጂድ ኢማም የሆኑት የሸኽ አሊ ቤትም ያለፍርድ ቤት ማዘዣ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡ ይህን በመቃዎም ሴት ወንዱ ወጣት ሽማግሌ ሳይል ሁሉም ህብረተሰብ በከተማይቱ መንገዶች ላይ የተቃውሞ ድምፁን በማሰማት ላይ ነው፡፡

ድምፃችን ይሰማ

ተጨማሪ ማሳሰቢያ

ከደሴና ከሌሎችም አካባቢዎች የመንግስት አድማ በታኞችና የጸጥታ ኋይሎች ከፍተኛ ተቃውሞ ወደተነሳባቸው ገርባና ደጋን ከተሞችና አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች በማቅናት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ገርባ በከፍተኛ ውጥረት ላይ የምትገኝ ሲሆን ከተማዋም በታጣቂ ኋይሎች ከበባ (siege) ላይ ናት፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በከተማዋ መስጊዶች አሁንም ተክቢራ እያደረገ እንደሆነና አድማ በታኞቸም አስለቃሽ ጋዝ በሰላማዊው ሕዘብ ላይ በመተኮስ ላይ መሆናቸውን የዓይን እማኞች እየገለጹ ነው፡፡ መንግስት ለሁሉም የሕዝብ ጥያቄ የኋይል እርምጃን እንደ ብቸኛ አማራጭ እየተመለከተ መሆኑ በጣም አሰሳቢ ነው፡፡ ይህ ለዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የማይመጥን እና እጅግ የወረደ ኋይል ተኮር አጸፋ አገሪቷን ወደ አፋኝ ሥርዓት (ፖሊስ ስቴትነት) እየለወጣት መሆኑን በትክክል እያስተዋልን ነው፡፡ መንግስት ከሕዝብ ጋር እልህ በመያያዝ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶችን ለእንግልትና ስቃይ አየዳረገ ነው፡፡ ይህን ከአንድ አገር አስተዳዳሪ የማይጠበቅ የመንግስት ባሕሪ በበርካታ ክስተቶች ላይ ደጋግመን እያየነው ነው፡፡ አሁንም በድጋሚ እንገልጻለን ማንኛውም ዓይነት በመንግስት በኩል የሚወሰድ የኋይል እርምጃ የአገሪቷን ሰላም ወደ ብጥብጥና ኹከት አቅጣጫ ይመራዋል፡፡ ይህን ስንል ስለ ጥቂት ዜጎች ሳይሆን ስለ ሚሊዮኖች እያወራን በመሆኑ ሁኔታዎች ወደተለመደው ሰላማዊ ከባቢ እንዲለወጡ ጥብቀን እንጠይቃለን፡፡


 

 
 

Saturday, October 20, 2012

Amharic & Afan Oromo mixed new anashid for anti ahbash campaign.

Amharic & Afan Oromo mixed new anashid for anti ahbash campaign.
song by Artist Seyfalislam
lyrics by brother Khalid ibn Walid
Lyrics Editor Arkemit Maximilian

Friday, October 19, 2012

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ እኛ በፓርላማ!

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ እኛ በፓርላማ!

ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ህልፈተ ህይወት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረጉን የተረከቡት የተከበሩት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጥቅምት 6/2005 በፓርላማ ተገኝተው በሚያደርጉት ንግግር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጉዳይ እንደሚያነሱ በሁሉም ዘንድ ተጠብቆ ነበር፡፡ እንደተጠበቀውም ሙስሊሞችና የምናደርገውን ትግል አስመልክቶ ከአንድ የፓርላማ አባል በቀረበላቸው ጥያቄ የጥቂት ደቂቃዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚሁ ንግግራቸውም የሃይማኖት እኩልነት በኢትዮጵያ እንደሰፈነና መንግስትም በሃይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጭራሽ እጁን እንደማያስገባ በህገመንግስቱ መደንገጉን በመጥቀስ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የተደረገው ‹‹ምርጫ›› በመጠናቀቁ ሕዝበ ሙስሊሙን ‹‹እንኳን ደስ አለህ!›› ብለዋል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነት በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ያለ ችግር መሆኑንም ለመጠቃቀስ ሞክረዋል፡፡ እኛም በንግግራቸው ዙሪያ የተወሰኑ ነጥቦችንና ግንዛቤዎችን ለማስቀመጥ ወደድን፡፡

ፍትህን ፍለጋ አዲስ ነሽዳ

Ahmed Sulieman - Beautiful Dua


The Grand Anwar Mesjid Demonstration Oct19, 2012
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩሕሩሕ

የተሳካ የተቃውሞ ውሎ በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሂዶ ዋለ!

መላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎት በላያቸው ላይ የተጫነው የጭቆና ቀንበር ሸክሙ በከበደበት በዚህ ሰዓት መላ አገሪቱን ያካለለ ፍፁም ሠላማዊው የተቃውሞ ስርዓት ተካሂዷል ፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የመጀመሪያ የፓርላማ ንግግራቸውን ባቀረቡበት አጋጣሚ ከብዙኃኑ ሙስሊም ህብረተሰብ ፍላጎት በተቃራኒ በመሰለፍ የጥቂቶችን ድምፅ በማስተጋባት በብዙኃኑ ላይ የማሸማቀቅ ሙከራ ቢያደርጉም እነሆ “ብዙሃኑ ያሸንፋል!” ሲል ሙስሊሙ ዜጋ ዛሬም ለተቃውሞ አደባባይ ላይ ውሏል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በታ
ላቁ አንዋር እና በኑር መስጂዶች (በኒ መስጂድ) የተሰበሰበው ኡማ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያሳየው የተቃውሞ ሂደት ስኬታማ እንደነበር ለማየት ተችሏል፡፡

ፍፁም ሠላም ወዳድ ከመሆናችን ጋር በተያያዘ በየትኛውም ሰዓትና አጋጣሚ ተቃውሟችንን ማካሄድ መቻላችንን በመተማመን እና ለሁኔታዎች ፋታ በመስጠት ምርጫው በተካሄደበት እሁድ መስከረም 27 እና ባለፈው ጁምዓ ተቃውሞ እንዲኖር ከፍተኛ የሕዝብ ግፊት የነበረ ቢሆንም ሁለቱም ቀናቶች ምንም ዓይነት ተቃውሞ ሳያስተናግዱ አልፈዋል፡፡
ይሁንና ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሰከነ ልቦና ሚዛናዊነታቸው ተጠብቆ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ ሁኔታዎች ይሰራባቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው በይፋ እየተስተዋሉ የነበሩት ተግባራት አሸማቃቂ፣ የሙስሊም ልብ የሚያቆስል እና ይበልጥ ተቃውሞው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚገፋፉ ብቻ ነበሩ፡፡

በዛሬው ዕለት መላ አገሪቱን ያካለለ ተቃውሞ ተመሳሳይ ገጽታ ተላብሶ ሲካሄድ እንዲያስተላልፍ የተፈለገው መልዕት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በዒድ አደባባይ ለሚደረገው ታላቁ የተቃውሞ ትዕይንት እንደ መንደርደሪያ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ታላቅ ታሪክ በመስራት ላይ የሚገኘው ሙስሊሙ ኡማ እየተደረገበት ያለውን ሁለንተናዊ ጫና በመቋቋም እያሳየ ያለው የአቋም ጽናት እጅግ አኩሪ ነው፡፡ የህግ የበላይነት ሰፍኖባታል ተብሎ የሚታሰብባት አገር ዜጎች መብታችን ተጥሷል በማለት ስርዓቱን በተከተለ መንገድ በስልጣን ላይ ለሚገኘው መንግስት አቤቱታችንን ስናቀርብ ልንሰማ ሲገባን በተቃራኒው መንግስት አስከፊ ተግባራትን መፈፀሙን ቢቀጥልበትም ዛሬም እንደትላንቱ አንድነታችንን ጠብቀን ለተሻለና ፍፁም ሠላማዊ ለሆነ የትግል ስልት ራሳችንን በማዘጋጀት ከወዲሁ መቀነታችንን ጠበቅ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

በመጪው ጅምዓ በአንድ ቦታ ላይ የሚያሰባስበን የኡዱሒያ ቀን ታላቁ የተቃውሞ መድረክ መሆኑ ግንዛቤ የተወሰደ ከመሆኑ ጋር በዛሬው ጁምዓ በተቃውሞ ቦታ ላይ የተገኘው እጅግ በርካታ ሕዝብ እጅ ልእጅ በመተሳሰር አንድነቱን በማጠናከር በአንድ ድምፅ ቃል ገብቶ ተለያይቷል፡፡

የዛሬው የተቃውሞ ውሎ ከመዲናችን አዲስ አበባ በተጨማሪ በከሚሴ፣ በሀረር በባቲ እና በሌሎችም የአገራችን ክፍሎች ተካሂዶ ውሏል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

Thursday, October 18, 2012

ነገም ተቃውሞአችን ይቀጥላል!


ነገም ተቃውሞአችን ይቀጥላል!

ነገ ጁሙዓ ነው፡፡ ብሶታችን እና ድምጻችንን አገሪቷን እየመራ ያለው አስተዳደር እንዲያደምጥ የምንጠይቅበት ቀን፡፡ ይህ ቀን ለታላቁ አምላካችን አላህ ሱ.ወ ያለንን እምነትና መንፈሳዊ መተማመን የምናሳይበትም ነው፡፡ ግን ለምን ጁሙዓ ብቻ? ግን ለምን ተክቢራ ብቻ? የሚሉት ጥያቄዎች የሁላችንንም ምላሽ ይጠይቃሉ፡፡ በየሳምንቱ ጁሙዓ እየተገናኘን ብቻ የምንፈጽመው የተቃውሞ መርሐ ግብር እየደረሰብን ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረፍ እና ዳግም እንዳይከሰትም ዋስትና እነደማይሰጠን ሁላችንም እንረዳለን፡፡ ይህም በመሆኑ መረጃዎችን ተከታትሎ የማግኘት ጥረታችን፣ ያገኘነውን መረጃም የማሳወቅ ሓላፊነታችን እና አላህ ከፈተናው እንዲጠብቀን የምንማጸንበት ዱዓችን ሁሉ የትግላችን አካሎች መሆናቸውን በመረዳት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንን ከእነዚሁ ተግባራት ጋር ማያያዝ ግድ ይለናል፡፡

ዲናችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ፣ የማመን መብታችን ላይ የተፈጠረውን እክል በ10 ወራት ትግል ብቻ ሙሉ በሙሉ ልንቀርፈው አንችልም፡፡ የመሪ ተቋም እጦት እና አሕባሽን የመሳሰሉ አጀንዳዎችን ዛሬ ብንቀርፋቸው እንኳ ነገ ዳግም ላለመከሰታቸው ዋስትና የለንም፡፡ ለዚህ ደግሞ ማንም ወገን ዋስትና አይሰጠንም፡፡ የዋስትና ካርዱ በእጃችን ነው፡፡ ዋስትናችን ትግላችን ብቻ ነው፡፡ ትግላችን ጊዜን እና ሁኔታዎችን እያገናዘበ የሕይወት ዘመን ልምምዳችን እና ተልእኮአችን ሲሆን በእስልምናችን የመኖር መብታችን ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ይሆናል፡፡ ዛሬም በግልጽ ልናምን የሚገባው መብታችንን ማንም ለክቶ እና ቆርሶ እንዲሰጠን ልንጠብቅ አይገባም፡፡ ባለፉት 10 ወራት በፈጠርነው ንቅናቄ ምንያህል አመርቂ ጥቅሞችን እንዳገኘን
አንዘነጋውም፡፡ ይህ ንቅናቄያችን በቀናት ብቻ የተገደበ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ትግላችን በጥቂት ቀናት ብቻ የተገደበ እንዲሆን ተጨባጫችን ፈጽሞ አይፈቅድም፡፡ የመኖራችን ዋስትና የሙሉ ጊዜ ትግላችን ብቻ ነው፡፡ ትግላችን በጁሙዓ ብቻ የተገደበ አይሁን - የሙሉ ጊዜ የ24 ሰኣታት ይሁን፡፡ እምነት የሕይወት ዘመን ጉዞ ነውና፡፡

ነገ ጁሙዓ እለት ነው፡፡ የእለቱን የጁሙኣ ሶላት ካጠናቀቅን በኋላ የዘወትር ተቃውሞአችንን እናካሂዳለን፡፡ ነገ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ እና በፒያሳው ኑር መስጊድ እንሰባሰባለን፡፡ በክልሎች ደግሞ በዋና ዋና የከተማ መስጊዶች በመሰባሰብ የጁሙዓን ሶላት በጋራ እናከናውናለን፡፡ የጁሙዓው ሶላት እንደተጠናቀቀ ባለንበት ቦታ ሆነን አላህ ከጠላቶቻችን ሴራ እንዲጠብቀን ለ3 ደቂቃዎች ያህል በፍጹም ተናናሽነት ዱዓ እናደርጋለን፡፡ ቀኑ የዙልሂጃ ሦስተኛ ቀን በመሆኑ ዱዓችን ዒላማውን ይመታ ዘንድ ቀኑን በጾም ማጀባችን ለሁላችንም ቢሆን ጠቃሚ ነው፡፡ ለ3 ደቂቃዎች ያህል የምናደርገው ዱኣ እንደተጠናቀቀ ከጎናችን የሚገኙ ሰዎች ጋር እጅ ለእጅ ለ2 ደቂቃ ያህል በመያያዝ ዛሬም በአቋማችን፣ በወንድማማችነታችን፣ በእህትማማችነታችን ከሁሉም በላይ ደግሞ ለኮሚቴዎቻችን ያለንን ፍቅር እና ታዛዠነት እናሳያለን፡፡ በዚያውም የእለቱ ተቃውሞአችን ተጠናቅቆ ያለምምን ተክቢራ በሰላም እንበተናለን፡፡

ይህ ተቃውሞአችን በመጪው የኢደል አድሀ አረፋ በዓል ለምናደርገው አገር አቀፍ ሰላማዊ ተቃውሞ መዘጋጃ በመሆኑ በአዲስ አበባ ሁሉም ሙስሊም ኅብረተሰብ በቁጥር በመብዛት ለሃይማኖቱ መከበር ያለውን ቀናዒነት ለማሳየት አንዋር እና ኑር መስጊድ በመሄድ ተቃውሞውን ማከናወን ይኖርበታል፡፡ በክልሎችም የተገለጸውን የ5 ደቂቃ ተቃውሞ በማሳካት ለአገር አቀፉ የኢድ ተቃውሞ እንድንዘጋጅ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
አላሁ አክበር!

Tuesday, October 16, 2012

Muslims in Ethiopia suffer discrimination and alienation, , Crescent Magazine

Muslims in Ethiopia suffer discrimination and alienation, , Crescent Magazine

ጠ/ሚር ፓርላማ ስለሙስሊሙ ተጠይቀው የሰጡት መልስ


ጥያቄችን እንዳይመለስ ነክሶ የያዘው የመንግስት አካል የሠለጠነው በረብሻ ነው፡፡ እኛ ግን የሠለጠንነው በሠላም ነው፡፡


• ትግሉ አልቆመም፤ አይቆምም!!!
• ጽንፈኞቹን ‹ሠላም› በተባለ በማያውቁት ሜዳ እንፋለማቸዋለን
• ከእስካሁኑ የትግል መንገድ ላይ የቀሩንን 998 መንገዶች አንድ በአንድ እየጨመረን ያለመታከት እንታገላለን
• ትግላችን ውጤታማ አይደለምን?
• የቢጫና ቀይ ትርጉም ምንድነው?
የትግላችንን ፍሬ እለት ተዕለት እያየን ነው፡፡ የልፋትን ውጤት ጌታችን እያሳየን እየረካን ነው፡፡ ሆኖም፤ ጥያቄያችን ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ ከቶም አናፈገፍግም፡፡ ጥያቄችን እንዳይመለስ ነክሶ የያዘው የመንግስት አካል የሠለጠነው በረብሻ ነው፡፡ እኛ ግን የሠለጠንነው በሠላም ነው፡፡ በሠላም እያሸነፍን ነው፡፡ በሰላም በመታገላችን የአህባሽ ጠመቃው እጅግ በጣም ቀንሷል፡፡ ሰላማዊ በመሆናችን በኛና በኃይማኖታችን ላይ የሚደረገውን ፕሮፓጋንዳ አሸንፈናል፡፡ በሰላም በመታገላችን ‹‹መጅሊስን መቃወም መንግስትን መቃወም ነው›› ብሎ ሲያቅራራ የነበረው መንግስት ሳይወድም ቢሆን ምርጫ መሰል ቅርጫ ለማካሄድ ተገዷል፡፡ እንዲያውም የተከበሩ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአደባባይ እንደነገሩን የልማት ስራ እንኳ አቁመው ጉዳያችንን ሲያቦኩ ከርመዋል፡፡ መጀመሪያ ግን ‹‹እነ አህመዲን ጨሎ ሕጋዊ ናቸው›› የሚል አጉል ክርክር ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው? ስለሁሉም አላህ የተመሰገነ ይሁን፡፡

Sunday, October 14, 2012

የአኒቲ ብሎግ Aniti's Blog: ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው

የአኒቲ ብሎግ Aniti's Blog: ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው: Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind First Audition የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳ...

Friday, October 12, 2012

ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው

Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind

First Audition

የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳችን ፕሮግራም አምድ ላይ ተጋባዥ ያደረግነው የጭንቅ ቀን ደራሹ የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ ከሆነው ሳላሀዲን ሰዒድ ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

የእምነት ነፃነት መፅሄት፡ ሳላሀዲን መቼም በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ (ልምምድ ላይ እንደመሆንህ መጠን) ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ሆነህ ስለመጣህ እያመሰገንን በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን ስም እንኳን በደህና መጣህ ለማለት እንወዳለን፡፡

ሳላሀዲን እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ የመጀመርያ እንግዳም ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡

ጥያቄ፡ ሙስሊም እንደመሆንህ መጠን የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ መባሉን እንዴት ነበር ያየህው?

ሳላሀዲን፡ በግልምጫ፡፡

ጥያቄ፡ ለምን?

ሳላሀዲን፡ ምክንያቱም ድርጊቱ በመረብ ኳስ ሜዳ ላይ ጎል ተክሎ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን የመጫወት ያህል ነው፡፡

ጥያቄ፡ የመንግስት አካላት ምርጫው በቀበሌ መሆኑ ህገመንግስቱን አይፃረንም ባዮች ናቸው አንተ ምን ትላለህ?

ሳላሀዲን፡ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆንኩ የመረዳት አቅም የለውም በእግር ማሰብ አይደለም እንደማትለኝ እያመንኩ፡፡ ይህ ቀላል ጥያቄ ነው በሚቀጥለው ምርጫ 2007 የመንግስት ተወካይን ለመምረጥ የሀገሪቱ ህዝብ በመስጊድ እና በቤተክርስታን ማከናወን እንደሚችል ቃል ከገቡና በምርጫ ቦርድ ወይም በፓርላማው እንደ አንድ ፖሊሲ ካፀደቁት ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡

ጥያቄ፡ በሌላ መንገድ እምነት እና ፖለቲካን (ሰርግና ሞት አንድ ነው ጨፍር ምንድነው) እንደሚለው የሀገራችን ቢሂል ካደረጉት እንደማለት ነው?

ሳላሀዲን፡ አግኝተህኛል (ፈገግታ.. )

ጥያቄ፡ እንዴት ነው ህዝቡ እንደምታውቀው በሰላማዊ መልኩ ተቃውሞውን ላለፉት 11 ወራት ሲያካሂድ ነበር እንዴት ነው አንተስ ድምፅህን የምታሰማበትን አጋጣሚ ነበረህ?

ሳላሀዲን፡ በእርግጥ እንደዛ አይነት አጋጣሚን አላገኘሁም ብዙን ግዜ ጌሞች ስለሚደራረቡብን እና ከካንፕ የምንንቀሳቀስበት ግዜ በትሬኒንግ የተጨናነቀ እንደመሆኑ መጠን ምንም አላገኘሁም፡፡ ነገር ግን በውስጤ ሁሌም እፀልያለሁ፡፡

ጥያቄ፡ እንደ አንደ የሀገራችን የእምነቱ ተከታይ ብሎም ታዋቂ እንደመሆንህ መጠን ተቃውሞህን ለማሰማት ያሰብከው ነገር አለ?

ሰላሀዲን፡ ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ፡፡ በእርግጥ ቀደም ብዬ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ብዙ አይነት የመቃወሚያ መንገድ እንደመኖሩ መጠን እኔ እስካሁን ሳደርገው የነበረው ፀሎት ወይም ዱዓን ነበር፡፡ ፈጣሪ ከተበዳዮች ጎራ እንደሚቆም አልጠራጠርም፡፡

ጥያቄ፡ ሌላ ለማድረግ የፈለግከው ነገር እንዳለ ከጓደኞችህ ሰምቻለው፡፡ ተቃውሞህን ለማሰማት ወሳኙ በሆነው በነገው ጫወታ ላይ፣ በሱዳን አቻችሁ ላይ ጎል እንዴት ነው አላስቆጥርም ብለህ ነበር እንዴ?

ሰላሀዲን፡ በፍፁም! በፍፁም! ይሄ የአንዳንድ ካድሬ የቤህራዊ ብድናችን ተጫዋቾች አስተሳሰብ ነው፡፡ አንተም ሆንክ እነሱ ግን ለመስማት ከፈለክ፣ እኔ እንደ ማንኛውም ሙስሊም የሀገርን ህልውና እና ሠላምን በማይረብሽ ብሎም እንዲሁም ልክ እንደ ሌሎች የሀገሬ ሙስሊም ወጣቶች ተቃውሞ ኮሽታን በማያሰማ አካልን ሳይሆን ልብ ያለው እእምሮ ላለው ጨቋኝነን በሚቆረቁር መንገድ ነው የማሰማው፡፡ እንደወትሮው ከቻልኩኝ ከአንድም ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ጥረት አድርጌ ባገባሁ ቁጥር ሀዘኔን እና የሙስሊሙ ጉዳይ እኔንም እንደ አንድ ሙስሊም የሚያሳስበኝ እንደሆነ ለመግለፅ፡፡ አግብቼ የማልፈነድቅ ወይም የማልሮጥ ሲሆን ወደ መሬት ሱዱጅ በመውረድ ተቃውሞዬን የምገልፅ ይሆናል፡፡ ይሄው ነው፡፡

ጥያቄ፡ መልካሙን ሁላ እየተመኘንልህ በመጨረሻ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ እድሉን ልስጥህ፡፡

ሳላሀዲን፡ አመሰግናለሁ ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድናችን፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመንግስት ለእምነት ነፃነት ጥያቄያ ድምፃችን ይመጣ ዘንድ ምኞቴ እና መልዕኬቴ ነው፡፡
My own art to tell you the point
ከጫወታው አንድ ቀን በፊት
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››በህልሜ ካዋራኝ የተወሰደ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹

TPLF boss says Muslim protests have to be stopped

Negash Debretsion Gebremichael, TPLF spy chief who also doubles as Minister of Communication and Information Technology, appears to suggest that the ruling party has mobilized to crush peaceful Muslim protests.  Debretsion used Addis Ababa University as a platform to declare war on what he called “religious radicalism” and “terrorism.”


Eskedar Kifle | Capital Ethiopia
October 8, 2012
The Addis Ababa University, the longest serving higher institution in Ethiopia, gave a three day seminar to its teachers in all campuses, Capital learned. The meeting was originally intended to take place at one location from October 3 to 5, but they later decided to carry it out separately on different campuses.
The notorious Debretsion who intercepts email, other electronic communications
When the seminar came to a close at the Sidist Kilo Main campus on Friday, October 5, Debretsion Gebremichael (PhD), Minister of Information and Communication Technology gave guidance to the participants saying that in the coming years the university must focus on the problems of religious radicalism and the dangers of terrorism.
“We don’t want to have a destabilization movement under the guise of religion. In every religion we trace fundamentalism which is contrary to the basic principle of religion that teaches coexistence with each other,” Debretstion was quoted as saying. This movement has to be stopped, he strongly warned.
He also attended the meeting at the Arat Kilo Science Faculty on Thursday, October 3. Sources told Capital that at Science Faculty like in other faculties raised questions about the teachers’ salary increase. Dr. Debretsion discouraged the issue out of hand by saying:
“This time don’t expect a pay raise. You have the capacity to generate additional income by having additional work elsewhere. We don’t like that option. But on the government side there is no plan to increase the salary of teachers at this time,” he said.
A teacher who preferred anonymity because of the sensitivity of the issue told Capital that he is not happy with the response of Debretsion. “Inflation is extremely high. So life is difficult to manage with the salary we are receiving now. House rent is increasing literally every month. The government wants us to provide a quality education. With this small pay it is impossible to have first class teachers. So the fall of the standard of education, due to mediocre teachers, is an avoidable fact,” he said.
But Dr. Debretsion was positive about the housing question. “I know that the late Prime Minister wanted the housing problem of the university teachers to be tackled. Accordingly something has been done in that direction all through. So we will exert every effort to resolve the housing problem that the teachers face,” Dr. Debretsion said.
The other major discussion point was about the quality of education. There was a consensus that the quality of education has tremendously gone down. Though all of them agreed to improve the quality of education, no viable future plan was put in place. “We all said that we will improve the quality of education.  This is a cliché like saying we shall realize the dreams of the visionary leader,” remarked one disgruntled teacher. But making change requires a backbreaking job, he concluded.