Monday, December 31, 2012

365 ቀናት ለሃይማኖት ነጻነት!

365 ቀናት ለሃይማኖት ነጻነት!


የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ መንፈሳዊ ግልጋሎት ይሰጠኛል ብሎ የመሰረተው መጅሊስ የ1987ን የአንዋር መስጊድ ግርግር ተከትሎ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ገብቶ ለ17 ዓመታት ዘልቋል፡፡ ይህ በህገ መንግስት የተደነገገውን መርህ የሚጥሰው የመንግስት እርምጃ ሙስሊሞችን ለ17 ዓመታት በቁዘማ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ የተጣሰው ሕገ መንግስታዊ መርህ ሳይቃና መንግስት በ2003 የጀመረው አዲስ ጨዋታ ነገሩን ሁሉ ግልጽ አደረገው፡፡ መንግስት የራሱ የግሉ ተቋም ካደረገው እና ከቀዳሚው ስሙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በተግባር ወደ የኢሕአዴግ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትነት ከተለወጠው መጅሊስ ጋር በጋራ በመሆን አሕባሽ የተባለ መጤ ቡድን ለመጫን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎችም በወቅቱ አሕባሽ የጽድቅ መንገድ እንደሆነ ሰበኩ፡፡

Friday, December 28, 2012


አዲሱ መጅሊስ የመውሊድን ካርድ መልሶ ለመሳብ እየሞከረ ነው፡፡

አዲሱ የኢህአዴግ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) በመውሊድ ሰበብ ክፍፍል ለመፍጠርና ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡ መጅሊስና አሕባሽ የተነሳባቸውን ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ለማርገብ የተለያዩ ስልቶችን ባለፉት 12 ወራት ይጠቀሙ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ ሱፊያ እና ሰለፊያ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም ሕዝበ ሙስሊሙን ለመከፋፈል የሞከሩበት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት መውሊድን ታክኮ የቀድሞ መጅሊስ አመራሮች መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ አድርገው የነበረ ቢሆንም ፈጽሞ ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነበር፡፡

መጅሊስ በዋነኝነት መውሊድን አድምቆ በማክበር ስም መጅሊሱንና አሕባሽን የሚቃወሙት ወሀቢያዎች እና የመውሊድ ጠላቶች ናቸው የሚል ሐሜት በመንግስት እና በአንድ አንድ ለገንዘብ ባደሩ ሚዲያዎች ሲነዙ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የዚህም ዋነኛ ዓላማ የነበረው የሙስሊሙ አንድነት ስላስበረገጋቸው እና አንድነቱንም ለመሰንጠቅ ነበር፡፡ መጅሊሶች ግን ምንም ሳይሳካላቸው በሀፍረት ተሸማቀቁ፡፡ በወቅቱ መሪዎቻችን ‹‹መውሊድ አይለያየንም›› በሚል ርእስ በአወሊያ እና በሌሎችም መስጊዶች የሰጧቸው ገለጻዎች የሙስሊሙን ልብ ከጫፍ እስከጫፍ አያይዘውት ነበር፡፡ ሙስሊሙ በጋራ ‹‹መውሊድ አይለያየንም›› ሲልም ተደመጠ፡፡

ያለፈውን ዓመት ልምድ በመመርኮዝና የመሪዎቻችን ወህኒ ቤት መሆንን በመመልከት አዲሱ መጅሊስ በመውሊድ ስም ክፍፍል ለመፍጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ተረድተናል፡፡ መጅሊስ በሚቆጣጠራቸው በተለያዩ መስጊዶች ሕዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ እየተጠየቀ ሲሆን መዋጮ የማያደርጉም አሸባሪ እና አከራሪ የሚል ታፔላ እየተለጠፈላቸው ይገኛል፡፡ ይህ የመጅሊስ አመራሮች አሳፋሪ እርምጃ ወደየት እያመራ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እኛ ግን የመጅሊስም ሆነ የመንግስት አካሄድ ገና በጊዜ የተገለጠልን በመሆኑ የመጅሊስ እድሜ ማርዘሚያ የልዩነት አጀንዳዎች እኛ ዘንድ ምንም ቦታ እንደሌላቸው እናረጋግጥላቸዋለን፡፡

አላሁ አክበር!

Friday, December 21, 2012

ፍትህ የናፈቃቸው ጥሪዎች ዛሬም በሐበሻ ምድር ተስተጋቡ!


ፍትህ የናፈቃቸው ጥሪዎች ዛሬም በሐበሻ ምድር ተስተጋቡ!

አመቱን ሙሉ ሲስተጋባ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገ መንግስታዊ መብት የማስከበር ትግል ዛሬም የአገሪቱን አራት ክልልች በተቃውሞ አድምቆ ዋለ፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሐረር ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተመረጡ መስጊዶች እጅግ በደመቀ ስነስርአት የተተገበረው ተቃውሞ ዛሬም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሷቸውን የሃይማኖት ጥያቄዎች ሳያስመልሱ እና በግፍ የታሰሩ መሪዎቻቸውን ነጻ ሳያወጡ ወደኋላ እንደማይሉ ለሚመለከታቸው አካላት ያለጥርጥር ያረጋገጠ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡

በደሴ ከተማ በተካሄደው ታላቅ ተቃውሞ የደሴ አፋፍ ላይ የምትገኘው የሸዋበር መስጊድ በሺዎች ተሞልታ የነበረ ሲሆን ከጁምአ ስግደት በኋላ በደሴ ፋኖዎች የተባበረ ድምጽ ተንጣለች፡፡ ‹‹በአገራችን ሰላም አጣን! ፍትሕ ናፈቀን! ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!›› ሲሉም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማስተጋባት፣ ወረቀቶችንም በማውለብለብ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ፍትህ የናፈቀው የደሴ ሙስሊም ዛሬም በድጋሚ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ


ፍትህ የናፈቀው የደሴ ሙስሊም ዛሬም በድጋሚ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ!!

አዎ! ፍትህ ናፍቆናል!! በሃገራችን ፍትህ ተጠምተናል!! የኮሚቴዎቻችንን ስቃይ ማየት አልቻልንም!! ይህ ነበር የዛሬው ድምፅ፡፡ ዛሬ ደሴ ሙስሊም ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት ነበር፤ በኮሚቴዎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሁሉንም ልብ ሰብሯል፡፡ ለህዝብ ሲሉ ተሰቃይተዋል፣ ሙስሊሙ ሲሉ ጊዜያቸውን ሰውተዋል፣ ለዲናቸው ብለው ህይወታቸውን ለግሰዋል፤ ውድ ኮሚቴዎቻችን፡፡

ዛሬም የደሴ ሙስሊም የነሱ ስቃይ ምን ያህል እንደተሰማው አሳይቷል፣ በኮሚቴዎቻችን ላይ የሚፈፀመውን ግፍ አውግዟል፡፡ በዛሬው ደማቅ ተቃውሞ ላይ ኮሚቴዎቻችን ለሙስሊሙ ከምንም በላይ እንደሆኑ ድምፃችንን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡
“ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!” ፣ “በሀገራችን ሰላም አጣን!” ፣ “ፍትህ ናፈቀን” ፣ “መንግስት የለም ወይ?” በዛሬው ደማቅ ተቃውሞ ላይ የተሰሙት መፈክሮች ነበሩ፡፡

የደሴ ህዝብ ዛሬ ኮሚቴዎቻችን ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፅሙትን የሽፍታ ጥርቅሞች መቼም ይሁን እንደሚፋረዳቸው አሳውቋል፡፡ የዛሬው ደማቅ ተቃውሞም በሰላም ተጠናቋል፡፡ ኮሚቴዎቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ ከማንኛችንም ልብ ውስጥ የሚወጣ አይደለም!! ግፈኞቹንም በህግ እንፋረዳለን!!

ድል ለኢትዮጵያ ሙሊሞች!
አላሁ አክበር!

Thursday, December 20, 2012

ቃላችን አይታጠፍም፤ ወንጀለኞችን እንፋረዳለን


ቃላችን አይታጠፍም፤ ወንጀለኞችን እንፋረዳለን

የሽፍታ ቡድን የፈለገውን ዓይነት ወንጀል ቢሰራ እንኳ አንድ ቀን በሕግ ቁጥጥር ስር ሊውል እንደሚችል ያስባል፡፡ ነገር ግን፤ በመንግስትና በሕግ የተጠለለ ወንጀለኛ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር እንደማይውል ስለሚያስብ አውሬነቱ ለከት የለውም፡፡

በድሃዋ ሐገራችን ከሚገኙ አሰቃቂና ገሀነማዊ ቦታዎች ዋነኛው መሃል አዲስ አበባ የሚገኘው ማዕከላዊ እስር ቤት ነው፡፡ ይህ እስር ቤት የደርግ አብዮት ጠባቂ ‹‹መርማሪዎች›› እስረኞቻቸውን የሚያሰቃዩበት የገሃነም ደጃፍ ነበር፡፡ ዛሬም ይህ ቦታ የስቃይ መንገዱና ዱላው ከመቀነስ ይልቅ ዘመናዊ የስቃይ መሳሪያዎችን ጨምሮ ቀጥሏል፡፡ ከ15 ቀናት በፊት በኮሚቴዎቻችን ላይ ከደረሱት ዘግናኝና ነውረኛ ድርጊቶች ውስጥ እጅግ ጥቂቱን ለመግለጽ ሞክረናል፡፡ ሐገሪቱን እና የሙስሊሙ ወቅታዊ ሁኔታ ለሚከታተሉ ሁሉ በኮሚቴዎቻችን፣ በዱኣቶቻችን፣ በጋዜጠኞቻችንና በአርቲስቶቻችን ወዘተ ላይ የተፈጸሙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግፎች ፈጻሚዎችን በሙሉ አንድ በአንድ የምንፋረድ መሆናችን እና መቼም ከሕሊናችን የማይጠፋ ወንጀል መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ታሪክ ምስክር ነው፡፡
ሠላማዊነቱ ከሐገራችን አልፎ በዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ ከበሬታ ያገኘው እንቅስቃሴያችን ከመነሻው ጀምሮ በሕዝብ የተመረጡ መፍትሄ አፈላላጊዎች አሉት፡፡ ሕዝባችን ጥያቄውን ሲያቀርብ መንግስት በሕሊናው እንደሚያስብ የፍትህ አካላም ሕግ እንደሚያከብሩ በመገመት ነበር፤ ነውም፡፡ ነገር ግን፤ በማዕከላዊ ምርመራ የነበረው ሁኔታ ኮሚቴዎቻችንና ኡስታዞቻችን የሕግ ከለላ ባለው የሽፍታ ቡድን ቁጥጥር ውስጥ የገቡ አስመስሎታል፡፡

መሪዎቻችን ዳግም የስቃይ ቤርሙዳ ውስጥ

መሪዎቻችን ዳግም የስቃይ ቤርሙዳ ውስጥ

መሪዎቻችን ላይ በማዕከላዊ ሲፈጸም የነበረው ቶርች ቃሊቲ ውስጥ በአዲስ ስልት ተጀምሯል፡፡ በአገሪቱ ሕግ የሚገዛው የፍትህ አካል ለአይን እንኳ እየጠፋ ነው፡፡

ዘግይቶ በደረሰን መረጃ ያለምንም መረጃ ከሕግ አግባብ ውጪ በግፍ ባፈጸሙት ወንጀል በሀሰት ተከሰው በማዕከላዊ ወህኒ ቤት ግፍና በደል ሲፈጸምባቸው የቆዩት መሪዎቻችን እና ወንድሞቻችን በቃሊቲ ማረሚያ ቤትም ዘግናኝ ግፎችን ማስተናገድ መጀመራቸውን አረጋግጠናል፡፡ በተወሰኑ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞኖች ውስጥ ያሉ መሪዎቻችንና ወንድሞቻችን በሚያሳፍር መልኩ ራሳቸውን መቆጣጠር ከማይችሉና አእምሮአቸውን ከሳቱ የአእምሮ ህሙማን ጋር በጋራ እንዲታሰሩና መኝታ እንዲጋሩ መደረጋቸው ታውቋል፡፡ ይህ የመንግስት ስልት ከዚህ ቀደምም በቃሊቲና በሌሎች ወህኒዎች ሲሰራበት የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የታሳሪዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ በመክተት በማንኛውም አጋጣሚ አደጋ ሊያደርስ ከሚችል የአእምሮ እመምተኛ ጋር መኝታ ማጋራትና መዘዙን መሪዎቻችን እንዲሸከሙት የማድረግ ስልት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

Tuesday, December 18, 2012

ፍትህ የማግኘትን ተስፋ ያዳፈነው የፍ/ቤት ውሎ

ፍትህ የማግኘትን ተስፋ ያዳፈነው የፍ/ቤት ውሎ

ፍ/ቤቱ ብዙዎቹን መቃወሚያዎች ውድቅ አድርጓቸዋል

‹‹ወንጀል ተፈጽሞብኛል እንጂ ወንጀል አልፈጸምኩም››ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው

ማለዳ ላይ የተሰየመው የልደታ ፍ/ቤት አቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሀሰት ክስ ተንተርሶ የመሪዎቻችንን እና ወንድሞቻችንን ጠበቆች መቃወሚያ እንዲሁም የአቃቤ ሕጉን የመቃወሚያ መቃወሚያ አድምጦ ውሳኔ ለማሳለፍ ነበር ቀጠሮ የሰጠው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ ፍ/ቤቱ ለውሳኔ የሚረዱኝ የመቃወሚያ ግልባጮች በጽሁፍ ተገልብጠው አልደረሱኝም በሚል ምክንያት ውሳኔውን መስጠት ሳይችል ቀርቶ ነበር ቀጠሮው ወደ ታህሳስ 8 የዞረው፡፡ ሆኖም በእለቱ ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ ሁኔታ መሪዎቻችን እና ወንድሞቻችን ፍ/ቤት እንዳይቀርቡ ተደርጓል፡፡

Monday, December 17, 2012

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ክስ ያየው ፍርድ ቤ ት 2ኛውን ክስ ውድቅ አደረገ በአንደኛው ክስ ላይ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ለጥር 14 እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ

ሰበር ዜና

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ክስ ያየው ፍርድ ቤ ት 2ኛውን ክስ ውድቅ አደረገ በአንደኛው ክስ ላይ የአቃቤ ህግ ማስረጃ ለጥር 14 እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ


ዛሬ ታህሳስ 8/2005 ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛወንጀል ችሎት ቀደም ሲል በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች ጠበቆች በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ያቀረቡትን መቃወሚያ እና አቃቤ ህግ ያቀረበው የመቃወሚያ መቃወሚያ ካስታወሰ በዃላ የሚከተሉትን ብይን ሰጥቷል፡-.

“Allah Waa Akbar”…The cry of Ethiopian Muslims from Menagesha’s torture chambers

“Allah Waa Akbar” – The cry of Ethiopian Muslims

The Horn Times breaking News 14 December 2012

“Allah Waa Akbar”…The cry of Ethiopian Muslims from Menagesha’s torture chambers

by Getahune Bekele
“Oh my Ethiopia what have you become?” wails a 39 year old Anbesa metro bus driver, Geremew Balcha (not his real name) who lives in the vicinity of the notorious Menagesha police station holding cells, about 25 KMs west of Addis Ababa.
Built along the road to Holeta Genet town, opposite to a vast flower farm owned by top TPLF cadre, Ato Sibehatu, father of the ruling junta’s mouth piece Mimi Sibehatu, the Menagesha police station has been used as torture and execution chamber since the Muslim uprising began several months ago.
The sheer brutality of the ruling minority junta against Muslim protesters
The sheer brutality of the ruling minority junta against Muslim protesters
“Every night from 10 am we hear the cry of Allah Waa Akbar, from the compound of the police station, we even count the crack of the whip as it landed on the victim’s body. Few minutes later the cry goes silent until the next victim starts screaming aloud, Allah Waa Akbar…” the tearful father of three explains.
“It is heart breaking to hear the agonizing cry of female victims. Even when the torturers put a gag, we kept counting the bang…I just send my 7-month pregnant wife away to the town of Ambo as the trauma becomes unbearable. The community of Menagesha is severely traumatized. At times we hear mothers openly crying from nearby houses when gun shots rang out in the middle of the night. Are the federal police members executing prisoners? I don’t know.”Adds Geremew Balcha.
The Horn Times reporter who travelled to Menagesha on Tuesday evening 11 Dec 2012, further uncovered  volley of bullets  were in fact heard in the farm’s compound but he find it difficult to establish if the federal police executes intransigent prisoners there and dump bodies elsewhere.
Again on Wednesday 12 Dec, the same reporter observed more than 200 shackled prisoners crossing in to the farm on foot where they are going to work as slave laborers on a- meal- a- day payment.
It is a sad case of so-called liberators turning Voracious colonizers.
Affectionately known by the faithful around the world as the children of Billal-the Abyssinian, the moderate and peaceable Ethiopian Muslims are currently refusing to be ruled by a genocidal Tigre sheikdom and their struggle for religious freedom is gaining momentum, making the junta blanch with fright.
The ruling elite views this peaceful struggle as a prerequisite for more anti- TPLF insurrection by resuscitating patriotism laced with religious fervor firmly rooted in Ethiopiawenet.
The warlords also know that such wide spread movement has the potential to end the 21 year plunder and enslavement of Ethiopia.
According to a well respected political analyst based in Addis Ababa, making torture perfectly legal and the  building of phony detention facilities shows the junta’s desperate attempt to crash the rebellion; and to Ethiopians, this brutality is a stark reminder of the 2005 genocidal massacre.
In another related news, an organizing committee member for Sunday’s march to Kality prison called on all Ethiopians from all walks of life to join their Muslim brothers and sisters in front of the main gate of the prison at 8 pm.
infohorntimes@gmail.com

Sunday, December 16, 2012

Ahbash Muslimun Siyatemqu siyakefru

ታሪካዊ ቀን ጥቅምት 16/2005 ዓ.ል ታላቅ ተቃዉሞ በሐረር ከተማ ጥቂቶች አይደለንም!!


የ ኢህአዴግ መንግሥትና የመብት ጥሰቶች

Article contributor - አህመድ አባቡልጉ (Ahmad Abagulbu)  ababulgu@gmail.com

መግቢያ
የተከበራችሁ አንባብያን ይህቺን ጽሑፍ ለመጻፍ ያኔሳሳኝ ላለፉት ሁለት አስርት ዓምታት ከነበሩኝ ገጠመኞችና ተመክሮዎች አንጻር ዛሬም በሃገራችን እየተፈጸመ ያለው ሁኔታ፥ የክስተቶች መዴጋገምና ብልሹነት የተነሳ የማውቃቸውን ዕውነታዎች ለሌሎች ማካፈሉ ለግንዛበም ሆነ ለአንዳንድ ጥንቃቄዎች ይረዳል ብዬ በማሰብ ነው፡፡
በሀገራችን በተካሄዱት የለዉጥ ሂደቶች በአወንታ ሊጠቀሱ የሚገባቸዉ ተግባራት እንደመኖራቸዉ በዓሉታም የሚነሱት በርካቶች ናቸዉ፡፡ በተለይም የመሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ዙሪያ የተፈፀሙ ስህተቶች ሰፊና የጎሉ ናቸዉ፡፡ ያለፈዉም ስህተት ለዛሬዉ ክስተት ትምህርት መሆን እያቃተዉ ይልቁንም በመንግስትና በገዢዉ ፓርቲ ዘንድ እንደ መልካም ተመክሮ መወሰዳቸዉ በዝምታ ሊታይ አይገባዉም ከምል እምነት ነዉ፡፡
Read Full Article

ዛሬ በደሴ ከተማ ልዩ የዚያራ ፕሮግራም ተደረገ!!



ዛሬ በደሴ ከተማ ልዩ የዚያራ ፕሮግራም ተደረገ!!

መንግስት የሚያደርስበትን ጫና በመቋቋም ሰላማዊ ትግሉን ሲያካሂድ የቆየው የደሴ ህዝብ ዛሬም በማረሚያ ቤት ተገኝቶ ቆራጥነቱን እና ለዲኑ ያለውን ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል፡፡ በዛሬው የዚያራ መርሀ ግብር ላይ እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያለው ህዝብ የተገኘ ሲሆን ከሀይቅና ከኮምቦልቻ ከተሞችም በዚያራው ፕሮግራም ላይ እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ያለምንም ክስ ከአራት ወር በላይ የታሰሩትን ውድ ኢማሞቹንና ወንድሞቹን ለመዘየር ህዝብ ቁጥር ገና ከጧቱ 2፡30 በማረሚያ ቤት የተገኘ ሲሆን በየጊዜው የህዝቡ ቁጥር ጨምሮ የማረሚያ ቤቱን ግቢ ሞልቶ ለሰልፍ እንኳን አስቸግሮ ነበር፡፡ ይህን የተገነዘቡት የማረሚያ ቤት አስተባባሪዎች ሙስሊሙን ለማንገላታት “ስንቅ ያልያዘ ይመለስ” በማለት ህዝቡን ሊበትኑ ቢሞክሩም በሙስሊሙ ቆራጥነት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በዛሬው የዚያራ ፕሮግራም ላይ አንዳንድ ደህንነቶች በሰው መሃል ገብተው ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ሙስሊሙ እስከዛሬ ድረስ ባሳየው የሰላም ወዳድነት ባህሪ ዛሬም በድጋሚ ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

በዛሬው እለት የደሴ ሙስሊም ለኢማሞቹ ያለውን ፍቅር ከመግለፅ አልፎ ለአሚሮቹ ያለውን ታዛዥነትና አክብሮት በድጋሚ አሳይቶ አልፏል፡፡ መንግስት ምንም ያህል የሙስሊሙን ሰላም ለማደፍረስ ቢጥርም ሙስሊሙ ግን ዛሬም ፣ ነገም ምርጥ የሰላም አምባሳደር እንደሆነ እያሳየ ይገኛል፡፡ ይህን ምርጥ ትውልድ የሁሉም ጌታ የሆነው አላህ ይጠብቀው ዘንድ እንማፀንዋለን፡፡ በግፍ የታሰሩትን ኮሚቴዎቻችንን እንዲሁም ኢማሞቻችንን አላህ ነጃ ያውጣቸው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!
አላሁ አክበር!

Saturday, December 15, 2012

ጥቂት ማለት ስንት ነው? ብሎ የጠየቀው የዛሬ የተቃውሞ ውሎ

ጥቂት ማለት ስንት ነው? ብሎ የጠየቀው የዛሬ የተቃውሞ ውሎ

ተቃውሞው በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫዎች በተወከሉ ከተሞች ተከናውኗል

የመንግስት ፖሊሶች ሴቶችን መደብደብና ማሰር ልምድ አድርገውታል

ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ ላይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአልጀዚራ እንግሊዝኛ ክፍል ሰጥተውት በነበረው ቃለ መጠይቅ ቅዋሜ የሚያነሱት ሙስሊሞች ቁጥር በጣም አናሳና ጥቂት ናቸው ብለው ተናግረው ነበር፡፡ እኛም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ ቁጥራችንን እያወቁት? ስንል በወቅቱ ጠይቀናቸዋል፡፡ ለነገሩ የመንግስት ባላስልጣናት አንድ ጊዜ ጥቂቶች ናቸው፣ ሌላ ወቅት አሸባሪዎች ናቸው፣ አንድ አንዴም ሳት እያላቸው በጥቂቶች የተሳሳቱ ብዙሀን ብለው የሚጣረሱ መግልጫዎች ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ይሄ ሁሉ ከእውነት እና ከሐቅ ሽሽት መሆኑ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥራችንም ሆነ በጥያቄዎቻችን ሕጋዊነት ላይ ጥርጣሬ ካላቸው ይኸው ዛሬም አደባባይ ወጥተን፣ በታላቅ ሕዝባዊ ማእበል አጅበን በተመረጡ የአገሪቱ ከተሞች ጥያቄዎቻችንን ዳግም ለሚመለከተው አካል አቅርበናል፡፡

Friday, December 14, 2012

today's dec-14-2012 Anwar peaceful protest against TPLF(weyanne) by E.A

ሀገር አቀፉ ተቃውሞ!!! December 14, 2012

ሀገር አቀፉ ተቃውሞ!!!
በዛሬው ዕለት ከጁምአ ሰላት ቡሃላ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መሰጂድ፣በመቱ ከተማ በነጃሺ መስጂድ ፣በደሴ ሸዋበር መስጂድ፣ በ ሐረርከተማ በ ታላቁ ኢማን መስጂድ (4ተኛ መስጂድ) ፣ በጅማ ከተማ ፈትህ መስጂድ በወልቂጤ ከተማ በረቢዕ መስጂድ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተመረጡ መስጂዶች ላይ ሙስሊሞች ታላቅ ተቃውሞ አካሄዱ፡፡ በተለይ በአንዋር መስጂድ ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም የተገኘ ሲሆን፤ በተቃውሞው ላይ ሙስሊሙ የተለያዩ መፈክሮችን አሰምቷል፡፡ከነሱም መካከል፡- ህጉ ይከበር፤ መብታችን ይከበር፤ህዝብ ይከበር ፣እኛ ሚሊየኖች ነን፤ መጅሊስ አይወክለንም፤ መጅሊስ ህገ ወጥ ነው፤ ኮሚቴዎቻቻን ይፈቱ፣አህባሽ አይመራንም እና ሌሎችንም በርካታ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡ በመላው ሀገሪቱ የተካሄዱት ተቃውሞዎች በሰላም የተጠናቀቁ ሲሆን በታላቁ አንዋር መስጂድ ተቃውሞ ከተጠናቀቀ ቡሃላ ግን በሴቶች በኩል ፌደራል ፖሊሶች አንዲት ኒቃብ ያደረገች ሙስሊም ሴትን በመያዝ ክፉኛ በመደብደባቸው ህዝቡ ለማስጣል ባደረገው ጥረት ግርግር ተፈጥሮ ነበር፡፡በርካታ እህቶችም በፌደራል ፖሊሶች ክፉኛ የተደበደቡ ሲሆን የቻለው በመሮጥ ያመለጠ ሲሆን የተቀረው ደግሞ መስጂዱ አካባቢ በሚገኙ የንግስ ዱቆች ውስጥ በመግባት ከድብደባ ለመትረፍ ችለዋል፡፡ በርካቶችም በአረመኔዎቹ ፌደራል ፖሊሶች እየተደበደቡ በመኪና ተጭነው ወደ አራተኛ ፖሊስ ጣብያ ተወስደዋከል፤ባጠቃላይ በመላው ሃገሪቱ የተደረጉት ተቃውሞዎች አላማቸውን ያሳኩ ሲሆን የሙስሊሙን አንድነትና ፅናት ዳግም አረጋግጦ በሰላም መጠናቀቅ ችሎል፡፡
አላሁ አክበር!!!

የሙስሊሞች ትኩስ ዜና 4!!!
የመቱ ከተማ ተቃውሞ!!!
ዛሬ ከጁምአ ሰላት ቡሃላ በመቱ ከተማ በነጃሺ መስጂድ ከባድ ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ልዩ የተቃውሞ ውሎ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ ፣ አህባሽ አይመራንም፣ህዝብ ይከበር እና ብዙሀን እንጂ ጥቂቶች አደለንም እንዲሁም ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ተቋውሞውን በተሳካ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር!!!!!!!

የሙስሊሞች ትኩስ ዜና 3!!!
ዛሬ በደሴ ሸዋበር መስጂድ ከባድ ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ልዩ የተቃውሞ ውሎ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ ፣ ህዝብ ይከበር እና ብዙሀን እንጂ ጥቂቶች አደለንም እንዲሁም ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ተቋውሞውን በተሳካ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር!!!!!!!

የሙስሊሞች ትኩስ ዜና 2!!!
ዛሬ በወልቂጤ ረቢዕ መስጂድ ከባድ ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ልዩ ተቃውሞ ውሎ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ ፣ ህዝብ ይከበር እና ብዙሀን እንጂ ጥቂቶች አደለንም እንዲሁም ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ተቋውሞውን በተሳካ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር!!!!!!!
 
 

የሙስሊሞች ትኩስ ዜና!!!
ዛሬ በ ሐረር ታላቁ ኢማን መስጂድ (4ተኛ መስጂድ) በአይነቱ ልዩ የተባለለት ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ልዩ ተቃውሞ ውሎ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ ፣ ህዝብ ይከበር እና ብዙሀን እንጂ ጥቂቶች አደለንም እንዲሁም ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ተቋውሞውን በተሳካ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር!!!!!!!
 

በደሴ ከተማ ሸዋበር መስጂድ የጁመዓ ውሎ!!!!! Jumea gathering in dessie Shewaber mesjid...



የሙስሊሞች ትኩስ ዜና 3!!!
ዛሬ በደሴ ሸዋበር መስጂድ ከባድ ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ልዩ የተቃውሞ ውሎ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ድምፃች ይሰማ ፣ ህዝብ ይከበር እና ብዙሀን እንጂ ጥቂቶች አደለንም እንዲሁም ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ተቋውሞውን በተሳካ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር!!!!!!!

Thursday, December 13, 2012

ታላቁን አሊም ሸይኽ ዙበይር አብዱልመጂድ

የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን ትላንት ኢትዮጵያ ገቡ

ሰበር ዜና

የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን ትላንት ኢትዮጵያ ገቡ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ መንግስት አማካኝነት እየተፈጸመባቸው ያለውን ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመተቸት መግለጫ ያወጣው የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ልኡካን አባላት ትላንት ኢትዮጵያ መግባታቸው ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ኮሚሽኑ አውጥቶት በነበረው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በኢስላማዊ የሃይማኖት ተቋም (መጅሊስ) ውስጣዊ አመራር ውስጥ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት ማሳየቱ፣ አዲስ አስተሳሰብ (አሕባሽ) በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ላይ ለመጫን መሞከሩ፣ በርካታ ኢማሞችም በዚሁ ሰበብ ከኢማምነት መነሳታቸው፣ መንግስት በአዲሱ የመጅሊስ ምርጫ ላይ ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት መፈጸሙን አስረግጦ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ወቅቶች የመንግስት ወታደሮች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት፣ በኮሚቴ አባላት እና በሌሎች ሙስሊሞች ላይ የተመሰረተውን የሽብርተኝነት ክስ በማውገዝ የታሰሩ የሙስሊሙ ኅብረተሰብ አመራሮችን በሙሉ መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔት እንዲፈታ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

Tuesday, December 11, 2012

ምነው ጠቅላይ ሚኒስትር… ምነው ጥቂቶች እንዳልሆንን እያወቁ!?

ምነው ጠቅላይ ሚኒስትር… ምነው ጥቂቶች እንዳልሆንን እያወቁ!?

ከሳምንት በፊት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አመራራቸውን እና አገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን አስመልክተው ከአል ጀዚራ የእንግሊዝኛ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ባለፈው ቅዳሜ ለእይታ በቅቷል፡፡ ቃለመጠይቁ ብዙዎችን ብዙ እያናገረም ይገኛል። እኛም የበኩላችንን ለማለት ወደድን።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሃይማኖታዊ ነጻነት ትግል የአል ጀዚራዋ ጋዜጠኛ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሳችው ጥያቄ ሁለተኛው መሆኑን ሁላችንም አስተውለናል። ጣቢያው የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለሚያደርገው ቃለ መጠይቅ የኛን ጥያቄ ትኩረት መስጠቱ በራሱ ጉዳዩ (ቢያንስ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች እይታ) አንገብጋቢ መሆኑን ይጠቁማል የሚል ግንዛቤ ልንወስድበት እንችላለን። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ‹‹መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቶ አህባሽን እየጫነብን ነውና ይቁምልን›› የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንና የመንግስት እርምጃም ከባድ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ጋዜጠኛይቱ ብትጠቅስም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰጡት መልስ ግን በጣም አሳዛኝ ነበር። ‹‹ይሄ የጥቂቶች ጥያቄ ይመስለኛል›› ሲሉ ነበር የጀመሩት። (‹‹ይመስለኛል›› ማለታቸው በራሱ የተናገሩትን እንደማያምኑበት አያሳይም ትላላችሁ?)

Sunday, December 9, 2012

አቶ ሀይለማሪያም ሆይ እርሶስ ለምን የነባሩ ክርስትናን ትተው ኦርቶዶክስን ትተው ፔንጤ ፕሮቴስታት ሆኑ?


Eski entenfesew
አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ስለሙስሊሙ ህብረተሰብ ወቅታዊ ሁኔታ ተጥይቀው የሰጡትን ምላሽ ትላንት ማታ አንድ ወዳጄ መኪና ላይ ቁጭ ብለን ስናይ በጣም ገርሞኛል :: ያው ውሸትና ቅጥፈትን የሌለ ነገርን አለ ማለትን የለመድነው ቢሆንም ከሁሉ ግን ሁሌም የሚከነክኝ አንድ ነገር አንግበገበኝ ምነው ጋዜጠኛዋን በሆንኵ አስባለኝ ይህውም የኢትዮፒያ ሙስሊም የነባሩ እስልምና አለ እሱ በጣም አሪፍ ስለሆነ እሱ ስልጠና እንዲሰጥ ትብብር እያደረግን ነው አክራሪነት እንዳይስፋፋ ብለው ተናገሩ ጥያቄ አለኝ የተከበሩ በሙት መንፈስ ህዝብን ለሚመሩ ፎቶ ኮፒ ሚንስትሩ ድሮም ዛሬም እስልምና አንድ ነው ብንላቹሁ ስለደነቆራቹህ ይህን እንጠይቃቹ
አቶ ሀይለማሪያም ሆይ እርሶስ ለምን የነባሩ ክርስትናን ትተው ኦርቶዶክስን ትተው ፔንጤ ፕሮቴስታት ሆኑ አዲስ ከምኔቴ ያፈነገጠ እምነት ኢምፖርት አድርገው በ21ኛው ክፍለ ዘመን በግድ እኔን ወደ ነባሩ ተመለስ እያሉ እየገረፉ እያሰሩ እርስዎ ግን ከሀገር ቤት አልበቃዎት ብሎ ከውጭም ፔንጤ እያስመጡ አባይ ይግደባል እየሱስ ያድናል እያሉ መውጫ መቀመጫ አሳጡ የኛዎቹን ዳኢዎች ግን እንኳን ለኢትዮፒያዊ ወገን ለጠላት እንኳን የማይሰራ ግፍ ይፈፅማባቸዋል ::
የተከበሩ ሚኒስትሩ በርግጥ አንድ ወቅት የናትዎ ፔንጤ አለመሆን እንዳሳዘነዎት እናቴ አልዳነችም እየሱስን ትቀበልልኝ እያሉ የተናገሩትን ኢንተርቪው አንብቤ
ሲገርመኝ ነበር የናትዎን የምነት ነጻነት ያልተቀበሉ ሰው ነገ ጠዋት በቃ አህባሽንም ተውት እየሱስን ተቀበሉ ሳይሉ ይቀራሉ ::

Saturday, December 8, 2012

አገር አቀፍ የመረጃ እና የግምገማ ሳምንት

አገር አቀፍ የመረጃ እና የግምገማ ሳምንት

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ታሪክ ዳግም ያደሰ፣ የሰላምንና ሰላማዊነት ምንነትን ተተግብሮ እንዲታይ ያደረገ፣ ለሃገርና ለህዝብ ሰላም ሲል ለስቃይና ለመከራ ራሱን አሳልፎ የሰጠ ትውልድ የታየበት፣ እየተበደሉም መብትን ከመጠየቅ የማይቆጠብ ፅኑ ህዝብ ያየንበት የኛ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ከተነሳ ድፍን አንድ አመት ሊሞላው ጥቂት ሳምንታት ቀሩት፡፡ ክብር እና አድናቆት የሚገባቸው የአወሊያ ተማሪዎች መጅሊሱ የወሰዳቸውን ሕግ ወጥ ተግባሮች በመቃወም ተቃውሞ ማሰማት የጀመሩበት ታኅሳስ 24/2004 አንድ ዓመት ሊሞላው ከሦስት ሳምንት ያልበለጠ ጊዜ ብቻ ይቀረዋል፡፡

Friday, December 7, 2012

Demonstration of Ethio. Muslims demanding the Government to respect Arti...

ደማቁ የ 27 ተቃውሞ


ደማቁ የ 27 ተቃውሞ

ገና በማለዳው ነበር የአዲስ አበባ ሙስሊም ወደ አንዋር መስጊድ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረው፡፡ ብዙም ሳይቆይ መስጊዱ እንደተለመደው ሞልቶ ወደውጭ ሰው ማፍሰስ ጀመረ፡፡ የፈሰሰው ሰው አንዋርን እና ዙሪያውን ሞልቶ እስከ ሲኒማ ራስ እና ተክለሃይማኖት መድረሻ፣ በመርካቶ በኩልም እስከጣና አጥለቅልቆት ቦታውን ረመዳን ወር የገባ አስመሰለው፡፡ እንደ ሁልጊዜው ለሽያጭ የመጡ የመስገጃ ካኪዎች በቂ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ እናም ሁሉም በያለበት ልብሱን እያወለቀ ለሰላት ያነጥፍ ነበር፡፡ ሁሉም ጁምአን ለመስገድ፣ ከፈጣሪው ጋር ለመገናኘት ጓጉቷል፡፡ ለሰላት ቆሞ መንግስት ሙስሊሞች ላይ የሚያደርሰውን በደል አላህ ሃይ እንዲልለት፣ ለስቃዩ መቆሚያ እንዲያበጅለት፣ መሪዎቹን በሰላም ከእስር እንዲያወጣለት ጌታውን አጥብቆ ይለምናል፡፡ ገሚሱ እምባውን ያወርዳል፤ የአላህን ራህመት ይከጅላል፡፡

today anwar full video (27tgenawu anqets yekeber)

Ethiopian muslims protest in addis ababa "27" "27"ህግ ለማያውቅ መንግስት ህግን ልያስተምር የመጣው የአዲስ አበባ ሙስሊም ማ/ሰብ አላህ አክበር!!!! - Dec. 7 2012

ሬኔ ሌፎ ስለ ኢትዮዽያውያን ሙስሊሞች የመብት ትግል ምን አለ ?

Thursday, December 6, 2012

አስደንጋጭ መረጃዎች


አስደንጋጭ መረጃዎች

ኮሚቴዎቻችን፣ የማዕከላዊ ዘግናኝ ግፎችና ግፈኞቹ

ከዚህ በፊት ታማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮች ባገኘነው መረጃዎች ላይ ተመስርተን ባስነበብናቸው የተለያዩ ዘገባዎች ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች ታሳሪ ወንድሞቻችን ላይ በማዕከላዊ የደረሰባቸውን ግፍና ሰቆቃ በመጠኑ ለማስቃኘት ሞክረናል፡፡ ዘወትር ሰላምን ሲሰብኩና መቻቻልን ሲያስተምሩ የኖሩትን ኮሚቴዎቻችንንና ዓሊሞቻችንን በግድ የሽብር ድርጊት ልትፈጽሙና ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ስትንቀሳቀሱ እንደነበር የሀሰት ቃል ስጡ በሚል አንድ ኢትዮጵያዊ የራሱ ወገን የሆነ ኢትዮጵያዊ ላይ ያደርሰዋል ተብሎ የማይታሰብ አረመኒያዊ ድርጊት ፈጽመውባቸዋል፡፡ ከነዚሁ ታማኝ ምንጮች የደረሰን ተጨማሪ መረጃ ደግሞ እነዚህ ተርቦ እንደተለቀቀ አንበሳ ደም የጠማቸው የማዕከላዊ መርማሪዎች እነማን እንደሆኑና ሲያደርሱባቸው የነበረው ሰቆቃ ምን ይመስል እንደነበር ዘርዘር ባለ ሁኔታ ያሳያሉ፡፡

ባለ 27 ቁጥር ጁመዓ


ባለ 27 ቁጥር ጁመዓ

አገራችን ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሰው ልጆች መብቶችን ለማስጠበቅ የሚያግዝ ሕገ መንግስት ማጽደቋ ይታወሳል፡፡ ይህ ሕገ መንግስት ከጸደቀ እነሆ በመጪው ቅዳሜ ኅዳር 29 18ኛ ዓመቱን ይደፍናል፡፡ ይህ ሕገ መንግስት በውስጡ የሰብዓዊ መብቶችን ጨምሮ በርካታ ውብ አናቅጽትን በውስጡ አቅፏል፡፡ እነዚህ ውብ አንቀጾችን ከወረቀት ላይ በዘለለ ግን በተግባር ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ ከእነዚህ የሕገ መንግስት ውብ አንቀጾቸ አንዱ አነቀጽ 27 በዋነኝነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ አንቀጽ 27 እንዲሕ ይላል፡፡
  • የመሪዎቻችንን ጠበቆች መቃወሚያ፤ ሁሉም ሊያነበው የሚገባ፡፡

    ከሰሞኑ እንደተገለጸው የታሳሪ ወንድሞቻችን ጠበቆች ‹‹ደንበኞቻችን የታሰሩት በሕግ ወጥ መንገድ በመሆኑ ፍ/ቤቱ በነጻ ያሰናብታቸው›› ብለው መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ጠበቆቹ ለዚህ መቃወሚያቸው መሰረታዊ መሟገቻ ነጥቦችን ከሕገ መንግስቱና ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች አቅርበዋል፡፡ በጣም በሚያስደንቅ መልኩ የመሪዎቻችን ጠበቆች በኢትዮጵያ ታሪክ እስከአሁን ያልተሞከረና ያልተደፈረ መንገድ በመምረጥም ጭምር ነው መከራከሪያቸውን ያቀረቡት፡፡ እንደሚታወቀው መሪዎቻችን በዋነኝነት ክስ የተመሰረተባቸውና በርካታ ሕገ ወጥ ተግባራት ከተያዙበት እለት ጀምሮ የተፈጸመባቸው በ2001 መጨረሻ በጸደቀው አዲሱ የጸረ ሽብር ሕግ በመመርኮዝ ነው፡፡ ይህን ሕግ መንግስት በርካታ ንጹሐንን በአሸባሪነት በማስፈረጅ ፖለቲካዊ ዓለማውን እያስፈጸመበት ይገኛል፡፡ ይህ ሕግ በትክክልም ሕገ መንግስታዊ ቢሆን ኖሮ ብዙም ባላስከፋ ሆኖም ከሕገ መንግስቱ መርህ ያፈነገጠ ነው፡፡

Tuesday, December 4, 2012


Malcolm King
ይድረስ ለወያኔ፤
BY Malcolm king (M.K.)
ይድረስ በንጹሃን ደም እየትንቦራጨክ የሰፊወን ህዝብ ድምጽ ኣፍነህ ወሸትን ሰንቀህ ሃሰትን ኣንግበህ በስልጣን ጥማት ሰክረህ በ፰፪ ሚሊዮን ህዝብ ላይ ኣላግጠህ ሲሻህ ኣሰረህ ሲሻህ ገርፈህ ኣስፈራርተህ ኣስፈላጊም ሲሆን ገለህ ኣውቀህ እንዳልሰማ ሆነህ በቀን ህልም ወስጥ ለምትዋኝው ወያኔ ሆይ፤ እኛ ሙስሊሞች የጠይቅናቸውን ጥያቄወች ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ መልሰህ ኮሚቴወቻችንን

UN Special Rapporteur on Freedom of Religion: Stop Government Intolerance of Islam in Ethiopia

Alemayehu Weldemariam
Petition by
Austin, United States

ድምፃችን ይሰማ


ሰበር ዜና

እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአገር ውስጥ በኢትዮጵያ መንግስት አማካኝነት ሙስሊም በመሆናችን ብቻ እየደረሰብን ያለውን ሁሉን ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቃወምና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ የፔቲሽን ሥራ ተጀምሯል፡፡ ፔቲሽኑ ለተባበሩት መንግስታት የሃይማኖት ነጻነት ልዩ ክፍል ገቢ የሚደረግ ሲሆን የሁሉም እምነት ተከታዮችም በፔቲሽን መሙላቱ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ ፔቲሽን የኢትዮጵያ መንግስት እየተከተለ ያለው እስልምናን የማግለል እና የማጥቃት ፖሊሲ ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ለማሳደርና ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ወሳኛ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ፔቲሽን መሙላት በጣም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

ፔቲሽኑ የሚሞላው ኦንላይን ላይ ሲሆን፤ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ተከትሎ በመሄድ የሚሞላውን ፔቲሽን ማግኘት ይቻላል፡፡ የሚሞላውም በስተቀኝ ላይ በሚገኘው ስፍራ Sign this petition ከሚለው ጽሑፍ ዝቅ ብሎ ስም፣ ኢ-ሜይል እና የመኖሪያ ከተማ ብቻ በመጻፍ መጨረሻ ላይም Sign የምትለዋን በመጫን ነው፡፡ በዚህ ተግባር እኛም ሆንን ቤተሰቦቻችን፣ የስራ ባልደረቦቻችን፣ ጓደኞቻችን እና ማንኛውም ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚጨነቅ ሰው ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ፔቲሽኑን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንዲሞላውም ሁላችንም በሁሉም መልኩ ከፍተኛ ጥረት እናድርግ፡፡

አላሁ አክበር!!
Assalamu Alaykum Warahmatullah Wabarakatuh

Dear All,

Please follow the link below and SIGN the petition that will be submitted to the United Nations Special Rapporteur on Freedom of Religion. Let us Sign the Petition NOW and make our voice be heard by the World Body.

http://www.change.org/petitions/un-special-rapporteur-on-freedom-of-religion-stop-government-intolerance-of-islam-in-ethiopia-2

Global Council office



የቢላል ኮሚኒኬሽን አራተኛ አመቱን በድምቀት አከበረ
አዲስ አበባ ሬድዮ ቢላል ህዳር 24/2005
ቢላል ኮሚኒኬሽን ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአማረኛና የኦሮመኛ ክፍል ጋዜጠኞች ባለሙያዎች በሙሉ በተገኙበት በቢላል ኮሚዩኒኬሽን በአዲስ አበባ ቢሮው አራተኛ የምስረታ በዓሉን በድምቀት አክብሯል፡፡
በቢላል ኮሚኒኬሽን የቦርድ ፕሬዝዳንት ሐጂ ነጂብ ከዋሽንግተን በእንኳን አደረሳቸው ንግግር የተከፈተው ልዮ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ቢሮ በቢላል ኮሚኒኬሽን የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ፅናት እና የቢላል ኮሚዩኒኬሽን የሚዲያ ሰራተኞች ኃላፊ አቶ ጀማል አህመድ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡
የቢላል ኮሚዩኒኬሽን የታክስ ፎር ኮሚቴ አባል የዕለቱ ፕሮግራም መሪ አቶ መሐመድ ካሳ በበዓሉ ስፍራ ያለውን በመላው ዓለም ለሚገኙ የሬዲዮ ቢላ አድምጮች አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ የሬዲዮ ቢላል ስቲዲዮ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ 23 በሚጠጉ ጋዜጠኞች በአንድ ክፍል በመሰባሰብ የማይረሳ የእራት ጊዜን ያሳለፉ ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት ቢላል ኮሚዩኒኬሽን በሁለት እግሩ ለማቆም የተከፈለውን ዋጋና ጋዜጠኞች በስራ ላይ ያጋጠማቸውን አስገራሚ አስደንጋጭና አስደሳች ገጠመኞቻቸውን አቅርበዋል፡፡

Saturday, December 1, 2012

የዛሬ ኅዳር 21 የችሎት ውሎ


ድምፃችን ይሰማ
የዛሬ ኅዳር 21 የችሎት ውሎ

* አቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት በመደናበር የዛሬውን ችሎት ደግሞ በሽወዳ ፈጽሞታል
* ሕግ የማይገዛቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ዛሚ ኤፍ.ኤም ‹‹ሕግ ይግዛችሁ›› ተብለዋል
* ልደታ አካባቢ ፌዴራል ፖሊሶች ‹‹እስላም ማየት አስጠላን›› ሲሉ ውለዋል

ባለፈው ሳምንት ገልጸነው እንደነበረው ዛሬም መሪዎቻችንን ከሕዝብ እይታ ለመሰወር ፖሊስ በደረቅ ሌሊት ነበር ከቃሊቲ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ያመጣቸው፡፡ ሌቱ እስኪነጋና የችሎት ሰዓት እስኪጀምርም በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ በፖሊስ ጥበቃ እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ችሎቱ ከተሰየመ በኋላም የመሪዎቻችን ጠበቆች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ዛሚ ኤፍ.ኤም ጣቢያዎች ደንበኞቻችን በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሳይባሉ ጣቢያዎቹ ግን በተቃራኒው ከፍተኛ የስም ማጥፋት ስራ ላይ ስለተሰማሩ እዚህ ችሎት ውስጥ ካሉ ይውጡልን ብለው ጠይቀዋል፡፡ ዳኛው ችሎቱ ለማንም ክፍት በመሆኑ ይህን ሊያዙ እንደማይችሉና ጣቢያዎቹ የተባለውን ተግባር እየፈጸሙ ከሆነ ግን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አዘዋል፡፡